gram news
Аватар канала @hakezel hayat

@hakezel hayat

@hakezel_hayat

اللهم اجعل القرآن ربيع قلوبنا @abuna124

ПроектыARРелигия

3,990подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • @hakezel hayat

    20 сент., 09:25

    حُبُّ النَّبِيِّ طَهَارَةٌ لِلْقُلُوبِ، وَنُورٌ فِي الظُّلُمَاتِ، وَوُصُولٌ إِلَى رَبِّ الْعَالَمِينَ.የነቢዩ ፍቅር ለልቦች ንፅህና፣ በጨለማ ውስጥ ያለ ብርሃን💥እና ወደ ዓለማቱ ጌታ መድረሻ መንገድ ነው
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    17 сент., 18:27

    ምን እንኳን ስራዬ ቢነትብም ቢደብስም ምንም ከንቱ ብሆን ባልመጥን ላንቱ ስም ዉጤቴ ስራዬ የትም ባያደርስም ስሞት ነዉ ሰይዲ ህይወቴ ያንቱ ስም ምን እንኳን ባልመጥን ላንቱ ስም ባልደርስም ህይወቴ እስትንፋሴ አለቅም ያንቱ ስም ሰይዲ በስሞት ደምቄ እኖራለዉ በስሞት ዉዬ በስሞት አድራለዉ ሩህ ሁላ ነፍሴ ላንቱ ሰጥቻለዉ ምክንያቱም ሀያቴ ዉዴታ እስኪደመም እኔ እወዶታለዉ!!!
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    16 сент., 09:21

    ጥፍጥና ቆራጩን ሞትን እናስታውስ !
  • @hakezel hayat

    14 сент., 18:03

    አንዳንድ ጊዜ ይህ ቀን መች ያልፋል ብለን ስንጠብቅ፣ ስንጠብቅ፣ ስንጠብቅ ...... ጊዜው ማለፉን ትቶ ዕድሜያችን ያልፋል።ዱንያ፣ ዱንያ፣ ዱንያ ... ትዕግስት፣ ትዕግስት፣ ትዕግስት ....ዱንያ ባትሠለች ነው የሚገርመው
  • @hakezel hayat

    14 сент., 08:49

    ታውቅበታለህ እንባ ማበሱን ልብን ፈውሰህ ሳቅ መመለሱን🥀 . . . ኢላሂ.....
  • @hakezel hayat

    11 сент., 09:06

    اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين❤️🫀
  • @hakezel hayat

    10 сент., 07:26

    ከሐራም ነገር ከባዱ የመጀመሪያው ነው። ከዚያ ሲደጋገም እየቀለለ ይሄዳል። ከዚያ እንዲሁ ተራ ነገር ይሆናል። ከዚያ ልማድ ይሆናል። ከዚያ ይጣፍጣል። ከዚያ ልብ ይሸፈናል። ከዚያ ልብ ሌላ ሐራም መፈለግ ይጀምራል።አንድ ሷሊሕ ሰው እንዲህ ይላል፦ "ነፍስህ ወደ ወንጀል ከጋበዘችህ በዚች አንቀፅ አጭር ቃለ መጠይቅ አድርግላት :- { أَذَ ٰ⁠لِكَ خَیۡرٌ أَمۡ جَنَّةُ ٱلۡخُلۡدِ ٱلَّتِی وُعِدَ ٱلۡمُتَّقُونَۚ } "ይሄ ነው የሚሻለው ወይስ ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት የዘለዓለሟ ጀነት?" [አልፉርቃን፡ 15]በዚህ ሐራም ነገሮችን መዳፈር በበዛበት ዘመን ይህቺን አንቀጽ ማስተዋል ምንኛ አንገብጋቢ ነው?!IbnuMunewor
  • @hakezel hayat

