gram news
Аватар канала Addis Admass

Addis Admass

@adissadmas

የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ

ПроектыENПолитика

18,700подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Addis Admass

    26 сент., 14:19

    ኔታንያሁ በተመድ ጉባኤ ላይ ሲናገሩ 28 አፍሪካውያን አገሮች ጥለው ወጥተዋል የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ በቆሙበት ሰዓት፣ ቢያንስ 28 የአፍሪካ አገራትን ጨምሮ ከ77 በላይ አገሮች ከአዳራሹ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ከእነዚህ አገሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራ እና ዩጋንዳን
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 13:28

    ገና በ5 ዓመቱ ሮቦት የሠራው አፍሪካዊ ታዳጊ! የ10 ዓመቱ ግብፃዊ ማርቲሮስ ሚና በዓለም አቀፍ የፓይተን ፕሮግራሚንግ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ በማሸነፍ ከዓለም አቀፍ ተወዳዳሪዎች ምርጥ 2 በመቶ ውስጥ ተካትቷል። በቻይና በተዘጋጀው በዚህ ትልቅ ውድድር ከ31 አገሮች የተውጣጡ ከ7 ሺሕ በላይ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል። ማርቲሮስ የቴክኖሎጂ ችሎታውን ማሳየት የጀመረው በጣም በለጋ ዕድሜው ነበር፡፡ ገና
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 13:11

    "ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው" ‹‹መስከረም 16›› "ደመራ" ማለት ደመራ ደመረ ከሚለው መነሻ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መሰብሰብ ማከማቸት ማለት ነው። የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። በዚያም የመስቀሉን ስፍራ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ፈለገች።
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 12:23

    የቲና ተርነርን "WE DON'T NEED ANOTHER HERO" ማዳመጥ መረጥኩቻናል 4 እና ዲደብሊውን ጨምሮ የአልጀዚራና ቢቢሲን ትኩረት በሳበው የቀድሞ ጠላቶች አጋርነትና በኢትዮጵያ ዳግም በተቀሰቀሰው ጦርነት ዙሪያ የምለው ብዙ ነገር ነበረኝ።እንዳለመታደል ሆኖ ይህን ሁኔታ ለመግለጽ ብዙ ጊዜና ጉልበት ይጠይቃል። ስለዚህም፣ በኢትዮጵያ ዳግም በተቀጣጠለው ጦርነት ጉዳይ ላይ ዝምታንና የቲና ተርነርን WE DON'T NEED ANOTHER HERO ዘፈንን ማዳመጥን መረጥኩ።Kiflu Hussainማስታወሻ፡- የቲና ተርነር «ዌ ዶንት ኒድ አናዘር ሄሮ» ዘፈን ዋና መልዕክት በጦርነትና በግጭት ፈንታ ሰላምንና ፍቅርን ማስቀደም አስፈላጊ መሆኑን ማሳየት ነው። ሕዝቡ በሰላም ለመኖር የሚያደርገው ጥረት ከጦርነት እና ከኃይል እርምጃ እንደሚበልጥ ይገልጻል።
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 11:20

    "ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው"‹‹መስከረም 16›› "ደመራ" ማለት ደመራ ደመረ ከሚለው መነሻ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መሰብሰብ ማከማቸት ማለት ነው።የታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ፣ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክቡር መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። በዚያም የመስቀሉን ስፍራ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ፈለገች።በኋላ ኪራኮስ የተባለ አረጋዊ ስፍራውን ነገራት። ንግሥት ዕሌኒም ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ በጸሎት ተማፀነች። የዕጣኑም ጢስ ወደ ሰማይ ወጥቶ መስቀሉ ወደተቀበረበት ስፍራ ተመልሶ መራት።በዚያም በቁፋሮ የጌታችንን ክቡር መስቀል ከሁለቱ ወንበዴዎች መስቀሎች ጋር አገኘች። የጌታችንን መስቀልም የለየችው በተአምራቱ ነው፤ ድውያንን ፈወሰ፣ አንካሳዎችን አበረታ፣ ጎባጣዎችን አቀና፣ የዕውራንንም ዓይን አበራ።እርስዋም መስከረም ፲፯ ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት ፲ ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች፤ የደመራ ሥርዓት ከዚህ ሲያያዝ የመጣ ነው። ስለዚህ በየዓመቱ የመስቀልን በዓል ስናከብር ደመራ የምንደምረውና የምናበራው ንግሥት ዕሌኒን አብነት በማድረግ ነው።የደመራ በዓል የበረከትና የሰላም በዓል ያድርግልን! 🙏Henok Abebe-የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 11:07

