gram news
Аватар канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

@mkaddisababacentermedia

ПроектыENРелигия

4,950подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    22 сент., 15:58

    4ኛው ዙር ፍኖተ አግናጥዮስ ጉዞ መርሐግብር መደረጉ ተገለጸ።በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የቅዱስ አግናጥዮስ ትምህርትና ሥልጠና ማእከል የክረምት አዳሪና የተመላላሽ ሰልጣኞችና ወላጆች በጋራ መሆን 4ኛው ዙር ፍኖተ አግናጥዮስ ጉዞ ወደ አስኮ ቃሉ ተራራ አቡነ ሀብተማርያም ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን 2019ዓ.ም ማድረጉን አሳወቀ።የመርሐግብሩ ዓላማ የቅዱስ አግናጥዮስ ፕሮጀክት ከሙከራ ትግበራ ወደ ቋሚ የትግበራ ምእራፍ መሸጋገሩንእና የቅዱስ አግናጥዮስ ቤተሰብ የቀጣይ የአገልግሎት አቅጣጫዎችን ለመጠቆም ያለመ ነው።በዕለቱም ትምህርት በተጋባዥ መምህር፣የቅዱስ አግናጥዮስ ትተኪ ተውልድ ማፍሪያ ፕሮጀክት አተገባበር እና የቅዱስ አግናጥዮስ ቤተሰብ ምስረታ የመተግበሪያ ስልት በአቶ በረከት መሠረት የአዲስ አበባ ማእከል ም/ሰብሳቢ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በመርሐግብሩ ከ400 በላይ ወላጆች እና ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።የቅዱስ አግናጥዮስ ትምህርትና ሥልጠና ማእከል ከ1000 ሠልጣኞችን በአዳሪና በተመላላሽ ያፈራ ሲሆን በሃይማኖትና በምግባር የታነጹ ታዳጊዎችን ማፍራት ሁለንተናዊ ተጽእኖ ፈጣሪ ፣ባለ ተልእኮ ትውልድን ማፍራትን ለሀገርም ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ መሆኑ የተናገሩት የማእከሉ ኢንቨስትመንትና ሀብት ልማት ቦርድ ሰብሳቢ ኢ/ር ዮናስ አያሌው ናቸው ።በመጨረሻም የሰልጣኝ ወላጆች በፕሮጀክቱ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን የበጋው የሥልጠና መርሐግብር ጥቅምት 7ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ እንደሚጀመር ተገልጾ መርሐግብሩ ተጠናቋል።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    22 сент., 12:40

    ‹‹መስቀል ኀይላችን፣ ጽናታችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው››ዘወትር ማክሰኞ፡-ትምህርተ ወንጌል✝️በኢየሩሳሌም ምድር፣ በቀራንዮ ዐደባባይ፣ በዕለተ ዓርብ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ሥቃይ ተቀብሎ ለሰዎች ድኅነት ሲል መሥዋዕት የመሆኑና የፍቅሩ መገለጫ ‹መስቀል› ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን እንዲሁም የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ ‹‹አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምነዋለን፤ ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን፤ ድነናልም›› እያልንም ዘወትር በጸሎታችን እየመሰከርን ስላደረግልን ነገር ሁሉ አምላካችንን እናመሰግነዋለን፡፡ መስቀል ጥንት ጠላት ሰይጣን የተሸነፈበት እና የጌታችን ክርስቶስ ቤዛነት የተረጋገጠበት የድኅነት ኃይል ነውና፡፡✝️በሀገራችን ኢትዮጵያ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል የተለየ ክብር አለው፡፡ የሰውን ዘር በሙሉ ለማዳን ሲል ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለበትንና ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስ ያገኘንበት ግማደ መስቀሉ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ከእስክንድርያ ወደ ኢትዮጵያ የመጣበትን የመታሰቢያ በዓል በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን እናከብረዋለን፡፡✝️በ፫ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ንግሥት ዕሌኒ በዕጣን ጢስ አመልካችነት መስቀሉን ከተቀበረበት ቦታ ለማውጣት ቍፋሮ ያስጀመረችበትን የመታሰቢያ በዓል በየዓመቱ መስከረም ፲፮ ቀን ደመራ ደምረው በመለኮስ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት በዐደባባይ እናከብራለን፡፡ በማግሥቱ መስከረም ፲፯ ቀንም ንግሥት ዕሌኒ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረችበትን የመታሰቢያ በዓል ታቦት አውጥተው ዑደት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡✝️ከዚህም ጋር ተያይዞ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    22 сент., 07:00

