Последние посты

ATC NEWS
26 сент., 16:54изменён
የፈተና ክፍያ ተመን ጭማሪ ተደረገየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመራበት ደንብ ቁጥር 260/2004 መሠረት የሚሰጣቸውን የፈተና አገልግሎቶች በመንግሥት በጸደቀ ተመን መሠረት ያስተዳድራል።በአዲሱ የመንግሥት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም መሠረት የተሻሻለው ክፍያ ተመን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 593/2016 መሠረት ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተገቢ ሆኗል።በመሆኑም በተሻሻለው ተመን መሠረት በእያንዳንዱ ተፈታኝ ላይ ለምዝገባና ለፈተና አሰጣጥ:-👉 ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና 2,000 ብር👉 ለድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና 3,500 ብር👉 ለሙያ ብቃት ፈተና ምዘና 3,500 ብር እና👉 ለሊቃውንት ማረጋገጫ ፕሮግራም ፈተና 950 ብር በምዝገባ ሲስተሙ ላይ በተቀመጠው የክፍያ ሥርዓት የሚፈጸም ይሆናል።እንዲሁም የተሻሻለው ተመን ከመውጣቱ በፊት ለተከፈሉ ፈተናዎች የሚከፈል ቀሪ ክፍያዎች 750 ብር በእያንዳንዱ ተፈታኝ ተሰልፎ እንዲፈጸም፤ ያልተከፈሉ ክፍያዎችም የተሻሻለው ተመን በሲስተሙ ላይ ከመጫኑ በፊት በመክፈል ተገቢውን አገልግሎት እንድታገኙ እናሳስባለን።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
3,960Открыть в Telegram
ATC NEWS
26 сент., 14:11
የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የስልጠና ዘርፎችን በማካተት ለ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።ኢንስቲትዩት የሚሰጣቸውን የስልጠና መስኮች የሚያስተዋውቅበት የመረጃ ሳምንት ከመስከረም 14/2019 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ሆኗል።ተቋሙ የሚሰጣቸው የስልጠና መስኮች፦ ➻ በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች ➻ በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች ➻ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) (ደረጃ 8) በሁለት ፕሮግራሞችበኢንስቲትዩቱ የሚሰጠው ስልጠና 50 በመቶ የንድፈ-ሃሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ እንደሆነ ተገልጿል።ተቋሙ በ16 የሳተላይት ካምፓሶች እና በሁለት ማዕከላት አማካኝነት ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
5,490Открыть в Telegram
ATC NEWS
25 сент., 12:29
ምደባ ይፋ ሆነ።በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ። 👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placementቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placementእንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news

11,600Открыть в Telegram
ATC NEWS
24 сент., 13:24
#ጥቆማየኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታቸውን አጠናቀው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም (Extension) መመዝገብ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
12,700Открыть в Telegram
ATC NEWS
24 сент., 12:16
ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ ገቢ ተማሪዎች!!በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና በመውሰድ ያለፋችሁ በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል በየትምህርት ቤቶቹ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ የመግቢያ ቀን መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤቶቹ ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው፤1. ለ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፤ ለምሳሌ፡- ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ ወዘተ፣2. ለመኝታ አገልግሎት የሚያስፈልጉ አንሶላና ብርድ ልብስ፣3. እስካሁን ሲማሩበት ከነበረው ትምህርት ቤት የተሰጣቸውን መሸኛና የትምህርት ውጤታቸውን የሚገልጽ ትራንስክሪፕት ይዘው መገኘት ይጠበቅባቸዋል፤4. ተማሪዎች ወደ ተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች ከደረሱ በኋላ የሚያስፈልጋቸውን ዩኒፎርም በራሳቸው ወጪ የሚያስዘጋጁ በመሆኑ፣ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