    የመስቀል ደመራ በዓል ከፌደራል ፖሊስ ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል በቀጥታ ክትትል ስር!የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል በዓሉ በሰላም፣ በድምቀት እና ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና ካሜራዎች የታገዘ ቀጥተኛ የክትትል ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 10:57

    የደመራ በዓል ምስጢር፡ ህብረት፣ አንድነት እና አብሮነት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል መምህር የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ሐዋዝ ካሳዬ እንደገለጹት፣ የደመራ በዓል ዋና ምስጢር "ህብረትን፣ አንድነትን እና መተባበርን" የሚያሳይ ነው። በርካታ ትንንሽ እንጨቶች ተሰብስበው ችቦዎች እንደሚሰሩ እና ችቦዎች ተሰባስበው አንድ ትልቅ ዳመራ እንደሚፈጥሩ ሁሉ፤ ይህም የሰው ልጅ
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    26 сент., 10:34

    የደመራ በዓል ምስጢር፡ ህብረት፣ አንድነት እና አብሮነትበመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል መምህር የሆኑት መጋቤ ሐዲስ ሐዋዝ ካሳዬ እንደገለጹት፣ የደመራ በዓል ዋና ምስጢር "ህብረትን፣ አንድነትን እና መተባበርን" የሚያሳይ ነው። በርካታ ትንንሽ እንጨቶች ተሰብስበው ችቦዎች እንደሚሰሩ እና ችቦዎች ተሰባስበው አንድ ትልቅ ዳመራ እንደሚፈጥሩ ሁሉ፤ ይህም የሰው ልጅ ህብረትና ትብብር ትልቅ ኃይልንና ውጤትን እንደሚያስገኝ ያሳያል።በዚህም የተባበረ ሕዝብና አገር ኢኮኖሚውን፣ ፖለቲካውን እና ማህበራዊ አቅሙን በማጠናከር ለማንኛውም ዕድገትና ልማት መብቃት እንደሚችል ተመላክቷል። መጽሐፍ ቅዱስም "ሁለትም ሦስትም ሆናችሁ በስሜ የምትሰበሰቡ በመካከላችሁ እገኛለሁ" (ማቴዎስ 18÷20) እንደሚል፣ እግዚአብሔር የሚገኘው በህብረትና በፍቅር መካከል መሆኑ ተገልጿል።ሀገራችን ካሏት በርካታ ልዩነቶች አንፃር ሰላምን አግኝተን ወደ አንድነት ከመጣን የራሳችንን ልማት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን አፍሪካን ጭምር ማልማት የሚቻልበት አቅም እንዳለ ተጠቁሟል። በችግር ጊዜ አንዱ የወደቀውን በማንሳት፣ በመጸለይና በመተሳሰብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ መፈጸም እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፤፣ በህብረት የሚሰራ ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚባርከው መልእክት ተላልፏል።AMN-የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:58

    "ከ10 ዓመታት በኋላ ወንድሜን ዶክተር ቴድሮስን በኒው ዮርክ ድንገት በማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ።" - አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:46

