gram news
Аватар канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@beteafework

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

ПроектыENРелигия

55,600подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    23 сент., 17:32изменён

    “ፍቅር የሕይወት ሰንሰለት፣ የነዳያን እናት፣ የባለጸጎች መምህር፣ የወላጅ አልቦች ተንከባካቢ፣ የአረጋውያን ጠባቂ፣ የምስኪኖች ሀብት፣ የተጎዱ ኹሉ የጋራ ወደብ ነው።'' ፍቅር ደግሞ ክርስቶስ ነው።ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    23 сент., 10:21

    ተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም"በባልንጀራህ ላይ የምትቆጣ ከሆነ የአንተ ቁጣ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡ በባልንጀራህ ላይ ቂምን በልብህ የያዝክ ከሆነ ቂምህ በጌታህ ላይ ነው፡፡ ባልንጀራህን በከንቱ የምትቆጣው ከሆነ ኃጢአት በአንተ ላይ ይሠለጥንብሃል፡፡ ነገር ግን ልብህን የፍቅር ማደሪያ ካደረግኸው በምድር ላይ አንዳች ጠላት አይኖርብህም፡፡አንተ እውነተኛ የሰላም ሰው ከሆንክ በሌላ ሰው ላይ የክፋት ወጥመድን አትዘረጋም፡፡ አንተ በእውነት ጻድቅ ከሆንክ በባልንጀራህ ላይ ከፋትን አታደርግም።ነገር ግን ቁጣን የምታፈቅራት ከሆነ በኃጢአትህ ላይ ተቆጣ፡፡ ይህ ተገቢ የሆነ ቁጣ ነውና፡፡ ጦር መግጠም ከፈለግህ እነሆ ሰይጣን ጠላትህ፤ በእርሱ ላይ ጦርነትህን ከፈት፡፡ ማመፅም ካማረህ፣ ለመርከስህ ምክንያት በሆኑ አጋንንት ላይ አምፅ።በእግዚአብሔር አርዓያ የተፈጠረውን የምትሰድብ ከሆነ የነፍሰ ገዳዩ እጣ ፈንታ ይደርስብሃል፡፡ በሰው ላይ በአመፃ የምትነሣሣ ከሆነ በእግዚአብሔር ላይ እንደተነሣሣህ ቁጥር ነው፡፡ ለባልንጀራህ አክብሮትን የቸርከው ከሆነ እነሆ እግዚአብሔር አከበረህ፡፡ ነገር ግን ባልንጀራህን የምታዋርድ ከሆነ የባልጀራህ ቁጣ በአንተ ላይ እንዲነሣሣ እወቅ፡፡“እግዚአብሔር አምላክህን፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ (እንደችሎታህ መጠን) ውደድ” (ዘዳግ.6፥4-6) የሚለው ሕግ እርሱ የመጀመሪያው ሕግ ነው። እግዚአብሔርንም ስለማፍቀርህ ምልክቱ ባልጀራህን እንደራስህ መውደድህ ነው፡፡ ነገር ግን ባልንጀራህን የምትጠላው ከሆነ የአንተ ጥላቻ በእግዚአብሔር ላይ ይሆናል፡፡ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርህ በእግዚአብሔር ፊት ለጸሎት የምትቆም ከሆነ፣ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ በከንቱ ቃላትን እያበዛህ እንደሆነ የገዛ ሕሊናህ ይመሰክርብሃል፡፡ ሕሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡አምላከህ ክርስቶስ ስለገዳዮቹ በመስቀሉ ላይ ሳለ ይቅርታን ለመነ፤ እንዴት አንተ ፍጥረትህ ከትቢያ የሆነ ቁጣን በፈቃድህ በራስህ ላይ ታቀጣጥላለህ? በወንድምህ ላይ ቂምን ይዘህ ሳለ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅ የሚሆን ይመስልሃልን? በአንተ ምክንያት ከአንተ ጋር ያለ፣ ነገር ግን በኃጢአትህ ተባባሪ ያልሆነው ሰው ድንኳን መተላለፍህ ያገኘዋል፡፡ በአንተ ምክንያትም ጸሎቱ አይሰማለትም።መራርነትን ከሰውነትህ አርቅ ከዛም ጸሎትህን አቅርብ፡፡ ባልንጀራህ በቁጣ ውስጥ ከሆነ፣ ምንም ቁጣው በአንተ ላይ ባይሆን፣ ቁጣን ከሰውነቱ ያርቀው ዘንድ እርዳው፤ ምክንያቱም በሰውነቱ ርኩሰት ይነግሥበታልና፡፡አንተ መንፈሳዊ ተፈጥሮ አለህ፡፡ ነፍስህም የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ናት፡፡ እናም ከሰው ሁሉ ጋር በፍቅር በመኖር የእግዚአብሔር አርዓያ የሆነችውን ነፍስህን አክብራት፡፡ በምትኖርባቸው ዘመኖችህ ሁሉ በተቻለህ መጠን ሰውነትህን ከቁጣ ጠብቅ፡፡ ያለበለዚያ አንተን ወደ ሲአል ታወርድሃለች፤ ጎዳናዎቿም ወደ ገሃነም የሚያመሩ ናቸው፡፡እናም ቁጣን በልብህ አታኑራት፡፡ መራርነትንም በነፍስህ አታሳድር፡፡ በነፍሰህ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህምና ነፍስህን መልካም በማድረግ ጠብቃት፡፡"(ስብከት ወተግሣጽ ዘቅዱስ ኤፍሬም ገጽ ሶርያዊ 66-67 - በመምህር ሽመልስ መርጊያ የተተረጎመ)
    3,4908464Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    22 сент., 23:39изменён

