gram news
Аватар канала Abiy Ahmed Ali

Abiy Ahmed Ali

@abiyahmedaliofficial

ነጻነት ለህዝባችን - ብልጽግና ለአገራችን! Bilisummaan uummata keenyaaf - badhaadhinni biyya keenyaaf! Freedom to our People – Prosperity to our Nation!

ПроектыENПолитикаПодтверждён Telegram

180,000подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Abiy Ahmed Ali

    15 сент., 23:02

    በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎ ‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ። ‎ ‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው። ‎ ‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው። ‎ ‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። ‎
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    15 сент., 06:57

    🇪🇹 Come to Ethiopia — get a 7-year age discount!It’s 2026 in much of the world, but on September 11, Ethiopia welcomed 2019.Come for the 7-year age discount. Stay for the ancient history, epic landscapes, legendary coffee, vibrant culture, and unforgettable hospitality.Ethiopia — where time is younger and the adventure is timeless.
  • Abiy Ahmed Ali

    14 сент., 08:21изменён

    በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የነበረን ቆይታ ቅኝት፦ ‎አዲሱን ዓመት የጀመርነው ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችን በተረጋገጡበት እና የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ባለበት ታሪካዊ ስኬት ነው! ‎ ‎🇪🇹
  • Abiy Ahmed Ali

    13 сент., 12:21

    Economic uncertainty is testing our countries. BRICS has already reshaped the global conversation. Our responsibility now is to help shape a fairer international system and widen economic opportunity.
  • Abiy Ahmed Ali

    13 сент., 06:35

    በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት።🇪🇹 🇨🇳
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    13 сент., 06:26

    የብሪክስ ጉባኤ ሁለተኛው ቀን ላይ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል። ‎በዲጂታላይዜሽን፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በመከላከያ መስኮች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት እና ‎በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል።🇪🇹 🇰🇿
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 15:57

    BRICS 2026 Summit Remarks
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 14:41

    ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግን አግኝቸ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ትብብራችንን ማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎🇪🇹 🇻🇳
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 13:52

    ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ‎ ‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል።‎🇪🇹 🇷🇺
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 13:15

    ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መክረናል።‎በቆይታችንም በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።‎🇪🇹 🇦🇪
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 12:54

    ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል። ‎ ‎በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ ናት። ‎ ‎በተጨማሪም በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ይኖርብናል። ‎ ‎የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው።
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 08:47

    ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተናኝተን መክረናል። ‎ ‎በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል። ‎ ‎ውይይታችን ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው።🇪🇹 🇲🇾
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 07:01

    በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተናል። ‎ ‎ከጉባኤው ጎን ለጎን ባደረግነው ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል።🇪🇹 🇮🇷
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    12 сент., 06:47

    በሕንድ ይፋዊ የሥራ ጉብኝቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በመገናኘት፣ የኢትዮጵያ-ሕንድ አጋርነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ሃሳብ ተለዋውጠናል። ‎ ‎ውይይታችን የመከላከያ ትብብርን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን አጋርነት ማጠናከር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እነዚህ መስኮች በተግባር የታገዘ ትብብራችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና ለሕዝቦቻችን አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም አላቸው። ‎ ‎ኢትዮጵያና ሕንድ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር፣ የዘመናት የባህል ግንኙነት እና በሕዝቦቻችን መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አለን፤ ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉት በርካታ አቅሞች ገና ያለተነኩ ናቸው። ያለንን የጋራ ታሪክና ትብብር በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት፣ በኢንቨስትመንት፣ በዘላቂ ልማት እና ይበልጥ በጠነከረ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ወደተመሠረተና የላቀ የጋራ ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥ አጋርነት ለመለወጥ አሁን ትክክለኛው ጊዜ ነው ብዬ አምናለሁ። ‎ ‎🇪🇹 🇮🇳
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    10 сент., 13:01

    እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ፣ አደረሰን!!
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    10 сент., 12:11

    እናልማለን፤ እንተጋለን፤ እንፈጽማለን ።
  • Abiy Ahmed Ali

    10 сент., 09:14

    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali
  • Abiy Ahmed Ali

    10 сент., 09:14

    ኢትዮጵያ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ጉዞ፡ በተግባር የታነጸበት ስራዛሬ በሞጆ ተገኝተን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና የሚጫወተውንና በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፍያ የመጀመሪያ ምዕራፍ አስመርቀናል። ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ባለ 20 ጫማ ኮንቴነሮች የማስተናገድ አቅም ያላቸው ጣቢያዎችና ዘመናዊ መጋዘኖች ያሉት ሲሆን፣ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ እንድናሽግ ማስቻሉ፣ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎቻችን ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።ሙሉ አሰራሩ በዘመናዊ ዲጂታል መሰረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ፣ ለተገልጋዮች ፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎትን ያሳልጣል። ይህ ማዕከል ከኢትዮ-ጅቡቲ መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል ሲሆን፤ ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ደረጃ ላይ ያላትን ስፍራ የሚያሻሽልና የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስራችንን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር ትልቅ ድል ነው።
    Иллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed AliИллюстрация к посту канала Abiy Ahmed Ali