Последние посты

URIM | ኡሪም
19 сент., 04:48
переслано из @evasue58
አብዛኛውን ጊዜ፣አንድን ሰው ስናጣ፣ ችግር ውስጥ ስንገባ፣ውጤት አልመጣ ሲለን፣ ብቸኝነት ሲሰማን እና ነገሮች እንዳሰብነው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ እግዚአብሔር እንደተወን እናስባለን፤ ተስፋ እንቆርጣለን። አምላካችን ማን እንደሆነ እንረሳለን።ይህ በእኛ አልተጀመረም። በኢሳይያስ ምዕራፍ 40:27ን ብናይ፣ እስራኤላውያን መብታቸው በእግዚአብሔር እንደተዘነጋ፣ እንደተተዉ እና እንደተረሱ ስለተሰማቸው፣ በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ መቁረጣቸውን እናያለን።እኔም ብዙ ጊዜ ይህን አድርጌያለሁ። ዓለም በዙሪያዬ እየፈራረሰ እንደሆነ ፣ እግዚአብሔር ግን የትም እንደሌለ የተሰማኝ ወቅቶች ነበሩ። እግዚአብሔር ግን ለእስራኤላውያን የሰጠውን መልስ ቁጥር 28 ላይ እዩ።የእስራኤላውያን ትኩረት ሁኔታቸው ላይ ስለነበር፣ እግዚአብሔር ትኩረታቸውን ወደ እርሱ ማንነት መለሰ። ስለ ታላቅነቱ በማስታወስ፣ እርሱ የምድር ፈጣሪ መሆኑን፣ የማይደክም፣ የማይታክት፣ ብርታት ሰጪ አምላክ እንደሆነ ዘርዝሮ፣ ተስፋ የሚጣልበት አምላክ መሆኑን አሳያቸው።


URIM | ኡሪም
16 сент., 10:20
переслано из @prolifegenerations
May God bless this Family 😇


URIM | ኡሪም
15 сент., 05:28
5 በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ 6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል።— መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-6 (አማ54)
URIM | ኡሪም
13 сент., 22:42
"ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ከኢየሱስ የተቀበልሁትን አገልግሎት እርሱም የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌልን መመስከር እፈጽም ዘንድ ነፍሴን በእኔ ዘንድ እንደማትከብር እንደ ከንቱ ነገር እቆጥራለሁ።"— የሐዋርያት ሥራ 20:24አንዳንዴ መፅሀፍ ቅዱስን ሳነብ በዚህ ዘመን የሆንነውን ያለውን እንቅስቃሴ ስመለከት እጅጉን ቤተክርስቲያን ተሀድሶ እንደምትሻ ነው የምረዳው።በመጀመርያዋ ቤተክርስቲያን የነበሩት ሀዋርያት በዚህ ደረጃ Bold ነበሩ ስለ ጌታቸው ወንጌል ነፍሳቸውን እንኳ እንደ ከንቱ ነገር የሚቆጥሩ ቆራጦች ነበሩ።በእርግጥ ወንጌልን በደንብ ለተረዳው ሰው ይህን ማድረግ ትክክለኛ ነው። የኛ ዘመን ቤተክርስቲያን ወንጌል አልገባት ይሁን? እኔስ? እናንተስ? እኛስ? ያልተረዳነው ነገር ይኖር ይሆን?ብቻ መንፈስ ቅዱስ ያድሰን ወደ ጌታችን ያስጠጋን።@Urim7
URIM | ኡሪም
13 сент., 14:58
переслано из @antiworld77
Christian, remember this: your life is short, your duties are many, your assistance is great, and your reward is sure!
