gram news
Аватар канала Bahir Dar University,Ethiopia

Bahir Dar University,Ethiopia

@bahir_dar_university

It is a channel about Bahir Dar University all Campuses! www.bdu.edu.et

ПроектыENОбразование

22,000подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Bahir Dar University,Ethiopia

    26 сент., 06:37

    👍በተመጣጣኝ ዋጋ በአስተማማኝ ሁኔታ👇የኮምፒዩተር ጥገና 👉ሶፍትዌር ማስተካከል 👉 window os መጫን 👉ሃርድዌር ማስተካከል 👉laptop charger ጥገና 👉ስክሪንና ቦርድ ቅያር @Feleke23 0918304419የተበላሹ ፍላት ቲቪ: ኮምፒዩተርና ሞባይል እንገዛለን!አድራሻ: ባ/ዳር ቀበሌ 12 ዋርካው ህንጻ ፊትለፊት አፍሪካ ሞባይል አዳራሽ ሱቅ ቁጥር 9
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    26 сент., 06:27

    To all BDU boarding Students:The university has arranged transportations from airport to the campus. Students must contact assigned representatives found in the exit of the terminal and use buses. Please use the following contact address for further information for your travels. Mrs Alemken: 0920152172
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    26 сент., 05:35

    የርዕይ ጥበብ ቁጥር ፪ የ2018 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች ዕቅድ ትውውቅ መድረክለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ስታፍ አባላት በሙሉ፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ያዘጋጀ በመሆኑ በሚከተለው መርሃ ግብር መሠረት በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ጥሪዉን አስተላልፏል፡፡📌 ተጋባዥ አካላት፡ #የአካዳሚክ ዘርፍ፡ ኮርስ ተጠሪዎች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ ዲኖችና ምክትል ዲኖች፣ እንዲሁም የትምህርት ክፍሉ አንጋፋ መምህራን#የአስተዳደር ዘርፍ፡ ዳይሬክተሮች እና ሥራ አስፈጻሚዎች 📅 ቀን፡ ሰኞ፣ መስከረም 18/2019 ዓ.ም ⏰ ሰዓት፡ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ 📍 ቦታ፡ ጥበብ አዳራሽ (ጥበብ ሕንፃ)ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ "ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ!"
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    25 сент., 17:04