    "ምንም እንኳን መንፈሳዊ ሕይወትህ ደካማ ቢሆንም ተስፋ አትቁረጥ ተስፋ መቁረጥ ዲያቢሎስ በእጆቹ ትወድቅ ዘንድ ሞራልህን የሚያዳክምበትና ችሎታህን የሚያጠፋበት ውጊያ ነው።"(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    22 сент., 15:17изменён

    "​​ልጄ ሆይ ወዳጅ ማለት ሰው አይምሰልህ። ነገር ግን ወዳጅ ማለት ጊዜ ነውና በጊዜህ ሁሉ ይወድሃል አለ ጊዜህ ግን ወዳጅህ እንኳን ይጠላሃል። ጊዜ ማለትም ቀንና ሌሊት አይምሰልህ። ነገር ግን ጊዜ ማለት የእግዚአብሔር አሳብ የሚፈፀምበት ነው ስለዚህ በሆነውም በሚሆነውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ፍቃድ ይሁን እያልህ ተቀመጥ።"(ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ)
    5,9301543619Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    22 сент., 11:18изменён

    “​​​​​​​​​ምስጋና ማለት ታላላቅ በረከቶችን ለመቀበል የምትዘረጋ እጅ ናት። ስላለህ ጥቂት ነገር እግዚአብሔርን ማመስገን ስትጀምር፣ የሰማይን መስኮቶች ለተጨማሪ በረከት ትከፍታለህ። የሚያጉረመርም ልብ በጨለማ ውስጥ ይኖራል፤የሚያመሰግን ነፍስ ግን ሁልጊዜ በብርሃን ውስጥ ነው።’’(ማር ይስሐቅ ሶርያዊ)
    6,2301383317Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    22 сент., 06:26

    "ማንንም አትወንጅል ማንንም አትዳኝ ስህተታቸውን አትዘርዝር ድካማቸውን አታጉላ ራስህን ብቻ ውቀስ ለራስህም 'እኔ ነኝ መጥፎ ኃጢአተኛ' በለው ይህ ነው የመንፈሳዊ ሕይወት ጅማሮ አንዱ መንገ።" (አባ ሴራፊም)
    6,820194221410Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    21 сент., 17:11изменён

    በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው።(ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ -የኤፍራጥስ ወንዝ ገጽ 87)
    7,2601865861Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    21 сент., 10:29изменён