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው ።በዚችም ቀን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢይኢሳይያስ ላከው ይቅርም ብሎት ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስ ሒዶ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለውና ከደዌው እንዳዳነው በዕድሜውም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እንደ ጨመረለት ይነግረው ዘንድ አዘዘው ። ሚስት አግብቶም ምናሴን እስከወለደው ድረስ እንዲሁ ሆነ ።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ በሚካኤል አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።አርኬሰላም ለምቅዋምከ ዘልዑል ማዕረጋ ። እምቅዋመ አእላፍ እንግልጋ ። ሚካኤል መንፈስ ዘእንበለ ሥጋ ። ታድኅን ዘተመንደበ ለማዕበለ ባሕር እምጹጋ ። ወለእለ በበድው ትባልሕ በጸጋ ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    21 сент., 14:29

    "ልጆቻችን ሃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ኑሩ እርስ በእርሳችሁ ተደጋገፉ" ብፁዕ አቡነ እንጦንስበማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ዋና ክፍል ሲያስተምራቸው የነበሩ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ የቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን መስከረም ፲/፳፻፲፱ ዓ.ም የሽኝት መርሐ ግብር ማድረጉን አሳውቋል።በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል በዲ/ን እስጢፋኖስ ደሳለኝ፣ የበገና ዝማሬ በቅድመ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን ከግቢ ጉባኤ ተመርቀው በወጡ ወንድሞች የግቢ ጉባኤ ሕይወትና የግቢ ፈተናን በተመለከተ ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።በመርሐ ግብሩ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ እንጦንስ “ለተማሪዎች ሃይማኖታችሁን ጠብቃችሁ ኑሩ እርስ በእርስ ተዋደዱ ፣ተደጋገፉ” በማለት አባታዊ መልእክትና ቡራኬ በመስጠት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የመጽሐፍ ሽልማት አበርክተዋል።በመጨረሻም ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምርት ተቋማት ሲሄዱ እንዳይቸገሩ የማእከላት የግቢ ጉባኤ አድራሻ ፣ውዳሴ ማርያም፣የ፳፻፲፱ ዓ.ም የእንኳን አደረሳችሁ ፓስት ካርድ የተሰጠ ሲሆን በዕለቱ የዋና ክፍሉ ኃላፊ አቶ አማረ ምትኩ ለተማሪዎች በምትሄዱበት ሁሉ ቤተ ክርስቲያንን፣ ማኅበረ ቅዱሳንንና ግቢ ጉባኤን እንዲያገለግሉ የአደራ መልእክታቸውን በማስተላለፍ መርሐግብሩ ተጠናቋል።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    21 сент., 12:11

    ፰. የአጥቢያ ሰበካውን የሰውና የገንዘብ ኃይል በየዓመቱ እየመዘገበ ካለፈው ዓመት ጋር ያለውን ልዩነት እያነጻጸረ በሠንጠረዥ ወይም በሥዕላዊ መግለጫ ያሳያል።፱. ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር በመገናኘት ለአጥቢያው የሚያስፈልገውን አኃዛዊ መረጃ ሁሉ ይሰበስባል።፲.ሰበካ ጉባኤ የተቋቋመበትን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ ለማድረስ ተመራጭ የሰበካ ጉባኤ አባላትን እያማከረ የአጥቢያው ምእመናን የአባልነት ክፍያ በወቅቱ እንዲከፍሉ ያስተባብራል።፲፩. የቤተ ክርስቲያኗ ገቢ የሚያድግበትን ሁኔታ እያመቻቸና የሰበካ ጉባኤ አባላትን እያስተባበረ ይሠራል።
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    21 сент., 12:10

