gram news
Аватар канала Orthodox Apologetic Theology

Orthodox Apologetic Theology

@orthodox_chrstianity

ኦርቶዶክሳዊ የአባቶች ትምህርት[patrology(ዜና አበው) & patristic] ሚተላለፍበት ኦርቶዶክሳዊ ገጽ ! ☆ Christ Jesus [is] our Lord, and God, and Savior, and King ☆

ПроектыENРелигия

4,290подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Orthodox Apologetic Theology

    22 сент., 18:56

    አለች ደሞ ልብን በሙሉ ተስፋ ሙልት የምታደርግ ቃል “እግዚአብሔር ያውቃል”የኔ እግዚአብሔር ተመስገን ስለ ሁሉም !https://t.me/orthodox_chrstianity
    20824721Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    22 сент., 15:17

    ሞት ⚰⚰ [2]ሞት አስፈሪ ነው። ፍርሃቱ ያለው ደግሞ አፈር ከመሆናችን ብቻ አይደለም፤ ከአስጨናቂው አላዋቂነቱ፣ ፍጹም ከሚመስለው ባዶነቱና ከማይመለሰው መስመሩ ላይ ነው። የምንወደውን ነገር ሁሉ የምንደክምለትን ሕልም፣ በደስታና በሀዘን የገነባነውን ማንነታችንን በአንድ ቅጽበት በኖራ እንደተጻፈ ጽሁፍ አብሶ የሚያጠፋ ጨለማ ነው። የቱን ያህል ብንጠነቀቅ፣ ብንበለጽግ ወይም ብንገዝፍ፣ በሞት ፊት ሁላችንም አቅም የለንም። የሰውን ልጅ በትዕቢቱ፣ በኩራቱና በወጣትነቱ ላይ የሚያፌዝ፣ መጨረሻውን በጽኑ መቃብር የሚያስር አስፈሪ እውነት ነው።ክርስቶስ በሞት ሸለቆ ውስጥ የዘላለምን መንገድ ጠረገ! ​ሰው ሁሉ ፈርቶ ይንቀጠቀጥበት የነበረውን የመቃብር ስፍራ እርሱ የድል አደራረግ መድረክ አደረገው። የሞትን ሰንሰለት አበጠሰ፣ ስቃዩንም ቀማው። አሁን በክርስቶስ የሚያምን ሰው በሞት ጥላ ውስጥ እንኳ ቢሄድ አይፈራም፤ ምክንያቱም ሞት ከእንግዲህ የመጨረሻው ጥፋት ሳይሆን ወደ ዘላለም አባቱ ቤት መግቢያ በር ሆኗል።ኦ እግዚእ ኢየሱስ አዕርፍ ነፍሰ እሁነ በሰላም🥹 !https://t.me/orthodox_chrstianity
    Иллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic TheologyИллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic Theology
    4231081Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    22 сент., 09:26