    ከአስር ሺህ በላይ የብራና መጻሕፍት ወደ ዲጂታል ተቀየሩከአስር ሺህ በላይ የብራና መጻሕፍት በዲጂታል ቅጂ ተዘጋጅተው ለጥናትና ምርምር ዝግጁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ታሪክና የብራና ጽሑፎች ተመራማሪው አቤሜሌክ ኤርሚያስ ገለጹ። ተመራማሪው እንደገለጹት፤ እስካሁን በተከናወኑት በዲጂታል የማዘጋጀት ጥቂት ሥራዎች እንኳን፣ ቀደም ሲል ማንም ሊደርስባቸው ያልቻላቸው አዳዲስ የንግድ መስመሮች እንደነበሩ ማወቅ ተችሏል። በተጨማሪም የብራና ጽሑፎችን ለሰዎችና ለተመራማሪዎች በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።በዲጂታላይዜሽን ሥራው አማካኝነት የብራና መጻሕፍቱ ባለቤትነትና የት እንደሚገቡ በግልጽ ማወቅ በመቻሉ፣ ቀደም ሲል ተሰርቀው የነበሩ በርካታ የብራና ጽሑፎችን ማስመለስ እንደተቻለም ተመራማሪው አቤሜሌክ ገልጸዋል። ይህ አዲስ ስኬት የአገሪቱን ጥንታዊ የታሪክና የባህል ቅርስ ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው መድረክ ላይ ተመልክቷል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:36

    «ኢትዮጵያ ለአንድ ሰው ልትሰጥ የሚገባትን የመጨረሻ ክብር ሰጥታኛለች!»የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው "ድል ቁርሱ" የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ። በ8 ምዕራፎችና በ355 ገጾች የተቀነበበው ይህ መጽሐፍ፤ የፊልድ ማርሻሉን ከልጅነት እስከ ዕውቀት ያሳለፉትን ውጣ ውረድ፣ ለሀገር ያበረከቱትን አስተዋጽኦ እና የሰጡትን ቁርጠኛ አመራር በስነ-ጽሑፋዊ ለዛ ይተርካል።በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ በራሳቸው ሕይወት ላይ መጽሐፍ ለማሳተም ፍላጎት አልነበራቸውም፤ ነገር ግን ታሪካቸው ለቀጣዩ ትውልድ አርአያ ሊሆን ይችላል በሚል በብዙዎች ጉትጎታ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። "በበላይ ዘለቀ፣ በአብዲሳ አጋ ሀገር ይገነባል፣ በፊልድ ማርሻል ብርሃኑም ይገነባል፤ ነገር ግን የሆነን ሰው ለማግነንና ለመካብ መሆን የለበትም" ሲሉ ተናግረዋል።አክለውም "ኢትዮጵያ ለአንድ ሰው ልትሰጥ የሚገባትን የመጨረሻ ክብር ሰጥታኛለች፤ እኔም ለኢትዮጵያ የሰሰትኩት አንዳች ነገር የለም" በማለት የላቀ ምስጋናቸውንና ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ይህ መጽሐፍ የነገን መከላከያ ለመገንባትና ትውልድን ወደፊት ለማሸጋገር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም አፅንኦት ሰጥተውበታል።ENA-የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:28

    የመተሃራ ከተማ ከንቲባና አሽከርካሪያቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈበኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን መተሃራ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ አዲሱ ዋቆ እና አሽከርካሪያቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ አደጋው የደረሰው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከመተሃራ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር በማይሞላ «ኢላላ» በተባለ ቦታ ላይ ሲሆን፣ የነበሩበት ተሽከርካሪ ከቦቴ መኪና ጋር በመጋጨቱ ምክንያት የተከሰተ እንደሆነ ታውቋል።እንደ አካባቢው ነዋሪዎች እና የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ገለጻ፣ አሽከርካሪው አደጋው በደረሰበት ዕለት ወዲያውኑ ሕይወቱ አልፏል። ከንቲባ አቶ አዲሱ ዋቆ ግን አደጋው ቢደርስባቸውም በወቅቱ ተርፈው በኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ የቆዩ ቢሆንም፣ ሕይወታቸውን ማዳን ሳይቻል ቀርቶ ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:18