    የአኃዛዊ መረጃ ስታትስቲክስ ክፍል ሥራና ኀላፊነትዘወትር ሰኞ ፡-ቃለዓዋዲ ምን ይላል ?፩.በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ነዋሪ ለሆኑ ምእመናን ቋሚ መዛግብት ሆነው የሚያገለግሉትን:- ሀ) መዝገበ ልደትና ጥምቀት ለ) መዝገበ ሕያዋን፤መዝገበ ሙታን እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መዛግብትን ሁሉ እንዲሠራባቸው ያደርጋል።፪. የአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ስምና አድራሻ፣የትክል ዓይነትና ዘመን፣የሕንጻውን አሠራር፣ቅርጽና ዓይነቱን፣ቁመቱንና ስፋቱን አይቶና አጣርቶ ባለሙያ እያማከረ ይመዘግባል።፫. የአጥቢያውን ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናት፣ ቀሳውስት፣ መምህራን፣ሰባክያን፣ ዲያቆናት፣መዘምራንና ልዩ ልዩ ሠራተኞች ብዛት እንዲሁም የምእመናንን ብዛት በጢስ፣በቤተሰብ ፣በእድሜ፣በፆታና በትምህርት ደረጃ ለይቶ ይመዘግባል።፬.በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ የጉባኤ መምህር ካለ ስሙንና የተማሪዎችን ብዛት የትምህርቱን ዓይነት እና የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎችን ብዛት የሚማሩትንም የትምህርት ዓይነት ይመዘግባል።፭. ሕፃናት አርባ ቀንና ሰማንያ ቀን ሞልቷቸው በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ክርስትና ሲነሱ በመዝገበ ልደት፣ጥምቀትና በአጠቃላይ ለአጥቢያው ካህናትና ምእመናን በተዘጋጀው መዝገበ ሕያዋን ላይ ይመዘግባቸዋል።፮. ከዚህ አለም በሞት የሚለዩትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ስማቸውን በመዝገበ ሙታን ያሰፍራል ።፯. በዓመቱ መጨረሻ በጠቅላላ በአጥቢያው ቤተ ክርስቲያን በነዋሪነት የተመዘገቡትን ክርስቲያኖችና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብዛት እንዲሁም የተወለዱትንና በዓመቱ ውስጥ በሥራ
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    21 сент., 06:33

    ከንጉሥ ኑማርያኖስ ሴቶች ልጆች አንዲቱ ወደርሱ በመስኮት ተመለከተች ወደደችውም መልምላም ወስዳ አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰይማ አነገሠችው ። ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖታትን አመለከ ቅዱስ ፋሲለደስም ሰምቶ እጅግ አዘነ የመንግሥትንም አገልግሎት ተወ ።ከዚህም በኋላ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው የጠላቶቻቸውንም አገሮች አጥፍተው ደስ ብሏቸው ተመለሱ ። ነገር ግን የነገሠው ዲዮቅልጥያኖስ የክብርባለቤት ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን አቁሞ አገኙት እጅግም አዘኑ ተቆጥተውም ተነሡ ሰይፎቻቸውን መዝዘው ዲዮቅልጥያኖስን ገድለው የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደዱ ፋሲለደስም ከዚህ ሥራ ከለከላቸው ።ከዚህም በኋላ ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን፣ ሠራዊቱን፣ አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው ሁሉም እንዲህ ብለው መለሱለት አንተ በምትሞትበት ሞት እኛ ከአንተ ጋር እንሞታለን በዚህም ምክርበአንድነት ተሰማሙ ።ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብርይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና ።የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኀርማኖስም ወደ ግብጽ አገርይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲአሠቃዩአቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር፣ አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ፣ ገላውዴዎስ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    21 сент., 06:31

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥራ አንድ በዚች ቀን ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸውና መካሪያቸው የሆነ ቅዱስ ፋሲለደስ በሰማዕትነት አረፈ ።እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት ። ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት ።ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ ፋሲለደስን እኅት አግብቶ ዮስጦስን፣ ገላውዴዎስን፣ አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው ። የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለቅዱስ ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ ።በዚያም ወራት የቊዝና የፋርስ ሰዎች የሮምን ሰዎች ሊወጓቸው በላያቸው ተነሡ ያን ጊዜ የንጉሥ ልጅ ዮስጦስን የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስን ከጦርሠራዊቶቻቸው ጋር ለውጊያ ላኳቸው ።ንጉሡ ኑማርዮስም ሌሎች ጠላቶች በተነሡበት በኩል ለጦርነት ሒዶ በውጊያው ውስጥ ሞተ የሮም መንግሥትም የሚጠብቃትና የሚመራት የሌላት ሆነች ።እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት ስለ ጦርነት ለመደራጀት የሮም ሰዎች ከሀገሩ ሁሉ አርበኞች የሆኑ ሰዎችን ሰበሰቡ ከውስጣቸውም ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አለ ። እርሱንም መኳንንቱ ወስደው በመንግሥት ፈረሶች ላይ ባልደራስ አድርገው ሾሙት እርሱም በጠባዩና በሥራው ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ ነበር ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    20 сент., 04:37