URIM | ኡሪም
12 сент., 06:09изменён
ካቻምናን ስንፈራ፤ ለአምናውም አድርሶናል፤ አምናንም ስንፈራ፤ ዘንድሮ አድርሶናል፤ ዘንድሮን ስንፈራ፤ ደረስን አሁን፤ ታዲያ ምን አሰጋን የወደፊቱን።መሸሸጊያ ዋሻ፤ መከታ ጋሻችኝ፤ ጦራችን አንተ ነህ፤ ጠላትን መውጊያችን፤ አንተም ተዋጊ ነህ፤ ስምህም እግዚአብሔር ነው፤ እንኮራብሃለን ደስታ ሃይላችን ነው።መሸሸጊያ ዋሻ -ታደሰ እሸቴ@Urim7
URIM | ኡሪም
11 сент., 04:36
መልካም አዲስ አመት ውድ የ URIM ቤተሰቦች🥰
URIM | ኡሪም
5 сент., 18:32
переслано из @romans148
በፈተና ላሉ ማጽናኛ (Comfort for the Tempted) የ Charles H. Spurgeon ስብከት በ 1ኛ ቆሮንጦስ 10፡13 ላይ እጣሬ (መስከረም 27፣ 1883 እ.አ.አ)"ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።" (1 ቆሮ 10፡13)1. ለብቻችንን አይደለንም - የትኛውም የምታልፉበት ፈተና ሌሎች አማኞች ያለፉበት ወይም እያለፉበት ያለ ነው። - አንዳንዴ ጠንካራ የሚመስሉ አማኞችን ስንመለከት በፈተና ያላለፉ ይመስለናል። ነገር ግን አማኞች ብዙ ጊዜ ጠንካራ በሆኑበት በዛው ጉዳይ ተፈትነው ይወድቃሉ። ለምሳሌ፣ ያዕቆብ እዮብ ታጋሽ እንደሆነ ይነግረናል። ታዲያ እስቲ አስቡ ስለ ኢዮብ እለመታገስ ሰምታችሁ አታውቁምን? - ታዲያ ያሽነፉት ሁሉ ያሸነፉት በእግዚአብሔር መንፈስ እርዳታና በጌታ በኢይሱስ ደምና ጽድቅ ነው። - ሌላው፣ ጌታ ሆኖ ያላለፈበት አዲስ ፈተና አልገጠማችሁም። - ስለዚህ የምታልፉበት ፈተና እናንተ ብቻ የምታልፉበት እንደሆነ ታስቡ። እንዲህ ያለው ሃሳብ በናልፍበት ፈተና ላይ ተጨማሪ ሸክም ይሆናል። 2. እግዚአብሔር ታማኝ ነው - እግዚአብሔር የሰጠንን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝ ነው። - አረሳችሁም አልጥላችሁም ያለውን ተስፋ ሊፈጽም ታማኝ ነው። - እግዚአብሔር ታማኝ ብቻ ሳይሆን፣ ተስፋው ሊፈጽም ባለንበት ሁኔታ ላይ የበላይ ተቆጣጣሪ ነው። 3. እግዚአብሔር ለፈተናችን ገደብን ያበጃል - እግዚአብሔር በማንችለውን
URIM | ኡሪም
2 сент., 08:06
ከሰሞኑ ከአንድ አገልጋይ የተማርኩበት ልቤን የያዘውን ሀሳብ ላጋራቹትዝ ይላችዄል ያኔ የእስራኤል ህዝብ ከግብፅ ባርነት የወጣ ሰሞን የሆነው ነገር። እግዚአብሔር ህዝቡን ከብዙ አመታት ቀንበር ለመገላገል በተገለጠ ሰአት እስራኤል ከግብፅ በአምላኳ መሪነት የወጣችበት ወቅት ነበር።በእርግጥ በባርነት ላሳለፈ እጅጉን ተማርሮ ወደ አምላኩ ጮሆ በድንቅ በተአምር ከባርነት ለወጣ ህዝብ ይህ ብቻውን ድል ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር ከነአንን ቃል ገብቷልና ወደ ከነአን መጓዝ ደግሞ ግዴታ ነው።