Последние посты

ነገረ ወንጌላውያን
21 сент., 09:21



ነገረ ወንጌላውያን
21 сент., 09:21
አንድ ጥሩ መጽሐፍ በቅርቡ ታትሟል። ጥሩ የተባለበት ምክንያት የሚያነሳው ርእሰ ጉዳይ ነገር ነው። More than Intelligence ይሰኛል መጽሐፉ። ጥሩ ሙግትን አንግቧል። ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ፈርጆ ከመነሳት ይልቅ በተላያዮ ማእቀፎችና አውዶች በመመልከት ስነ ሰብእ ላይ የሚያሳድረውን የብያኔና የመረዳት ዳራ ይዳስሳል። ጸሐፊው ያነሳውን ርእሰ ጉዳይ ግልጽና እጥር ባለ መልኩ የማቅረብ ክህሎቱ እንዲሁም የበይነ ዲሲፒሊኒያዊ አቅሙ ላቅ ያለ ነው። መጽሐፉን ለማንበብ ትጓጉ ዘንድ ይህንን ብሏል:-“ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የብዙዎችን ትኩረት የሳበው ሰው ስራሽ አስተውሎት (AI) በአንዳንዶች ዘንድ ለቀጣዩ የሰው ልጆች ታሪክ ምዕራፍ እንደ ፈር ቀዳጅ የተስፋ ምንጭ ሲቆጥሩት በሌላ ጎኑ ደግሞ የሰው ልጆችን ለከፋ ጭቆና እና ጥፋት እያሰናዳ ያለ አደገኛ ኃይል አድርገው በዓይነ ቁራኛ የሚመለከቱት እና የማስጠንቀቂያ ደውል የሚደውሉም ተበራክተዋል። More Than Intelligence የተሰኘው መጽሐፍ ከእነዚህ ሁለት ፅንፎች ባሻገር ቴክኖሎጂው ስለ ሰው ልጅ ማንነት የሚገልፀው አንድ እውነት ላይ ያተኩራል። ከሰው የተገኘው ይህ ፈጠራ ፈጣሪውን ሰው መልሶ ከመቅረጽ ባሻገር ስለ ፈጣሪው ማንነት የመናገር አቅምም አለው።ማሽኖች ማመዛዘን መተንተን መፍጠር እና በአንድ ወቅት የሰዎች ብቻ ክህሎት ናቸው ተብለው ይታሰቡ የነበሩ ተግባራትን ማከናወን ከቻሉ እንዲሁም "አእምሯዊ ብልህነትን" (intelligence) መተካት ከተቻለ እኛን ታድያ 'ሰው' የሚያደርገን ምንድን ነው ብለን እንድንጠይቅ ይደርገናል። ይህ መፅሀፍ
ነገረ ወንጌላውያን
10 сент., 16:51
#አንተ_ነህ_ወይስ_እነርሱ_ናቸው?አምላኬ ሆይ፥ ልጠይቅህ ነው፤ አትቀየመኝ። ያለፈው ዓመት በዚህ ጊዜ በስምህ በርካታ ተስፋዎች ተነግሮኝ ሁሉንም አምኛቸው በመጠበቅ ከርሜ ነበር። የሰማኋቸው የበረከትና የጥርመሳ እንጂ የፍርድና የፊዳ ቃሎች አልነበሩም። እኔ በፊትህ ጽድቅ የሌለኝ፣ በጎነት የማይገባኝ ምስኪንና ድኩም ኀጢእ እንደሆንኩ ስለማምን፥ "ፊዳ ይመጣብሃል" ብትለኝ ሳልቀየም ተቀብዬ ሱባኤ ለመግባት ፈቃደኛ ነበርኩ። የተነገረኝ ግን ፍርድና ፍዳ ሳይሆን፥ በረከትና ብልጽግና ነው። ካንተ ጋራ የመሟገት ጽድቅ የሌለኝ ኀጢእ በመሆኔ፥ አንተን ለኢፍትሓዊነት የመክሰስ መብት ባይኖረኝም፥ በተነገረኝ ቃልና ባሳለፍኩት ሕይወት መካከል የነበረው ተቃርኖ፥ ቃሉን ይዤ እንድጠይቅህ ዕድል ይሰጠኛል!"