Последние посты

Ahmed — أحمـــد
7 сент., 20:42
እንደምን ቆያችሁ? አዎን ጠፍቻለሁ … ቢሆንም በኔ ዙሪያ ያላችሁን ማንኛውንም አይነት አስተያየት፣ ትችት እና ወቀሳ በዚህ አቅርቡልኝ፦ @Ahmedresbot
Ahmed — أحمـــد
6 сент., 19:02
አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ በአረብ ሀገር በሳዉዲ አረብያ የምትኖር እህታችን ሀናን አህመድ በዚሁ የቲክቶክ መድረክ ወንድሞችንና ኡስታዞችን ስታግዝ ስታበረታታና ለበጎ ስራ ስትሽቀዳደም የነበረች መልካም እህታችን ነች። ሆኖም ግን በድንገት ባጋጠማት ከፍተኛ የጤና እክል ምክንያት ሶስት ጊዜ ያህል አባድ የሰርጀሪ ህክምናዎችን ለማድረግ ተገዳለች። በዚህም ምክንያት ያላትን ጥሪት በሙሉ ለመድኃኒትና ለሕክምና ጨርሳ አሁን ላይ ከባድ የሰው ዕዳ ውስጥ ወድቃ
Ahmed — أحمـــد
20 авг., 17:39
“One apple fell and the whole world knew gravity however, millions of bodies fell and no one knew humanity!“
Ahmed — أحمـــد
12 авг., 08:24
переслано из @abdulfetahou
በነቢይነታቸው አሥረኛ ዓመት፣ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ባለቤታቸውን እናታችን ኸዲጃን እና አጎታቸውን አቡ ጣሊብን በሞት ካጡ በኋላ፣ በቁረይሾች በኩል የሚደርስባቸው መከራና እንግልት በእጅጉ በረታ። በዚህም ምክንያት የመካ ሰዎች ጥሪያቸውን ባለመቀበላቸው፣ የእስልምናን መልእክት ለማድረስና ድጋፍ ለማግኘት ከአጎታቸው ልጅ ዘይድ ኢብኑ ሐሪሳ ጋር በመሆን ወደ ጣኢፍ ለመሄድ ተነሱ። ወደ ጣኢፍም በሄዱ ጊዜ የሰቂፍ ጎሳ መሪዎች ወደሆኑት ወደ ሦስቱ ወንድማማቾች — ዐብድ ያሊል፣ መስዑድ እና ሐቢብ — ዘንድ በመሄድ የእስልምናን ጥሪ አቀረቡላቸው፤ ከቁረይሾች ጥቃትም እንዲጠብቋቸው ጠየቋቸው። ነገር ግን መሪዎቹ በጥሪው ላይ አፌዙ፤ በጣም ባልተገባና ነቀፌታ በተሞላው መንገድ ጥሪያቸውን ውድቅ አደረጉት። መሪዎቹ ጥሪውን ውድቅ ከማድረጋቸውም በላይ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአስቸኳይ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ አዘዙ። ከከተማዋ ሲወጡም የከተማዋን እብዶች፣ ባሪያዎችና ሕፃናት በሁለት መስመር አሰልፈው ድንጋይ እንዲወረውሩባቸው አደረጉ። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና ዘይድ ኢብኑ ሐሪሳ ከተማዋን ለቀው እስኪወጡ ድረስ በድንጋይ ተደበደቡ፤ እግራቸው በደም ተለወሰ፤ ዘይድም ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) ለመከላከል ሲሞክር ራሱ ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰበት።ከከተማዋ ትንሽ ራቅ ብሎ በሚገኘው የቁረይሽ ከበርቴዎች በነበሩት በኡትባ እና ሸይባ የአትክልት ስፍራ በደረሱና ባረፉ ጊዜም፣ ውዱ ነቢይ ወደ አላህ እንዲህ ሲሉ ጥሪያቸውን አሰሙ፦ "اللَّهُمَّ إِلَيْكَ أَشْكُو ضَعْفَ قُوَّتِي، وَقِلَّةَ حِيلَتِي، وَهَوَانِي
Ahmed — أحمـــد
21 июл., 07:55изменён
No Reaction!
