Последние посты

Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
24 сент., 04:06
ሁለት መረጃዎች‼️ 📌ህወሓት በትግራይ ክልል የቴሌኮም እና የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ ማዘዙ ተሰምቷል። የሰሜኑ ጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ህወሓት የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሰራተኞች እነዚህን ወሳኝ መሰረታዊ አገልግሎቶች በአስቸኳይ እንዲዘጉ እና እንዲያቋርጡ አዟል።📌የህወሓት ሃይል ዛሬ መስከረም 14/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 11፡30 ጀምሮ አዲስ የውጊያ ግንባር ከፍቷል። አዲሱ ውጊያ የተጀመረው በራያ ጨርጨር፣ቢሶበር እና ያሎ (አፋር) አካባቢዎች አቅጣጫ ነው። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
24 сент., 04:05
ለንግድዎ የሚገባው ቦታ ይህ ነው!አሚባራ ላይ ንግድዎን ያስቀምጡ -ሰዎች በሚኖሩበት ፤ በሚዝናኑበት እና በሚሰሩበት ቦታ ላይ የገበያ እድሉን ይጠቀሙ!ዛሬውኑ ያግኙን!+251901616161 +251969363636Amibara Properties Built Different.


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 19:42
የህወሓት ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አማኑኤል አሰፋ የአሜሪካ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባወጡት መግለጫ ማዘናቸውን የገለፁ ሲሆን የሚፈፀመውን የአየር ጥቃት ማውገዝ ነበረባቸው ብለዋል። ህወሃት የመቀሌ፣ የአክሱም እንዲሁም የሽሬ ኤርፖርት ጠባቂዎችን አፍኖ በመውሰድ በራሱ ታጣቂዎች መተካቱና የሰዎችን እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ተገቢ አለመሆኑን የአፍሪካ ኅብረት ባወጣው መግለጫ ህወሓትን ወቅሷል። አሜሪካ እና የአፍሪካ ህብረት በህወሓት ላይ ያቀረቡት ጠንከር ያለ ክስ ህወሓት ተቀባይነት እያጣ መሆኑን አመላካች መሆኑን ተንታኞች እየገለፁ ይገኛሉ። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s



Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 16:48
የድሮን ጥቃት‼️ ዛሬ በረያ ኮረም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የከባድ መሳሪያ ማዕከል ላይ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ። አንድ ቢኤም እና ተኮሾቹ ጉዳት አስተናግደዋል። ዛሬ በዛታ ግንባር፣ በአብአላ እና ጀመዶ መስመር ከባድ ሰብዓዊ ጉዳት ያደረሰ ውጊያ ሲደረግ ውሏል። [አዩዘሀበሻ] ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 16:37изменён
አሜሪካ በህወሓት ላይ ከፍተኛ ቁጣዋን ገለጸች‼️ ተጨማሪ ኃይለኛ ማዕቀቦችን እንደምትጥልም ዝታለች!በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ጄ. ማሲንጋ ዛሬ ባወጡት እጅግ ጠንካራ መግለጫ የህወሓት አመራሮች የጀመሩትን አዲስ እና መጠነ ሰፊ ጥቃት አጥብቀው ኮንነዋል። አምባሳደሩ የቡድኑን እርምጃ "ማሸነፍ የማይቻልበት እና ለህዝብ ምንም የማይፈይድ አደገኛ ውሳኔ" ሲሉ አጣጥለውታል።በቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አደራዳሪነት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የተጀመረውን የሰላም ውይይት ወደ ጎን በመተው ህወሓት ዳግም ወደ ጦርነት ማምራቱ አሜሪካን ክፉኛ አሳዝኗል። ይህንኑ ተከትሎም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ከዚህ እብደት እና የጥፋት ጦርነት እራሳቸውን እንዲያርቁ እና ከስህተቱ እንዲማሩ አምባሳደሩ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል።በ2026 ዓመት መጀመሪያ ላይ በህወሓት አመራሮች ላይ ማዕቀብ መጣሏን ያስታወሰችው አሜሪካ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሳሳተ አዘቅት በሚገፉ ተጨማሪ አመራሮች ላይም ኃይለኛ ማዕቀብ ለመጣል የሚያስችል ሙሉ አቅምና መሳሪያ እንዳላት አስጠንቅቃለች። ምንም እንኳን አሜሪካ ይህን የቅጣት በትር ለማሳረፍ ዝግጁ መሆኗን ብታሳውቅም፣ አሁንም ቢሆን ከጥፋቱ ለመመለስ ትክክለኛው መንገድ ምክንያታዊ የሆነ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ ብቻ መሆኑን አምባሳደር ማሲንጋ በአፅንዖት አሳስበዋል። (አዩዘሀበሻ) ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 12:21изменён