    9 сент., 19:43

    ረቢዕ ማለት ብራ ነው፤ ብራ ማለት ደግሞ ፀደይ። በፀደይ የአበቦች ሽታ ይጣራል፤ በረቢዕ የርሣቸው መዓዛ ያውዳል። ለወትሮ በዝምታ የሚንፏለለው የናፍቆት ጅረት ረቢዕ ላይ ኃያል ይሆናል። የናፋቂዎች ህመም ይጠናል። … ረቢዕም አይደል?اللهم صلِ و سلم على سيدنا محمد ﷺ💚
  • @hakezel hayat

    9 сент., 18:26

    ከዲንህ ጋር እንዴት ነህ? ተብሎ ሲጠየቅ"በወንጀል እየቀደድኩት በእስቲግፈር እየሰፋሁት አለሁ " አላቸው🥹 ❤️‍🩹
  • @hakezel hayat

    9 сент., 11:08

    አላህ ሆይ ልቤም ደክሞታል አይኔ አሻግሮ ማየት አልቻለም ኢላሂ ፈረጃህን አቅርበዉ🤲
  • @hakezel hayat

    8 сент., 05:57

    ህያው ቀልብ…አንድ የአላህ ወዳጅ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፦«አንድ ሰው አላህ ዘንድ ቅርብ መሆኑን በምን ያውቃል?»እርሱም እንዲህ መለሰ፦ «ቀልቡ አላህን ሲያስታውስ ይረጋጋል፤ ነፍሱ ከኃጢአት ስትርቅ ደስ ይላታል፤ ከሰዎች ጋር ደግሞ በርህራሄ ይኖራል።»የሰው ሕያውነት ከውጭ አይጀምርም፤ ከቀልብ ውስጥ ይጀምራል። በዚክር ቀልብህን አጽዳ። በተውበት ነፍስህን ያሳርፍ። በርኅራኄህ የአላህን እዝነት ጥራ። በነቢዩ [ﷺ] ፍቅር ምግባርህን አሳምር። በደጋጎች ተረክ መንገድህን አቅና። ትኩረትህን የአኺራ ስኬት ላይ አንጠልጥል። ለምትኖርባት ዱንያም መልካምን አበርክት። አላህ ያግዝህ!
  • @hakezel hayat

    7 сент., 05:46

    ልክ እንደ ዩሱፍ "ህልሜ እኮ እውን ሆነ" የምንልበትን ቀን ቅርብ ያድረግልን!
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    6 сент., 20:10

    ባንቱ'ኮ ነው ከጉድ የራቅኩት እንኳን ዲኔን ዱንያን ያወኩት ኑር ዊላዳው ሆኖልኝ ዛዴ ባንቱ አይደሎይ ቆሜ መህዴ🥰
  • @hakezel hayat

    6 сент., 04:45

    መከራን ያረከሰ ፍቅር… የኡሁድ ቀን ነበር። የጦርነቱ ዜና ወደ ሐምና ቢንት ጀሕሽ [ረዲየላሁ ዐንሃ] መጣ። መጀመሪያ አባቷ ጀሕሽ ኢብኑ ሪአብ መሰዋታቸው ተነገራት። እሷም፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ብላ ጠየቀች። ከዚያ ወንድሟ ዐብዱላህ ኢብኑ ጀሕሽ [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋቱ ተነገራት። እንደገና፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ከዚያ ባሏ ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋቱ ተነገራት። አሁንም ጥያቄዋ አንድ ነበር፦ «ነቢዩ ﷺ ምን ሆኑ?!»…በመጨረሻም አጎቷ ሐምዛ ኢብኑ ዐብዱልሙጦሊብ [ረዲየላሁ ዐንሁ] መሰዋታቸው ተነገራት። እሷ ግን እንደገና፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ነበር ጥያቄዋ።…ከዚያም የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሕይወት እንዳሉና ደህና እንደሆኑ ሲነገራት፣ ወደ እርሳቸው በፍጥነት ሄደች። እርሳቸውን ባየች ጊዜም፣ በአትኩሮት ደህንነታቸውን ተመልክታ ካረጋገጠች በኋላ፦«كل مصيبة بعدك جلل» «ከእርስዎ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም መከራ ትንሽ ነው።» አለች።
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    4 сент., 07:25

