Последние посты

AAU-Official
22 сент., 09:27
የመጀመሪያው የአፍሪካ የውሃ ዋስትና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነውኮንፍረንሱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር፤ የአፍሪካ ውሀ ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን የኮንፈረንሱ ዋና ትኩረት አቅጣጫዎች ውሃን እንደ ትልቅ የሪጅናል ኮርፖሬሽን ማዕከል አድርጎ ማስተሳሰር እና የኢትዮጵያን የውሃ አስተዳደር አጠቃላይ ገጽታ ለሌሎች አገሮች ማካፈል መሆኑ ተመላክቷል።በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከ20 ሀገሮች ከ300 በላይ ተመራማሪዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች እና በመሬት ላይ ያለውን ስራ የሚሰሩ አስፈፃሚዎች ተሳታፊ ይሆኑበታል። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ የውሃ ልቀት ማዕከል ኃላፊ ፕሮፌሰር ፈለቀ ዘውገ እንደገለፁት፣ አገራዊና አህጉራዊ የውሃ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ሰፊ ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።በጉባኤው ላይ የተገኙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀኛጀ የውሀ ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ደበበ ደፈርሶ በበኩላቸው የሳይንስ ማህበረሰቡንና የፖሊሲ አውጪዎችን ግንኙነት በማጠናከር የውሃ ሀብት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የሚቀጥሉት የኮንፈረንሱ ቀናት ውይይቶች እንደሚያደርጉባቸው ተነግረዋል።የመጠጥ ውሃና የውሃ ደህንነት፣ሥነ ምህዳር እና የውሃ ደህንነት፣ድንበር ተሻጋሪ ውሃና የውሃ ደህንነት በሚሉ ሀሳቦች ዙሪያ የተሰሩ ሌሎችም ጥናታዊ ፅሁፎች ይቀርባሉ።ከሶስቱ ቀን ጉባኤና የምርምር ስራ የሚገኘው ውጤት ተሰንዶና መልክ ይዞ ለሚመለከታቸው አስፈፃሚና ፖሊሲ አውጪዎች እንዲደርስ ይደረጋል ተብሏል። በተጨማሪም


AAU-Official
21 сент., 10:40
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ1978 ዓ.ም. የመካኒካል ምህንድስና ምሩቃን 40ኛ የምረቃ ዓመታቸውን አከበሩ።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ፋካልቲ ኮሌጅ የ1978 ዓ.ም. የመካኒካል ምህንድስና ምሩቃን ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ተገናኝተው ትዝታቸውን ያደሱበትና ቀጣይ ትብብራቸውን የመከሩበት ልዩ መርሐ ግብር ተካሄደ።በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው፣ ምሩቃኑ ባለፉት ዓመታት ያካበቱትን የሙያና የሕይወት ተሞክሮ ለተማሪዎች እንዲያጋሩና ለዩኒቨርሲቲው የልማት ጥረቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።በውይይቱም የምሩቃኑን ልምድ ከዩኒቨርሲቲው የለውጥ ሂደት ጋር ማስተሳሰር፣ በምርምር፣ በፈጠራ፣ በዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ ትስስር እንዲሁም በተማሪዎች የሙያ እድገት የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር በዋናነት ተነስተዋል።መርሐ ግብሩ ምሩቃኑ በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ አዳዲስ ሥራዎችንና ዋናውን ግቢ በመጎብኘት ተጠናቋል።


AAU-Official
21 сент., 10:37изменён
We are now accepting first year students whose Average Result is 50 % and above. All interested can apply.


AAU-Official
18 сент., 12:01
Africa Water Security Conference (AWS-2026): Towards a Water-Secure and Resilient AfricaFrom September 21 to 23, 2026 at Adwa Victory Memorial HallJointly Organized byAddis Ababa University, Africa Center of Excellence for Water Management (ACEWM), and Ministry of Water and EnergyFor more information https://www.aws-2026.org/