12,000Открыть в Telegram
ATC NEWS
24 сент., 12:14изменён
ለወሊሶ ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ፦በወሊሶ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስትማሩ ለነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እንዲሁም በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት የምትገቡበትን የመግቢያ ቀን በቀጣይ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን እስኪገለጽ ድረስ በትዕግሥት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።ማሳሰቢያ፦ በሌሎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተገኝታችሁ ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ወደ ትምህርት ቤቶቹ በምትገቡበት ጊዜ መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እየደወላችሁ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑ እንገልጻለን፣ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
8,920Открыть в Telegram
ATC NEWS
24 сент., 11:36
#WolaitaSodoUniversityከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተመርቃችሁ ዋናውን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ ምሩቃን፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ከማተሚያ ቤቱ በቀጥታ ታትሞ የሚመጠ በመሆኑ ዋናውን ዲግሪ ያልወሰዳችሁና እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ አማካኝነት ምዝገባ እነድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScdSQ0xfAxNe-o-Smi82foG6X9u72V2-cC2_PuWzdgh5wGmGw/viewformበወጪ መጋራት (Cost Sharing) የተማራችሁ አመልካቾች ኦሪጅናል ሰርተፊኬታችሁን ለመውሰድ የክፍያ ግዴታችሁን መፈፀማችሁን ወይም በአገልግሎት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
8,710Открыть в Telegram
ATC NEWS
24 сент., 11:08
የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሸን ሊቀ መንበር የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጠየቁ‼️የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሕሙድ አሊ ዩሱፍ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ውጥረት እና ወታደራዊ መካረር "እጅግ እንዳሳሰባቸው" ገለጹ። ግጭቱ "በአፋጣኝ እንዲቆምም" አሳስበዋል።ዛሬ ረቡዕ መስከረም 13/2019 ዓ. ም. ማምሻውን ባወጡት መግለጫ፤ የመቀለ፣ የአክሱም እና ሽረ አውሮፕላን ማረፊያዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው፣ ህወሓት የፌደራል መንግሥት ሠራተኞችን መያዙ እና የሕዝብ አገልግሎት መስጫዎች መቋረጣቸው እንዳሰጋቸው አስታውቀዋል።ረቡዕ ማለዳ ላይ የትግራይ ኃይሎች መቀለ የሚገኘውን አውሮፕላን ማረፊያ መቆጣጠራቸው ከተገለጸ በኋላ ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ጋር ጦርነት መቀስቀሱ ተሰምቷል።የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ እና የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባጋሩት ጽሑፍ የህወሓት ኃይሎች "ጦርነት መክፈታቸውን" ገልጸዋል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
10,000Открыть в Telegram
ATC NEWS
22 сент., 17:07