የመሻገር ዓመትህ ነው" ተብዬ፥ በኑሮ ውጣውረድና በችጋር ማዕበል ሰጥሜ አሳልፌያለሁ። "የጥርመሳ ዓመትህ ነው" ተብዬ የኑሮ ውድነትና መከራ ጠርምሶኝ ከርሜያለሁ። "የድል ዘመንህ ነው" ተብዬ የሽንፈት ጽዋ ስጎነኝ ሰንብቻለሁ። "የብልጽግና ዓመትህ ነው" ተብዬ በድኽነት ደቅቄያለሁ። ይህ አልበቃ ብሎ ይሀው ዘንድሮም ተመሳሳይና ልዩ ልዩ ተስፋዎችና ምኞቶች በስምህ በየአዳራሹ እየዘነቡ ነው!!አምላኬ ሆይ፥ አትቀየመኝና ልጠይቅህ። አንድ ምስኪን ተስፈኛ ድኻ በተስፋና በምኞት ማእበል እያላተምክ ማንገላታትህ ለምን ነው? ማነው እየዋሸኝ ያለው? አንተ ነህ ወይስ እነርሱ? ቃሉ ትዋሽ ዘንድ ሰው እንዳልሆንክ፥ ሐሰትን ትናገር ዘንድ ሥጋ ለባሽ እንዳልሆንክ ይናገራል።አንተ ሐሰተኛ እንዳልሆንክ፥ ቃልህም ሐሰት እንዳልሆነ አውቃለሁ፤
ነገረ ወንጌላውያን
5 сент., 15:30
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከአለምአቀፍ ሜኖናይት ኮንፍረንስ (#MWC) አባልነት መውጣቷን አሳወቀች።የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እያካሄደች በምትገኘው 95ኛው ጠቅላላ መሪዎች ጉባኤ ከአለምአቀፍ ሜኖናይት ኮንፍረንስ (Mennonite World Conference /MWC) ለመውጣት ወሰነች።በጉባኤው ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለፉት 59 አመታት በዚህ ተቋም ውስጥ የነበራት ተሳትፎና ግንኙነት በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ከዚህ ጥናት ጋር የቤተ ክርስቲያኒቱ ስነመለኮት ኮምሽን ያዘጋጀው ምክረሃሳብም ተካቷል።በዚህ መሠረት ጠቅላላ ጉባኤው በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ (መአመጉ) የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ በመቀበል ቤተ ክርስቲያኒቱ አባል ሆና ለ59 አመታት ከቆየችበት የሜኖናይት አለምአቀፍ ኮንፍረንስ (MWC) እንድትወጣ አጽድቋል።የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ከተቋሙ ጋር ምንም እንኳ የገንዘብና የሥራ ግንኙነት ባይኖራትም በዚህ ግብረሰዶማዊነትን በአካታችነት በተቀበለ ተቋም ውስጥ አባል በመሆኗ ምክንያት ላለፉት ወራት ስሟ በተለያየ መንገድ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል። ከዚህ ጋር በተገናኘ የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር በቀጣይ ማብራሪያ የሚሰጥ ይሆናል።#የእግዚአብሔርን_ድንቅ_ስራ_ከትውልድ_ወደ_ትውልድ_እናስተላልፋለን! መዝሙር 145፥4
ነገረ ወንጌላውያን
4 сент., 12:53



ነገረ ወንጌላውያን
29 авг., 07:20

2,029Открыть в Telegram
ነገረ ወንጌላውያን
29 авг., 07:20