AAU-Official
18 сент., 11:06
Addis Ababa University Model Community School: Where Future Talent is nurtured and Future Leaders are shaped.
AAU-Official
17 сент., 14:33
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል ኮሚዩኒቲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት ሥራ ጀመረ::ለ75 ዓመታት በከፍተኛ ትምህርት፣ በምርምርና በሀገራዊ አገልግሎት የተገነባውን ልምድ፣ ዕውቀትና ኃላፊነት ከታዳጊው ትውልድ ጋር ለማገናኘት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ አዲስ በር ከፍቷል። ለበርካታ ጊዜያት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየውን ዘመናዊ ሞዴል ኮሚዩኒቲ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ተማሪዎች እና ወላጆች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም. በታላቅ ሥነ-ሥርዓት መርቆ ሥራ አስጀምሯል።የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት፣ የትምህርት ቤቱ መመረቅ የዩኒቨርሲቲው የረጅም ጊዜ እቅድ ፍሬ ያፈራበት ታሪካዊ ዕለት ነው ብለዋል። አክለውም ትምህርት ቤቱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የዋጁ የላቦራቶሪ ክፍሎችን፣ የስፖርት ማዕከላትን፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የመማሪያ ክፍሎችን እና ምቹ ከባቢን ያካተተ በመሆኑ የሀገራችንን የቀጣይ ዘመን ተስፋዎች የሚቀርጹ ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል።በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የቢሮው ተወካይ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ብቻ ሳይወሰን የመጀመሪያ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት መክፈቱ ትውልድን በእውቀት ለመቅረጽ ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ተናግረዋል። በተጨማሪም ይህ የማህበረሰብ ትምህርት ቤት የዩኒቨርሲቲው አካል በመሆኑ




AAU-Official
17 сент., 09:56
Notice to Prospective Students and UsersProspective students and users who have inquiries or require assistance regarding registration-related issues are kindly requested to submit their inquiries through the website below or by scanning the QR code provided above.Website: Help DeskThank you for using the designated channels for registration-related inquiries.AAU Registrar



AAU-Official
17 сент., 09:34
ለ2019 ትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተወዳድራችሁ በመደበኛው መርሃ - ግብር ቅበላ ላላገኛችሁ አመልካቾች በሙሉ:የዩኒቨርሲቲውን መግቢያ ፈተና (UAT) 50 እና ከዚያ በላይ ያገኛችሁ በተከታታይ ትምህርት (Extension) ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይማሩ: ህልሞን ያሳኩ::አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር
AAU-Official
17 сент., 07:09
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅበላ ላገኛችሁ በሙሉ የመመዝገቢያ ይለፍ ቁጥር (Password) በፖርታል (www.portal.aau.edu.et) እንድትከታተሉ በትሕትና እንገልፃለን
AAU-Official
17 сент., 06:14
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ


AAU-Official
16 сент., 19:33




AAU-Official
16 сент., 14:58изменён
ልጆቻችሁን በሞዴል ኮምኒቲ ትምህርት ቤቱ ላስመዘገባችሁ ወላጆች!ትምህርት ቤቱ አዲሱን ግቢውን በይፋ የሚከፍትበትንና ስራ የሚጀምርበትን ቀን በመሆኑ የመርሐ-ግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።• ቀን፦ ሐሙስ፣ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም.• ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 6:00 ሰዓት• ቦታ፦ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢበመርሐ-ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲው የበላይ ኃላፊዎች፣ የክብር እንግዶች እና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የሚገኙ ሲሆን፣ ጠቃሚ መልእክቶች ይተላለፋሉ፤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱም በድምቀት ይከናወናል ተብሏል።የትምህርት ቤቱ አስተዳደር


AAU-Official
16 сент., 14:49
Last Call for applications for admission to graduate programs for the First Semester of 2026/27 (2019 E.C.) Academic Year Addis Ababa University (AAU) has opened up the call for the academic year of 2026/27(2010 E.C.) first semester in Masters (regular and extension) as well as PhD programs listed on the link https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms. Applicants are required to follow the steps described as follows: A. The AAU Graduate Admission Test (GAT) Applicants must have taken and scored passing marks along with GAT certificate GAT results from the previous year (as of September 2025) remain valid for the current application cycle. B. General steps for applying to the AAU Graduate Program Open the portal of Addis Ababa University https://portal.aau.edu.et Click on the Apply for Admission link on the second bar on the left side On the top bar, you will find the Graduate
AAU-Official
15 сент., 15:00



AAU-Official
14 сент., 15:48



AAU-Official
14 сент., 15:48



AAU-Official
14 сент., 14:37



AAU-Official
12 сент., 13:20



AAU-Official
10 сент., 16:21
የአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልእክትመልካም አዲስ አመት - Happy Ethiopian New Year 2019ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌየ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት
AAU-Official
10 сент., 16:00
የአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁ መልእክትመልካም አዲስ አመት - Happy Ethiopian New Year 2019ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌየ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት
Ссылки
