Последние посты

አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
21 сент., 09:23изменён
አል-ዋዓድ ኢስላማዊ ድርጅት በወረዳው የአክፍሮት ኃይል እንቅስቃሴን ለመግታት ያለመ የመጀመሪያውን የፓናል ውይይት አካሄደቀን፦ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ል (10/01/2019) አዘጋጅ፦ አል-ዋዓድ ኢስላማዊ ድርጅት ርዕስ፦ በወረዳችን እየተካሄደ ያለውን የአክፍሮት ኃይል እንቅስቃሴ መግታትና መከላከል አል-ዋዓድ ኢስላማዊ ድርጅት በወረዳችን በስልታዊ መንገድ እየተስፋፋ የመጣውን የአክፍሮት ኃይል እንቅስቃሴ በጥናት ለመለየትና ለመከላከል ያለመ የመጀመሪያውን የፓናል ውይይት መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ል በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።በመድረኩ ላይ በተለያዩ የዳዕዋ ዘርፎች የሚንቀሳቀሱ ታዋቂ ዱዓቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የዳዕዋ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በጉዳዩ ላይ ሰፊና ጥልቅ ውይይት ተደርጓል።የውይይቱ ዋና ዋና ትኩረቶችና የተነሱ ነጥቦች በውይይቱ ወቅት በወረዳው እየታየ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ዳሰሳ የተደረገ ሲሆን፣ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ከስምምነት ተደርሷል፦ ✓የአክፍሮት ኃይል እንቅስቃሴን በጥናት መለየት፦ በወረዳው በስልታዊ መንገድ የሚካሄዱ ህገ-ወጥና የእምነት መሸርሸር እንቅስቃሴዎችን በጥናትና ምርምር ላይ ተመስርቶ መለየትና ሳይንሳዊ የመከላከያ መንገዶችን መተግበር።✓ኢስላማዊ እውቀትን በስፋት ማሰራጨት፦ ማህበረሰቡን በተለይም ወጣቱን ክፍል ከተሳሳቱ አስተሳሰቦችና ጥቃቶች ለመጠበቅ ትክክለኛና ጥራት ያለው ኢስላማዊ እውቀት በስፋት ማዳረስ የሁሉንም አካላት ግንባር ቀደም እርምጃ መሆን እንዳለበት ተስመሮበታል።✓የባለድርሻ
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
21 сент., 09:22





አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
17 сент., 04:27
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🎊 ልዩ የዳዕዋና የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 🎉 __ 🔉 እነሆ የፊታችን ጁሙዓ 📅 ቀን፦ 8/01/2019 ኢ.አ ⏰ ሰዓት፦ ከምሽቱ 3፡00 ጀምሮ (በኢትዮ) በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌግራም ግሩፕ ⏬ ተጋባዥ እንግዶቻችን ⏬ 🎙 ኡስታዝ ዐብዱናስር መኑር 🎙 ኡስታዝ አቡ ሱፊያን አል በናን 🔗 የፕሮግራሙን የሚተላለፍበት ግሩፕ ሊንክ 👉 https://t.me/Ibnu_Abas_Mesjid_wku 


አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
16 сент., 05:50
አሁን ላይ ጠዋት ሲነጋ ህይወትህ ለመግፋት ብለህ ለስራ ከቤት ትወጣለህ ስራ ጨርሰህ ወደ ቤት ትመለሳለህ (ወጥተህ ሳትሰራ ወደ ቤት የተመለስክ ቀን ለጊዜው ታዝናለህየሆነ ቀን ደሞ ከዱኒያ ላትመለስ ለቀህ ትወጣለህ (ለዛውም ላትመለስ ሳትሰራ ያ ሩቅ ሀገር የተገናኘህ ቀን ለዘላለም ታዝናለህአበቃ ይህ ነው እውነታው
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
15 сент., 20:01
🎙ወንድም አቡበከር '📖 ይህ ወንድማችን ሞቷል፣ አላህ ይርሀመው። ቲላዋውን በማሰራጨት፣ ስንቁን እናብዛለት
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
14 сент., 04:16
ልጆችቻችሁ የሆነ ነገር ሲያጠፉ የሚፈሩት ሰው ስም እየጠራችሁ ከማስጠንቀቅ ይልቅ አሏህ ይቆጣል የምትለዋ ቃል እየደጋገማችሁ ማስፈራራትን ልመዱ ስለ አሏህ ልቅና ከልጅነታቸው በልባቸው እንዲቀረፅ ያደርጋቸዋልእገሌ ከመጣ ያየሀል ከምትሏቸው አሏህ ያየሀል እያላችሁ አለማምዷቸው ከዛ የትም ቢሆኑ አሏህ እያያቸው እንደሆነ ማገናዘብ ይጀምራሉ
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
11 сент., 18:34
السلام عليكم ورحمة الله وبركاتهየሥራ ቅጥር ማስታወቂያበጉራጌ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች የዳዕዋና የትምህርት አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ ኡስታዞችን መቅጠር እንፈልጋለን።የሥራው መስፈርቶችአመልካቾች፦- ቁርአንን በተጅዊድ ማስተማር የሚችሉ፤ - ሙኽተሰር ኪታቦችን ማስቀራትና ማስተማር የሚችሉ፤ - ኹጥባ ማድረግ የሚችሉ፤ - ዳዕዋ ማድረግ የሚችሉ፤ - በአማርኛ ወይም በጉራጌኛ ቋንቋ መግባባት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።የደመወዝ ሁኔታደመወዝ፦ በስምምነት የሚወሰን።Telegramأبو محمدلِّمَنِ الْمُلْكُ الْيَوْمَ ۖ لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
11 сент., 03:23
ጥያቄ ለነፍሴና ለናንተ🕹ስልክህ ያለ ምንም ፓተርን/ፓስዎርድ ለጓደኞችህ ወይም ለቤተሰብ ያለ ፍርሀት ትሰጣቸዋለህን❓ አንቺስ እህቴ ትሰጫቸዋለሽ❓ መልሱ "አዎ" የሆነ ሰው በርግጥም ታድሏልመልስህ ለራስህ ያዘውና ይቺን የቁርአን አያህ ግን አስተውላት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 يَسْتَخْفُونَ مِنَ النَّاسِ وَلَا يَسْتَخْفُونَ مِنَ اللَّهِ وَهُوَ مَعَهُمْ إِذْ يُبَيِّتُونَ مَا لَا يَرْضَىٰ مِنَ الْقَوْلِ ۚ وَكَانَ اللَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطًاከሰው ይደበቃሉ፡፡ አላህም እርሱ (በዕውቀቱ) ከእነሱ ጋር ሲኾን ከንግግር የማይወደውን ነገር (በልቦቻቸው) በሚያሳድሩ ጊዜ (ከእርሱ) አይደበቁም፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
10 сент., 05:20
ዱኒያ ለጠበበቻቸው ሁሉ አፋጣኝ መፍትሄ ነበር ግን ምን ዋጋ አለው መጠቀም አቃተን ۚ وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱመውጫን ያደርግለታል፡፡ 👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆 .....وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ ከማያስበውም በኩል ሲሳየን ይሰጠዋል፡፡ይህ የምታዩት አያህ ሱረቱ አል_ጠላቅ 3ተኛ አያህ ላይ ይገኛል ከዚህ አያህ ቀድሞት የመጣው አያህ ምን እንደሆነ ያወቀ ሰው እና በደምብ አውቆት የሚጠቀምበት ሰው ወሏሂ ወቢላሂ ወተሏሂ ምንም አይቸግረውም ብልጡ ማለት ያ ሰው ነው በሁለቱም ሀገር የተድላ ህይወትን ይኖራልአሏህ ከሚጠቀሙበት ያድርገን🤲
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
9 сент., 13:26
« በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ እርም ( ሃራም)የሆኑ ነገሮችንና ዘፈኖችን ለሚያሰራጩት ሰዎች፣ ከሞቱ በኋላ ማንም እንደማይሰርዛቸውና ከአላህ ጋር ቀጠሮ እንዳላቸው ንገሯቸው።»


አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
7 сент., 05:09изменён
ሀቂቃ በጣም የሚገርመው ነገር ብዙ ሰዎች ሲያወሩ የምሰማው እንደምንም አልፎልኝ ስኬታማ ብሆን ብለው የሚያስቡት ነገር ብዙ ሰርተው ሀብት አከማችተው ልጥጥ ሀብታም መሆን ነው የመሄጃ ቀንቀጠሮ ግን ከዚህ የፈጠነ ሆኖ ሳለ ብዙዎቻችን ዘንግተንዋል አሏህ ይዘንልንhttps://t.me/alwaadislamic1446
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
2 сент., 04:10изменён
አንዳንዴ ዱዓእ አድርገህ ቶሎ ምላሽ ላያገኝ ይችላል ያኔ ለምን የሚል ጥያቄ ከተመላለሰብህ አሏህን በድብቅ ስታምፀውም ለምን ቶሎ አልቀጣኝም የሚልም ነገርም በዛው ቆም ብለህ አስብ❗️ ያኔ የአሏህ እዝነት ይገባሀል ምናልባት ዱዓውም ያዘገየብህ ላንተ በይበልጥ ሚያስፈልገህ ሰአት እሱ ያውቀዋልና ለዛኔ ሊሰጥህ አዝኖልህ ይሆናልእና ወንድሜ አትቸኩል እህቴ አትቸኩዪ ዱዓእ አድርግ ከዛ ምላሽ እንደምታገኝ እርግጠኛ ሁን ከዛ በትግስት ጠብቅ https://t.me/alwaadislamic1446
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
24 авг., 04:09
"የነበረህ ክብር ይቀንሳል"ሰዎች የሚጠጣ ውሀ እንኳ እንዲያቀብሉህ ብትጠይቃቸው በጠየካቸው ነገር ልክ እነርሱ ዘንድ የነበረህ ክብር ይቀንሳል!!" ይላሉ ሼኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ራሂመሁሏህ)ወሏሂ ወጣቶች በስራ ላይ ጠንክሩ የሰዎችን እጅ የማታዩበት ሪዝቅ አስፍቶ እንዲሰጣችሁምአል_ራዚቁን አጥብቃችሁ ተማፀኑት ይቺ የማትረባ ዱኒያ ከፊሎችን ከፍ ከፊሎችን ዝቅ ታደርጋለችና
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
22 авг., 21:07
መውሊድእና የጭካኔ ጥግ
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
22 авг., 10:57
🔈 የጁሙዓ ኹጥባህ📖 ርዕስ፦ መውሊድ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 📍 ቦታ፦ አዲስ አበባ 🌇 መስጅድ፦ አል-ፈትህ መስጅድ✓ ሱና ላይ መፅናት ✓ ነብዩ صلى الله عليه وسلم መቼ ተወለዱ ✓ መውሊድ መቼ ተጀመረ ✓ መውሊድ ማን ጀመረው ✓ የጀመሩት ሰዎች ስንት ልደት ያከብሩ ነበር ✓ መውሊድ ላይ የሚነሱ ብዥታዎችየተዳሰሰበት ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🎙 አቅራቢ፦ አቡ መሀመድ አብዱልናስር መኑር አል-ጃቢሪይhttps://t.me/twhidsunabegegnea
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
18 авг., 17:52
переслано из @sle_qelbachn1
📢 አስደሳች ዜና ለጠቅላላው የሙስሊም ማህበረሰብ!ኢኽላስ የቁርኣን እና የተርቢያ ማዕከል የ10 ወር የቆይታ ጊዜ ያለው የበጋ ልዩ ኮርስ ማዘጋጀቱን በታላቅ ደስታ ይገልፃል!💡 የፕሮግራሙ ልዩነት፦ በዚህ 10 ወር ውስጥ ማንኛውም የእውቀት ፈላጊ ጧሊበል ዒልም ሊቀራቸው የሚገቡ መሠረታዊ የሸሪዐ የትምህርት ፈኖችን በጥልቀት የሚያስጨብጥ እና ጠንካራ መሠረት የሚጥል ልዩ የእውቀት ማዕድ ተዘጋጅቶልዎታል!ልጆቻችሁን እና እራሳችሁን በቁርኣን፣ በስነ-ምግባር እና በእስልምና እውቀቶች ለማነፅ እና ለማበልፀግ የቀረበ ወርቃማ አጋጣሚ! የትምህርቱ በወንድም አብዱረዛቅ አል-ባጂ አስተምህሮ የሚሰጥ ይሆናል።📚 የሚቀሩት ፈኖች ● ዓቂዳህ ● ፊቅህ አሻፊኢይ ● ኡሱሉል ፊቅህ ● ቀዋዒዱል ፊቅሂ ● አዳብ እና ሱሉክ


አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
15 авг., 21:31
የመውሊድ ትልቅ አደጋ
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
14 авг., 13:33
🔈 የጁሙዓ ኹጥባህ📖 ርዕስ፦ ነቢዩ (صلى الله عليه وسلم) የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 📍 ቦታ፦ አዲስ አበባ 🌇 መስጅድ፦ አል-ፈትህ መስጅድ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🎙 አቅራቢ፦ አቡ መሀመድ አብዱልናስር መኑር አል-ጃቢሪይhttps://t.me/twhidsunabegegnea
አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
5 авг., 07:32

አል- ዋዓድ ኢ/ማ/ቻናል
3 авг., 12:25изменён