    "በመንፈሳዊው መንገድ ላይ የምትጓዙ ከሆነ እንዳትወድቁ በራሳችሁ አትደሰቱ። ትዕቢትን የምንፈራው እድገታችንን እንዳያቆመው ብቻ ሳይሆን እንዳይጥለንም ነው። መጽሐፍ ይህን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል፦"ትዕቢት ጥፋትን ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።" ምሳ 16፥18..."(መንፈሳዊው መንገድ - በአቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    20 сент., 18:06

    እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል። በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9
    7,230167251222Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    20 сент., 10:24

    ሰላም እንደምን አላችሁ! ​ከዚህ ቀደም ለ2019 የትምህርት ዘመን ለ10 ችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ለማሟላት ባቀረብነው ጥሪ መሠረት፣ አንድ ደግ ወንድማችን የሁሉንም ተማሪዎች ወጪ ሙሉ በሙሉ ችሎልን ዛሬ መስከረም 10/2019 ዓም አስረክበናል። ​በዚህም፦ ​ለ8 ተማሪዎች፦ ሙሉ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም፣ እያንዳንዳቸው 1 ደርዘን ራዲካል ደብተር፣ 6 እስክርቢቶ እና 3 እርሳስ ተሟልቶላቸዋል።​ለ2 እናትና አባት ለሌላቸው ሙስሊም እህትማማቾች፦ የደብተር እና የዩኒፎርም መግዣ የሚሆን በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዳቸው 4,450 ብር (በጠቅላላው 8,900 ብር) ማስረከብ ችለናል። ​ ይህ እንዲሆን ያደረገው ደግ ወንድማችንን ልዑል እግዚአብሔር ያክብርልን፣ ያሰበውን መልካም ሥራ ሁሉ ይባርክለት። በሥራው፣ በጤናውና በቤቱ ሰላሙን፣ ጤናውንና በረከቱን ያብዛለት፤ ቅድስት ድንግል ማርያም በእናትነት ፍቅሯ ትጠብቀው፤ የህፃናቱ ደስታና የወላጆቻቸው ጸሎት ዘወትር ከእሱና ከቤተሰቡ ጋር ይሁን!​ለዚህ መልካም ስራ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጋችሁና በጸሎት ለደገፋችሁን በሙሉ እግዚአብሔር ይስጥልን!
    Иллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
    6,87081163Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    20 сент., 09:52изменён

    “አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    20 сент., 09:05изменён

    የቤተክርስቲያን ጌጥ የሆንክ መምህራችን ዶክተር ሮዳስ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ በፍቅር ያኑራችሁ!
    Иллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
    5,940317211311Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    19 сент., 05:43

    ወንድሞቼ ሆይ! ቃሉን ስታነቡ ዝም ብላችሁ ቃላትን ለመቁጠር ብቻ አይሁን። ነገር ግን በቃሉ ውስጥ ያለውን መንፈሳዊ ጣዕም ለማግኘት ጸልዩ። የምታነቡትን በተግባር ለመተርጎም ትጉ። 'ቃሉን የሚሰሙ ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉት ይጸድቃሉ' ተብሏልና። አንድ ምዕራፍ እንኳ ብታነቡ ያቺ ለአንድ ቀን ስንቅ ትሆናችኋለች። ንስሐ የገባ ሰው ልቡ በቃለ እግዚአብሔር ካልታጠበ ዳግመኛ ወደ ኃጢአት ጭቃ መመለሱ አይቀርም። ቃሉ ግን ልባችሁን ይጠብቃል፤ አእምሮአችሁንም ያበራል።ሰዎች ሆይ! መጻሕፍትን አትናቁ። እነርሱ ከሰማይ ወደ እኛ የተላኩ ደብዳቤዎች ናቸው። የሰማዩ ንጉሥ የላከልህን ደብዳቤ ችላ ብለህ እንዴት ሰላምን ታገኛለህ? በመጻሕፍት ውስጥ የታመሙት ፈውስን፣ ያዘኑት መጽናናትን፣ የወደቁት መነሳትን፣ ንስሐ የገቡት ደግሞ የተስፋን ብርሃን ያገኛሉ። በቃለ እግዚአብሔር የምትታጠብ ነፍስ ዘወትር ለምለም ትሆናለች።ስለዚህ በቤታችሁ መጻሕፍትን ለማንበብ ጊዜ መድቡ። ልጆቻችሁንም በቃለ እግዚአብሔር ኮትኩቱ። ዓለማዊ እውቀት ለሥጋዊ ሕይወት ይጠቅም ይሆናል፤ መንፈሳዊ እውቀት ግን ለዘላለም ሕይወት ያበቃል። ንስሐችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ፣ ሕሊናችሁም ከክፉ ሐሳብ ይነጻ ዘንድ ዘወትር በመለኮታዊ መጻሕፍት ንባብ ተጉ። እግዚአብሔር ቃሉን በልባችን ይጻፍልን።"(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
    8,020160376Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    18 сент., 18:03изменён