Why do false prophets and false apostles shun preaching the cross of Christ? ሐሰተኛ ነቢያትና ሐሰተኛ ሐዋርያት ስለ ክርስቶስ መስቀል የማይሰብኩት ለምንድር ነው?በርካታ ጥቃቅን ምክንያቶች ቢኖሩም፥ ዋናዎቹ ሁለት ናቸው። አንዱና ትልቁ ምክንያት የሰይጣን አገልጋይነታቸው ነው። ሰይጣን ይህ የመስቀሉ እውነት እንዲነገር አይፈልግም። ምክንያቱም፥ሀ. መስቀሉ የሰይጣን የክሽፈቱና የሽንፈቱ፥ የድቀቱና የውርደቱ ስፍራና ታሪክ ነው። የራስን ሽንፈት ታሪክ ደጋግሞ መስማት የሚፈልግ ማን ነው? ማንም። ሰይጣን ይህንን መስማት አይፈልግም። ስለዚህ ምንደኞቹ ይህንን እንዲሰብኩ የተፈቀደ አይደለም። መስቀሉ ሰይጣን ድል የተነሣበትን ያህል፥ ከድል ነሺው ጌታ የተነሣ እኛም ድልን የተቀዳጀንበት ታሪክና ስፍራ ነው። መስቀሉ፥ የመስቀሉ ቃል ራሱ ኃይል ነው። የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና። 1ቆሮ. 1፥18።ለ. መስቀሉ የክስ ጽሕፈት የተጠረቀበት፥ የኃጢአት ዋጋ በሙሉ የተከፈለበት፥ ለሚቀበሉት የጽድቅ እና የኩነኔ ልውውጥ የተደረገበት ስፍራና ታሪክ ነው። በወለድ የሚኖር አበዳሪ የባለ ዕዳ ዕዳ መከፈሉን እንደመስማት የሚያስደነግጠው መሪር ኀዘን የለም። ሰይጣን ይህንን መርዶ መስማት አይፈልግም። በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል። ቆላ. 2፥14።ሐ. መስቀሉ ዕርቅ የተፈጸመበት፥ ሰላም የተደረገበት፥ ጥል የተገደለበት ስፍራና ታሪክ ነው።
ነገረ ወንጌላውያን
28 авг., 18:23
««ኀጢአተኛውን የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ፡ ርቱዕ ነገረ ድኅነት» የተሰኘው መጽሐፍ፣ ስለ ሰው ድኅነት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሙሉውን እውነት አጠቃልሎ የያዘና ለኹሉም አንባቢ ታሳቢ ተደርጎ የተከተበ ታላቅ የወንጌል መሣሪያ ነው።“ኀጢአተኛውን የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ" የተሠኘው ይህ መጽሐፍ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ የተገኘው ጽድቅና ድኅነት የሚገኝበትን የጸጋ መንገድ፥ በጠንካራ የቅዱሳት መጻሕፍት ብርሃንና ነገረ መለኮታዊ ትንተና የሚገልጥ ሲኾን፥ ለበርካቶች የእውነት ብርሃን ይኾን ዘንድ ጸሎቴ ነው"! ስለዚህ የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ሐዋርያ ዮሐንስ እንዳለው ሰዎች በክርስቶስ አምነው የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዴት እንደሚወርሱ የሕይወት መንገድን ማሳየት ነው። “ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል (ዮሐ. 20፥31)።” በተጨማሪም ሰው በፀጋ ከዳነ በኋላ እንዴት በክርስቶስ እግዚአብሔር እየመሰለ መኖርና መመላለስ እንዳለበትም ያሳያል።የምርቃት ቀን፦ቀን፦ ጳጉሜ 1 ቦታ፦ ሳርቤት፣ አዳምስ ፓቪሎን (Adams Pavilion) — ዐዲስ ሕይወት አዳራሽ ሰዓት፦ የኅብረቱን ፕሮግራም ሙሉ ቀን ሲኾን፣ የምርቃቱ መርሐ ግብር ሰዓት ግን ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ይኾናል፤ መጽሐፉን በቀኑ ከጧቱ ጀምረው ማግኘት ይችላሉ።