    ሞት ⚰⚰ [ 12-1-2019 ]ለሰዋዊ ማንነታችንና ለሥጋዊ አእምሯችን ሞት እጅግ አስፈሪ፣ መሪርና ሁሉንም ነገር የሚያበቃ ታላቅ ጠላት ይመስላል። ሰውን ከወደዳቸው ከለመዳቸውና ከተጋራቸው የሕይወት ውበቶች የሚነጥል፤ ባዶነትንና ወሰን የሌለው ሐዘን የሚያተርፍ የፍጥረት ውድቀት ውጤት ነው። እኛ ሰዎች የማይታወቀውንና ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነውን ነገር እንፈራለን፤ ሞት ደግሞ የሰው ልጅ ጥበብና ኃይል የማይመልሰው ትልቁ እንቆቅልሽ በመሆኑ ለሰዋዊ ተፈጥሯችን የፍርሃቶች ሁሉ አክሊል ነው።ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆነ ሰው የሞት ትርጉም በመሠረቱ የተቀየረ ነው። ሞት ከእንግዲህ የመጨረሻው ምዕራፍ ሳይሆን ወደ እውነተኛውና ዘላቂው ሕይወት የሚያሸጋግር ድልድይ ነው፤ የሥጋ ድካም የእንባና የሕመም ማብቂያ፣ የታላቅ እረፍትም ደጃፍ ነው። ክርስቶስ በመስቀል ላይ የሞትን መርፌ ስለሰበረውና በትንሣኤው ሞትን ድል ስላደረገው በንስሐ ላለ አማኝ ሞት ሽንፈት ሳይሆን ወደ አባቱ ቤት የመግቢያ መንገድ ነው። በምድር ላይ ያለን ሕይወት እንግድነትና አላፊ ጉዞ ሲሆን በክርስቶስ የሚገኘው ሞት ደግሞ ወደ እውነተኛው ሀገራችን የመመለስ ያህል ነው። ስለዚህም ተስፋችን ያለው በራሳችን ጽድቅ ሳይሆን በእርሱ ማቂያ በሌለው ምሕረት ላይ ነው። በሞትና በሕይወት መካከል በቆምንበት በዚህ አላፊ ዓለም ልባችን ወደ እርሱ ዘንበል ብሎ በመስቀል ላይ የተሰቀለውን የወንበዴውን ያህል የጸጋውን ታላቅነት ይለምናል። በአባታችን በዚያኛው ቤት የኃጢአት ጨለማ፣ የሐዘን ጥላና የሞት ሥልጣን አይደርስም።ጌታ ሆይ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ፣ የጸጋህ
    6881776Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    21 сент., 08:59

    "ብዙ ሕዝብም አንካሶችን፥ ዕውሮችንም፥ ዲዳዎችንም፥ ጉንድሾችንም፥ ሌሎችንም ብዙ ይዘው ወደ እርሱ ቀረቡ፥ በኢየሱስም እግር አጠገብ ጣሉአቸው፤ ፈወሳቸውም" [✍️ማቴ 15 ፥30]ችግሮቻችን ብዙ ዓይነት ናቸው መድኃኒቱ ግን አንድ ብቻ ነው። ዓለም ያጎሳቆለችው፣ በቀንበሯ የሰበረችው፣ በመርዟ የነደፈቻቸው ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ እግር ስር ሲወድቁ እንደ ንስር ታድሰው ይነሳሉ። ወዳጆቼ ክርስቶስ ኢየሱስ እግር ስር የጣልነውን ነገር የምናገኘው በቀድሞው ሁኔታ አይደለም። የታመመው ድኖ፣የተሰበረው ተጠግኖ፣ የሞተው ተነስቶ ነው።ዛሬ ትዳራችሁ ያነከሰባችሁ፣ ጤናችሁ የታወረባችሁ፣ በስስት በሽታ የተያዛችሁ፣ በዝሙት መንፈስ የተጠመዳችሁ፣ በጫት በሲጃራ ሱስ የተተበተባችሁ፣ በስርቆት ቤተሰብ ጎረቤት የተማረረባችሁ፣ ራስን በራስ በማርካት የሰይጣን ቀንበር ውስጥ የወደቃችሁ ሁላችሁ ችግራችሁን የምታራግፉበት አዲስ ሰው ሆናችሁ ቀና የምትሉበትን መድኃኒታችሁ ከክርስቶስ እግር ስር ችግራችሁን መጣል ነው። ለሰው ያቃተ መፍትሄ አልባ ነው የተባለው ሙት ችግራችሁ ክርስቶስ እግር ስር ህይወት ይዘራል። እናንተን ያጎበጠ ዘመን አስቆጥሮ ህይወታችሁን ያስመረረው ነገር ሁሉ በክርስቶስ ድል ይነሳል።ወዳጆቼ እኔ በህይወቴ ምስክር ነኝ ክርስቶስ ኢየሱስን አምናችሁ ከመጣችሁ አፍራችሁ አትመለሱም፤ ከችግራችሁ ጋር መኖር ዛሬ ይብቃ ክርስቶስን ሙጥኝ በሉት። ብቻ ኢየሱስ ጋር ድረሱ እንጂ የናንተ ነገር እንደ አዲስ ያብባል።https://t.me/orthodox_chrstianity
    6993553Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    20 сент., 12:57изменён