Ahmed — أحمـــد
15 июл., 13:20
ከንጽጽራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ Specially በቪድዮ ካልሆነ በጽሑፍ እየተዘጋጁ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን በዚህ አስቀምጡልን፦ @Kieran32n
Ahmed — أحمـــد
6 мая, 18:44изменён
አፖሎጄቲክስ መጽሄት አዲስ አበባ - 01https://t.me/ethiomuslimapologetics
Ahmed — أحمـــد
15 апр., 13:27изменён
ምሁራኑ ይህንን ጥያቄ ከ ተፈጥሮ ሥርዓት ጋር አያይዘው ሰፋ ያለ መረዳታቸውን አስቀምጠዋል። አምላክ አለምን የሰራት ዘፈቀዳዊ ሳይሆን ቋሚ በሆኑ ህግጋት (Laws Of Nature) እንድትመራ አድርጎ ነው። እነኚህ እንደ ስበት፣ ሙቀት፣ እንቅስቃሴ ያሉ መሰል ህግጋት ካልተለወጡና ቋሚ ከሆኑ ብቻም ነው ዓለም ሥርዓት አላት ልንል የምንችለው። ዛሬ የምበላውን መብል ያሞቀ እሳት ነገ ያቀዘቅዘዋል ብለን የማንጠብቀው፣ ድንጋይ ከላይ ሲለቀቅ ወደ ታች እንደሚወድቅ እርግጠኛ መሆን የምንችለው የተፈጥሮ ሕግ ቋሚ እና የማይለዋወጥ ስለሆነ ነው። በሃይማኖት ፍልስፍና (Philosophy Of Religion) ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረው አሜሪካዊ ፈላስፋ 'ብሩስ ራይከንባክ' እነዚህ ሕጎች በጎ ነገርን ለማምጣት አስፈላጊ የሆኑትን ያህል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሥቃይን የማምጣት ውጤት ይኖራቸዋል ሲለን እንግሊዛዊው ደራሲ 'ሲ. ኤስ. ሉዊስ' እ.ኤ.አ በ 1910 ባበረከተው "The Problem Of Pain" የተሰኘ መጽሐፉ ላይ የሰው ልጆች እርስ በርስ ለመግባባትና ነፃ ምርጫቸውን ለመለማመድ ገለልተኛና የማይለወጥ መድረክ ያስፈልጋቸዋል። ይህ መድረክ ደግሞ ቋሚው የተፈጥሮ ሕግ ነው። ሕጎቹ እንደፈለጉ የሚቀያየሩ ቢሆኑና አምላክ ጣልቃ ቢገባ ማኅበራዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር ሊኖር አይችልም ነበር ሲል አበክሮ ይሟገታል።ከነዚህ ትርጓሜዎች በመነሳት ተፈጥሯዊ እኩይ (Natural Evil) በ ኢስላማዊው ሥነ-መለኮት ውስጥ ሁለት ተያያዥ ገጽታዎችን ይይዛል። የመጀመሪያው የሥነ ፍጥረቱ ሥርዓት አካል መሆኑን ቁርዓን እንዲህ ሲል ያስረዳል
Ahmed — أحمـــد
15 апр., 13:26изменён
የ ነገረ እኩይ (Problem Of Evil) ፍልስፍናዊና ሥነ-መለኮታዊ ትንታኔ — ክፍል ሁለት … ባለፈው ክፍላችን የ እኩይ ምንነቱን በማስረዳት የጀመርነውን ጉዞ አጠናቅቀን በሌላኛው ሀተታ የ እኩይ ለምንነቱ'ን ለሚያነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሚሆኑ ትንተናዎች የ እኩይ መኖር በፍትሐ መለኮት (Theodicy) ሚዛን ላይ ሲቀመጥ ምን ይመስላል? የሚለውን የምንቃኝ ይሆናል።የ 18ኛው ክ/ዘመን ጀርመናዊው ፈላስፋ 'ጎትፍሪድ ዊልሄልም ላይብኒዝ' እ.ኤ.አ በ 1710 ዓ.ል ባበረከተው "Théodicée" የተሰኘ ታዋቂ መጽሐፉ ላይ እኩይ'ን ዲበ አካላዊ (Metaphysical)፣ ምግባራዊ (Moral) እና ተፈጥሯዊ (Physical/Natural) ሲል በ ሦስት መሠረታዊ መደቦች ከፍሎ ይመለከተዋል።