ነገረ ወንጌላውያን
23 июл., 06:29



ነገረ ወንጌላውያን
23 июл., 06:29
ሐሰተኛ - መንጋሐሰተኛ መንጋ (ምዕመን) ማለት ምኞቱን እና ምቾቱን ብቻ የሚከተል ለቃለ እግዚአብሔር ባዕድ የሆነ በጭፍን የሚራመድ ሃይማኖተኛ መሳይ ህዝብ ነው። ሐሰተኛ መንጋ አገልጋዩ ማንም ይሁን ፣ ምንም ያድርግ ለመመርመር ፍላጎት የለውም። "አንደ ገዛ ምኞታቸው አስተማሪ ያከማቻሉ" እንዲል ቃሉ መንጋው "ብቻ ምኞቴን ይስበክልኝ አንጂ እከተለዋለሁ" ብሎ ማንንም የሚከተል እውነትን የተቀማ አእምሮውንም የጣለ ህዝብ ነው። እንዲያውም ምኞቱን በደንብ አድርጎ የሚሰብክለትን ካገኘ ያንን ሰው ከማምለክ ወደ ኋላ አይልም።ይህ ሐሳዊ መንጋ (ምዕመን) ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወድ "በምንም በኩል አድርገህ ብቻ ወደ ስጋዊ ምኞቴ አድርሰኝ" የሚል ፣ ጠንቁለህም አስደግመህም አስመትተህም ገንዘብ እንዳገኝ እርዳኝ የሚል በምኞቱ የሰከረ ስለ ወንጌል፣ ስለ ነፍሳትም ሆነ ስለ ትውልድ ምን ግዴ የሆነ ህዝብ ነው።መንጋው" የምኞቴ ሰባኪዎች ናቸው" የሚላቸውን ሐሳውያን እንድትነካበት ፈፅሞ አይፈልግም። ሰባኪዎቹን እና ተንባዮቹን ስትቃወምበት ከምኞቱ ፍፃሜ ያዘገየኸው ፣ ተስፋዬ ብሎ የጨበጠውን የነጠቅኸው ስለሚመስለው ይቆጣል (ሰዎቹም በእኔ በኩል ነው በረከትህ ብለውት የለም?)። ስለዚህ ይሰድብሃል ይዝትብሃል ያስፈራራሃል። የሚገርምህ የምኞቱን ሰባኪዎች ደጀን ሆኖ የሚጠብቀውም ራሱ መንጋው ነው። ሐሳውያኑም ይህቺን ያውቃሉ። መንጋውን እንደ ጫካ ተጠቅመውም ጤናማው ትምህርት ላይ መርዛቸውን ይተኩሳሉ። ወንጌልን በመበከል የአባታቸውን የዲያቢሎስን ፈቃድ ይፈፅማሉ።ታዲያ አሳዛኙ ጉዳይ ግን እንዲሀ ያለው የሐሳውያን
ነገረ ወንጌላውያን
6 июл., 21:55



ነገረ ወንጌላውያን
6 июл., 21:55
አናጓራም፣ አናገሳምም!የምድራችን ሐሰተኛ ነቢያትና ሐዋሪያት ዳግም "ለኢትዮጵያ አግሱ" (ወይም ምናልባት አጓሩ!) በሚል ርዕስ በነሐሴ ወር በምዝገባ (ማለትም በክፍያ) የሚገባባት "ልዩ" ኮንፍራንስ ማዘጋጀታቸውን አውጀዋል። በዚህ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ መርዙን እንዲረጭ የተጠራው ሰው ደግሞ በዘመናችን የሐሰት ትምህርቶች ቁንጮ የሆኑ ሕፀጾችን ከሚያስተምሩት አንዱ የሆነው "መጋቢ" ጆን አኖሲኬ ነው።ሐሰተኛው ሰባኪ አኖሲኬ ስፕሪት ረቨሌሽን የሚባል የቤተሰብ ኩባንያ "ቤተ ክርስቲያን" በማሰኘት መሥራች ነው። ራሱን የክርስቶስ ባሪያ ብሎ ይጠራል። ሕዝቡን ደግሞ የራሱና የቤተ ሰብ ኩባንያው ባሪያ አድርጎ ይገዛል።