    የዝክር ግዜ 🤩ደሞ ሮዳስ ጋ አይደለም ሮዳስ ጋ እነ አንድሮሜዳ፣ ጠፈር፣ ህዋ እና ጸሀይ በተጋባዥነት ደሞ እነ ጨረቃ ነው ያሉት🙂
    Иллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic TheologyИллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic Theology
    8043074Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    20 сент., 09:58

    አይዟችሁ የዚህ ገጽ አባላት ለእናንተም ቀን ይወጣል😊
    Иллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic TheologyИллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic Theology
    83046177421Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    20 сент., 06:59изменён

    ሮዳስ'ም አገባ ይሜ 😍🙌እኔና እናንተ ብቻ ቀረን የሰው ሰርግ እያዳመቅን 😅
  • Orthodox Apologetic Theology

    20 сент., 05:17

    ዘወትር የማይደርቅ ትኩስ ደምየብሉይ ኪዳን ካህናት የእንስሳቱን ደም ይዘው ይገቡ ነበር፤ ጌታ ክርስቶስ ግን "ካህን፣ መስዋዕት እና መሥዋዕት ተቀባይ" ሆኖ የራሱን ደም ይዞ ወደ ሰማያዊቷ መቅደስ ገብቷል።​ምልጃው በየቀኑ የሚደረግ ልመና አይደለም። አንድ ጊዜ የፈሰሰው ደሙ ሁልጊዜ በምህረት የሚናገር [Speak] መሆኑን ያመለክታል።¹ክርስቶስ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ የሰዋው መሥዋዕት ሕያው ስለሆነ ዛሬም ትኩስ ነው።​ "ስለ እኛ ይማልዳል" ሲባል ደካማ ሆኖ ሳይሆን ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና የድኅነታችንን ዋጋ ለአብ ያሳያል [Manifests]።²“ከአቤል ደም ጀምሮ እስከ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ የቅዱሳን ነብያት ደም አለምን ለማዳን እንዳልጠቀመ ባየ ጊዜ ቤዛ መድሀኒት የሚሆን ልጁን ሰደደልን ፈፅሞ ያድነን ዘንድ...” ³የእንስሳት ደም ከፈሰሰ በኋላ ወዲያው ይረጋል፣ ይደርቃል፣ ይበሰብሳልም። ​የክርስቶስ ደም ግን ሕያው ስለሆነ ዛሬም እንደፈሰሰ ትኩስ ነው፤ የማንጻትና የማዳን ኃይሉም ቅንጣት ታህል አልቀነሰም ዛሬም ያንን ህያው ደም በቅዱስ ቁርባን እንቀበለዋለን።በእውነት ጌታ ኢየሱስ ሆይ ስለዚህም እናመሰግነዋለን ወጣትነታችንን፣ እድሜያችንን በፊትህ እንሰጣለን !¹‑ዕብ 7፥25፣ ዕብ 9፥12፣ ዕብ 9፥14፣ ዕብ 9፥26፣ ዕብ 10፥12፣ ዕብ 8፥3 ²‑ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ Homilies on Romans ³‑ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስhttps://t.me/orthodox_chrstianity
    9042242Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    18 сент., 17:00изменён

    With God’s grace, we will accomplish great things in 2019, starting with our new website coming soon..!ጌታ ይመስገን እየተገባደደ ነው ጌታ ያግዘን በተለይ እስካሁን ከዚህ ገጽ ጋ የነበራችሁ የተጠቀማችሁ ደሞም በሀሳብም በጸሎትም የደገፋችሁኝ፤ አሁንም ያለ መታከት አብራችሁኝ ያላችሁ ቀን በቀን እየጠየቃችሁኝ ምታበረቱኝ ... በሙሉ ልፋታችን ሁሉ የናንተም ጭምር ነው🥰ዌብሳይታችንን በቅርቡ ጠብቁት ከላይ የላኩት ናሙና ነው ሰፊ መስመር ይዘን እየሄድን ነው በቅርቡ ይጠናቀቃል..
    Иллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic TheologyИллюстрация к посту канала Orthodox Apologetic Theology
    1,08046421Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    18 сент., 08:35