    በጎዳናውም እየተጓዘ ሳለ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ወንበዴዎች ተነሡበት ሊሸሽም ወደደ ከዚያቺም ሥዕል መንገድህን ሒድ የሚል ቃል ወጣ የተከተለውም ሳይኖርመንገዱን ተጓዘ ። ሁለተኛም ነጥቆ ሊበላው አንበሳ ተነሣበት ያን ጊዜም ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረው ።አባ ቴዎድሮስም ይህን ሁ ድንቅ ተአምር በአየ ጊዜ ያቺን ሥዕል ወደ አገሩ ሊወስዳት ወደደ ግዛልኝ ላለችው መበለት ይሰጣት ዘንድ አልፈለገም ።ከዚህም በኃላ በመርከብ ተሳፍሮ በሌላ አቅጣጫ ሲጓዝ ታላቅ ነፋስ ተነሣበት ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያም ወሰደው ከመርከቡም ወርዶ ከብዙ እንግዶች ጋርወደዚያች መበለት ቤት ሔደ ማንነቱንም አልገለጠላትም እርሷም አላወቀችውም ።በማግሥቱም ተሠውሮ ወጥቶ ወደ አገሩ ሊሔድ በፈለገ ጊዜ የቅጽሩን ደጃፍ አጥቶ ሲያጥመሰምስ ዋለ በመሸ ጊዜም ወደ ማደሪያው ተመለሰ ። ያቺም መበለት በአየችው ጊዜ ታደንቃለች እንዲህም ሁኖ እስከ ሦስት ቀን ኖረ በመሸ ጊዜ በሩን ያየዋል ነግቶ መሔድን ሲሻ የበሩ መንገድ ይሠወረዋል ። ያቺም መበለት ያዝ አድርጋ አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን ስትቅበዘበዝ አይሀለሁና ምን ሆነህ ነው አለችው ።ከዚህም በኃላ ከዚያች ሥዕል የሆነውን ሁሉ ነገራት ራሱንም ገለጠላት ። ያቺንም ሥዕል ሰጣት ተቀብላም የተጠቀለለችበትን ልብስ ፈታች ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች ። ከደስታዋም ብዛት የተነሣ የዚያን መነኩሴ እጆቹንና እግሮቹን ሳመች ።ከዚህም በኃላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር የምትቀመጥበትን አዘጋጅታ አኖረቻት ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    20 сент., 04:36

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዐሥር በዚች ቀን ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምርተገለጠ ።ይቺንም ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው ይባላል ። ወደ ጼዴንያ አገርም የመጣችበት ምክንያት አንዲት ስሟ ማርታ የሚባል መበለት ሴት ነበረችና ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ናት ። አምላክን የወለደች እምቤታችን ድንግል ማርያምንም እጅግ ትወዳት ነበር ። በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላታለች ።በአንዲት ቀንም ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኩሴ ከእርሷ ዘንድ እንግድነት አደረ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግሥቱም ስተሸኘው አባት ሆዮ የምትሔደው ወዴት ነው አለችው ። እርሱም በከበሩ ቦታዎች ውስጥ ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም እሔዳለሁ አላት እርሷም ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ግዘሰልኝና በመመለሻህ ጊዜ አምጣልኝ አለችው ። እርሱም በራሴ ገንዘብ ገዝቼ አመጣልሻለሁ አላት ።ከዚህም በኃላ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ ከቅዱሳት መካናት ተባረከና ሥዕሏን ሳይገዛ ወደ ጎዳናው ተመለሰ ። ያን ጊዜም ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰማ ወደ ገቢያም ተመልሶ ላሕይዋና መልኳ ያማረና የተወደደ የሆነ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ገዛት በሐርና በንጹሕ ልብስም ጠቀለላት ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    19 сент., 06:22