[¹] ዲበ አካል (Metaphysics) የነገሮችን ምንነት፣ ህልውና እና መሠረታዊ ባሕርይ የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ሲሆን ከዚህ እይታ በመነሳት የ አንድ ነገር ህልውና በጎ (Good) ወይም እኩይ (Evil) ሊባል የሚችልበት እሴት ካለው የህልውና ሙላት እና ፍጽምና የሚመነጭ ነው ሲል ያስረዳል።ከ ዲበ አካላዊ እኩይ (Metaphysical Evil) መረዳቱ ጋር ተያይዞ ፈላስፋው 'ላይብኒዝ' ይህንን የ እኩይ መደብ አምላክ ፍጹም ሲሆን ፍጥረተ ዓለሙ አምላክ ስላልሆነ ፍጽምና ሊኖረው አይችልም። ፍጡር በ ባሕሪው ውስን መሆኑ ደግሞ ለስህተት በር ይከፍታል በሚል ያብራራዋል። ለምሳሌ፦ አንድ ሰው ስለ ነገ የሚያውቀው ነገር ውስን በመሆኑ ዛሬ ትክክለኛ ያልሆነ ውሳኔ ሊወስን ይችላል። ይህም የውሳኔ ስህተት የመጣው ከክፋቱ ሳይሆን
Ahmed — أحمـــد
7 апр., 13:59изменён
የ ነገረ እኩይ (Problem Of Evil) ፍልስፍናዊና ሥነ-መለኮታዊ ትንታኔ — ክፍል አንድ … “ያ የጎጃም ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፣ ቁርስ አርጎ ጨረሰው ጣልያንን በአንድ ሌት” (ገጣሚው ያልታወቀ) የተባለላቸው የጎጃሙ 'ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት' (የቀድሞው ራስ አዳል ተሰማ) በጽኑ በታመሙ ጊዜ፣ በወቅቱ የነበረው ማኅበረሰብ “ንጉሥ በቀላሉ እንዲህ አይታመምም፤ ካልመረዙት በቀር— በጭንቅ አይያዝም።” የሚል ጽኑ ጥርጣሬ የነበረው በመሆኑ ይኸው ጥርጣሬ እስከ ቤተ መንግሥቱ ድረስ ይገባና፣ የንጉሡ የበኩር ልጅ 'በለው አዳል' “አባቱን መርዟል” በሚል ተጠርጥረው ወደ ወህኒ ይወርዳሉ።'አያ በለው አዳል' በወህኒ ውስጥ ከባድ ሥቃይና መከራ ሲቀበሉ፣ በደረሰባቸው ግፍ እና የብቸኝነት ስሜት እጅጉን ተማረሩ። በዚህ የፍትሕ መጓደልና የግራ መጋባት ሁኔታ ውስጥ፣ የሰው ልጅን ዘላለማዊ የሕልውና ጥያቄ የሚያነሳ ይህን ዝነኛ ቅኔም ተቀኙ፦ “አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል፤ የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል።” ይህ የ በለው አዳል እሮሮ፣ የሰው ልጅ የመኖር ትርጉምን እና መለኮታዊ ፍትሕን ለመፈለግ ያለውን ጥልቅ እና ዘላቂ ጥያቄ ያንጸባርቃል። በምድር ላይ የሚታየው መከራና ግፍ “የተገፉትን የማይሰማ አምላክ አለ?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ያደርጋል።ይህ በሀገራችን ታሪክ የተመለከትነውን መሰል እሮሮ በምዕራባውያኑም ዘንድ በ 341 ዓ.ዓ አካባቢ ተወልዶ በ 270 ዓ.ዓ ገደማ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው የ "ኢጲቆሮሳዊነት" የፍልስፍና ትምህርት መስራች 'ኢጲቆሮስ ሳሞስ' ልክ እንደ አያ በለው ሁሉ ምንም እንኳ የአምላክን
Ahmed — أحمـــد
31 мар., 18:05изменён
ነገ ረቡዕ፣ ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ (Ethiopian Local Time) ከኡሥታዝ ቃለ-አሚን ፀጋዬ ጋር በቲክታክ የቀጥታ ስርጭት (Live) እንገናኛለን።ቆይታችንንም በኡሥታዝ ሳላህ ዘይን ከተዘጋጀው «ሰማዕቱ ብራና» የተሰኘ ስራ ጋር በማድረግ በመጽሐፉ ዙሪያ ሰፊ ግምገማ የምናካሂድ ይሆናል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። እንዳትቀሩ!