    ጥብቅ ማስጠንቀቂያ !እኚ መንገድ ለይ ሚሰብኩ ጴንጤዎች በሌላ አይነት ዘዴ መጥተዋል። ዛሬ ጠዋት ከቤት ወጥቼ ወደ ቢሮ እየሄድኩ እያለ መንገድ ለይ የሆነች ቆንጅዬ [እንደ'ኔ ስዕል የመሰለች] ልጅ አቁመው ወረቀት እያደሉ ነበር። እኔ ወንድማችሁ ቆንጆ ሴት መጣች ብዬ ምሰናከል እንዳልሆንኩ መቼስ ታውቃላችሁ😂 አልፌያት ሄድኩ።ወንድ ሆይ በስስ ጎንህ መተዋልና ተጠንቀቃቸው 😒!
    1,1503824533Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    18 сент., 04:43

    ጌታችን እጅ ላይ በቤቱ እድሜያችን ይለቅ፣ ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ሳንለምድ ቤቱ ውስጥ መሸምገል ከእሱ ውጪ ሌላ ሳናውቅ ዘመናችንን መጨረስ ይሁንልን!መልካም ቀን 😍https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,19050102Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    17 сент., 15:58

    እንዳታምኗቸው🙂‍↔️እኔን እመኑኝ እህቶች🫠
    1,300видео40622Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    17 сент., 13:37

    😳🤣
    1,210видео20431Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    17 сент., 05:58

    ኦርቶዶክሳዊት ክርስቲያን ሴት ሰውነቷ የቅዱሱ መንፈስ ማደሪያ መሆኑን ታምናለች። ስለዚህ አለባበሷ ይህንን ክብር የሚመጥንና ሰውነቷን በአግባቡ የሚይዝ መሆን አለበት። አለባበስ በሌሎች ላይ [በተለይ በወንድሞች ላይ] መጥፎ ሐሳብን ወይም ፈተናን የማይጭር፤ ይልቁንም ለጸሎትና ለተመስጦ የሚረዳ መሆን ይገባዋል።መጽሐፍ ቅዱስ 'በልብ ውስጥ ያለ ስውር ሰው' [1 ጴጥ 3፥3-4] ይለዋል። አንዲት ሴት በውስጧ ሰላም፣ ትሕትና እና የዋህነት ካላት ይህ ማንነቷ በውጭ አለባበሷ ላይ ይንጸባረቃል። ክርስቲያናዊ አለባበስ፤ ክብር [Dignity]፣ ጭምትነት [Modesty] እና ንጽሕና [Purity] መግለጽ አለበት። ልብሱ ከሰውነቷ በላይ ማንነቷንና እምነቷን የሚገልጽ መሆን አለበት።በተለይ ቀሚስ ምታደርግ ሴት 😍🤌https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,4304081Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    16 сент., 16:27