የአፋር ክልል መግለጫ አውጥቷል‼️ ህወሃት ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በአፋር ህዝብ ላይ መጠነ-ሰፊ ጦርነት ከፍተው ማደራቸውን የአፋር ክልል መንግሥት አስታወቀ። ከትናንት ጥፋቱ የማይማር ለጥፋትና ለእልቂት የተደራጀው የህወሓት ተላላኪ ቡድን ለፈጸመው ወረራ መራር ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል ብሏል። ከአሁኑ ሰአት ጀምሮ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋነኛ ተግባሩ የህዝቦቹን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ ስለሆነ፣ ከሌሎች ወዳጅ ሀይሎች ጋር በመሆን አጸፋዊው ራስን የመከላከል እርምጃ የሚወስድ ይሆናል ሲል በመግለጫው ላይ አስፍሯል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 11:31изменён
“ጦርነቱን ማስቀረት አልተቻለም” ጌታቸው ረዳ‼️የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ጌታቸው ረዳ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ የተደረው ጥረት አለመሳካቱን አስታውቀዋል፡፡ ጌታቸው በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባሰራጩት መልዕክት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብን ጨምሮ ብዙዎች በትግራይ ሌላ ጦርነት እንዳይከሰት ጥረት ቢያደርጉም፣ የሕወሓት መሪዎች ዛሬ ማለዳ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በሚገኙ የመንግሥት ኃይሎች ላይ ሁለንተናዊ ጥቃት መክፈታቸውን አስታውቀዋል፡፡ጌታቸው “እጅጉ ልብ የሚሰብር ነው” ያሉትን ጦርነት ዳግም መቀስቀስ ያረጋገጡት፣ ህወሓት “መከላከል” ያለውን ጦርነት በይፋ መጀመሩን በገለጸበት አጋጣሚ ነው። ሕወሓትበትግራይ ክልል የሚገኙና በፌዴራል ቁጥጥር ሥር ያሉ አየር ማረፊያዎችን በመቆጣሩ፣ ወደ ክልሉ የሚደረጉ በረራዎች እንዲቋረጡ መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡ አዩዘሀበሻ 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
23 сент., 11:11изменён
#የትግራይ ባለሥልጣናት የክልሉ ታጣቂ ኃይሎች «የመከላከል ውጊያ» እንዲያደርጉ መታዘዛቸውን ገለጹ‼️በትግራይ እና #በአፋር ክልል ወሰን አቅራቢያ በትግራይ እና በፌደራል ኃይሎች መካከል ውጊያ መጀመሩን የሚጠቁሙ ዘገባዎች እየወጡ ባለበት በዚህ ሰአት፣ የትግራይ ክልል ባለሥልጣናት የታጠቁ ኃይሎቻቸው ወደ «የመከላከል ውጊያ» እንዲገቡ መታዘዛቸውን ዛሬ መስከረም 13/2019 ዓ.ም አስታውቀዋል። አዩዘሀበሻ 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 18:48
ጌታቸው ረዳ እና ዶክተር ቴዎድሮስ‼️ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም እና አቶ ጌታቸው ረዳ ከ10 ዓመታት በኋላ በአሜሪካ ተገናኙ።የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም እና የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከ10 ዓመታት ገደማ በኋላ በኒውዮርክ ከተማ ተገናኙ።አቶ ጌታቸው ረዳ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባሰራጩት መረጃ፣ ከዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ከረጅም ዓመታት በኋላ በመገናኘታቸው የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።ይህ ያልተጠበቀ እግጣሚ የተከሰተው ሁለቱ አመራሮች በተለያዩ አህጉራዊ እና ቀጣናዊ ጉባኤዎች ላይ ለመካፈል በኒው ዮርክ በሚገኙበት ወቅት እንደሆነ ታውቋል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 17:31изменён
በቻይና ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስወገድ እንዲቧጨሩ የሚያደርግ ልዩ የቧጨራ ሳሎን ተከፈተ‼️በቻይና የ32 ዓመቱ ዣንግ ሺያኦቻኦ ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስታገስ በሰራተኞች በቀስታ የሚቧጨሩበትን ልዩ የአገልግሎት ሳሎን ከፍቶ በወር ወደ 100,000 ዩዋን ያህል ገቢ እያገኘ መሆኑ ተዘግቧል።ዣንግ ይህን ያልተለመደ የንግድ ሀሳብ ያገኘው በኢንተርኔት ላይ ባየው አጭር ቪዲዮ መሆኑን ገልጿል። በቪዲዮው ላይ አንዲት ሚስት የባለቤቷን ጀርባ በቀስታ ስትቧጭ ተመልክቶ አስተየየት ሰጪ የነበሩ ሰዎችም “እንዲህ ያለ አገልግሎት ቢኖር ገንዘብ እንከፍላለን” የሚሉ መልዕክቶቹን በመመልከቱ ወደዚህ ስራ መግባቱ ተናግሯል።የመጀመሪያው የቧጨራ ሳሎን ከተከፈተ ብዙም ሳይቆይ ሁለተኛ ሳሎን መክፈት ችሏል ሁለቱም ሳሎኖች በአጠቃላይ በወር ወደ 100,000 ዩዋን የሚጠጋ ገቢ እንደሚያገኝ ተነግሯል።ደንበኞች በጀርባቸው ተኝተው ሰራተኞች በልዩ የፕላስቲክ ጥፍሮች በመጠቀም ሰውነታቸውን በቀስታ ይቧጫሉ። ዣንግ ይህን ሥራ ለመጀመር ልዩ የቧጨራ ቴክኒኮችን ራሱ መመርመርና መፍጠር እንደነበረበት ገልጿል።አንድ ሰዓት የቧጨራ አገልግሎት 300 ዩዋን ያስከፍላል።የንግዱ ዋና ዓላማም ሰዎች የከተማ ሕይወት የሚያመጣውን ጭንቀት እንዲያስታግሱና የእንቅልፍ ጥራታቸውን ለማሻሻል ዘና የሚያደርግ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።ዣንግ የከተማ ነዋሪዎች የጭንቀት ደረጃ ከፍ ያለ በመሆኑ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ፍላጎት እንዳለ በመግለጽ አንዳንድ ደንበኞችም አገልግሎቱ ከማሳጅ ይልቅ የበለጠ ዘና እንደሚያደርጋቸው እንደነገሩት


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 17:17изменён
መረጃ‼️ "የብርሃኑ ጁላን የጀግንነት ጉዞ የሚተርክ 'ድል ቁርሱ' የተሰኘ መጽሐፍ ተመረቀ"መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወት፣ የአመራር እና የጀግንነት ጉዞ የሚተርከው “ድል ቁርሱ” የተሰኘ መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመርቋል።መጽሐፉ ከገጠር ተነስቶ እስከ ጦር ሜዳ ውጣ ውረድ የደረሰን ግለሰባዊ ታሪክ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገር በፈተና ውስጥ በነበረችበት ወቅት የነበረውን የፅናት መንፈስ የሚያሳይ ተደርጎ ተስሏል ተብሏል። ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 16:58изменён
ተመድ በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የጸጥታ ስጋት ላይ ያለውን ከፍተኛ ስጋት ገለጸ‼️የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የጸጥታ ስጋት፣ አዲስ የታጠቁ ቡድኖች ጥምረት መመሥረትን እና አሁንም በቀጠሉት የድሮን ጥቃቶችና አለመረጋጋቶች ዙሪያ የሚወጡ ዘገባዎችን በተመለከተ ያለውን ጥልቅ ስጋት ሰኞ ዕለት ገልጿል።የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ዋና ቃል አቀባይ እስቴፋን ዱጃሪክ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ "ውጥረት በነገሰበት በዚህ ወቅት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁኔታውን የበለጠ ሊያባብሱ የሚችሉ ድርጊቶችን ወይም ንግግሮችን ከማድረግ እንዲቆጠቡ እንጠይቃለን።በተጨማሪም ለውይይት አዲስ ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ እናስሰብባለን፤ ምክንያቱም ወታደራዊ እርምጃ የፖለቲካ ልዩነቶችን አይፈታም ወይም ሥር የሰደዱ አቤቱታዎችን ምላሽ አይሰጥም" ብለዋል።ዱጃሪክ አክለውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውጥረቶችን ለመቀነስ እና የፕሬቶሪያውን ስምምነት ትግበራ ለማስቀጠል የአፍሪካ ህብረት የሚያደርገውን ጥረት መደገፉን እንደሚቀጥል ከ ጅንዋ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 15:40
በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት(confirmed)‼️ ዛሬ መስከረም 12/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 ጀምሮ በአላማጣ ከተማ እና አካባቢው በህወሓት ወታደራዊ ማዕከላት ላይ በርካታ ቦታዎች ላይ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን መዘገባችን ይታወሳል። ጥቃቱ የተፈፀመው 17 ጊዜ ነው ስለደረሰው ጉዳት የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀበሻ እንደሚከተለው ገልፀዋል። 📌በእያሱ በርሄ ትምህርት ቤት ላይ በተፈፀመው የድሮን ጥቃት እሳቱ አሁንም እየተቀጣጠለ ነው (አልጠፋም)፣በትምህርት ቤቱ ውስጥ የነበረ የመሳሪያ እና ጥይት ክምችት እየፈነዳ ነው።🔴በመለስ መታሰቢያ ትምህርት ቤት፡ በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ በተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። መድፎች ወድመዋል።🔴በንስር ጣቢያ፡ የጦር ሰራዊቱን አባላት በጫነ ተሽከርካሪ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።🏥 የታጣቂዎች ጉዳት እና የሆስፒታል ሁኔታ፡🔴ከ200 በላይ የቆሰሉ ወታደሮች በአላማጣ ሆስፒታል በረንዳ ላይ ጭምር እየተታከሙ ይገኛሉ።🔴በመታከሚያ ቦታ እጥረት ምክንያት በ1 አውቶቡስ እና በ 2 አምቡላንስ ወደ ሞኮኒ ተልከዋል።🔴 55 ህይወታቸው ያለፈ ታጣቂዎች በአላማጣ ከተማ ተቀብረዋል። 🔴የመረዋ ጤና ጣቢያ በቆሰሉ ሰዎች ሞልቷል፣መደበኛ የጤና ባለሙያዎቹ ተባረዋል። 🔍 የአካባቢው ህዝብ ማረጋገጫ እና የውስጥ መረጃ👉ጥቃቱ ሙሉ በሙሉ ኢላማውን የጠበቀ እና የተጠና ነበር። ምንም የሲቪል ሰዎች ጉዳት አልደረሰም፣ ነገር ግን በጥቃቱ የፈነዳ መሳሪያ አንድ ሰው ላይ ጉዳት እንደደረሰ የአካባቢው ምንጮች ለአዩዘሀሻ ገልፀዋል። አዩዘሀበሻ



Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 09:40изменён
ቪዲዮ‼️ ዛሬ መስከረም 12/2019 ዓ.ም በራያ አላማጣ ከጠዋቱ 3:15 ጀምሮ እስከ 4:30 አካባቢ በርካታ የድሮን ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ወደ አላማጣ ሆስፒታል ማንም እንዳይገባ ተከልክሏል። በካርታ የህወሓት ታጣቂዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጥቃቱ ሲፈፀም የሚያሳዩ ምስሎችን ነዋሪዎች አጋርተውናል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 09:36
እንኳን አደረሳችሁ ጊፍት ሪል እስቴትየምስራች ለቤት ፈላጊዎች በሙሉ ከጊፍት ሪል እስቴት በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት ልናደርጋችሁ መተናል ?በ2% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት መሆን ከፈለጉ ጊፍት ሪል ስቴት በለገሃር መንደር የሚያዘጋጀውን ልዩ የሽያጭ ኤክስፖ ይጎብኙ፡፡👉የአዲስ አመት ልዩ ኢክስፖ ከነሃሴ25/2018 - መስከረም 25/2019 ዓ.ም. በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል፡፡በኤክስፖው እስከ 10% ልዩ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ 👉 ባለ 1 መኝታ 65 ካሬ 👉 ባለ 2 መኝታ 108 ካሬ 👉ባለ 3 መኝታ 163 ካሬየንግድ ሱቅ / ቢሮ ከ18 ካሬ ጀምሮመኖር በጊፍት መንደር!ጊፍት ሪል ስቴት
Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 08:21изменён
ሰበር❗ከባድ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ‼️ ዛሬ መስከረም 12/2019 ዓ.ም በራያ አላማጣ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ተደጋጋሚ ከባድ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ። ጥቃቱ የጀመረው 4:10 አካባቢ ሲሆን በአላማጣ ከተማ ዋጃ መውጫ ሓውጃኖ ትምህርት ቤት ላይ፣#ፋጫ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ንጉስ_ቸኮለ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና አላማጣ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ላይ ሲሆን በሓውጃኖ ትምህርት ቤት ብቻ 17 የህወሓት ታጣቂዎች መሞታቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ አረጋግጠዋል። የቆሰሉ ታጣቂዎች በአምቡላንስ ወደ መሆኒ እየተወሰዱ ይገኛሉ። [አዩዘሀበሻ] 🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊 ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 08:21