ዲላ ዩኒቨርሲቲ በፖስት ቤዚክ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ፕሮግራሞች በመጀመሪያ ዲግሪ በመደበኛ ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።የትምህርት ፕሮግራሞች፦ ➻ ሜዲካል ላቦራቶሪ ➻ ሚድዋይፈሪ ➻ ነርሲንግ ➻ ፋርማሲየማመልከቻ ጊዜ 👇 እስከ መስከረም 21/2019 ዓ.ምየማመልከቻ ቦታ፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳያኣ ግቢ፣ ሕንፃ ቁ. 609፣ ቢሮ ቁ.04በአካል ማመልከት የማትችሉ አመልካቾች በ http://portal.du.edu.et/Web/Announcement አማካኝነት መመዝገብ ትችላላችሁ።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
4,019Открыть в Telegram
ATC NEWS
22 сент., 17:06
🌟 የልጅዎ ትምህርት የወደፊት ስኬቱ መሠረት ነው! 🌟📚 ለ2019 ዓ.ም. አዲሱን የትምህርት ዘመን በተሻለ ዝግጅት ይጀምሩ!🏠 Home-to-Home የግል ትምህርት 💻 Online Tutoring 👨🏫 ብቁና ሙያዊ አስተማሪዎች 🎯 ለልጅዎ የተለየ ትኩረትና የግል የትምህርት ድጋፍ 📝 የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት 📖 ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች✨ ለልጅዎ ተስማሚውን አስተማሪ ያግኙ — እውቀት፣ ብቃት እና ስኬት ከእኛ ጋር!📞 ለመመዝገብ ዛሬ በ 0900537696 ይደውሉ!📍 በመላው አዲስ አበባ Home-to-Home አገልግሎት🔥 የልጅዎን ስኬት ለነገ አትተዉት — ዛሬውኑ ይመዝግቡ! 🔥#EthioturkishTutoringAgency #HomeToHomeTutoring #Tutoring #AddisAbaba #2019ዓም #ExamPreparation #Education #የግልትምህርት #ትምህርት #አዲስአበባ
3,610Открыть в Telegram
ATC NEWS
22 сент., 13:27
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴርትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት

6,750Открыть в Telegram
ATC NEWS
22 сент., 05:02
በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚገኙ የጫት እና ቁማር ቤቶችን ለመቆጣጠር ልዩ ዳይሬክቶሬት ተቋቋመበአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚደረጉ አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል እስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን የከተማዋ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገልጿል።የባለስልጣኑ የደንብ መተላለፍ ክትትል፣ ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደመስቀል ለአሐዱ ራድዮ እንደገለጹት፤ ትምህርትን ሊያስተጉሉ የሚችሉ ድርጊቶችን ለመከላከል ሲባል ብቻ ተለይቶ የተዋቀረ ዳይሬክቶሬት ወደ ስራ ገብቷል።ከእነዚህ አዋኪ ድርጊቶች መካከል በትምህርት ቤቶች አቅራቢያ የሚገኙ የጫት ማስቃሚያዎች እና የቁማር ቤቶች የሚጠቀሱ ሲሆን፤ ችግሩን በዘላቂነት ለመቆጣጠር በእቅድ እየተሰራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች በሚገኙ ክበባት አማካኝነት ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።ባለስልጣኑ አሁን ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ከወላጆች ጀምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የክትትልና ቁጥጥር ስራዎችን ያከናውናል።በአሁኑ ወቅት የመዲናዋ ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸውን የጀመሩ ሲሆን፤ በዙሪያቸው የሚደረጉ ሕገ-ወጥና አዋኪ ድርጊቶችን ሕብረተሰቡ በጋራ ሊከላከል እንደሚገባ ተመላክቷል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
9,230Открыть в Telegram
ATC NEWS
21 сент., 10:21изменён