    ከዚህም በኋላ መኰንኑ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ አዘዘ የሕይወት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ። የቅዱስ ቢሶራ ሥጋው ግን ንሲል በሚባል አገር እስከ ዛሬ ይኖራል ።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።አርኬሰላም ለቢሶራ አቃቤ መርዔቱ ለልዑል ። ኤጲስቆጶስ ዘሀገረ መጺል ። ወሰላ ካዕበ ወእሊአሁ መድበለ ። ቢስኮስ ወሰናቢክስ ወቴዎድሮስ ኃያል ። ወተሰነዓዉ ኅቡረ በገድል ።
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    19 сент., 06:21

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ዘጠኝ በዚች ቀን መጺል የምትባል አገር ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አባት አባ ቢሶራ በሰማዕትነት አረፈ::ይህም ቅዱስ በግብጽ አገር እግዚአብሔርን በምትወድ መጺል በምትባል ከተማ ኤጲስቆጶስ ሆነ ። ዲዮቅልጥያኖስም ነግሦ ክርስቲያኖችን በሚያሠቃያቸው ጊዜ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ ይህ አባት ወደደ ።ሕዝቡንም ሀሉ ሰብስቦ በቤተ መቅደሱ ፊት በዐውደ ምሕረቱ አቆማቸው ሊጠብቁት የሚገባውን ለጽድቅ የሚያበቃቸውን ትእዛዝ ሁሉ አዘዛቸው ። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም ደሙን ማፍሰስ እንደሚሻ ነገራቸው ይህንንም በሰሙ ጊዜ ታላቆችም ታናሾችም በላዩ አለቀሱ ።የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ የምትተወን ምን ያደርግልሃል እኛስ እንድትሔድ አንለቅህም አሉት ሊይዙትም ቃጡ ግን አልተቻላቸውም ተውትም እርሱም ወደ ክብር ባለቤት ክርስቶስ አደራ አስጠበቃቸውና ሰላምታ ሰጥቷቸው ከእነርሱ ዘንድ ወጥቶ ተጓዘ ። እነርሱም መሪር ልቅሶን እያለቀሱ ሸኙት ።ስማቸው ቢስኮስ ፊናቢክስ ቴዎድሮስ የሚባሉ ኤጲስቆጶሳት አብረውት ሔድ መኰንኑ ወደ አለበት አገርም ደርሰው የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ። እርሱም መኰንኑ አሠቃያቸው ኤጲስቆጶሳትም እንደሆኑ አውቆ ሥቃያቸውን አበዛ እሊህ አባቶች ግን በታላቅ ትዕግሥት የጸኑ ናቸው ። ክብርይግባውና ጌታችን ክርስቶስ ያጸናቸዋልና ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    18 сент., 17:22

    ቴሌግራም፦👇https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia ፌስቡክ፦👇 https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacenter ቲክቶክ:- 👇 tiktok.com/@mk.aa.maekel.mediaየማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    18 сент., 08:19изменён

    ቴሌግራም፦👇https://t.me/MkAddisAbabaCenterMedia ፌስቡክ፦👇 https://www.facebook.com/MKidusanaddisababacenter ቲክቶክ:- 👇 tiktok.com/@mk.aa.maekel.mediaየማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    18 сент., 06:01

    ሕፃናትንም ከገደላቸው በኋላ ዮሐንስ ክርስቶስ እንደሆነ ሄሮድስ አሰበ ተጠራጠረ ከአባቱ ከዘካርያስ ዘንድ ሕፃኑን ይሹ ዘንድ ወታደሮቹን ላከ ዘካርያስም ሕፃኑ ያለበትን ወይም እናቱ ያለችበትን እኔ አላውቅም አለ ። ሄሮድስም ልጅህን ካላመጣህልኝ እኔ እገድልሃለሁ አለው ። ዘካርያስም ከእርሱ ዛቻ የተነሣ አልፈራም ወታደሮቹንም አዝዞ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል ገደሉት ክብርይግባውና እግዚአብሔርም ሥጋውን ሠወረ ደሙ ግን እንደ ደንጊያ ሆነች ።ካህናቱና ሕዝቡ እንደ ልማዳቸው ለጸሎት በመጡ ጊዜ ከካህናት አንዱ ወደ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገባ ። የረጋ ደምን አገኘ ከመጠዊያውም እንዲህ የሚል ቃልን ሰማ እነሆ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ተገደለ የሚበቀልም እስሚመጣ ደሙ ስትጮኽ ትኖራለች ።እንዲህ የሚልም አለ ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት የሆነ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ይህ አይደለም ያ አልተገደለም በዕድሜው ኡረት በሚባል አገር ሞተ እንጂ ሥጋውም በዚያ ያለ ጥፋት ተገኝቶ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለታል ። የዚህ ዘካርያስ ግን ሥጋው አልተገኘም ስለ መገደሉ የደሙ ድምፅ ምስክር ሆነ እንጁ ።ደግሞ እንዲህ ተባለ ሄሮድስ ሕፃናትን በገደላቸው ጊዜ ከአይሁድ አንድ ሰው መጥቶ የእግዚአብሔር መልአክ ትወልዳለህ ብሎ ነግሮት ለዘካርያስ ልጅ ተወልዶለታል ምናልባት እርሱ ክርስቶስን ይሆን አለው ። ስለዚህ ሄሮድስ ሕፃኑን ዮሐንስን ይገድሉት ዘንድ ወታደሮችን ላከ ።ዘካርያስም ወታደሮችን እንዲህ አላቸው ሕፃኑን እኔ ወደሌላ ቦታ ወስጄዋለሁ ከእኔ ጋራ መጥታችሁ ራሳችሁ ከዚያ ቦታ ውሰዱት ወደ ቤተ መቅደስም እስከ አስገባቸው ድረስ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    18 сент., 06:00