    የኖርዲክ የምግብ ሳምንት በማርከስ አዲስ ተጀመረበአዲስ አበባ የሚገኘው የፊንላንድ ኤምባሲ እንዳስታወቀው፣ በታዋቂው ኢትዮጵያዊ-ስዊደናዊ ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን የሚመራው «ማርከስ አዲስ» ሬስቶራንት የኖርዲክ የምግብ ሳምንትን ማስተናገድ ጀምሯል። በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት 47ኛ ፎቅ ላይ የሚገኘው ይህ ሬስቶራንት፣ የከተማዋን ማራኪ እይታ እያሳየ ልዩ የምግብ ተሞክሮ ያቀርባል። ኤምባሲው እንደገለጸው፤ የምግብ ባህል ሰዎችን የሚያቀራርብና ባህልን የሚያስተዋውቅ ትልቅ ድልድይ ነው።በቀጣዮቹ ሳምንታት የኖርዲክ ሀገራት የምግብ ባህላቸውን የሚያስተዋውቁ ሲሆን፣ የፊንላንድ ሳምንት ደግሞ ጥቅምት 7 ይጀምራል። ኤምባሲው የፊንላንድን ባህላዊ ጣዕሞች በአዲስ አበባ ለማስተዋወቅ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ፍላጎት ያላቸው ሁሉ ተገኝተው ይህንን ልዩ ተሞክሮ እንዲካፈሉ ጥሪ አቅርቧል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 19:07

    የክቡር አቶ ይልማ ደሬሣ የአሜሪካ የሚሲዮን ግብ ምንና ምን መሆኑ እንደተገለጸው፤ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዋና መልዕክተኛ ዋሽንግተን እንደደረሱ፤ ከኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የተላከውን ልዩ መልዕክት ለአሜሪካው መሪ ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ለማቅረብ ቀጠሮ ጠየቁ፡፡ የስቴት ዴፓርትመንት፤ (ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር) እና የዋይት ሐውስ ቤተመንግሥት ኃላፊዎች ከተወያዩበት በኋላ፤ የተሻለው መንገድ ፕሬዚዳንት ሩዝቬልት እ.ኤ.አ ሐምሌ 7 ቀን 1943 ዓ.ም የዓለም የእርሻና የምግብ ጉባኤ የመልዕክተኞች መሪዎች የሆኑትን የሬሴፕሽን ግብዣ በማድረግ ስለሚቀበሉ! በዕለቱ ክቡር አቶ ይልማ ደሬሣን የንጉሠ ነገሥቱን ልዩ መልዕክት ለማቅረብ እንዲችሉ ተወሰነ፡፡በመሠረቱ አቶ ይልማ ዴሬሣ የያዙት ዋናው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በእንግሊዞች ወታደራዊ አስተዳደር የደረሰባትን ችግር በተቻለ ያህል ለአሜሪካው መሪ በቃል ለማስረዳትና በሜሞራንደም (ማስታወሻ) ያዘጋጁትንም ጽሑፍ አያይዞ በእጅ - ለመስጠት ነው።በተጨማሪም ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለወዳጃቸው ለፕሬዚዳንት ሩዝቬልት ፈርመው የላኩትን የመታሰቢያ ፎቶግራፍ ለማቅረብ አቶ ይልማ ተዘጋጅተዋል፡፡ ነገር ግን የዋይት ሐውስ ፕሮቶኮል ሹም አቶ ይልማ ዴሬሣ ፕሬዚዳንቱን እንዲያነጋግሩ የፈቀደላቸው ጊዜ፤ ከሰባት ደቂቃዎች የማይበልጥ ስለሆነ በዚች ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ዋና ዋና ችግሮች አሟልቶ ለማስረዳት ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መልዕክተኛ እጅግ የከበደ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ( School Of Economics ) የተመረቁትና ጣዕም ያለው እንግሊዝኛ ተናጋሪ የሆኑት
    TelegramAddis Admassየአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ ===== አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv የእርስዎና የቤተሰብዎ
  • Addis Admass

    22 сент., 19:07

    "እናንተ ኢትዮጵያውያኖች አገራችሁ ያላትን የተከበረ ጥንታዊ ታሪክና ባሕል የማንፀባረቅ ተሰጥዎ ያላችሁ ናችሁ."-ፕሬዚዳንት ሩዝቬልትክቡር አቶ ይልማ ደሬሣ.......ታላላቆቼ ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስና ክቡር አቶ መኮንን ሀብተወልድ የገለጻችሁልኝ አስተያየት በአዕምሮዬ ስለተቀረጸ፤ ለሥራዬ መልካም ድጋፍ ሆኖ እንደሚረዳኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እዚህ ላላችሁት ለታላላቆቼና ለጓደኞቼ በአጭሩ ለማረጋገጥ የምፈልገው፤" .........ለእኔ ለይልማ ደሬሣ በዚህ ዓለም ከኢትዮጵያ የሚበልጥብኝ ነገር የለም......."፡፡ ስለዚህ ለተላኩበት ለአሜሪካ ለሚያዳምጡኝ የአገሬን ችግር በተቻለኝ ዘርዝሬ አስረዳለሁ፡፡ ለሚከራከሩኝም በተቻለኝ ጠንክሬ እሟገታለሁ፡፡ አንድ ጊዜ ክቡር ጸሐፊ ትዕዛዘ አስተያየት ሲሰጡ፤ ሥራ ሳይጀመር ብዙ የሚናገር ብዙ አይሠራም" ብለዋል፡፡ ስለዚህ እኔም ጥቂት የምናገርና ብዙ የምሠራ ሆኜ ለመገመት እንድችል፤ ንግግሬን ማሳጠር እወዳለሁ፡፡ ለሰጣችሁኝ ጥልቀት ላለው ምክርና ለገለጻችሁልኝ የጋለ መልካም ምኞት ከልብ የሆነ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በሰላም ይግጠመን ብዬ እሰናበታችኋለሁ፡፡ይህንን የተናገሩት ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳ ሃገራቸውን ከእንግሊዝ ሞግዚትነት ለማላቀቅ ይቻል ዘንድ ወደ አሜሪካ መልዕክት ይዘው እንዲሄዱ ኃላፊነት የተሰጣቸው በሽኝት መርሃ ግብር ቀን ላይ ነበር።ክቡር አቶ ይልማ ደሬሳ [ በአሜሪካን --- ዋሸንግተን ዲሲ ]⬇️⬇️
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 18:50

    የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን እስር ኮነኑበትግራይ ክልል የሚገኙ የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች 6 የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ሰኞ ዕለት ማሰራቸው ተሰምቷል። መምህራኑ በታጠቁ ኃይሎች ተይዘው የተወሰዱት ከዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውጭ ከሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ውስጥ እንደሆነ ከምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ድርጊቱን አጥብቀው የኮነኑ ሲሆን፣ በትግራይ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያደፈርሱ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እስር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱን ህልውናና የተማሪዎችን የወደፊት እድል አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 18:42

    በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አሳስቦኛል፡ ተመድየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ይበልጥ ሊባባስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለው ገለጸ። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቲፋኒ ዱጃሪክ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ በአገሪቱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መፍጠራቸው፣ የድሮን ጥቃቶች መደጋገማቸውና የጸጥታ ችግሮች መቀጠላቸው ለስጋቱ ምክንያቶች መሆናቸውን ጠቅሰዋል። አክለውም ወታደራዊ ርምጃ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንም ሆነ ነባር ቅሬታዎችን ሊፈታ እንደማይችል በመግለጽ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን ይበልጥ ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ አጥብቀው ጠይቀዋል።በተያያዘ ዜና፣ በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኦዞኒያ ኦጄሎ በአገሪቱ ሰላም፣ መተማመና አብሮነት እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል። ሃላፊው የሁኔታውን አሳሳቢነት በማንሳት፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሉትን ልዩነቶች በሰላማዊ ንግግር ብቻ እንዲፈቱ እና ከምንም በላይ ለዜጎች ደኅንነት ቅድሚያ እንዲሰጡ አሳስበዋል።የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 17:38