ጣሊያን በትምህርት ቤቶች ቡርቃ እና ኒቃብ ልብስን ልታግድ ነውየጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የቡርቃ እና የኒቃብ አለባበስን የማገድ ዕቅድ እንዳላቸው አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሯ ይህንን የገለጹት በሮም በተካሄደ የፓርቲያቸው የወጣቶች ክንፍ ስብሰባ ላይ ሲሆን፥ እርምጃው ስደተኞች ከሀገሪቱ ባህል እና ሕግ ጋር እንዲላመዱ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።ከዚህ በተጨማሪም መንግሥታቸው በአንድ ክፍል ውስጥ የሚማሩ የውጭ ሀገር ተማሪዎችን ቁጥር ለመገደብ አነስተኛ የሆኑ የውጭ ሀገር ወላጆች የጣሊያንኛ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያስገድድ ሕግ ለማውጣት ማቀዱን ገልጸዋል።ይህ የሕግ ረቂቅ ለአፈጻጸም ከመብቃቱ በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና በፓርላማ መጽደቅ ይኖርበታል።በአሁኑ ወቅት በጣሊያን የፊት መሸፈኛ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ባይሆንም፥ ከ1975 ጀምሮ የወጡ ሕጎች ለማንነት ፍተሻ ሲባል ፊትን መሸፈንን በከፊል ይገድባሉ።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
11,400Открыть в Telegram
ATC NEWS
21 сент., 09:01
በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤በ2019 ዓ.ም በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተመዝግባችሁ የመግቢያ ፈተና ወስዳችሁ ተጠባባቂ ለሆናችሁ ተማሪዎች፣ በተመዘገባችሁበት ሊንክ በመግባት ስማችሁንና ሪፈረንስ ቁጥራችሁን በማስገባት እስከ መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ እንደምትችሉ እንገልጻለን።ማሳሰቢያ ፦ ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆናቸው በተጠባባቂነት ከተያዙ መካከል የተሻለ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑን እየገለጽን ምደባ የሚካሄደው ክፍት ቦታዎች ባሏቸው ት/ቤቶች እንደሚሆን እናሳውቃለን።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
10,600Открыть в Telegram
ATC NEWS
21 сент., 09:01
🌟 የልጅዎ ትምህርት የወደፊት ስኬቱ መሠረት ነው! 🌟📚 ለ2019 ዓ.ም. አዲሱን የትምህርት ዘመን በተሻለ ዝግጅት ይጀምሩ!🏠 Home-to-Home የግል ትምህርት 💻 Online Tutoring 👨🏫 ብቁና ሙያዊ አስተማሪዎች 🎯 ለልጅዎ የተለየ ትኩረትና የግል የትምህርት ድጋፍ 📝 የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት 📖 ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች✨ ለልጅዎ ተስማሚውን አስተማሪ ያግኙ — እውቀት፣ ብቃት እና ስኬት ከእኛ ጋር!📞 ለመመዝገብ ዛሬ በ 0900537696 ይደውሉ!📍 በመላው አዲስ አበባ Home-to-Home አገልግሎት🔥 የልጅዎን ስኬት ለነገ አትተዉት — ዛሬውኑ ይመዝግቡ! 🔥#EthioturkishTutoringAgency #HomeToHomeTutoring #Tutoring #AddisAbaba #2019ዓም #ExamPreparation #Education #የግልትምህርት #ትምህርት #አዲስአበባ
9,990Открыть в Telegram
ATC NEWS
20 сент., 10:12
የጉግል ምርት የሆነው «ጀሚኒ» ኤአይ የሦስት ኩባንያዎችን የሳይበር ደህንነት መጣሱ ተገለጸ።የጉግል የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴል የሆነው "ጀሚኒ" የሳይበር ደህንነት ብቃቱ በሚፈተሽበት ወቅት ያለምንም የሰው ልጅ ትዕዛዝ በራሱ ተነሳሽነት የሦስት ኩባንያዎችን የደህንነት ከለላ ሰብሮ መግባቱን ዎልስትሪት ጆርናል መዘገቡን ተከትሎ የዕለቱ መነጋገሪያ ዜና ሆኗል።በግንቦት ወር በተካሄደው በዚህ ሙከራ ጀሚኒ ለሕዝብ ይፋ የሆኑ መረጃዎችን እና የይለፍ ቃላትን በመገመት ወደ ድረ-ገጾቹ የገባ ሲሆን፣ ድርጊቱን የፈጸመው ድረ-ገጾቹ የሙከራው አካል እንደሆኑ በማሰብ መሆኑን የጉግል የደኅንነት ክፍል ምክትል ፕሬዝዳንት ሄዘር አድኪንስ ገልጸዋል።የኤአይ ሞዴሉ ወደ ኩባንያዎቹ የመረጃ ሥርዓት ከገባ በኋላ በራሱ ውሳኔ እንቅስቃሴውን ማቆሙና ጉግል ጥቃቱ ለደረሰባቸው ተቋማት መረጃ መስጠቱንና ክስተቱም በኤአይ ሥልጠና ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ ማሳየቱን አስረድቷል ተብሏል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
12,400Открыть в Telegram
ATC NEWS
20 сент., 10:11
ጎጆ Shine የጽዳት አገልግሎት - የንፅህና አጋርዎ! / Your trusted cleaning partner./ለ መኖሪያ ቤቶች ለ ሆቴሎች ለ ሬስቶራንቶች ለ ካፌዎች ለ Guest house ለ ትምህርት ቤቶች ለ ሆስፒታሎች ለ ኮንስትራክሽን ሳይቶች ለ ሱፐር ማርኬቶች ለ ቢሮዎች ለ GYM ቤቶች ለ event አዳራሾች ሙሉ የ ቤት ጽዳት አገልግሎት እንሰጣለን።ቤትዎ ወይም የመስሪያ ቦታዎ ንጹህ፣ ማራኪ እና ምቹ እንዲሆን ይፈልጋሉ? ጎጆ Shine ዘመናዊ በሆኑ ማሽኖች እና በሰለጠኑ ባለሙያዎች ጥራት ያለው የጽዳት አገልግሎት ይሰጥዎታል።□ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦ 🛋️ የሶፋ እና የ ፍራሽ እጥበት
10,800Открыть в Telegram
ATC NEWS
20 сент., 10:11
🌟 የልጅዎ ትምህርት የወደፊት ስኬቱ መሠረት ነው! 🌟📚 ለ2019 ዓ.ም. አዲሱን የትምህርት ዘመን በተሻለ ዝግጅት ይጀምሩ!🏠 Home-to-Home የግል ትምህርት 💻 Online Tutoring 👨🏫 ብቁና ሙያዊ አስተማሪዎች 🎯 ለልጅዎ የተለየ ትኩረትና የግል የትምህርት ድጋፍ 📝 የ6ኛ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት 📖 ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች✨ ለልጅዎ ተስማሚውን አስተማሪ ያግኙ — እውቀት፣ ብቃት እና ስኬት ከእኛ ጋር!📞 ለመመዝገብ ዛሬ በ 0900537696 ይደውሉ!📍 በመላው አዲስ አበባ Home-to-Home አገልግሎት🔥 የልጅዎን ስኬት ለነገ አትተዉት — ዛሬውኑ ይመዝግቡ! 🔥#EthioturkishTutoringAgency #HomeToHomeTutoring #Tutoring #AddisAbaba #2019ዓም #ExamPreparation #Education #የግልትምህርት #ትምህርት #አዲስአበባ
10,300Открыть в Telegram
ATC NEWS
19 сент., 10:12изменён
በአማራ ክልል ለ2019 የትምህርት ዘመን ከ4.7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል። - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮበክልሉ በ2019 የትምህርት ዘመን 7.6 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደ ምዝገባ ከ4.7 ሚሊዮን በላይ (62 በመቶ) ተማሪዎች መመዝገባቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡የትምህርት ቀናት እንዳይባክኑ ምዝገባን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሲሠራ መቆየቱን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ለሪፖርተር ተናግረዋል።ምዝገባ ያላደረጉ 38 በመቶ ቀሪ ተማሪዎችን ምዝገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።የተመዘገበው አፈጻጸም ከዚህ ቀደም እስከ ጥቅምት፣ ኅዳር እና ታኅሳስ ወራት ድረስ ይቀጥል የነበረው የምዝገባ ሥራ በዚህ ዓመት እንደማይኖር አመላካች ነው ብለዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከማኅበረሰቡና ከተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ውይይት በማድረግ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot ➡️ https://t.me/atc_news
12,400Открыть в Telegram
ATC NEWS
19 сент., 10:12
በአማራ ክልል ለ2019 የትምህርት ዘመን ከ4.7 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ተመዝግበዋል። - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮበክልሉ በ2019 የትምህርት ዘመን 7.6 ሚሊዮን ተማሪዎች ለመመዝገብ ታቅዶ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደ ምዝገባ ከ4.7 ሚሊዮን በላይ (62 በመቶ) ተማሪዎች መመዝገባቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡የትምህርት ቀናት እንዳይባክኑ ምዝገባን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ሲሠራ መቆየቱን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ለሪፖርተር ተናግረዋል።ምዝገባ ያላደረጉ 38 በመቶ ቀሪ ተማሪዎችን ምዝገባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።የተመዘገበው አፈጻጸም ከዚህ ቀደም እስከ ጥቅምት፣ ኅዳር እና ታኅሳስ ወራት ድረስ ይቀጥል የነበረው የምዝገባ ሥራ በዚህ ዓመት እንደማይኖር አመላካች ነው ብለዋል።ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከማኅበረሰቡና ከተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር ውይይት በማድረግ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል።
9,710Открыть в Telegram