    “በአውሎ ነፋስ መካከል ብትሆን እንኳ አትፍራ፤ መርከቧን የሚመራት ክርስቶስ እስካለ ድረስ ማዕበሉ አያሰምጥህም፤ እግዚአብሔር ፈተናውን ባያርቀው እንኳ ፈተናውን የምትችልበትን ኃይል ይሰጥሃል።’’ሊቁ አውግስጢኖስ
    7,4202002831Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    18 сент., 17:15

    #የሐዲስ_ኪዳን_መምህሩን_ሕይወት_እንታደግ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በርካታ ደቀ መዛሙርትን እያነፁ የሚገኙት መምህር ቀለመወርቅ አመሃ ዛሬ የእኛን የደግነት እጅ መዘርጋት የሚሻ ከባድ የልብ ሕመም ገጥሟቸዋል። በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ጉባላፍቶ ወረዳ በድጎ ደብረ ኢየሱስ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ5 ዓመታት ተምረው ከተመረቁ በኋላ፣ በጉባላፍቶ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን
    7,4105811Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    18 сент., 04:29

    ንስሐና ምጽዋት የነፍስ ሁለት ዓይኖች ናቸው። አንዱ ቢጠፋ ሌላኛው ብቻውን ሙሉ እይታ አይሰጠውም።ኃጢአትህ እንዲፋቅልህ ትፈልጋለህን? እንኪያስ የምሕረት በርን በምጽዋት አንኳኳ። 'የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ ምሕረትን ያገኛሉና' ተብሏል። አንተ ለባልንጀራህ ካልራራህ እግዚአብሔር እንዲራራልህ እንዴት ትጠይቃለህ? ምጽዋት ሰጪውን ከኃጢአት እስራት ትፈታዋለች፤ ተቀባዩንም ከችግር ታሳርፈዋለች።ወንድሞቼ ሆይ! አትሳሳቱ፤ ገንዘባችሁ እዚህ ምድር ላይ ይቀራል። ይዛችሁት የምትሄዱት ምጽዋታችሁን ብቻ ነው። በሕይወት እያላችሁ ለነፍሳችሁ ስንቅ አዘጋጁ። ድሆች የእግዚአብሔር መሠዊያዎች ናቸው። በቤተክርስቲያን ያለውን መሠዊያ እንደምታከብሩ ሁሉ፣ እነዚህን ሕያው መሠዊያዎች (ድሆችን) አክብሩ። በድሃው እጅ ላይ የምታስቀምጠው ስጦታ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር እጅ ይደርሳል። ስለዚህ ንስሐችሁ ፍሬ እንዲያፈራ፣ ጸሎታችሁም እንዲሰማ ዘወትር በምጽዋት ትጉ።"ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
    8,400157243Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    17 сент., 17:49

    "ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድምህ ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ
    8,17023923182Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    17 сент., 00:53