    የኢራን መሪ ሞጅታባ ካሜኒ በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ይፋ ሆነየኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙኃን ማክሰኞ ዕለት የሀገሪቱ የበላይ መሪ የሆኑት ሞጅታባ ካሜኒ በእጅ የተጻፈ ነው ያሉት አንድ ደብዳቤ ይፋ አደረጉ።ይህ ደብዳቤ፣ በየካቲት ወር በአባታቸው ቢሮ ላይ ከደረሰ ጥቃት መሪው በሕይወት መትረፋቸውን ሊያሳይ የሚችል የመጀመሪያው ምልክት ሊሆን ይችላል ተብሏል። አባታቸው አሊ ካሜኒ በዚያው ጥቃት ሕይወታቸው አልፏል።ከጥቃቱ ወዲህ ሞጅታባ ካሜኒ በሕዝብ ፊት ታይተውም ሆነ ድምፃቸው ተሰምቶ አያውቅም። ምንም እንኳ በስማቸው የተለያዩ መግለጫዎች ቢወጡም፣ እውነተኛ ፎቶግራፋቸው፣ ቪዲዮአቸው ወይም የድምፅ ቅጂያቸው ፈጽሞ አልወጣም።አዲስ የወጣው ደብዳቤ ነሐሴ 1 ቀን የተጻፈ ሲሆን፤ የተላከውም ለኢራን አብዮታዊ ዘብ የኤሮስፔስ ኃይል አዛዥ ለሆኑት ማጂድ ሙሳቪ ነው። ደብዳቤው አዛዡ ያቀረቡትን ሪፖርት አድንቆ፣ የቁሳቁስ አቅርቦት ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል።በተጨማሪም መሪው ለአዛዡ ሲጽፉ «የእርስዎን እና የሠራተኞችን ውድ ሕይወት መጠበቅ ጥብቅ አደራዬ ነው» በማለት አጽንኦት ሰጥተዋል።Iran International -የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
    1,010711Открыть в Telegram
  • Addis Admass

    22 сент., 17:35

    የብርቱካን ሚደቅሳ ገንቢ መልዕክት በርካታ የዘመኑ ወጣቶች ሙያን፣ሥራ እና ክህሎትን የሚይዙበት መንገድ እጅግ ይገርመኛል። ለዓመታት ተምረው ከተመረቁበት ሙያ ፍጹም በተለይ መስክ/ክህሎት (አንድም ለገቢ ሲልም ለደስታ) ራሳቸውን አሠልጥነው ብዙ ዓይነት ስራ ያለምንም መጎረባበጥ ጎን ለጎን ያስኬዳሉ። ሀኪሟ ትዘፍናለች፤ ኢንጂነሩ ይስላል ...ወዘተ። ይህን እውን ለማድረግ ሲሉ እኛ ከለመድነው በተለየ
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass
  • Addis Admass

    22 сент., 17:11

    የብርቱካን ሚደቅሳ ገንቢ መልዕክትበርካታ የዘመኑ ወጣቶች ሙያን፣ሥራ እና ክህሎትን የሚይዙበት መንገድ እጅግ ይገርመኛል። ለዓመታት ተምረው ከተመረቁበት ሙያ ፍጹም በተለይ መስክ/ክህሎት (አንድም ለገቢ ሲልም ለደስታ) ራሳቸውን አሠልጥነው ብዙ ዓይነት ስራ ያለምንም መጎረባበጥ ጎን ለጎን ያስኬዳሉ።ሀኪሟ ትዘፍናለች፤ ኢንጂነሩ ይስላል ...ወዘተ። ይህን እውን ለማድረግ ሲሉ እኛ ከለመድነው በተለየ የፍሪላንስ ስራ ምቾት ይሰጣቸዋል -ከአንዱ ወደሌላው ሳይቸገሩ ለመሯሯጥ።በዚህ አይነት ትጋት እና ስኬት በተምሳሌትነታቸው ካስደነቁኝ ወጣቶች አንዱ የሆነው የሀዋሳው ብርቱ ሰው Base Berhanu (የህክምና ዶክተር በዛብህ ብርሀኑ) 'አንሙት Clinic' የሚል ርዕስ ያለው ሲትኮም ጽፎ እና ዳይሬክት አድርጎ በሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለእይታ አቅርቧል።ወዳጆች፣እንይለታ!?ያለንን አስተያየትም እንለግሠው።እንኳን ደስ ያለህ ቤዝ😍የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ… https://t.me/AdissAdmas
    Иллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis AdmassИллюстрация к посту канала Addis Admass