    በውሸት በጥፋት በኔነት በስሜት ለጉድ ተከብቤ እንዴት ወዳጆህ ተከታዮ ነኝ እላለው ከልቤ...🤕 ያሻፊየል ሙዝኒቢን
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    3 сент., 05:59

    አላህ ሆይ! የተሟላ ኢማንን፣ እውነተኛ እርግጠኝነትን፣ መልካም ሥራን፣ ሰፊ ሲሳይን፣ ላንተ የተዋረደና አንተን የሚፈራ ልብን፣ አንተን በማስታወስ የሚጠመድ ምላስን፣ ሐላልና መልካም ሲሳይን፣ ሁሉንም መልካም ነገር የሚያካትት በረከትን፣ የሚስሰማና ተቀባይነት የሚቸረው ዱዓን፣ ደህናና ሰላማዊ ቤትን፣ ጤናማ ሰውነትን፣ መልካም መጨረሻን፣ ጀነትን መታደልና በእሳት ከመቀጣት መዳንን እንለምንሃለን። : አላህ ሆይ፣ ሁሉንም ልመናዎቻችንን በችሮታህ ሙላልን። አሚን።
    Иллюстрация к посту канала @hakezel hayatИллюстрация к посту канала @hakezel hayat
  • @hakezel hayat

    31 авг., 18:59

    የወለድ አደገኝነት!ከጃቢር (🤎) ተይዞ: እንዲህ ይላል፦﴿لَعَنَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ آكِلَ الرِّبَا، وَمُؤْكِلَهُ، وَكَاتِبَهُ، وَشَاهِدَيْهِ. وَقَالَ : " هُمْ سَوَاءٌ﴾“የአላህ መልእክተኛ (🤎) ወለድ የሚበላንም፣ የሚያበላውንም፣ ፀሐፊውንም፣ ምስክሮቹንም ተራግመዋል፡፡ ‘ሁሉም በወንጀሉ እኩል ናቸው!!’ ብለዋል፡፡”ሙስሊም ዘግበውታል: 1598
  • @hakezel hayat

    31 авг., 17:55

    ያልፉ ይሆን ብለን ስንሰጋባቸው የነበሩ ቀናት ሁሉ ኮሽ ሳይሉ እንደዋዛ አለፉ።አልሐምዱ ሊላህ❤️‍🩹
  • @hakezel hayat

    30 авг., 19:07

    የታላቁ ነቢይ (📿) ስብዕና!ረሱል እንዲህ ብለዋል፦﴿لَوْ دُعِيتُ إِلَى كُرَاعٍ لَأَجَبْتُ، وَلَوْ أُهْدِيَ إِلَيَّ ذِرَاعٌ لَقَبِلْتُ﴾“በእንስሳ (በበግ እግር የተዘጋጀ መጠነኛ ግብዣም ቢሆን) ብጠራ ኖሮ እቀበል ነበር፤ ክንድም (ስጦታ) ቢበርከትልኝ ኖሮ በእርግጥም እቀበል ነበር።”ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5178
  • @hakezel hayat

    30 авг., 19:06

    የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦يا عَائشةُ، لا ترُدِّي المِسكينَ ولو بشِقِّ تَمرةٍ، يا عائشةُ، أحِبِّي المساكينَ، وقَرِّبيهم؛ فإنَّ اللهَ يقرِّبُكِ يومَ القيامَةِ."ዓኢሻ ሆይ! ምስኪንን (ባዶ እጁን) አትመልሺ፣ የአንድን ተምር ግማሽ እንኳ ቢሆን (ስጪ)። ዓኢሻ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ፣ አቅርቢያቸውም፤ አላህ በቂያማ ቀን ያቀርብሻልና።"[ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 2352]