Ahmed — أحمـــد
24 февр., 17:56изменён
“እያንዳንዱ ሰው የሚኖረው ከሁለት ዓለማት ጋር በሚያካሂደው መስተጋብር ነው። አንደኛው ዓለም ውጫዊ ዓለም ሲሆን፣ ሁለተኛው ዓለም ደግሞ በውስጡ ያለው ዓለም ነው። በውስጣችን ያለው ዓለም እኛ በህይወት እስካለን ድረስ ብቻ የሚኖር ሲሆን፣ ውጫዊው ዓለም ግን እኛ በህይወት ብንኖርም ባንኖርም የሚኖር ዓለም ነው። የአንድ ሰው ውስጣዊ ዓለም የሚባለው ግለሰቡ ያለውን አመለካከት፣ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ ስሜት ወዘተ … ያጠቃልላል። ስለሆነም አንድ ሰው ውጫዊውን ዓለም የሚመለከትበትም ሆነ መጠቀም የሚችልበት አቅም በውስጣዊ ዓለሙ ባለው ብቃት ይወሰናል። ይህም ማለት አንድ ሰው የሚያውቀው፣ የሚረዳውና ሊሠራ የሚችለው የተማረው ነገር ውጤት ነው እንደማለት ነው። ዛሬ በዓለማችን ያሉ ዜጎች የአኗኗር ልዩነት የመጣው በአብዛኛው ለመማር ባገኙት ወይም ባጡት ዕድል ላይ ተመሥርቶ እንደሆነ በገሀድ የሚታወቅ ሐቅ ነው።“ — የተወሰደ
Ahmed — أحمـــد
16 февр., 10:13изменён
የቆየች ጽሑፌ ብትሆንም ተጋበዙልኝ :)አላህ ‘ﷻ’ በቁርዓን ላይ እንዲህ ይለናል፦ “የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ።“ — Quranስለዚህም አይደል አላህ ለፍጥረታቱ በወሰነው ትክክለኛ የጊዜ ቀመር ለመገልገል ስንል አሥራ ሁለት ወራትን ያለምንም ተጨማሪ እና ተቀናሽ ወራት “Leap Month” የያዘውን የጨረቃ የቀን መቁጠሪያ “Lunar Calendar” ለመቁጠሪያነት የምንጠቀመው — ይህ የቀን መቁጠሪያ ከያዛቸው አሥራ ሁለት ወራት ውስጥ አሁን ያለንበት የረመዳን ወር አንዱ ሲሆን ረሡል ‘ﷺ’ ከመካ ወደ መዲና ጉዞ ባደረጉ በሁለተኛው ዓመት እንደ ኤሮፓውያንን አቆጣጠር በ 624 CE ለመላው ሙሥሊም ማህበረሰብ ረመዳንን እንዲፆም ታዘዘ፦ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡” — Quranረመዳን “رمضان” የሚለው ቃል ረመደ “رمض” ማለትም “አቃጠለ” ከሚለው ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን “አቃጣይ” “የሚያቃጥል” ማለት ነው። የጨረቃ የቀን መቁጠሪያ “Lunar Calendar” ከፀሃዩ የቀን መቁጠሪያ “Solar Calendar” በ 11 ቀን አካባቢ ያነሰ ሲሆን የረመዳን ወር በአራቱም ወቅቶች ማለትም፦ ፀደይ፣ በጋ፣ በልግ እና ክረምት ውስጥ በየ ሠላሣ ሦሥት አመቱ ያልፋል፡፡ ለምሳሌ፦ በሀገራችን የዘመን መቁጠሪያ
Ahmed — أحمـــد
6 дек. 2025 г., 14:30изменён
Different Realities💔
Ahmed — أحمـــد
15 нояб. 2025 г., 08:34изменён