🌟 በካዛንቺስ መሃል ከተማ — ያለምንም የዋጋ ጭማሪ እና ወለድ የቤት ባለቤት ይሁኑ! በአዲስ አበባ እምብርት ካዛንቺስ ሳይት፣ በሁሉም አቅጣጫ በሚያማምሩ ፓርኮች እና መዝናኛዎች የተከበበ፣ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት (የውሃ፣ የመብራት፣ የመንገድ) ስጋት የሌለበት ድንቅ የመኖሪያ መንደር! ከመንግስት ጋር በጋራ (70/30) እየገነባን ያለነውን ይህንን እጅግ ዘመናዊ አፓርታማ ከ2 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ እናስረክባለን። ✨ ልዩ ጥቅሞች፦ Fixed Rate፦ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ ወይም የወለድ ክፍያ የለውም! ምቹ አከፋፈል፦ በሂደት የሚከፈል ማራኪ የክፍያ ስልት። ታማኝነት፦ በኩባንያው ቀጥተኛ የሽያጭ ባለሙያ የሚስተናገዱበት አስተማማኝ እድል። 📐 ያሉን የአማራጮች እና የክፍያ ዝርዝር (15% ቅድመ ክፍያ ብቻ)🛏 ባለ 1 መኝታ (55 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 5,830,385 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 874,557 ብር🛏 ባለ 2 መኝታ (80 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 8,480,560 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,272,084 ብር🛏 ባለ 3 መኝታ (95 ካሬ) አጠቃላይ ዋጋ፦ 10,070,665 ብር 15% ቅድመ ክፍያ፦ 1,510,600 ብር



Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 06:13изменён
ጫት፣ አስካሪ አልኮል መጠጦች እና ጎጂ ልማዳዊ ጭፈራዎችን የሚያግድ አዋጅ ጸደቀ‼️ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ብሔረሰብ ምክር ቤት ጫት እና አስካሪ አልኮል መጠጦች በማህበረሰቡ ላይ የሚያስከትሉትን ከፍተኛ ጉዳት በማስመልከት ያወጣውን አዋጅ መነሻ በማድረግ፣ የባምባሲ ወረዳ ምክር ቤት መመሪያው በሚፈቅደው መልኩ አዋጁን አጽድቆ ስራ ላይ እንዲውል ማድረጉ ተገለጸ።የባምባሲ ወረዳ ምክር ቤት በ2019 ዓ.ም 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ባጸደቀው በዚህ አዋጅ መሰረት፤ ከጫት እና ከአስካሪ አልኮል መጠጦች በተጨማሪ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት የሚያስከትሉ ጭፈራዎች እንዳይደረጉ በህግ ክልከላ ተደርጎባቸዋል።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይህንን የወጣውን ክልከላ መተላለፍ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ተገንዝቦ ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 06:11изменён
🏢✨ ለስራዎ የሚመጥን ፕሮፌሽናል የቢዝነስ ቦታ ይፈልጋሉ? 📍 በተመራጭ አካባቢ የሚገኝ ዘመናዊ የንግድ ማዕከል! መርካቶ/ተክለሀይማኖት 💼 ለቢሮዎ፣ ለኩባንያዎ እና ለንግድ ስራዎ የሚመች 🏢 ለፕሮፌሽናል የቢሮ አጠቃቀም ✨ ዘመናዊ ዲዛይን • ምቹ የስራ አካባቢ • ለንግድዎ የሚመጥን አድራሻ 🔥 እስከ 15-20% ቅናሽ! 💰 ከ1,900,000 ብር ጀምሮ 640,000ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ 🇺🇸 🇬🇧 🇿🇦 🇦🇪 በውጭ ሃገር ለምትገኙ ፈላጊዎች ውል በ 3 ቀን ውስጥ ጨርሰን በ DHL እንልካለን። 📞 0920721082 /0952593949 ይደውሉ ወይም WhatsApp ላይ ይጻፉልን። ለቢዝነስዎ ቦታ ብቻ አይግዙ — የሚያሳድገውን ቦታ ይምረጡ! ✨


Ayu Zehabesha-Official አዩ ዘሀበሻ
22 сент., 04:59
" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል።በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም