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ስምንት በዚች ቀን የዓመቱ ወሮች መቍጠሪያ የሚሆን የመጀመሪያ ኮከብ ይወጣል ይኸውም መናዝል የሚለው የዐሥራ ሁለቱ ወር ኮከቦች ከእልሐመል እስከ ሑት ያሉ መገብተ አውራኀ አሉ ምግብ ናቸውን ፈጽመው በዚች ቀን እንደ ገና አንድ ብለው የሚጀምሩበት ነው ።በዚችም ቀን የበራክዩ ልጅ ካህንና ነቢይ የሆነ የከበረ ዘካርያስ በንጉሥ ሄሮድስ እጅ በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም ካህን ስለ ልጁ ዮሐንስ መወለድ የመላእክት አለቃ ገብርኤል በነገረው ጊዜ ነገሩን አምኖ አልተቀበለም ። ስለዚህም ሕፃኑ እስቲወለድ ዲዳ ትሆናለህ አለው ። በተወለደም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው የልጁንም ስም ዮሐንስ ነው ብሎ ጻፈ ። እርሱና ሚስቱ በእግዚአብሔርሕግ ያለ ነቀፋ የጸኑ ደጎች እንደሆኑ የከበረ ወንጌል ስለዚህ ምስክር ሆኗል ።ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም በተወለደ ጊዜ ሊሰግዱለት የጥበብ ሰዎች መጡ ። ሄሮድስም ስለ መንግሥቱ ፈራ ደነገጠም ። ስለዚህም ጭፍሮቹን ልኮ በይሁዳ አገር የቤተ ልሔምንና የገሊላን ሁሉንም ሕፃናት ዕድሜያቸው ሁለት ዓመት የሚሆናቸውን ከዚያም የሚያንሱትን ገደላቸው ሰነፍ የሆነ ሄሮድስ ክርስቶስን ከሕፃናት ጋር እንደ ሚገድለው አስቦ ነበርና ።ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጾለት ስለአዘዘው ጌታችን ሕፃኑንና እናቱን እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብጽ አገርመጡ ። ኤልሳቤጥ ግን ሕፃኗን ዮሐንስን ይዛ ወደ ዱር ወጣች ወደ ሲና በረሃም ሸሸች በዚያም ሕፃኗን እያሳደገች ሰባት ዓመት ኖረች
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    17 сент., 08:13изменён

    ✝️ይህ የመስከረም ወር ዐሥረኛው ቀን የእስራኤላውያን የንስሐ መግቢያ የጾም ቀን አድርገው ሲያከብሩት የነበረና በሕገ ኦሪት ተወርሶ በኢትዮጵያም የሚከበር እንደነበረና በኋላ ግን በዘመነ ሐዲስ የዐፄ መስቀል በዓል እንደተተካበት መዛግብት ያስረዳሉ፡፡✝️የዐፄ መስቀል በዓል ሕዝቡ ሁሉ ነገሥታቱን ‹‹እንኳን አደረሳችሁ›› ለማለት ወደ ነጉሥ ከተማ የሚወጣበትና መሪውን የሚያገኝበት በሀገር ላይ ስላለው ሁኔታም የሚወያይበት ቀን ሆኖ ይከበር ነበር፤ በዓሉም የሚከበረው መስከረም ፳፭ ቀን ነበር፡፡ (ክብረ በዓላት ገጽ ፶፬)✝️ቆይቶ ግን በዐሥረኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጌታችን ግማደ መስቀል በዐፄ ዳዊት አማካኝነት ከአሌክሳንደርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባው መስከረም ዐሥር ቀን ስለነበር የተቀጸል ጽጌ በዓል የዐፄ መስቀል በዓል እየተባለ ቀኑ ከመስከረም ፳፭ ወደ መስከረም ፲ ተዛውሮ ሲከበር ኖሯል፡፡✝️ምክንያቱም ንጉሡ መስቀሉን መስከረም ፲ ቀን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው ሲገቡ በኢትዮጵያና በአውራጃዎቿ ሁሉ ብርሃን ሆነ፡፡ በዚህም ምክንያት ሴቱም ወንዱም፣ ትንሹም ትልቁም፣ ሕዝቡም አሕዛቡም በፍጹም ደስታ በዓል አደረጉ፤ ዐፄ ዳዊትም መስከረም ፲ ቀን ከሠራዊታቸው ጋር ደስ እያላቸው በዓሉን አከበሩ፤ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እየረገጡ በሆታ ካህናቱ በዝማሬ ‹‹መስቀል ኃይልነ፣ መስቀል ጽንዕነ›› እያሉ ከፍ ባለ ደስታ በዓሉን አከበሩ፡፡✝️ይህንንም ልማድ አድርገው በኢትዮጵያ የነገሡ ነገሥታት ሁሉ በዓልን ሲያከብሩት ኖረዋል፡፡ ስሙንም ‹‹ዐፄ መስቀል በዓል›› ብለው ሰይመውታል፡፡ (መጽሐፈ ጤፉት ገጽ ፶-፶፩፣
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    17 сент., 08:11изменён

    ተቀጸል ጽጌ ማለት ምን ማለት ነው ? ለምንስ ይከበራል ? መቼ ተጀመረ ?ዘወትር ሐሙስ ፡-እናስተዋውቅዎ✝️‹‹ተቀጸል ጽጌ›› ማለት ‹‹አበባን ተቀዳጅ›› ማለት ሲሆን በዘመነ አክሱም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በነበሩት በዐፄ ገብረ መስቀል የተጀመረ በዓል ነው፡፡ ይህ የተቀጸል ጽጌ በዓል የክረምቱን መውጣት መሠረት አድርጎ መስከረም ፳፭ ቀን የሚከበር በዓል ሲሆን ሕዝቡ በክረምቱ ምክንያት፣ በዝናቡ ብዛት፣ በወንዙ ሙላት ተለያይቶ ይከርም ነበርና ለንጉሠ ነገሥቱ የአበባ አክሊል/ጉንጉን/ ሠርቶ በማምጣት የሚያበረክትበት በዓል ስለነበረ ‹‹ተቀጸል ጽጌ ገብረ መስቀል ሐፄጌ፤….ዐፄ ገብረ መስቀል አበባን ተቀዳጅ›› እየተባለ ይዘመር ነበር፡፡✝️ምንም እንኳን በታሪክ ደምቆ የሚታወቀው በዚህ መልኩ ቢሆንም ቀደም ያለ የታሪክና የትውፊት ውርርስ ያለው በዓል ስለመሆኑ ይነገራል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤልን በሰባተኛው ወር (ኤታኒም/መስከረም የመጀመሪያው ቀን ከሚከበረው በዓል መጥቅዕ /የመለከት በዓል/ በኋላ በዐሥረኛው ቀን የሥርየት በዓል አድርገው እንዲያከብሩት አዝዟቸው ነበር፡፡ (ዘሌ. ፳፫፥፳፭)
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    17 сент., 06:33

    ደግሞ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቄርሎስ ከተናገረው የአካላዊ ቃል ተዋሕዶ እንደ ነፍስና ሥጋ እንደ እሳትና ብረት ተዋሕዶ ነው ያለውን ቃል ምስክር አድርጎ በማምጣትም አስረዳ ። እሌህም የተለያዩ ሁለቱ ጠባዮች ስለ ተዋሕዷቸው አንድ ከሆኑ እንዲሁም የክብር ባለ ቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አንድ መሲሕ አንድ ጌታ አንድ ባሕርይ አንድ ምክር ነው እንጂ ወደ ሁለት አይከፈልም አላቸውከዚያም ከተሰበሰበው ጉባኤ ውስጥ ማንም ሊከራከረው የደፈረ የለም ከውስጣቸውም የእግዚአብሔር ጠላት ስለሆነው ስለ ከሀዲው ንስጥሮስ በኤፌሶን ጉባኤ አስቀድሞ ተሰብስበው የነበሩ አሉ ።ወደ ንጉሥ መርቅያኖስና ወደ ሚስቱ ንግሥት ብርክልያ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ከአባ ዲዮስቆሮስ በቀር ስለ ሃይማኖት ትእዛዛችሁን የሚቃወም የለም ብለው ነገርሠሩበት ።ቅዱስ ዲዮስቆሮስንም ወደ ንጉሥ አቀረቡት ከእርሱም ጋር ታላላቅ ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ከጉባኤው የሆኑ ነበሩ ከጥዋትም እስከማታ እርስበርሳቸው ሲከራከሩ ዋሉ ። የከበረ ዲዮስቆሮስም የቀናች ሃይማኖቱን አልለወጠም ንጉሡና ንግሥቲቱ በእርሱ ተቆጥተው እንዲደበድቡት አዘዙ ስለዚህም ደበደቡት ጽሕሙን ነጩ ጥርሶቹንም ሰበሩ እንዲህም አደረጉበት ።ከዚህም በኋላ የተነጨውን ጽሕሙን ያወለቁትንም ጥሩሱን ሰብስቦ ወደ እስክንድርያ አገር ላካቸው እነሆ የቀናች ሃይማኖት ፍሬ ይህ ነው አላቸው ። ለጉባኤውም የተሰበሰቡ ኤጲስቆጶሳትአሉት በዲዮስቆሮስ ላይ የደረሰውን መከራ በአዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ በእርሱ የደረሰ በእነርሱ ላይ እንዳይደርስ ስለዚህም ከመናፍቁ ንጉሥ ከመርቅያኖስ ጋር ተስማሙ
  • ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ

    17 сент., 06:31

    አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም መስከረም ሰባት በዚች ቀን የከበረና የተመሰገነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮስቆሮስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃያ አምስተኛ ነው ።ስለ ቀናች ሃይማኖትም ታላቅ ተጋድሎን ከተጋደለ በኋላ ዕረፍቱ በተሰደደበት በደሴተ ጋግራ ሆነ ። ይህም እንዲህ ነው ንጉሥ መርቅያኖስ ወደ ሰበሰበው ጉባኤ በጠሩት ጊዜ ሲደርስ ብዛታቸው ስደስት መቶ ሠላሳ ስድስት የሆነ ታላቅ ጉባኤን አየ ። አለ እንዲህም ይህ ታላቅ ጉባኤ እስቲሰበሰብ ድረስ በሃይማኖት ላይየተገኘው ጉድለት ምንድን ነው ።ይህ ጉባኤ የተሰበሰበው በንጉሥ ትእዛዝ ነው አሉት ። እንዲህም አላቸው ይህ ጉባኤ ስለ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆን ኖሮ እኔ ተቀምጬ እግዚአብሔር በሰጠኝ በአንደበቴ እናገር ነበር ግን የዚህ ጉባኤ መሰብሰብ በንጉሥ ትእዛዝ ከሆነ የሰበሰበውን ጉባኤ ንጉሡ እንዳሻው ይምራ ።ከዚህም በኋላ አንዱን ክርስቶስን ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ሁለት ምክርየሚያደርግ የክህደት ቃል በውስጡ የተጻፈበትን የሮሜ ሊቀ ጳጳሳት ልዮን የላከውን ደብዳቤ የከበረና የተመሰገነ ዲዮስቆሮስ ቀደደ ።በመንፈስ ቅዱስ የሚናገር የከበረ ዲዮስቆሮስም በጉባኤው ፊት እንዲህ ብሎ አስረዳ ሰው እንደመሆኑ ወደ ሠርግ ቤት የጠሩት ጌታችን ክርስቶስ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ለውጦ ወይን ያደረገው ከሀሊ ስለሆነ ሰውነቱና መለኮቱ በሥራው ሁሉ የማይለይ አንድ ነው ።
    Иллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያИллюстрация к посту канала ማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ሚዲያ