እስኪ ዛሬ ትንሽ ነገር ልጋብዛቹህ🤗'ነብዩ ሙሃመድ ሰ.አ.ወ ስሙ የገዘፈ የሰው ልጅ እሳቤ ማዕዘን ነው። ምንድን ነው የሚሉት? የሰው ልጅ የሁሉም ነገር ሚዛን ነው አይደል? በቃ ያ ሰው ሙሃመድ ሰ.አ.ወ ነው።የትኛውም የልዕልና ከፍታ የሰው ልጅን ህይወት አይዳስስም። አንዱ ስለ ሰላምና ፍቅር ይሰብክሃል ነገር ግን የሰው ልጅ ጦርነትን ይፈጥራል ያኔ ምን ታደርጋለህ? […ስለሰለም እየሰበክ ትኖራለህ?]ቡድሃ ኑሮ የለውም አንተ ግን አለህ!! እስኪ እሱን መሰረት አድርገህ ኑር። ግማሽ መንገድ ላይ ትቀራለህ። በህይወትህ ልክ ልክክ የማይሉ ታላላቅ ነፍሶች አሉ ግን በሚልየን መካከል እንዳለ አንድ ግለሰብ ለመኖር እንጂ እንደ ህዝብ አዳጋች ነው።የትኛውም በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ የሚከሰት ታላቅ ሰው አንዱን የህይወት መስክ መዝዞ ነው የምታገኘው። ወይ ፍቅር ሰብኮህ ያልፋል ወይ ጦር ያማዝዝሃል። ከላኦ ዙ እስከ ማህቪራ ፥ ከቡድሃ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ነብያቶች. . .ዳህማፓዳ ላይ ይሁን ሌላ ቦታ አንድ ታሪክ አለ። ቡድሃ ላይ ሰውየው ተፋበት። ቡድሃ በፍፁም ትዕግስት ውስጥ ነበር። ምንም አላለም ጭጭ።ዳግመኛ መጥቶ ይቅርታ ጠየቀ "ትናንት የነበረው ማንነታችን ዛሬ የለም ተፊውም የተተፋበትም ዛሬ የሉም""And whoever is patient and forgives – indeed, that is of the matters [worthy] of resolve.” (42:43)ይህ ግን ሁሌም አይሰራም። ቡድሃን መሆን አለብህ ነገር ግን ህይወት አንድ ቅርፅ ብቻ አይደለም ያላት። በዚህ ህይወት ውስጥ ተተፍቶብህ
Ahmed — أحمـــد
1 сент. 2025 г., 00:37изменён
ሀልዎተ ኢሥላም (ቅድመ ሙሐመድ 'ﷺ' ) ... የክርስቲያን አቃቢያን መታወቂያ ላይ የ አደጋ ጊዜ መውጫ ተብለው ከሰፈሩ ጥያቄዎች አንዱ ይህ "ቅድመ ሙሐመድ 'ﷺ' ባሉ ታሪካዊ ማስረጃዎች የእስልምና መኖር ሊረጋገጥ ይችላልን?" የተሰኘው ጥያቄ ነው ...ጥያቄውም እንደ ጥያቄ በአድማጩ ማህበረሰብ ላይ በተንሰራፋበት አውድ ተገቢውን መልስ ከማቅረብ አኳያ በኛ በኩል ካሉ አካላት ግልጽ እና አመርቂ እይታ ባለመመልከቴ ይህቺን መጣጥፍ አሰፍር ዘንድ ወደድሁ።የፍጥረተ አለሙ አስገኚ እኛ የሰው ልጆችን ሲፈጥር እሱን ለመገዛት የተመራን በመሆን ውስጥ ቃል የተገባልንን ገነት እንድናገኝ በሚል አላማ እንደሆነ በተከበረ ቃሉ አበክሮ ይነግረናል። (51፥56፣2፥21) ወደዚህች ምድር ሲያመጣንም እሱን ለመታዘዝም ሆነ ለማመፅ ከሚያበቃን የምርጫ ነፃነት “Free Will” ጋር ሲሆን ለፍጡራኑ ካለው ውዴታ በተነሳ ለገዛ ምርጫችን ሳይተወን በመልካም የሚያዙ በመጥፎ የሚያስጠነቅቁ ነብያትና መልዕክተኞችን ሲልክ ቆይቶ የነዚሁ ማገባደጃ እና ማብቂያ በማድረግ ነብዩ ሙሐመድን 'ﷺ' ከተከበረው ቃሉ ጋር ለአለም ልኳቸዋል። ይህ ነብያት የተላኩበት ለብቸኛው አምላክ እጅ የመስጠት (የመታዘዝ፣የመገዛት) መንገድ በዓረቢኛ የቃል አጠቃቀም ውስጥ ኢሥላም "اسلام" ተብሎ ሲጠራ የዚህ መንገድ አስኳል እና ምሰሶ የሆነው የአንድ እና ብቸኛ አምላክ አስተምህሮ "Monotheism" የነብያቱ መሠረታዊ አጀንዳ መሆኑን ጠቋሚ የሆኑ ዘርፈ ብዙ መረጃዎች ቢኖሩም በነዚህ መረጃዎች ላይ እንደ አንድ አርዕስት ለመመለስ በማሰብ በዛሬው ነጥብ ላይ አንዳንድ
Ahmed — أحمـــد
5 авг. 2025 г., 13:19
As Selamu Aleikum everyone Im Back✋🙂↕️Channel created
6 апр. 2025 г., 18:10