የእስራኤል ህዝብ ከብዙ አመታት ቀንበር ተገላገልኩ እፎይ ባለበት ወቅት የግብፅ ሰራዊት በፈርኦን መሪነት ከዄላ፤ ከፊት ደግሞ ትልቅ ባህር በእስራኤል ፊት ድቅን ሲል እናያለን።እስራኤልም በምሬት ሙሴን ለምን እንዲህ ሆነ በግብፅ ብንጠፋ ይሻለን ነበር ለምን አወጣኸን መቀበርያ እንኳ በሌለበት በዚህ ስፍራ ልታጠፋን ነው ብለው እጅግ አጉረመረሙ።የሚገርመው እስራኤል እንዲ ሲያጉረመርም ቀጣዩ ምእራፍ የምስጋና የድል እንደሆነ ባለማወቁ ነው። የሚሞቱ መሰላቸው ወደ ዄላ ሲመለከቱ የግብፅ ሰራዊት ወደፊት እናምልጥ እንዳይሉ ትልቅ ባህር ተደቀነባቸው። ምሬት ቀናቸው ሙሴ ላይ አማረሩ ሙሴም ከእግዚአብሔር ጋር አውርቶ አትፍሩ አትደንግጡ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃዊያን ለዘለአለም አታዩአቸውም አለ እንዳለውም ሆነ እግዚአብሔር ባህሩን ከፍሎ በድንቅ በተአምር አሻገራቸው።ወዳጆቼ ስለ እስራኤል ታሪክ ልነግራቹ አይደለም ግን ለአንድ ሰው መልእክት ቢሆን እንዲህ ልሞግተው ነው።ድልህ እጅግ ቀርቧል ምናልባትም አንድ ምእራፍ ብቻ ይሆናል
URIM | ኡሪም
30 авг., 18:28изменён
አይገርማችሁም ያኔ በፍጥረት መጀመርያ ሰሞን አዳምም ሄዋንም በሀጥያት እንደወደቁ መፅሀፍ ይነግረናል። ሀጥያት ክፉ ነው የአምላካችሁን ፊት በነፃነት እንዳታዩ ያደርጋቹሀል። መሳቀቅ መሸማቀቅ የእለት ተእለት ተግባራቹ ይሆናል።አዳምም እንዲሁ ሄዋንም ብትሆን ያደረጉት ይህን ነው። ከባለቤታቸው ከፈጣሪያቸው ለመሰወር ለመደበቅ ነበር የጣሩት የሀጥያት ውጤቱም ይህ አይደል።ስለ ሀጥያታቸው ላወራቹ አይደለም ግን ሰሞኑን ሳስበው የደነቀኝ ነገር አዳም እና ሄዋን ፈላጊ አልነበሩም መደበቅ ነበረ ምርጫቸው የሚገርማቹ አንዳች ጥረት እንዳላደረጉ በገሀድ ያለ ሀቅ ነው።አለ የሚፈልግ የወደቀውን ለማንሳት የሚመጣ ቸሩ ባለቤታቸው አዳም ሆይ እያለ ሲፈልጋቸው እናያለን ምን ይህ ብቻ የመውደቃቸው ነገር ግድ ብሎት እንደ ሰው ለመሸሸግ የተጠቀሙትን ቅጠል ቀይሮ ቁርበት ሲያለብሳቸው እናያለን።ወዳጆቼ ስለ አዳም እና ስለ ሄዋን አውርቼ ልተዋቹ አይደለም ፈላጊ እንዳለን ለአንዲት ነፍስ ላስታውሳት ነው። አለ የሚፈልግ የደከመን የሚያነሳ የሚሸልም የማይተው የማይጥል ወዳጅ አለ።ምናልባት የተደበቀች ነፍስ ትኖር ይሆን? ጌታዋን ማየት አፍራ ሀጥያት ደርቶባት አምላኳን ለማየት የምትሸማቀቅ ነፍስ ትኖር ይሆን? እኔን የሞገተኝን ጩኸት ዛሬ ለአንዲት ነፍስ እነግራታለው።አለ የሚፈልግ አለ የሚጣራ አለ ዛሬም ልጄ የሚል ዛሬም ተስፋ አለ መድህን በደጅ ቆሞ ይጣራል ልጄ ይላል እኛ አቤት እንበለው ድምፁን ሰምተን እንከተለው እንደወደደ አድርጎ በምህረቱ ያቆመናል ያድሰናል።@Urim7
URIM | ኡሪም
28 авг., 07:20
እግዚአብሔር የማትገፈተሩበትን ምንጭ ይስጣችሁ! በላይኛውም በታችኛውም ምንጭ ይባርካችሁ። እግዚአብሔር ኢያሱን ካንተ ጋር መሆኔን ለማሳየት በእስራኤል ሁሉ ዓይን ፊት ከፍ ከፍ አደርግሃለው እንዳለ ፤ እንዳለውም ደግሞ እንዳደረገ እግዚአብሔር በሚያውቋቹና በማያውቋችሁ ሰዎች ፊት ሞገስን ይስጣችሁ። እልፍ ሁኑ ፣ ያየቻችሁ ዓይን ሁሉ እግዚአብሔርን ስላደረገላችሁ ቸርነት ትመስክርላችሁ ። ምትሰሩትን ምትነኩትን ሁሉ ይባርክላችሁ። ተናግራችሁ ጣፍጡ ፣ እግዚአብሔር ቃላችሁን የክርክር መጨረሻ ያድርግላችሁ። እንቅፋት አይምታቹ። የጨለመ እየመሰለ ይንጋላችሁ ! አልቆ ያያችሁት ሁሉ ሞልቶ ይጠብቃችሁ። ተባረኩ 🙏❤️Bereket lema@Urim7
URIM | ኡሪም
27 авг., 13:04
переслано из @remnant_s
መቅበዝበዝ ሳበዛ በዓለም ስዋትት ክብር መስሎኝ ታይቶኝ ውርደት ሳካብት በበደሌ ብዛት ሞት የሚገባኝን ፀጋህን አብዝተህ በህይወት ኖርኩኝ ዛሬ ላንተ ቆሜ ባፌ ዘምራለሁ ያዳንከውን አዳዳን ገድልህን አወራለሁ ግነን በዓለማት ስምህ ከፍ ይበል በእርግጥ ከዚህ በቀር የለም የምከፍልህአንተን ያገኘሁ ለት መንገዴ ተቃና በእጆችህ መራኸኝ በህይወት ጎዳና ምክርህ ሰው ያደርጋል የአንደበትህ ቃል ፍቅርህ እንደ ጠል ነው ደረቁን ያፀድቃል (2)ስንከራተት ሳለ በምድረበዳ ላይ የሚረዳኝ የለም ግራ ቀኜን አላይ ባልጠበኩት ለታ ከሰማይ ድምፅ መጣ በእጁ እጄን ያዘኝ ተራራን አወጣኝ አንተ የኔ እኮ ነህ ልጄ እወድሃለሁ በእውነት ቃል አስቤህ ለክብር ወልጄሃለሁ
URIM | ኡሪም
20 авг., 16:42
#ከተማርኩት_ የብሉይ_ኪዳን_ዳሰሳየእስራኤል ህዝብ እና የከነአን ህዝብ ልዩነት።እስራኤላዊያን#ካህናት የአምልኮ መሪዎች ነበሩ #አንድ አምላክ ብቻ ያህዌ ይሉ ነበር #የሚቃጠል መስዋእት ለአምላካቸው ይሰዋሉ #መሰዊያቸው አራት ቀንዶች አለው #መቅደሳቸው ሶስት ክፍል አለው #እንስሳን ለመስዋእት ይጠቀሙ ነበርከነአናዊያን#ነገስታት ሀይማኖቱን ይመሩ ነበር #ብዙ አማልክት ያመልኩ ነበር #የሚቃጠል መስዋእት ያቀርባሉ #መሰዊያቸው አራት ቀንድ አለው #መቅደሳቸው ሶስት ክፍል አለው
URIM | ኡሪም
19 авг., 17:40
#ከተማርኩት_ የብሉይ_ኪዳን_ዳሰሳከነአን እና ግብፅ#ከነአን: በመፅሀፍ ቅዱሳችን ውስጥ የካም ልጅ ስም ከነአን ነው ( የኖህ የልጅ ልጅ ነው)ከነአን ተብሎ የሚጠራው ቦታ በዛሬይቱ እስራኤል አከባቢ እንዲሁም በሊባኖስ አከባቢ የምትገኝ ቦታ ነበረች።የከነአን በኩር ልጅ ሲዶን ይባላል- ሲዶና የምትባለውም ከተማ የመጣችው ከዚህ እንደሆነ እንረዳለን።ከነአን ግብፅ እና ሜሶጶጣሚያ መሀከል የምትገኝ ስፍራ ናት። ከነአን የብዙ ህዝብ ውቅር የነበረባት ስፍራ ነበረች ለምሳሌ#አምራዊያን #ሲዶናዊያን #ፊንቄያዊያን #ኬጢያውያን የመሳሰሉትን በውስጡ የያዘ ነበር።አበው: አብረሀም፣ ይስሀቅ እንዲሁም ያዕቆብ መኖርያቸው በድንኳን ነበር። የአኗኗር ዘይቤያቸውም የዘላን ነበር።የከብት ንብረት፣ የበጎች ንብረት እንዲሁም የባርያ ወይም የጦረኛ ባለቤት ነበሩ።