    ኮሌጁ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ መስከረም 14/2019 ዓ/ም፥ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር በዘንዘልማ ግቢ ውይይት አካሄደ።ኮሌጁ ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠውን ራዕይ ስኬት ላይ ለማድረስ ወቅታዊ፣ በዕቅድ የሚመራና፣ ጥራት ያለው ትምህርት በማዳረስ ላይ ተመስርቶ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈራረመዉን “Key Performance Indicaters (KPIs)’’ መሰረት በማድረግ የ2018 ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በመገምገም የ2019 በጀት ዓመታዊ ዕቅድ ከት/ክፍሎች ጋር በመሆን አዘጋጅቷል፡፡ የ2019 በጀት ዓመታዊ ዕቅድ ከ2013 እስከ 2022 ዓ.ም ኮሌጁ በመማር ማስተማር ዘርፍ ካዘጋጀው የአስር ዓመት ስልታዊ ዕቅድ የተቀዳ ሲሆን በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት አካዳሚክ ዘርፉ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮችም፦ 1) የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ቅበላ የማስፋት፣ 2) የድህረ ምረቃ ፕሮግራምን አደረጃትና አሰራር ማሻሻል፣ 3) የአካዳሚክ ፕሮግራሞችን አግባብነትና ጥራት መጠበቅ፣ 4) የተሻሻለ የትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች ምዘና መተግበር፣ 5) በመማር ማስተማር ውስጥ የአገር በቀል ዕውቀቶችን አሰናስሎ መጠቀም (Integrating indigenous knowledge use) 6) የበየነ መረብ ትምህርት አሰጣጥና የተማሪዎች ምዘና መተግበር (Strengthen online learning) ፣ 7) የመምህራን ልማት ማሳደግ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ የኮሌጁ ራዕይ/Vision፡ በ2030 በአፍሪካ በግብርና እና አካባቢ ሳይንስ ትምህርት፣ በፈጠራ እንዲሁም በማህበረሰብ ተሳትፎ ግንባር ቀደም የልህቀት ማዕከል መሆን እና በኢትዮጵያም የመጀመሪያ ምርጫ መሆን ሲሆን ተልዕኮው/Mission ደግሞ (1) በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ተፈላጊነት ያላቸውን ምሩቃን ማፍራት፤ (2) ለዕውቀት ዕድገት አስተዋፅኦ የሚያበረክቱና የማህበረሰቡን ችግሮች የሚፈቱ ተፅዕኖ ፈጣሪ ምርምሮችን ማካሄድ፤ (3) በመረጃ ላይ በተመሰረተና ለውጥ በሚያመጣ የማህበረሰብ ተሳትፎ የማህ/ሰቡን ሕይወት ማሻሻል፤ (4) ፍላጎትን መሠረት ያደረጉና ችግር ፈቺ የሆኑ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምክር አገልግሎቶችን መስጠት፤ (5) በፈጠራና በሥራ ፈጣሪነት (Entrepreneurship) የሀብት ፈጠራን ማሳደግ የሚሉት ይገኙበታል።የኮሌጁ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ብዛት በፒኤችዲ 15፣ በማስተርስ 24 እንዲሁም በየመጀመሪያ ዲግሪ 12 በድምሩ 49 ፕሮግራሞች ያሉት አንጋፋ ተቋም ሲሆን በመጀመሪያ ዲግሪ 986፣ በማስተርስ 60 እንዲሁም በፒኤችዲ 116 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል። ይህንን ፕሮግራም የሚመሩ እና የሚያስተምሩ በአጠቃላይ 109 መምህራን ያሉት ሲሆን 9 ሙሉ ፕሮፌሰሮች፣ 24 ተባባሪ ፕሮፌሰርሮች፣ 39 ረ/ፕሮፌሰሮች እንዲሁም 37 ሌክቸረሮች ይገኙበታል።በፕሮግራሙ መክፈቻ የኮሌጁ ዲን ፕ/ር መልካሙ አለማየሁ የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በተለይ ኮሌጁ እስካሁን በትኩረት በሰራባቸው ዋና ዋና ስራዎች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፨ በ2019 ዓ/ም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራባቸውን ዋና ዋና ስራዎችም፦ · በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የአዳሪ ትምህርት ቤት ማስጀመር · Outcome based UG & PG carriculum approval · Under graduate students exit exam · 4 laboratories international accreditation · Establishement of college level new research center · Infrastructural service improvement (transport, electricity, water) ዋና ዋናዎቹ ይገኙበታል። በመቀጠልም በኮሌጁ ም/ል ዲን ዶ/ር መንግስቴ ሞሴ “የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ” በሚል ርዕስ ገለፃ አድርጓል። ቀጥሎም “በድህረ ምረቃ፣ መማር ማስተማር እና ማህበረሰብ ተሳትፎ ቢሮ በኩል የ2018 ዓ/ም አፈፃፀም እና የ2019 ዓ/ም ዕቅድ” በሚል ርዕስ በኮሌጁ ድህረ ምረቃ፣ ምርምር እና ማህበረሰብ ተሳትፎ ም/ል ዲን ዶ/ር ሻሼ አየለ ገለፃ ተደርጓል።ከገለጻው በኋላ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተነስተው ጥልቅ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከቤቱ በተነሱ ጥያቄዎች ዙሪያ በፕ/ር መልካሙ፣ በዶ/ር መንግስቴ እና በዶ/ር ሻሼ ምላሽ እና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ወደፊት ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። በአመቱ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የእውቅና እና የሰርተፊኬት ሽልማት መረሃግብር ተካሂዶ ስብሰባው ተቋጭቷል።
    2,90012111Открыть в Telegram
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    23 сент., 11:59

    ቀን፡ 13/1/2019 ዓ.ም ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለሶሻል ሳይንስ ፋካሊቲ ሪጅስትራር ኃላፊ (በምክትል ዲን ማዕረግ) የኃላፊነት ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም በወጣው የመጀመሪያ ማስታወቂያ በቂ አመልካቾች ባለመገኘቱ በድጋሜ ማውጣት አስፈልጓል፡፡ ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ የሶሻል ሳይንስ ፋካሊቲ ሪጅስትራር ኃላፊ (በምክትል ዲን ማዕረግ) የማወዳደሪያ መስፈርት፡- 1ኛ. የትምህርት ማዕረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት 2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤ 3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤ 4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤ አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ጳጉሜ 01 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስተ) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ፡ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 2 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡ ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
    5,34020311Открыть в Telegram
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    23 сент., 09:15