    ኦርቶዶክሳዊት አጋር ከመፈለግ በፊት እኛ ራሳችን ለባል ብቁ ነን ?!ትዳር ማለት ሁለት ህይወቶች በወንጌል ፍቅር ተሳስረው ወደ አንድነት የሚሰደዱበት መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ሁሌ መልካም ሚስት ከመመኘት ይልቅ አስቀድሞ ለዚያች ሴት ፍጹም አፍቃሪ የሚሆን ባል ለመሆን ራስን መቅረፅና ወደ ጌታ መጸለይ ቀዳሚው ተግባር ነው። እኛ ክርስቶሳዊ ፍቅርን በልባችን ስናስድር አምላክ ደግሞ ክርስቶስ ኢየሱስን አብልጣ የምትወድ፣ በሃይማኖቷ የጸናች ውብ የህይወት አካል የሆነች ሚስት ይሰጠናል።ታላቁ አባት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ “ፍቅር በሁለት አካላት ውስጥ የምትኖር አንዲት ነፍስ ናት። ትዳር ደግሞ የሁለት ልቦች ጸጥተኛ መሸሸጊያ የችግር ጊዜ መጠጊያና ወደ እግዚአብሔር አብሮ የመጓዣ ታላቅ ክንፍ ነው” ይለናል። ስለዚህእውነተኛ ፍቅር ሰውን የመለወጥና የማንጻት ኃይል አለው። እኛ ለምንወዳት ሴት የህይወት አጋራችን የታመንን፣ በትዕግሥት የምንወድና እስከ መስዋዕትነት ድረስ ራሳችንን አሳልፈን ምንሰጣት ከሆነ ቤታችን የምድር ገነት፣ ፍቅራችን ደግሞ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርስ የህይወት ብርሃን ይሆናል። ስለዚህ ከምንም በላይ ልባችን በፍቅርና በትህትና እንዲሞላ የቤታችን ራስ ሚሆነው ጌታ እግዚአብሔርም ለሕይወታችን የሚመጥነውን መንፈሳዊት ሴት በበጎ ፈቃዱ እንዲሰጠን ሁልጊዜ በጸሎት እንትጋ።እኛ እውነተኛ ባል ለመሆን ራሳችንን ስናዘጋጅ፤ እግዚአብሔርም ልባችንን በደስታ፣ ትዳራችንንም በተባረከች ሴት ይባርከዋል።https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,5503121111Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    16 сент., 12:35

    ‛ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።’ [ኤፌ 2፥18]በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የተከፈተልን መንገድ እንዴት ድንቅ ነው! በቀደመው ማንነታችን ከእግዚአብሔር ርቀን በኃጢአት ተለይተን እንኖር ነበር። ዛሬ ግን በልጁ ደም ታጥበን፣ በከበረው መስዋዕትነቱ ወደ አብ መግባት ተሰጥቶናል።ይህ የጸጋ መንገድ በምንም ዓይነት በራሳችን መልካምነት ወይም ጥረት የተገኘ አይደለም። በእሱ በኩል ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና አሁን ወደ እግዚአብሔር የዙፋን ፊት በፍርሃት ሳይሆን በልጅነት ድፍረትና በነፃነት እንቀርባለን።ህይወት የሆንከን የአብ ልጅ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሰማያዊውን ክብር ትተህ ስለ እኛ ስለ ወረድክ በመስቀል ላይ በከፈልከው ውድ ዋጋ ወደ አብ የምንገባበትን ሕያው መንገድ ስለ ከፈትክልን አብዝተን እናመሰግንሃለን! ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን አውጥተህ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንባል ስላደረግከን እናመሰግንሃለን፤ ስምህም መንግስትህም በእውነት ለዘላለም የተባረከ ነው !“ እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም🥰” [ኤፌ 2፥19]https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,1302332Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    16 сент., 06:21

    pharmacy በምሰራበት ግዜ የዛሬ ሁለት አመት ይመስለኛል.. ሁለት የዘነጡ በአኔዷ በእድሜ ገፋ ያለች ሴቶች አንዷም ልጅ እግር ነገር ወደ መድኃኒት ቤታችን መጡ[እናትና ልጅ ናቸው]። እናም አረፍ ብለው(ጸሐይ ነበር) ንግግር ጀመሩ እና ወዲያውኑ ጭዌውን ወደ ስብከት ቀየሩብኝና... ዘለው ኦርቶዶክስ እንደዚህ ናት እንዲህ ናት .. እያሉ የተለመደውን የጴንጤ ወሬ ቀጠሉ። እናም ውይይት ጀምረን ነገሮችን በማስረጃ መንገር እና ማስረዳት ጀመርኩ። የሆነ ሰዓት ደረቅ ሆነው ማይሰሙት ነገር አላቸውና የትኛው denomination ናችሁ ስላቸው 'በጌታ ነን'😁 ሚሏት ነገርን ደጋገሙልኝ።የት ነው ምታመልኩት የትኛው ህብረት ስላቸው.. በስንት ምጥ 'መካነ ኢየሱስ' ነን አሉኝ። እዚህ ጋ ነው ነገሩ ለኔ የተመቸኝ☺️ አትሉም። ከራሳቸው የእምነት መግለጫ እና doctrine ለይ ነገሮችን እየጠቀስኩ ነገርኳቸው። እውነት ሴትየዋ ተቀያየረችብኝ ብትደበድበኝ ሁሉ ደስ ይላት ነበር🤦‍♂።ከዛ ሲጀመር መካነ ኢየሱስም ስህተት ናት እንደዛ ምታደርግ ከሆነ ብላኝ እርፍ [ስለ infant baptism እና Eucharist አንስቼላት ]መጨረሻ ለይ ጥል ጥል ሁሉ ብሏት ሁሉ ልጇ ይዛት ወጣች እላችኋለው😭።እናም እንኳን ጠንቋይ ጴንጤም ስለ ራሱ ለራሱም አያውቅ😄https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,0204582Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    15 сент., 18:15

    አሁን ከቢሮ መጥቼ ግቢ ከአከራዬ ጋ ቁጭ ብዬ ሳወራ የሆነ ታሪክ ነገሩኝ ስለ ንስሐ እያወራን ነው ታሪኩን ያካፈሉኝ።ታሪኩ እንዲህ ነው አከራዬ highschool እያለች አንድ የሰፈር ጓደኛዋ ታረግዝና ድንጋጤ ይመጣል .. ከዛ አዋቂ ቤት መድኃኒት ይሰጣል ለማስወረድ ተብሎ እዛ ተያይዘው ከልጅቷ ጋ ይሄዳሉ። እዛም እንደ ደረሱ ይገቡና ይቀመጣሉ ከዛ ከመጋረጃው መሀል ገለጥ አድርጎ ሲያየኝ ከነ ጫማዬ ነው የገባሁት አለችኝ😁ከዛ ቀወጠው አለች ውጪ ከዚህ 'ነቀርሳ ይወጣብሻል አለኝ' አለች ብዙ ሰው ነው ሚካድመው ራሱ ውስጥ አለችኝ.. ከዛ 'እራስህ ነቀርሳ ይውጣብህ' ብዬው ወጣሁ አለችኝ😂በየጊዜው ሰውነቴ ጓደኞቼ ቢያዩም ምንም የለም ከዛ ከአመት በኋላ ስሰማ ያ ጠንቋዩ ሰውዬ ራሱ ሞተ ተባልኩኝ አለችኝ😁እና ምን ልላችሁ ነው መሰላችሁ ጠንቋይ እንኳን ለሰው ለራሱም አያውቅም።Btw አከራዬ አሁን ንስሐ ገብታ ቆራቢ ናት፤ ንስሐ የገባሁበት በሚል ነገር እና ስለ ንስሐ ተጀምሮ የነገረችኝ ታሪክ ነው😊።https://t.me/orthodox_chrstianity
    1,03030102Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    15 сент., 13:47

    2016 መጨረሻ ይሁን 2017 ለይ እርግጠኛ አይደለሁም አንድ ጀለስ ነበረኝ። እና የሆነ ግዜ ወሎ ሰፈር [ወንጌላዊት ጀርባ] ሥላሴ ቤተክርስቲያን አለ። እና እዛ ጠርቶኝ ሄጄ ጠዋት አስቀድሰን ከጨረስን በኋላ ና ጸበል እንጠጣ ብሎኝ ከጀርባ ይዞኝ ሄደ..።ከዛ በታች በኩል ከጀርባ ለካ ሌላ ታሪክ ነው😂🤦‍♂ አገር የሆነ ጨቅ ህዝብ ነው ያለው ግብዳ በቆርቆሮ የተሰራ መጋዘን ሚመስል ጎን ጎኑ ለይ ክፍት የሆነ ቤት አለ ግማሹ ጸበል ይጠጣል ዘወር ስል ቢጫ አንጸባራቂ [parking ለይ ሚሰሩ ልጆች ሚለብሱት] የለበሱ ሰዎችም አሉ ካሜራ ምናምን እየተስተካከለ ነው .. ከዛ የሆነ ሰዓት ከግራ ከቀኝ ጩኸት ሰማሁ አትሉም😅 ለካ የአጥማቂያን መሸሸጊያ ቤተክርስቲያን ገብቼ ነው።ከዛ ጓደኛዬ ሆን ብሎ ነው የሄደው እና ተሰልፎ እያለ ከዛ ሁሉ መሃል አስተባባሪው ቢጫ የለበሰው ጠርቶት 'ከሆነ መዝሙረ ዳዊት ክፍል ጠቅሶ ይህንን ጸልይ ምናምን አለው.. ' ከዛ ጓደኛዬ ገርሞት 'በቃ የሆነ ነገር ገብቶት ነው ስለ'ኔ አለኝ አይገርምህም ከዚህ ሁሉ ሰው መሀል እኔጋ ሲመጣ' ምናምን አለኝ [ያውም አስተባባሪ ነው እኮ😭😂ብቻ በባሌም ይሁን በቦሌ ወጣን ጨርሶ.. የዛን ዕለት ጠዋት ሳገኘው ያለ ወትሮው ግብዳ መዝገበ ጸሎት ይዞ ይለዋል እኔ መች በሰላም መሆኑን አውቄ🤦‍♂ሲጀመር፦ ንስሐ አባቴ አይነ ጥላ ምናምን ሚል ሰውና ቄስ ጋ እንዳትደርስ ብለውኛል 😒አሁን ያ ጀለስ ሌላ ቤተ እምነት ለይ ነው ያለው😒በዚህ አመት በትምህርት ከምንወጋቸው መሐል አጥማቂያኑ አንደኛዎቹ ናቸው እነርሱ የቤተክርስቲያን ጸርና እጢ
    9591743221Открыть в Telegram
  • Orthodox Apologetic Theology

    15 сент., 09:36

    በእግዚአብሔር ዐይን ምን አይነት ሰው ነን ?የኔ ተወዳጆች፦ እግዚአብሔር በህመም፣ በኀዘን፣ በደስታ፣ በዙሪያችን ባሉ ሰዎች፣ በሚያጋጥሙን ሁኔታዎች፣ እንዲሁ አጠገባችን ያለ ሰውን በሞት ስናጣም ጭምር ያስተምረናል እንዲሁም በእኛ ለይ ይሰራል።The question has to be በዚህ በኩል እግዚአብሔር ለእኔ ምን ሊያስተምረኝ አስቧል።go and find out the tips from all the moments.ወጣትነታችንን የጌታ መቅደስ አካላችንን በሚያረክስ ተግባር በስካር፣ በዝሙት፣ በዘፈን እና በተለያዩ እግዚአብሔርን በሚያሳዝኑ ተግባራት ተጠምደን ከሆነ ዛሬውኑ ከዓለም እና ከክርስቶስ መምረጥ ይኖርብናል። ዓለም የኪራይ ቤት ናት ወይም ኮንትራት ናት መች እንደምታበቃ ኮንትራታችን ወይ እንደ ከረሜላ መች መጥጣ እንደምትጥለን አናውቅም። ከዚህ ሁሉ ለክርስቶስ መኖር ማትረፍ ነው በእውነት፥ ከረፈደ ሳይሆን ወይ ደግሞ ነገ ሳይሆን አሁን ነው መንቃት እና በንስሐ መመለስ ያለብን["...የመዳን ቀን አሁን ነው" 2ኛ ቆሮ 6፥2]። ከረፈደ እድሜያችንም ከሄደ በኋላ ብንመለስ ከእግዚአብሔር ጋር ያልኖርንባቸው ዘመናት ይቆጩናል ልክ እንደ ተወዳጁ አውግስጢኖስ እንዳለው “..ኦ ጥንታዊም አዲስም የሆንክ ውበት፥ ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ! እነሆ አንተ በውስጤ እያለህ እኔ ከራሴ ውጭ ነበርኩ.”[Confession,10]ለዚህም ነው የመዳን ቀን ከዛሬም አልፎ አሁን ነው የተባልነው፤ የጉብዝናችንን ወራት ወጣትነታችንን ጉልበታችን ሳይደክም ለክርስቶስ እንስጠው፣ ዓለም እንደ ከረሜላ መጣ ሳትጨርሰን ለጌታ ይሁን
    1,1602554Открыть в Telegram