URIM | ኡሪም
18 авг., 22:42
ታማኝ ጌታ🥹🥺@Urim7
URIM | ኡሪም
18 авг., 16:14
ተስፋ አለ!የዚህ አለም ውጣ ውረዱ ፈተናው ችግሩ ማለቂያ እንደሌለው ዥረት ሁሌም እንደፈሰሰ ነው። ከአንዱ ፈተና ወደ አንዱ መዛወራቹ የችግሩ ገደብ መች ነው ያስብላል ይህም እውን ነው። ግን አንድ ነገር በልባቹ ያዙ መቼም ቢሆን ተስፋ አትቁረጡ መቼም!አብረሀም ከሞተ ስጋው ይስሀቅን እንዳየ፣ ሳራም ካለማመን ሳቋ ወደ እውነተኛው ሳቅ እንደመጣች፤ የሀና እንባ ሳሙኤልን ይዞ እንደመጣ መቼ ይሁን ያላችሁት ጉዳይ መሆኑ አይቀርም ምክኒያት ብትሉኝ እግዚአብሔር ተስፋ የሚቆረጥበት አምላክ አይደለም።እንደ አላዛር በሞተ ነገራችን ላይ ትንሳኤን መዝራት ይችላል። ለምን? እርሱ ህያው አምላክ ነው። ያስጨነቀን ግራ ያጋባን ለምን? መቼ? እንዴት? ያልንበት ነገር በሙሉ በጊዜው ውብ ሆኖ እናየዋለን።በርቱልኝ ወዳጆቼ የያዘን አምላክ የሚጥል፣ የሚረሳ፣ የሚተው አይደለም!@Urim7
URIM | ኡሪም
18 авг., 11:04
የለም ያሉህ የሉም ዛሬም የሚሉህ ነገ አይኖሩም@Urim7
URIM | ኡሪም
18 авг., 05:21изменён
ፀጋው አለ!የበረታን የበረታን ሰሞን ብቻ ተገልጦ የደከምን ጊዜ የሚሸሸን አይደለም የእግዚአብሔር ፀጋ። እራሱ ፀጋው ከድካም አውጥቶ ወደ ብርታት ያሸጋግረናል። ፀጋውን እንደገፈው።@Urim7
URIM | ኡሪም
17 авг., 10:05
переслано из @reformedn
ብሔራዊ ኑዛዜቸር ነውና፣ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና። ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል? ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ ጽድቅን ሁልጊዜ የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው።እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል አስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤ ይኸውም የምርጦችህን ብልጽግና አይ ዘንድ፣ በሕዝብህ ደስታ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ ከርስትህም ክብር የተነሣ እጓደድ ዘንድ ነው።እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤ በደልን፤ ክፉም አደረግን።አባቶቻችን በግብፅ ሳሉ፣ ታምራትህን አላስተዋሉም፤ የምሕረትህን ብዛት አላሰቡም፤በባሕሩ አጠገብ፣ ገና ቀይ ባሕር አጠገብ ዐመፁብህ።እርሱ ግን የኀይሉን ታላቅነት ለማሳወቅ፣ ስለ ስሙ አዳናቸው። ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው። ከባለጋራቸው እጅ አዳናቸው፤ ከጠላትም እጅ ታደጋቸው። ባላንጦቻቸውን ውሃ ዋጣቸው፤ ከእነርሱም አንድ አልተረፈም።ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት።ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። በምድረ በዳ እጅግ መመኘት አበዙ፤ በበረሓም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት።እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው።
URIM | ኡሪም
15 авг., 20:38
переслано из @mere_protestantism
💥 የእግዚአብሔር ጥበቃትላንት አንድ ታካሚ ተመለከትሁ። ዐይኖቹ ደም መስለዋል፤ ፊቱ በእጅጉን ተጎሳቁሏል። ያለበት በሽታ Facial nerve palsy የሚባለው የነርቭ በሽታ ነው። ይህ ነርቭ ሰባተኛው ከጭንቅላት የሚወጣ ነርቭ (CN VII) ሲሆን ኦርቢኩላሪስ ኦኩላይ (Orbicularis oculi) የተባለውን በዐይናችን ቆብ ላይ የሚገኘውን እና ዐይናችንን መጨፈን እንድንችል የሚያደርገንን ጡንቻ የሚያዝ ነርቭ ነው። ይህ ታካሚ በገጠመው በሽታ ታዲያ አንድ ዐይኑን ጨርሶ መጨፈን አይችልም። አንድ ዐይኑ ሁልጊዜ እንደተከፈተ ነው፤ ግማሽ የሚሆነው ፊቱም ፓራላይዝ ሆኗል።ዐይናችን እጅግ ሴንሴቲቭ ከሆኑ የሰውነታችን ክፍሎች ቀዳሚው ነው። የዐይናችን ቆብ በየጊዜው የሚርገበገበውም ዐይናችንን ከውስጥ ድርቀት (እንባን በማሠራጨት) እንዲሁም ከውጭ አቧራ እና አደጋ ለመጠበቅ ነው። በዐይን ቆብ ያልታደለ ዐይን ግን ይደርቃል፣ ይቆስላል፣ ለከባድ ኢንፌክሽንና ዓይነ-ስውርነት ይጋለጣል።''ይህን ሁሉ ለምን አነሣህ?'' ካላችሁኝ፤ መዝሙረኛው በጸሎቱ እንዲህ ይላል፦ ''እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህም ጥላ ሰውረኝ፤'' (መዝ. 17፥8)አይገርምም?! በእግዚአብሔር ቆብ ውስጥ ሆነን እንደ ዐይኑ እንጠበቃለን። እግዚአብሔር እጅግ ሴንሴቲቭ እንደሆነ አካሉ አድርጎ በፍቅሩ ሸሸጎ ይጠብቀናል። ይህ ጥበቃውም ሁለት መልክ አለው፦1. ከውስጥ ድርቀት ይሰውረናል፦ የዐይን ቆብ እንባን በማሠራጨት ዐይን እንዳይደርቅ እንደሚያርሰው፣ የእግዚአብሔርም ጸጋ መንፈሳችን በሕይወት ውሃ ወንዝ ሁልጊዜ የረሰረሰ እንዲሆን ያደርጋል።
