Последние посты

bestletters
22 сент., 18:54изменён
መውደቅ normal ነገር ነው ፤ መሰበርም እንደዛው ። እስከተራመድክ እና እስከሮጥክ ድረስ በህይወት ውስጥ እንቅፋት፣መሰናክል እንዲሁም ፈተና ይገጥማል ። ወድቆ አለመቅረት ነው ፣ ተነስቶ ለመቆም ረፍዷል ብለህ ያለህበት እንዳትቀር ፣ ተነስ ካለፈው ሕይወት የገጠመህን የፈተና ፣ አቡዋራ አራግፍ ። በእንቅፋቱ ቂም እንዳትይዝ ፤ ቂምህን አራግፈው ። ከዛ መንገድህን ቀጥል ። በሌላ መንገድ ደግሞ ሂድ ፤ ወደ ነገህ ሂድ ።የ ተ ቀ ደ ደ ው ማስታወሻ ©ሶፊ


bestletters
22 сент., 18:32изменён
ና ብላ ጠራችኝ፤ና ስትለኝ.....ምንም የሚያስቸኩል ስራ ቢኖር ጥዬው ነው ወደ እሷ የምሄደው ፀባይዋን አውቀዋለሁ! የምትፈልገውን ለማግኘት በጣም ችኩል ነች ያሰበችውን ወዲያው አድርጋ እስክትጨርስ እንቅልፍ የላትም...! ና ልኝ አለችኝ የህይወቴን ብዙ ጊዜ የወሰደውን ፕሮጀክት ጥዬ ሄድኩ...ብዙ ጊዜ የምናዘወትርበት ቤት አለ...ቀድማ ደርሳ እየጠበቀችኝ ነበር ...ደረስኩ ..በር ላይ አስተናጋጇን ሰላምታ ሰጥቻት ስገባ በፈገግታ "ውስጥ ናት" አለችኝ። ወደ ውስጥ ገባሁ ዘውትር የምንቀመጥበት ቦታ ተቀምጣለች ሳያት ደስ አለኝ...እንደተለመደው ቀለል ያለ አለባበስ ለብሳለች...ጌጥ ማብዛትና መቀባባት አትወድም ለምን ብዬ ስጠይቃት "መንኳተት ነው።" ብላነግራኛለች።ያለኝ ይበቃኛል ብላ ስለምታስብ ይሆን? ...ስገባ ጀርባዋን ሰጥታ ተቀምጣ አገኘዋት። ኮቴዬን አጥፍቼ ተጠጋዋትና አይኖቿን በእጆቼ ሸፍኜ፤ድምፄን አጎርንኜ "እኔ ማን ነኝ?" አልኳት።ደስ በሚለው ፍልቅልቅ ሳቋ እንደታጀበች "የኔ ሶፊ አይደለህ?" አለችኝ። አንገቷን ስሚያት ከፊት ተቀመጥኩ። "ምነው ስራ የለም?" አልኳት እጇን ልይዛት እጄን እየሰደድኩ። "ዛሬ አብረን እንድንውል አስፈቅጄ መጣሁ።" "ዛሬ ምን ተገኘ?"አልኳት መልሷን ለመስማት በመጓጓት...ያለ አንዳች ምክንያት..ከስራ እንደማትቀር አውቃለሁ። "ምሳ እንድንበላ እና እናወራለን ብዬ ነው" አለቸኝ ፈገግ እንዳለች ። ከፈገግታዋ ላይ አንዳች ሐዘን አነበብኩ ውስጤ ፈራ...ምሳ ተመግበን እንደጨረስን ቡና ወደ ምንጠጣበት ስፍራ አመራን እዛ ለማውራት ይመቻል። ቡናችንን ጠጥተን ወሬ አልቆቡን ተፋጠጥን
bestletters
22 сент., 17:45изменён
ራስ ወዳድነት በጣም መሰረታዊ የሆነ የሰው ልጅ ባህርይ ነው።ለመኖርም አስፈላጊ ነው።ከሌሎች ጋር የምንኖረው ሌሎችን ስለምንወድ ሳይሆን ከሌሎች ጋር አለመኖር ስለማንችል ነው።ገዳም እንኳን ብትገባ ከሌሎች ገዳም ከገቡ ሰዎች ጋር ነው የምትኖረው።ከሌላው ማምለጥ የሚባል ነገር በህይወት ውስጥ የለም።በአንድ ወይም በሌላ መልክ አንተ ፈለክም፣አልፈለክም ሌሎች ለአንተ መኖር አስፈላጊ ናቸው📕ርዕስ፦አለመኖር ✍ደራሲ፦ዳዊት ወንድምአገኝ


bestletters
22 сент., 05:36
#12


bestletters
21 сент., 19:43
🔥


bestletters
20 сент., 18:33



bestletters
20 сент., 18:09
4 killo near to Jolly bar.


bestletters
20 сент., 14:04
Sunday ✨


bestletters
19 сент., 16:31
🔥


bestletters
18 сент., 18:59
I'm falling in love again... There will be a coming story on የተቀደደው ማስታወሻ


bestletters
16 сент., 18:57
ለሰይጣን ተስሎአልጋ ላይ ጋደም ባልኩበት ነበር ጓደኛዬ ወደ ስልኬ የደወለው ትንሽ ከጠራ ቡሃላ አንስቼ "ሄሎ" አልኩት በግድ የለሽነት "እ አንተ ጀዝባ" አለኝ እየጮኸ ከኋላው በሰማውት ዘፈን የት እንዳለና ለምን እንደደወለ ገባኝ "ምን ፈለክ ?" አልኩት "ምን አባህ ያኮሳትርሀል ወይስ ዛሬም philosophy mood ላይ ነህ " አለኝ እና ከት ብሎ ሳቀሳይታወቀኝ ፈገግ አልኩ በኔ እና በሱ ቋንቋ philosophy mood ማለት አንዳንዴ እኔ ከሰው መነጠል ያምረኛል ስለ ብቸኝነት ስለ ህይወት ብዙ ማሰብ እና መፈላሰፍ እጀምራለሁ ይህን ፀባዬን ሲያይ ነው philosophy mood ብሎ ስም ያወጣለት። "አዎ ባክህ" አልኩት ድብርቴ ባንዴ ለቆኝ እየተነቃቃው "በል በል አንተ እኮ ታበዛዋለህ ተነስ በቃ እዛው ና ጨዋታው ደርቷል ነው ምልህ አንተ ብቻ ነህ የቀረኸው በዛ ለይ ግብዣ በኔ ነው " "መጣው በቃ" አልኩት መደወሉ በጣም ነው ደስ ያለኝ ከዚ ስሜት መውጫ መንገድ ነበር የፈለኩት።4በ4 የሆነችው ክፍሌን ከነምስቅልቅሏ ትቻት ወጣው። ፀሀይዋ በረድ ብላ ቀዝቀዝ ያለ ነፋስ እየነፈሰ ደስ ወደ ሚል ስሜት ውስጥ ከተተኝ። አየሩን ያለ ከልካይ እየሳብኩ እኔ እና መሰሎቼ ወደምንሰበሰብባት አነስ ያለች ግሮሰሪ ደረስኩ። መሰሎቼ በረንዳ ላይ ክብ ሰርተው ያውካካሉ ። እንደነገሩ ሰላም ብያቸው ተቀላቀልኩ ።ገና ቁጭ ከማለቴ አይኔ የለመደውን ፍለጋ ወደዛ ወደዚ ማለት ጀመረ። አገኘውት....እብድ ልለው አልፈልግም ግን ሌላ ምን መጠሪያ አለው ? እዚ ግሮሰሪ መመላለስ ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ሁሌ አየዋለው ወጣት ነው
bestletters
16 сент., 08:26



bestletters
15 сент., 18:40
✍ በረከት በላይነህ


bestletters
14 сент., 18:59
"ምን አጊኝቶ ነው?" ብለው እስኪገረሙ ድረስ ፈጣሪህን አመስግነው። "እግዚአብሔር ይመስገን ። ©ሶፊ


bestletters
14 сент., 18:54
ድምፅም አልፈጠርኩ ከልቤ፤ ምላሴም አልተናገረ፣ አይኔ ነው እንጂ ፍቅርህን፤ ለፍፎ የመሰከረ፣ ብዕሬ ላይ ነው ሚነበብ፤ ክታቤ ላይ ነው ሚሰማ፣ የልብህ ወርቃማ ፊደል፤ የነፍሴ ወርቃማ ዜማ።ንብ እንደያዘው የ አደይ መስክ፤ ጣፋጭ ማር አንደሚሰራ፣ በሽቶ እንዳጠቡት ኩታ፤ ከርቀት እንደሚጣራ፣ አካሌም ነፍሴም አይኔም ላይ፤ ሁሉ ሰው እያስተዋለው፣ የመውደድህን መአዛ፤ እንደምን ልሸፋፍነው?!✍ Elu ⚡️


bestletters
13 сент., 17:46

bestletters
13 сент., 17:25
loyalty 🔥
bestletters
13 сент., 16:16
ያንን መነፅር አይኔ ላይ ጣል አድርጌ ፤ ዙሪያውን እየቃኘው ስንጎማለል ሰፈሩን ልገዛው ነው የምመስለው ። እኔ ግን ያለወትሮዬ ቤት መቀመጥ ጨንቆኝ ነው ። ©ሶፊ


bestletters
13 сент., 14:43
So I have received precious gift 🔥



bestletters
12 сент., 18:48
ብዙ ነው ያየሁት! . . . ከጊዜ ቀድሜ… በዚህች አጭር ዕድሜ. . . ብዙ ዐየሁ የማይታይ! ብዙ አጣሁ የሚታይ አፍርሶ እየሠራኝ፣ነቅሎ እየገጠመኝ፣ ምድር ከዘራችው፣የለም ያልገጠመኝ! ብዙ ነው ያየሁት. . . ሩቅ ነው የመጣሁት. . . ብቻ በመንገዴ “ደንታ” ነው ያጣሁት! ✍ፈይሠል_አሚን This is my G Faya please join him so you can enjoy poems 🔥 @huluezih