ምክንያቱም፦ የእኛው ሐሰተኛ ነቢያትና ሐዋሪያት እንደሚያደርጉት ሁሉ የግል ኩባንያቸው ንብረት በቤተሰብ የተጠበቀ ነው። በወታደር ልብስ በአብዛኛው ከባልዋ ጋር የምትታየው ሚስቱ ኦላ አኖሲኬ "መጋቢት እና የኩባንያው ግምጃ ቤት" ናት። ስለ ገንዘብ ጉዳይ "ልዩ መገለጥ ጌታ ሰጥቷታል" ብሎ ያሞካሻታል። የቤተ ክርስቲያኒቱን (ይቅርታ የግል ኩባንያውን) ሃብት መያዝ ብቻ ሳይሆን ስለ ገንዘብ እና የመባረክ መንገድ አስተማሪ እርሷ ናት። ትምህርትዋ ምን እንደሚሆን አያሻማም። "ስጡን፣ ይሰጣችኋል!"ሁለቱ ሴቶች ልጆቻቸውም ከኩባንያው ጠርናፊያን ቀዳሚ ናቸው። ገና ለጋ ናቸው። ዕድሜያቸው 17 እና 13 ቢሆንም በሚንስቴር ማዕረግ የወጣቶችና የታዳጊ ወጣቶች "መጋቢያንና ኃላፊ" ናቸው። እንዲሁም "ተዋጊዎች" ተብለው ይጠራሉ። መቼም የሚዋጉት ሰይጣንን እንዳይደለ ጀሌዎቻቸው አይገባቸውም! ወጣቶችና ልጆች
ነገረ ወንጌላውያን
30 июн., 08:57



ነገረ ወንጌላውያን
30 июн., 08:53
የሲኖፒው ማርሲዮንና የሐዋሳው ማርሲዮንየሲኖፒው ማርሲዮን የሚባል ሰው ነበር (85-160)። የመርከቦች ባለቤትነቱ ባለጠግነትን አስገኝቶለታል። በ140 ዓ.እ አካባቢ ወደ ሮም በመሄድ የራሱን ነገረ መለኮታዊ እሳቤ አዳብሯል። ይህ እሳቤው ለቤተክርስቲያን እንደ ኑፋቄ ተቆጥሮ የተወገዘ ነበር። ትምህርቱ በቤተክርስቲያን ውግዘት ቢገጥመውም ተቀባይነትን በማግኘት በሮም ግዛቶች ተስፋፍቶ ረዘም ላለ ወቅት ቆይቶ እንደነበር ታሪክ ያስረዳል።ማርሲዮን ነገረ መለኮቱን ያዳበረው ጽንፍ በወጣ የሕግና ፀጋ፣ ፍትህና ምህረት ልዮነቶች ላይ ነበር። ይባስ ብሎ በብሉዮና አምላክና በሓዲሱ ኪዳን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ሆኖ በተገለጠው እግዚአብሔር መኸከል ልዮነት መኖሩን ያትታል።እንደ ማርሲዮን የብሉይ ኪዳን ንባብ ከሆነ የብሉይ ኪዳኑ እግዚአብሔር የቁሳዊው ዓለም ፈጣሪ ነው። ፍትሐዊ ቢሆንም ግን ጨካኝ ነው። ቁጡ፣ ወግ አጥባቂ ፣ ለእስራኤል የሚያዳላና ለተከሰቱ ጥፋቶችና መከራዎች በሙሉ ዋነኛ ተጠያቂው እርሱ ነው። ማርሲዮን ይህንን አምላክ ውሱን፣ እውቀት አልባ (ignorant) እና የበታችነት ስሜት የሚያጠቃው አድርጎ ያቀርበዋል።የአዲስ ኪዳኑ እግዚአብሔር ደግሞ የብሉዮ ተቃራኒ ነው ይላል። ከዚህ ቀደም ያልታወቀው አምላክ አሁን ፍጹም መልካም፣ መኀሪ፣ አፍቃሪ፣ ይቅር ባይና ፍጥረቱን ከፍርድና ቅጣት በፀዳ መልኩ የሚያስተዳድር ነው ይላል። እንደውም በብሉዮና በሓዲሱ ኪዳን መካከል ምንም ትስስርና ቁርኝት አለመኖሩን ፈርጠም ብሎ ይናገራል። ክርስትና ከጁዳይዝም የቀጠለ ሳይሆን የተካ እንደሆነም ያትታል። የኢየሱስ ፍጹም
ነገረ ወንጌላውያን
29 июн., 20:14



ነገረ ወንጌላውያን
23 июн., 18:35
መታደም ፍላጎቱ ላላችሁ!