    #የሐዲስ_ኪዳን_መምህሩን_ሕይወት_እንታደግበሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ትርጓሜ በርካታ ደቀ መዛሙርትን እያነፁ የሚገኙት መምህር ቀለመወርቅ አመሃ ዛሬ የእኛን የደግነት እጅ መዘርጋት የሚሻ ከባድ የልብ ሕመም ገጥሟቸዋል።በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ጉባላፍቶ ወረዳ በድጎ ደብረ ኢየሱስ አዳሪ ትምህርት ቤት ለ5 ዓመታት ተምረው ከተመረቁ በኋላ፣ በጉባላፍቶ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜን ወንበር ዘርግተው በማስተማር ላይ ይገኛሉ።አሁን ላይ መምህሩ በገጠማቸው የልብ ሕመም ምክንያት በወልድያ ሆስፒታል ቢታከሙም ከአቅም በላይ በመሆኑ ወደ አዲስ አበባ ለከፍተኛ የልብ ሕክምና ተልከዋል። ሕይወታቸውንም ለማዳን ለሚደረገውን አስቸኳይ የልብ ቀዶ ጥገና ከ300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ያስፈልጋቸዋል።ሰውን ለማዳን ሰው መሆን በቂ ነውና መምህሩ እንደገና ወደ ወንበራቸው ተመልሰው ደቀመዛሙርትን ማፍራት እንዲችሉ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያንና ደግ አሳቢዎች በሙሉ የቻላችሁትን በሚከተለው አካውንት ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እንጠይቃለን።#በኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ለመምህር ቀለመወርቅ አመሃ በላይ 1000513559821#ለበለጠ_መረጃ፦ ➛ መምህር ቀለመወርቅ - +251920120104ሼር በማድርግ ይተባበሩ
    Иллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅИллюстрация к посту канала ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
    9,470922512Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    16 сент., 18:21

    ከእራት በኋላ ያለው ጊዜ የምስጋና ጊዜ ነው፡፡ ምስጋናን የሚያቀርብ ደግሞ ንቁና የተረጋጋ ይሆናል፡፡ ከእራት በኋላ ወደ ጸሎት እንጂ ወደ መኝታ አንሂድ፡፡ ያለበለዚያ ግን በደመ ነፍስ ከሚመሩት አውሬዎች የበለጠ በደመ ነፍስ የምንመራ እንሆናለን፡፡ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
    9,1501872913Открыть в Telegram
  • ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

    16 сент., 13:21изменён

    ሰይጣን ኃጢአት እንድትሠራ ሲገፋፋህ 'ድፍረትን' ይሰጥሃል። 'እግዚአብሔር መሐሪ ነው፣ አንድ ጊዜ ብትሠራው ምን ይልሃል? ቆይተህ ንስሐ ትገባለህ' እያለ በኃጢአት ላይ እንድትደፋፈር ያደርግሃል። አንተ ተሸንፈህ ኃጢአቱን ከፈጸምክ በኋላ ግን ሰይጣን ስልቱን ይቀይራል። ያን ጊዜ ደግሞ 'እፍረትንና ተስፋ መቁረጥን' ያመጣብሃል። 'እንዲህ ያለ ኃጢአት ሠርተህ እንዴት እግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ? አንተ ረክሰሃል፣ ንስሐህ ተቀባይነት የለውም፣ ሞትህም ለገሃነም ነው' እያለ በልብህ ይጮኻል።አንተ ግን የሰይጣንን ተንኮል አሸንፈው። ኃጢአት ልትሠራ ስትል 'እፈር'፤ ንስሐ ልትገባ ስትል ግን 'ደፋር ሁን'። ሰይጣን ግን ኃጢአት ስትሠራ እንድትደፍር፣ ንስሐ ስትገባ ደግሞ እንድታፍር ያደርግሃል። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ኃጢአት ቍስል ነው፣ ንስሐ ግን መድኃኒት ነው። ቍስል ያለው ሰው ቍስሉን ለሐኪም ለማሳየት አያፍርም፤ ካሳየው ይፈወሳል፣ ከሸሸገው ግን ይበሰብሳል። አንተም ኃጢአትህን ለእግዚአብሔር ንገረው፤ እርሱም ይፈውስሃል።(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ ባስተማረበት ድርሳኑ)
    11,30017236Открыть в Telegram