    STEM ማዕከል“እያንዳንዱ ሕፃን ዕድሉን ካገኘ ሳይንቲስት ይሆናል!’’በሚል መሪ ቃል ከተማሪ ወላጆችና መምህራን ጋር ውይይት አካሄደ (መስከረም 11/2019 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስናና የሒሳብ ማበልጸጊያ ማዕከል (STEM) የተማሪዎችን የትምህርት ሂደት፣ የፈጠራ አቅም እንዲሁም የወደፊት ዕድገት ለመደገፍና የወላጆችን ተሳትፎ ለማጠናከር ከተማሪ ወላጆችና መምህራን ጋር ውይይት አካሂደ። በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ለተሳታፊዎች “እንኳን ደህና መጣችሁ” ያሉት የቀድሞ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ሽፈራው (ዶ/ር) ሲሆኑ በንግግራቸው የወላጆች ተሳትፎ በተማሪዎች የትምህርትና የፈጠራ ጉዞ ውስጥ ያለውን ሚና አጽንዖት ሰጥተዋል። አያይዘውም፣ “ተማሪዎቻችን በክፍል ውስጥ በትምህርት ውጤታማ መሆን ብቻ በቂ አይደለም፤ በቴክኖሎጂና በፈጠራ ሥራ ላይ በመስራት ሳይንቲስት መሆን ያስፈልጋል” ብለዋል። መጨረሻም የወላጆች፣ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት ትብብርን በማጠናከር የተማሪዎችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ማሳደግ፣ የፈጠራ አቅማቸውን ማጎልበትና ለወደፊት የSTEM ባለሙያዎችን ማፍራት የማዕከሉ ዋና ትኩረቶች መካከል መሆናቸወን ገልጸው የተማሪ ወላጆች የልጆቻቸውን የፈጠራ አቅም ለማጎልበት በየጊዜው ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ማዕከሉ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሒሳብ (STEM) ዘርፎች የተለያዩ የመማር፣ የመሞከርና የመፍጠር ዕድሎችን ከመፍጠር ባሻገር በፕሮጀክት ሥራዎች፣ በላብራቶሪ ትምህርትና በፈጠራ ሥራዎች በመሳተፍ ተማሪዎች የችግር የምፍታት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ እንደሚያበረታታ በውይይቱ ተገልጿል።የማዕከሉ መስራች እና አሁን ያለውን ገጽታ እንዲኖረው ትልቅ ድርሻ ያበረከቱት ዶ/ር ብሬ ጌቴ፣ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ማዕከሉ በጥቂት ተማሪዎች ተመስርቶ ቢጀምርም፣ በሳይንስ ዘርፍ ለሀገር አለኝታ የሚሆኑ ተማሪዎችን እያፈራ መሆኑን ገልጸዋል። የማዕከሉ ምስረታ ዋና ዓላማም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ሳይንቲስቶችን ማፍራት መሆኑን ገልጸዋል። የSTEM ማዕከል በቀደሙት ዓመታትም የተማሪዎችን የፕሮጀክትና የፈጠራ ሥራዎች ለወላጆችና ለተጋባዥ እንግዶች በማቅረብ፣ የተማሪዎችን ችሎታ ለማሳየትና ወላጆች ልጆቻቸውን በተሻለ መልኩ እንዲደግፉ ዕድል ሲፈጥር ቆይቷል። የወላጆች፣ የመምህራንና የትምህርት ተቋማት ትብብርን በማጠናከር የተማሪዎችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፍላጎት ማሳደግ፣ የፈጠራ አቅማቸውን ማጎልበትና ለወደፊት የSTEM ባለሙያዎችን ማፍራት የማዕከሉ ዋና ትኩረቶች መካከል ናቸው።በመጨረሻም የፕሮግራሙ አዘጋጅ እና የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶ/ር አለሙ ተስፋዬ ከተማሪዎች እና ከመምህራኖቻቸው ጋር ውጤታማ የትምህርት፣ የሙከራና የምርምር አመት እንዲሆን ያለመ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በተለይም አዲስ ለገቡ ተማሪዎች ሰለ STEM ባህልና የስነምግባር መርሆች ጠንከር ያለ መልዕክት አስተላልፈዋል።
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    18 сент., 16:51

    Иллюстрация к посту канала Bahir Dar University,EthiopiaИллюстрация к посту канала Bahir Dar University,Ethiopia
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    18 сент., 16:51

    Иллюстрация к посту канала Bahir Dar University,EthiopiaИллюстрация к посту канала Bahir Dar University,Ethiopia
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    18 сент., 16:51

    ለሲኒማና ቴአትር ጥበባት ትምህርት የኤክስቴንሽን መርሐግብር ትምህርት ፈላጊዎች:-የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በሲኒማና ቴአትር ጥበባት (BA Degree in Cinema & Theatre Arts) በመደበኛ ያልሆነ/ማታ እና የቅዳሜና እሁድ (Extension Program) አዲስ ተማሪዎችን ይቀበላል!🎭 የትምህርቱ ዋና ዋና መስኮች- ትወናና ክዋኔ (Acting & Performance): የመድረክ፣ የፊልም እና የድምፅ ስልጠናዎች - ዳይሬክቲንግ (Directing): የመድረክ ቴአትርና የፊልም ዝግጅት - ድርሰት (Scriptwriting): ለቴአትር፣ ፊልም፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስክሪፕት መጻፍ - የፊልም ፕሮዳክሽን (Film Production): የካሜራ ቀረጻ (Cinematography)፣ ኤዲቲንግ እና የድምፅ ዲዛይን - ተግባራዊ ቴአትር (Applied Theatre): ማህበረሰብ ተኮር (TfD) እና ሀገር በቀል ክዋኔዎች - የጥበብ ስራዎች አስተዳደር (Arts Management): የፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ የሁነቶች ዝግጅት እና የህዝብ ግንኙነት📋 የመግቢያ መስፈርቶች1. የትምህርት ደረጃ: - የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አልፈው ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ የሚያበቃ ውጤት ያላቸው ወይም - የደረጃ 4 (Level IV) ሰርተፍኬት ያላቸው እና የብቃት ማረጋገጫ (COC) ያላለፉ/ያላቸው። 2. ችሎታ መመዘኛ: በትምህርት ክፍሉ የሚዘጋጀውን የተግባር ችሎታ መመዘኛ (Audition) እና ቃለ-መጠይቅ ማለፍ የሚችሉ።
  • Bahir Dar University,Ethiopia pinned a photo

    15 сент., 19:09

  • Bahir Dar University,Ethiopia

    15 сент., 16:31

    ተማሪዎቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ!
    Иллюстрация к посту канала Bahir Dar University,EthiopiaИллюстрация к посту канала Bahir Dar University,Ethiopia
    10,500541633Открыть в Telegram
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    14 сент., 17:11

    Иллюстрация к посту канала Bahir Dar University,EthiopiaИллюстрация к посту канала Bahir Dar University,Ethiopia
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    14 сент., 17:11

    ማስታወቂያ ለሁሉም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም 1ኛ አመት ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የትምህርት ክፍል ምደባ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተማሪዎች ከመስከረም 6-7 ቀን 2019 ዓ.ም ሪፖርት እንድታደርጉ ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ሪፖርት የምታደርጉበት ግቢ ለውጥ ስለተደረገ ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡1. የOther Social Science ተማሪዎች ከAbay Mola Chane እስከ Samrawite Fetene Mebratu ያላችሁ በSelam Campus 2. Other social Science ከ Samrawit Gashawtena Abate እስከ Zinalem Agalu Mekuria Peda 3. Engineering and Technology ከ Natenael Zemenu Adis እስከ Zekremariam Abiy Beze ያላችሁ Selam Campus 4. Engineering and Technology ከ Abatnew Ayayu Melaku እስከ Natnael Wessenu Amare) BiT/Poly 5. Other Natural Science ከAbaynew Mola Wondimhunegne እስከ Eyachew Andualem Admas ወንዶች በ Peda 6. Other Natural ከ Eyasu Bekele Sulamo እስከ Zewdu Kassa Baye ወንዶች በCoBE 7. All Other Natural Science ሴቶች በ COBE የተመደባቹህ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    ጷጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ምየምዝገባ ጥሪ ማስታወቂያ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም አማራጭ የመምህራን ስልጠና ስትከታተሉ ለነበራችሁ ሰልጣኞች በሙሉበ2018 ዓ.ም አማራጭ የመምህራን ስልጠና ስትከታተሉ ለነበራችሁ ሰልጣኞች በ2019 ዓ.ም ቀሪ ኮርሶችን ለማጠናቀቅ ምዝገባ የሚካሄደው ከመስከረም 07-08/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።በመሆኑም ሰልጣኞች በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳውቃለን።የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
    10,5002422Открыть в Telegram
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    4. Master of Science in Bioinformatics and Data Base Management PhD 1. Doctor of Philosophy in Biotechnology (Health Biotechnology, Agricultural Biotechnology, Industrial Biotechnology, Environmental Biotechnology)16. School of Veterinary Medicine Master Programs 1. Master of Science in Veterinary Epidemiology and Economics 2. Master of Science in Veterinary Microbiology 3. Master of Science in Veterinary Public Health
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    3. Master of Science in Geo-information Science 4. Master of Arts in Social Anthropology 5. Master of Arts in Environmental Management 6. Master of Arts in Social Work 7. Master of Arts in History 8. Master of Arts in Heritage and Museum Studies 9. Master of Arts in Political Science 10. Master of Arts in Peace and Conflict Studies 11. Master of Arts in Gender and Development Studies 12. Master of Arts in Sociology 13. Master of Arts in Urban and Regional Development Planning PhD Programs 1. Doctor of Philosophy in Geography & Environmental Studies 2. Doctor of Philosophy in History 3. Doctor of Philosophy in Political Science and International Studies 4. Doctor of Philosophy in Social Anthropology 5. Doctor of Philosophy in Geospatial Analytics and Remote Sensing 6. Doctor of Philosophy in Social Work and Social Development 9. Faculty of Humanities Master Programs
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    6. Master of Science in Biology (Zoological Science) 7. Master of Science in Ecological and Systematic Zoology 8. Master of Science in Chemistry (Analytical Chemistry, Physical Chemistry, Organic Chemistry and Inorganic Chemistry) 9. Master of Science in Physics (Space Physics, Solid State Physics, Physical Electronics, Quantum Optics, Laser, Atmospheric, Nuclear Physics, and Semiconductor.) 10. Master of Science in Statistics (Biostatistics, Industrial Statistics, Econometrics) 11. Master of Science in Industrial Quality Control and ManagementPhD Programs 1. Doctor of Philosophy in Mathematics (Algebra, Analysis, Differential Equations, Numerical Analysis, Optimization, Mathematical Modeling, Financial Mathematics, Inverse Problem) 2. Doctor of Philosophy in Physics (Space Physics, Solid State Physics, Applied Conduced Mater Physics, Atmospheric Physics) 3. Doctor of Philosophy in
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    21. MSc in in Emergency Medicine and Critical Care Nursing PhD Programs 1. Doctor of Philosophy in Public Health 2. Doctor of Philosophy in Public Health Nutrition 3. Doctor of Philosophy in Environmental Health 4. Doctor of Philosophy in Reproductive Health 5. Degree of Doctor of Philosophy in Epidemiology 6. Doctor of Philosophy in Biostatistics 7. Doctor of Philosophy in Nursing 8. Doctor of Nursing Practice Specialty 1. Specialty in General Surgery 2. Specialty in Gynecology and Obstetrics 3. Specialty in Internal Medicine 4. Specialty in Orthopedics and Trauma Management 5. Specialty in Pediatrics and Child Health 6. Specialty in Dermatovenerology 7. Specialty in Anesthesiology and critical care 8. Specialty in Ophthalmology 9. Specialty in Psychiatry
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    41. Master of Science in Artificial Intelligence and Data Science 42. Master of Science in Industrial Biotechnology 43. Master of Science in Industrial Management PhD Programs 1. Doctor of Philosophy in Hydraulic Engineering 2. Doctor of Philosophy in Hydrology and Water Resources Management 3. Doctor of Philosophy in Water Supply and Sanitary Engineering 4. Doctor of Philosophy in Irrigation Engineering and Management 5. Doctor of Philosophy in Construction Engineering and Management 6. Doctor of Philosophy in Structural Engineering 7. Doctor of Philosophy in Geotechnical Engineering 8. Doctor of Philosophy in Road and Transport Engineering 9. Doctor of Philosophy in Sustainable Energy Engineering 10. Doctor of Philosophy in Agricultural Mechanization Engineering 11. Doctor of Philosophy in Agricultural Machinery Engineering 12. Doctor of Philosophy in Mechanical Design 13. Doctor of
  • Bahir Dar University,Ethiopia

    11 сент., 06:00

    ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም ማስታወቂያ ለድኅረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዲግሪ (Master’s) እና በሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ሲመዘግብ መቆየቱ ይታወቃል። የትምህርት ዕድሉን ለማመቻቸት የማመልከቻ ጊዜው እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን እንገልጻለን። ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከታች በተጠቀሱት አማራጮች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። የማመልከቻ መንገዶች: - በኦንላይን፦ https://studentportal.bdu.edu.et ላይ በመግባት፤ በአካል፦ በሚመለከታቸው ኮሌጅ/ኢንስቲትዩት/ፋኩልቲ ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤቶች በመቅረብ፤ በኢሜይል፦ ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ማስረጃዎችን በመላክ፦ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ: firew.firew@gmail.com ማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ: yitayalabebe11@gmail.com ሂውማኒቲስ ፋኩልቲ: temesgenb35@gmail.com ህግ ትምህርት ቤት: meserettamir9@gmail.com ትምህርት ኮሌጅ: jjjase2016@gmail.com ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ: adamuyimer16@gmail.com የመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት: hailishmiss@gmail.com ሳይንስ ኮሌጅ: cos_registrar@bdu.edu.et ስፖርት አካዳሚ: berhanie98@gmail.com የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት: abrhamdestaw25@gmail.com የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት: