gram news
Аватар канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

@aradafmdigital

YouTube channel -https://www.youtube.com/@aradafm95.1 Facebook page -https://web.facebook.com/aradafm Website - aradafm.com

ПроектыENМузыка

46,100подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 12:23

    17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ምድቡን አውቋልመስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የአፍሪካ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ከ17 ቀናት በኋላ ይጀምራል።የምድብ ድልድሉ ዛሬ ይፋ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሶስት ሀገራት ባሉበት ምድብ ሁለት ተደልድሏል።ዩጋንዳ እና ቡሩንዳ ከኢትዮጵያ ጋር በምድቡ የተደለደሉ ሀገራት ናቸው።ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 09 ድረስ በሩዋንዳ ኪጋሊ ከተማ ላይ ይደረጋል።በውድድሩ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የሚያጠናቅቁ ሀገራት ወደ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ያልፋሉ።ሀብታሙ ምትኩየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 10:16

    አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡መስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም)ተወዳጁ ሙዚቀኛና የስፖርት ጋዜጠኛ ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ በ83 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል፡፡በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በወርቃማው የሙዚቃ ዘመን ከ60 በላይ የማይረሱ እና ተወዳጅ የጥበብ ስራዎችን ያበረከተ አርቲስት ነበር፡፡ግርማ ነጋሽ ምነው ተለየሺኝ ፣ የኔ ሀሳብ ፣ እንገናኛለን ፣ አልበቃኝም ገና እና በሌሎች ተወዳጅ ዘፈኖቹ ይታወቃል፡፡ድምፃዊው ግርማ ነጋሽ በአዲስ አበባ ከተማ ፊት በር አካባቢ በ1936 ዓ.ም የተወለደ ሲሆን በፖሊስ ኦኬስትራ በቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ በአሁኑ ብሔራዊ ቲአትር ለበርካታ አመታት በሙዚቃ ስራው አገልግሏል፡፡በ2011 በአዲስ አበባ ከተማ ከታዋቂው ወገብ-አልባ የጃዝ ባንድ ጋር በመሆን "የኔ ሃሳብ" የተሰኘውን ታሪካዊ ሙዚቃውን በመድረክ ላይ በደመቀ ሁኔታ የተጫወተ አንጋፍ ድምጻዊ ነበር ።ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ የ3 ወንዶችና የ1 ሴት ልጅ አባት የነበረ ሲሆን የቀብር ስነ ስርዓቱም ነገ ከቀኑ በ8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈፀማል ተብሏል፡፡ተመስገን ኡካሬየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 09:49

    የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጁባ ከተማ ገብቷልመስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያን የሚገጥመው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጁባ ከተማ ገብቷል።ብሔራዊ ቡድኑ ረፋድ ላይ በከተማው ሲደርሰም ደቡብ ሱዳናውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።በአሰልጣኝ ክዌሲ አፕያህ የሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ቡድን በሳዑዲ አረቢያ ታይፋ ከተማ ላይ ቆይታ አድርጎ ነው ወደ ጁባ ያመራው።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ምሽት ጨዋታውን የሚያደርግበት ከተማ ጁባ መግባቱ ይታወቃል።ሀብታሙ ምትኩየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 09:31

    የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ባትሪ በሀገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተካሄደ ጥናት አመላከተ።መስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም)የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ጋር በመተባበር ባካሄደው መድረክ ላይ እንደተገለፀው ፣ ጥናቱ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ልማት ጉዞ የሚያግዝና ዘላቂ የትራንስፖርት ሥርዓት ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው እንደሆነ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ ያጋራው መረጃ አመልክቷል።የBKG ተወካይ አቶ እንየው ዋሴ ድርጅታቸው ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠም ባለፈ ወደ ማምረት ደረጃ የመሸጋገር ፍላጎት እንዳለው ገልጸው፣ የዩኒቨርሲቲው ጥናት ለዚህ እቅድ ትልቅ ግብአት በመሆኑ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚደንት ሲሳይ ሙላቴ (ዶ/ር) በበኩላቸው የጥናቱን ውጤት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ወደ ተግባር ለመቀየር እንደሚሰራ አስታውቀዋል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 08:37

    የአራዳ ስፖርታዊ ዜናዎች መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ምየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 07:45

    አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን ይመሠረታልየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ አዲሱ የፌዴራል መንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በመጪው መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታወቁ።አፈ-ጉባኤው ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን ገልጸው፣ በሕገ-መንግሥቱ መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘው አካል ቀጣዩን የ5 ዓመት የሀገር መሪነት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 06:57

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ መቀሌ፣ አክሱም እና ሽሬ ከተሞች የሚያደርጋቸውን የሀገር ውስጥ የበረራ አገልግሎቶች ከዛሬ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው ማቋረጡን ይፍ አድርጓል።አየር መንገዱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ውሳኔው የተወሰደው በክልሉ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ሲሆን፣ ለጊዜው አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ተደርጓል።በበረራዎቹ መቋረጥ ምክንያት በክቡራን ደንበኞች ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መጉላላት አየር መንገዱ ከወዲሁ ይቅርታ የጠየቀ ሲሆን፣ ሁኔታዎች ተስተካክለው በረራዎቹ እንደገና በሚጀመሩበት ወቅት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጿል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    23 сент., 06:24

    በጣሊያን ናፖሊ ቤት ውስጥ 3.2 ሚሊዮን ዩሮ ጥሬ ገንዘብ ተገኘመስከረም 13፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም)በጣሊያን ናፖሊ ከተማ ካይቫኖ በተባለ አካባቢ በተካሄደ የፖሊስ ፍተሻ፣ በቤት ውስጥ በግድግዳ፣ በወለል ንጣፎች እና በቁም ሳጥኖች ውስጥ ተደብቆ የነበረ 3.2 ሚሊዮን ዩሮ ጥሬ ገንዘብ ተገኘ።የገንዘቡ ዋጋ በግምት 3.6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን ፣ የጣሊያን ፖሊስ እንደገለጸው፣ ገንዘቡ በሴሎፌን ተጠቅልሎ በተለያዩ ሚስጥራዊ ቦታዎች ተደብቆ ነበር። ፍተሻው የተካሄደው ለወራት በቆየ ምስጢራዊ ክትትል ተከትሎ ሲሆን፣ በፀረ-ማፊያ አቃቤ ሕግ ኒኮላ ግራቴሪ የሚመራው ምርመራ እንደነበር ተገልጿል።ከጥሬ ገንዘቡ በተጨማሪ፣ 11 የሮሌክስ የእጅ ሰዓቶች፣ መሳሪያዎች እና ከዕፅ ማከፋፈል ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችም ተይዘዋል።በተያያዘው ኦፕሬሽን፣ የወንጀል ድርጅት አባልነት እና የዕፅ ዝውውር የተጠረጠሩ 34 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ተጠርጣሪዎቹ ከ”አንጄሊኖ”ተብሎ ከሚጠራው የማፊያ ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ባለሥልጣናት ገልጸዋል።ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት፣ የተያዘው ገንዘብ በሕጋዊ ሂደት ከተረጋገጠ በኋላ የማፊያ ወንጀል ሰለባዎችን ለመርዳት ወደሚውለው የጣሊያን የፍትህ ፈንድ ገቢ ይደረጋል ተብሏል ።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 17:48

    1.8 ሚሊየን ኪሎ ግራም የሚጠጋ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ቢቻልም የፖሊሲ ክፍተት ዘርፉን እየፈተነው ነውመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) በኢትዮጵያ የክብ ኢኮኖሚ ስራ ፈጣሪዎች የ41 ሚሊየን ብር ገቢ ማስገኘታቸውና ከ1 ሺህ 800 ቶን በላይ ቆሻሻ መልሰው ጥቅም ላይ ማዋላቸውን ሰምተናል።ሆኖም አላስፈላጊ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ እንቅፋቶችን በማስወገድ፣ የክብ ኢኮኖሚ ምርቶችና አገልግሎቶች በቀላሉ ወደ ገበያ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቷል።በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን ከኢኮኖሚ እድገት ጋር የሚያያዙ የክብ ኢኮኖሚ (Circular Economy) ስራዎችን ለማጠናከር ስራ ፈጣሪዎችን፣ የፖሊሲ አውጪዎችንና የፋይናንስ ተቋማትን ያገናኘ ፎረም ተካሂዷል።መድረኩ በሪች ፎር ቼንጅ ኢትዮጵያ (Reach for Change Ethiopia) እና በአፍሪካ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ኔትወርክ (ACEN) አዘጋጅነት ነው የተካሄደው።ኢትዮጵያ ውስጥ ለክብ ኢኮኖሚ መፍትሔ የሚሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ያሉ ቢሆንም ፣ ይህንን አቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ግን ከገበያ፣ ከፋይናንስ፣ ከቴክኖሎጂና ከአሰራር ሥርዓቶች ጋር የተያያዙ ችግሮች ሊቀረፉ እንደሚገባ አፅንኦት ተሰጥቶበታል።እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያምየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 17:44

    ኒያ ፋውንዴሽን/ ጆይ ኦቲዝም ማዕከል የመጀመሪያውን ባለ 6 ወለል ህንጻ ግንባታን ጨርሶ የፊኒሽንግ ሥራ ለማስጀመር የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገለፀመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም)የማዕከሉ ግንባታ ኦቲዝም ላለባቸው ልጆች፣ ወጣቶችና ቤተሰቦቻቸው የሚያስፈልጉ የሕከምና፣ የትምህርት፣ የሙያ ስልጠናና የድጋፍ አገልግሎቶችን በስፋት ለማቅረብ ላቀደው አገልግሎት የሚውል ስለመሆኑ የተናገሩት የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እሌኒ ዳምጠው ናቸውየግንባታ ሂደቱ የሚቀሩት የፊኒሺንግ ሥራዎች ሊፍት እና ሌሎችም በመሆናቸው በቀጣይ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራው ላይ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በ9616 አንድ ብር ከማስገባት ጀምሮ እስከተቻለው በማገዝ ሰብአዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ወ/ሮ እሌኒ አክለው ተናግረዋልጆይ ኦቲዝም ሴንተር በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የኦቲዝም ልህቀት ማዕከል በማቋቋም ከ24 ዓመታት በላይ ልጆችን፣ ወጣቶችንና ቤተሰቦቻቸውን በማህበራዊ፣ በስነ-ልቦናዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ላይ በግልፅ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ የበጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑ ይታወቃልበዛሬው ዕለትም በተሰጠው መግለጫ ዳንኤል እቁባት ከወዳጆቹ በማሰባሰብ የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ የተገለፀ ሲሆን ሌሎችም አካላት በማገዝ ረገድ ከጎን እንዲቆሙ ጥሪ ቀርቧልሰናይት በየነየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 13:26

    የትልቁ አንጀት ካንሰርመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) ብዙዎች ይህ በሽታ 'የእድሜ ባለጸጎች በሽታ ብቻ ነው' ብለው ያስባሉ።ይህ ካንሰር የሚከሰተው በአምስት ጫማ ርዝመት ባለው ትልቁ አንጀታችን የውስጥ ክፍል ላይ ነው።አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምረው 'ፖሊፕ' (Polyp) በሚባሉ ትናንሽ የሴል ስብስቦች ሲሆን፣ እነዚህ ፖሊፖች መጀመሪያ ላይ ካንሰር ባይሆኑም ከጊዜ በኋላ ግን ወደ አደገኛ ካንሰርነት ሊቀየሩ ይችላሉ።በቀስታ የሚያድግ በሽታ በመሆኑ ገና ምልክት ማሳየት ሳይጀምር ቀድሞ መለየትና ፖሊፖቹን ማስወገድ ካንሰሩ እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳል።እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ የትልቁ አንጀት ካንሰር ዓለም ላይ በስርጭቱ ሦስተኛው አደገኛ ካንሰር ነው።ተጨማሪ ለማንበብ https://web.facebook.com/share/p/19cwASZn6i/የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 12:53

    የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ መካሄድ ጀመረመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በኒው ዮርክ መካሄድ ጀምሯል።ወደ 130 የሚጠጉ የአገራት መሪዎች በታደሙበት ጉባኤ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በመክፈቻው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።ለሳምንት በሚቆየው ስብሰባ አሜሪካ እና እስራዔል ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት፣ የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዋነኛ የመወያያ አጀንዳ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላላ ጉባኤው ከሶስት ቀን በፊት ቢጀመርም በጠቅላላ ጉባኤው አዳራሽ የሚካሄደው አጠቃላይ ክርክር ግን በዛሬው እለት ነው የተጀመረው።ይህ ክርክር መሪዎቹ በአዳራሹ ተገናኝተው አንዳቸው የአንዳቸውን ሃሳብ በግልጽ የሚያደምጡበት ሲሆን፥ በፈረንጆቹ መስከረም 28 ቀን በመዝጊያ ንግግር ይቋጫል።በአዳራሹ የምድራችን ሰላም እና የየአገራት የፖሊሲ ጉዳዮች የቀጣይ ቀናት መከራከሪያዎች ናቸው።ጉባኤውን የባንግላዴሹ ፕሬዚዳንት ኸሊሉር ራህማን እንደሚመሩት የሲ ኤን ኤን ዘገባ ያመላክታል።ምናለ ብርሀኑ የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 12:21

    አርቴታ ውላቸውን ሊያራዝሙ ነውመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) ስፔናዊው የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ያላቸውን ኮንትራት ለማራዘም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።አዲሱ ውል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ከአስር ዓመት በላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል ተብሏል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 11:35

    የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን ይከበራልመስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚከበር የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት አስታውቋል።"ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 ቀን በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 10:07

    የድምፃዊት ሙኒት መስፍን "መንገድ" አልበም ሊለቀቅ ነውመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) ድምፃዊት ሙኒት መስፍን "መንገድ" የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበሟን ለአድማጮች ለማድረስ ዝግጅት ማጠናቀቋን በማህበራዊ ገጿ ይፋ አድርጋለች።"መንገድ" የተሰኘው ይህ አዲስ አልበም ሙሉ በሙሉ በራሷ ግጥም እና ዜማ የተቀናጀ ሲሆን፤ የሙዚቃ ማቀናበሩን እንዲሁም ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሥራውን ኬኒ አለን ሠርቶታል።በተጨማሪም በርካታ ባለሙያዎች ተሳታፊ በመሆናቸው ለአድማጭ ለየት ያለ ቅኝት ያለው የሙዚቃ ጣዕም ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል ተብሎለታል።ድምፃዊት ሙኒት መስፍን ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሙዚቃ ሥራዎቿ፤ በተለይም በ"ኖሮ ኖሮ"፣ "ዓባይ"፣ "አድዋ" እና "ሰላም ሀገሬ" በሚሉ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችን ለአድማጭ አድርሳለች።ተመስገን ኡካሬየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 08:59

    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 08:58

    6ኛው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳልመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) 6ኛው የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት መርሃ ግብር ከመስከረም 19 እስከ 21 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሃድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታወቀ።በመርሃ ግብሩ ከ20 በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ በቱሪዝም ዘርፍ ውስጥ ያሉ አካላት እንዲሁም ከ100 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት አውደርዕይ አቅራቢዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።በመድረኩ የቱሪዝም ኤክስፖ፣ የንግድ ልውውጥ፣ ቱሪዝም ላይ ትኩረት ያደረጉ የፓናል ውይይቶች፣ የባህል ትውውቅ፣ የሚስ ኦሮሚያ 2019 ውድድር እና ሌሎችም ዝግጅቶች ይቀርባሉ ተብሏል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 08:44

    የአዲስ ባንክ የምንዛሪ ተመንየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 08:41

    የአራዳ የደቂቃ ስብስብ የሀገር ውስጥ ዜና መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ምየአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm@Arada_Fm
  • Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል

    22 сент., 08:38

    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ናይጄሪያዋ ፖርት ሀርኮርት በረራ ሊጀምር ነውመስከረም 12፣ 2019 (አራዳ ኤፍ ኤም) የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኅዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ናይጄሪያዋ የወደብና የነዳጅ ማዕከል ፖርት ሀርኮርት (ከተማ ቀጥታ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን ሰምተናል።አየር መንገዱ በሳምንት ለአራት ቀናት በሚያደርገው በዚህ አዲስ በረራ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።በተጨማሪም ወደ ናይጄሪያ ለሚጓዙ ነጋዴዎችና ተጓዦች ምቹና ፈጣን አማራጭ የሚፈጥር ሲሆን፥ ደንበኞች ከወዲሁ የጉዞ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ አየር መንገዱ ጥሪ አቅርቧል።የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑYoutube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1officalTelegram:-https://t.me/Arada_FmTelegram:-https://t.me/aradaFmdigitalFacebook:-https://web.facebook.com/aradafm
    Иллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታልИллюстрация к посту канала Arada FM 95.1 Digital-አራዳ ኤፍኤም ዲጂታል