ነገረ ወንጌላውያን
19 июн., 20:48

2,710Открыть в Telegram
ነገረ ወንጌላውያን
19 июн., 20:48
የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁኔታ በደረቁት ዐጥንቶች ተመስሏል። ለእነዚህ ዐጥንቶች እንደገና በሕይወት የመኖር ብቸኛ ተስፋና ምክንያት እግዚአብሔር ብቻ ነው! የቱንም ያህል የደረቁና ከተስፋ ውጭ ቢሆኑም እግዚአብሔር ሲናገር መስማት ችለዋል። እግዚአብሔር ሲናገር ሙታን ይሰማሉ፤ ሕይወት እንደገና መዝራት ይጀምራሉ። ነቢዩ በታዘዘው መሠረት ትንቢት ሲናገር፣ የኮሻኮሽ ድምፅ ተሰማ፤ ዐጥንቶቹም አንድ ላይ ሆኑ፤ ዐጥንት ከዐጥንት ጋር ተጋጠመ። ነገር ግን ጅማትና ሥጋ ቢወጣባቸውም፣ ገና እስትንፋስ አልነበራቸውም።ይህ እውነታ ዛሬም ትልቅ መልእክት አለው። ያለ እግዚአብሔር መንፈስ እስትንፋስ፣ መዋቅራዊ አደረጃጀትና ለውጥ ብቻውን ሕያው ሊደርገን አይችልም። ውጫዊ ፕሮግራሞችና ድርጅታዊ ጥንካሬዎች ብቻቸውን ሕይወት አይዘሩም። ለዚህም ነው ነቢዩ በተደጋጋሚ የጌታን ቃል እንዲናገር የታዘዘው። ቃሉን ለማጽናት ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሲመጣና ሕይወት ሲዘራባቸው እናያለን፦ “. . . እስትንፋስም ገባባቸው፤ ሕያዋንም ሆኑ፤ እጅግ ታላቅ ሰራዊት ሆነው በእግራቸው ቆሙ።” (ሕዝ. 37፥10)።በቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል የበላይ ባለሥልጣንነት ሲረጋገጥ የእግዚአብሔር መንፈስም ይሠራል። ታሪካዊውና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው የጴንጤቆስጣዊ እንቅስቃሴ፣ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መንፈሳዊ መነቃቃትን፣ አንድነትንና ፍሬያማ የወንጌል ሥርጭትን ያበረከተና አሁንም እያበረከተ ያለ ታላቅ ሕያው ቅርስ ነው። ይህን በጐ ታሪክና ስም ጥላ አድርገው ለወንጌላዊው ክርስትና ስም መጠልሸት ምክንያት የሆኑ ስሑት አስተምህሮዎችና
ነገረ ወንጌላውያን
19 июн., 20:48
ዐጥንቶቻችን ደርቀዋል . . . የጉብኝት ጩኸትእንደ አይሁዳዊ፣ ካህንና ነቢይ፣ ሕዝቅኤል በራእይ ራሱን ያገኘበት የደረቁ ዐጥንቶች የተበተኑበት ሸለቆ፤ የብሔራዊ ስብራት፣ የመንፈሳዊ እፍረትና የጉስቁልና መገለጫ ነበር። በኦሪት ሥርዓት መሠረት፣ ሕዝቅኤል በእነዚህ በደረቁት ዐጥንቶች መካከል በመገኘቱ ረክሷል (ዘሌ. 21፥1፤ ዘኁ. 19፥11)። ዐጥንቶቹ ይገልጹት የነበረው ርኩሰትን፣ እፍረትን፣ ውርደትንና ባዶነትን ነበር። እነዚህ ዐጥንቶች እንደገና በሕይወት ይኖራሉ ተብሎ ፈጽሞ ተስፋ የሚጣልባቸው አልነበሩም። የኪዳኑ ሕዝብ፣ “ዐጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ የለንም፤ ተቆርጠናል።” በማለት ለትድግናና ለተሐድሶ ያሰሙት የነበረው ጩኸት የጉስቁልናቸውን ጥልቀት ያሳያል።የቁልቁለቱ መንገድ . . .የአሦር ዓለም ዐቀፍ ፖለቲካዊ ተጽዕኖ በባቢሎን መዋጥ በጀመረበት ጊዜ፣ ይሁዳ (የደቡቡ ክፍል) በመንፈሳዊ ቀውስ ውስጥ ነበር፡፡ ቀደም ሲል እግዚአብሔር እስራኤልን (የሰሜኑ ክፍል) በኃጢአት መንገድ በመሄዱና ቃል ኪዳኑን ስላፈረሰ፣ በ722 ዓ.ቅ.ክ ለአሦር አሳልፎ ሰጥቷታል። በተመሳሳይ የኃጢአት ዓመፅ ይከተል የነበረውን ይሁዳንም፣ በወቅቱ የዓለም ኀይል ለነበረው ለባቢሎን መንግሥት የ70 ዓመታት ግዞት አሳልፎ ሰጠው።የመጨረሻው ንጉሥ ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ባቢሎናውያን በጭካኔ የገዛ ልጆቹን ገደሉበት፤ ከዚያም ሁለት ዐይኖቹን በማውጣት በናስ ሰንሰለት አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት። ይህም ዐይኑ የሚያየው የመጨረሻው መሪር ትዝታ እንዲሆን መፈለጉ የባቢሎንን የጭካኔ ጥግ ያሳያል። የእስራኤል ውበት የነበረውና በአንድ
ነገረ ወንጌላውያን
29 мая, 14:16
“መንፈሳዊ አባት”መጽሐፍ ቅዱሳዊ ደቀ መዝሙር አድራጊነት (disciple maker) መንፈሳዊ አባትነትንና ክትትልን የሚፈልግ አደራ መኾኑ ግልጽ ነው። አባታዊ ክት ትል አንድን አዲስ ሰው ክርስቶስን ወደ መምሰል ሕይወት በብስለት ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ነው። ወደ ክርስቶስ ያመጣናቸው ሰዎች ጤንነት ባለው መልኩ ማደግ እንዲችሉ ለማድረግ በጸሎትና በምክር ተከታትሎ ኮትኩቶ ማሳደግ መንፈሳዊ አባትነትን ይጠይቃል። ከዚህ አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን አባታዊ ክትትልና እንክብካቤ (mentoring) በብዙ ሥፍራዎች ይናገራል። ከነዚያ ክፍሎች አንዱ ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ ቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የተናገረው ነው። “በክርስቶስ አእላፍ ሞግዚቶች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።” (1ቆሮ. 4:15) ይላል። ይህ በክርስቶስ ባላቸው መንፈሳዊ ውልደትና ዕድገት ስለነበረው ሚና መናገሩን ያሳያል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ዘመን በጴንጤቆስጤያውያን ዘንድ ፈር ከለቀቁ ልምምዶች አንዱ “spiritual father - መንፈሳዊ አባት” በሚል ስም የሚሠሩ አጓጉል ነገሮች ናቸው። ለራሳቸው በሰዎች ላይ ሚዛናዊ ያልኾነ ሥልጣን የሚሰጡ “ነቢያት” & “ሐዋርያት” በሚል ስም ሹመት ያገኙ ሰዎች አንድ ስም አይረካቸውም “መንፈሳዊ አባት ነኝ” እያሉ መንፈሳዊ አባትነትን ለርኩስ ዓላማቸው እያዋሉት ይግኛሉ። እነዚህ “መንፈሳዊ አባት” እያሉ ራሳቸውን በመንጋው የሚሾሙ ሰዎች “ባባ” እየተባሉ በሰዎች ትዳር ጉዳይ፥ በግለሰቦች በጀት ጉዳይ፥ በሥራና ንግድ ጉዳዮች ሁሉ በሌሎችም ግላዊ
