gram news
Аватар канала በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

@betremariyamabebaw

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

ПроектыENРелигия

49,200подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    23 сент., 14:17

    🍎🍎ቈላስይስ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ክፍል 2🍎🍎🍊፩. ፍጹም መለኮቱ በከዊን የተዋሐደው ይላል። ፍጹም ብሎ በከዊን ሲል አይጋጭም?መልስ፦ አይጋጭም። የእያንዳንዱ አካላት ከሌሎች ኩነታት ጋር የሚገናዘብ ከዊን አላቸው። ይህ የሦስቱ ኩነታት ማለትም የቃል፣ የልብ፣ የእስትንፋስ መገናዘብም ባሕርይ ይባላል። አንዷ ባሕርይ ሦስት ከዊን አላት። ወይም ደግሞ የሦስቱ ኩነታት መገናዘብ አንድ ባሕርይ ይባላል። ሊቅም ዘውእቱ አሐዱ ብርሃን ዘይሠርቅ እምኔሁ ሥላሴ ብሎ የአንዱ ባሕርይ ሦስት ኩነታት እንዳሉት ገልጿል። መተርጉማን አንድም እምኔሁ ለሥላሴ ብለው ከሦስትነት የሚገኝ አንድ ብርሃን ብለውታል። ከሦስቱ ኩነታት በተለየ ባልተለየ ቃል ሰው ሆነ ማለታችን ፍጹምነቱን አይቀንሰውም። ሰው ማር ሲበላ ለምላሱ የሚታወቀው ጣዕሙ ብቻ ስለሆነ ተብሎ አካለ ማርንም፣ ቀለመ ማርን አልወሰደም አያሰኘውምና። ከዚያ ይልቅ ማር በጣዕሙ በምላስ በተለየ ታወቀ ያሰኛል እንጂ።🍊፪. ቈላ.2፥8 ላይ “በፍልስፍናና በከንቱ ማታለያ እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ” ሲል ሁሉንም ፍልስፍና ይቃወማልን ወይስ ክርስቶስን የሚቃረን ፍልስፍናን ብቻ ነው?መልስ፦ ፍልስፍና ብዙ ዓይነት ነው። ሐዋርያው ከዚህ የተቃወመው ፍልስፍና በልብ ወለድ የተመሠረተ እምነትን ነው። እምነት የግድ ከእግዚአብሔር መገለጥ የተገኘ መሆን አለበት። ሰው ተመራምሮ የሚደርስበት፣ የሰው ሥራ ከሆነ ግን ከንቱ ፍልስፍና ያሰኘዋል። በመገለጥ ላይ የተመሠረተ እምነትን መከተል ደግሞ መንፈሳዊ ፍልስፍና ይባላል። ይህንን መጽሐፈ መነኰሳትም ተፈልስፎ መንፈሳዊ በማለት ይገልጸዋል። ሌሎች እምነትን የማይሸረሽሩ ፍልስፍናዎችና ሥጋዊ ወይም መንፈሳዊ በቍዔት ያላቸው ፍልስፍናዎችን ሐዋርያው አልተቃወመም።🍊፫. ቈላ.2፥12 ጥምቀት ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ጋር እንዴት ይያያዛል?መልስ፦ ይህ አገላለጽ ምሳሌያዊ ነው። በጥምቀት ወደ ባሕር ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እንደምንል ሁሉ ክርስቶስም ሦስት ቀን በመቃብር ኖሯልና ጥምቀቱ በመቃብር ይመሰላል። ተጠምቀን መውጣታችን በትንሣኤው ይመሰላል። ሰው ሲጠመቅ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሰውነት ወደ ልጅነት ከፍ ይላል።🍊፬. ወደምሰሰ ለነ መጽሐፈ ዕዳነ ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ ይህ በሁለት ይተረጎማል። አንደኛው በትርጓሜ ትውፊት እንደሚነገረው አዳምና ሔዋን ስመ ግብርናት ጽፈው [የባርነት ውል የያዘ ደብዳቤን] ለዲያብሎስ ሰጥተውት ነበር። ዲያብሎስም ያንን በሲኦልና በዮርዳኖስ ጥሎት ነበር። በዮርዳኖስ ያለውን ክርስቶስ እንደሰውነቱ ተረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶታል። በሲኦል የነበረውን በአካለ ነፍስ በዕለተ ዓርብ ወርዶ አጥፍቶታል የሚል ነው። ሁለተኛው ትርጓሜ ደግሞ የዕዳ ደብዳቤ ሲቀደድ ነጻ እንደምንሆን ሁሉ ክርስቶስም ፍዳችንን አጠፋ ለማለት ነው። መጽሐፍ የሚለው ፍዳን መርገምን ነው።🍊፭. ቈላ.2፥18 በመታለልና ራስን ዝቅ በማድረግ ለመላእክት አምልኮ ትታዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአላየውም በከንቱ የሥጋው ምክር እየተመካ የሚያሰንፋችሁ አይኑር። ለመላእክት አምልኮ ትታዘዙ ዘንድ ወድዶ ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ መላእክት የሚለው በሁለት መልኩ ይተረጎማል። አንደኛው መንፈሳውያን መላእክት ሲሆን ሁለተኛው አለቆች ማለት ነው። መተርጉማነ ኢትዮጵያ በሁለተኛው ተርጉመውታል። ሰው ምን ጊዜም ቢሆን በባሕርዩ ፈጥሮ የሚገዛ እግዚአብሔር ስለሆነ ለእግዚአብሔር ባሕርያዊ መገዛት ይገባዋል። ፍጡራንን ማምለክና ለፍጡራን መገዛት አይገባውም ማለት ነው። ሐሳቡ በዋናነት በኦሪት ሥርዓት አትመሩ ማለት ነው።🍊፮. ቈላ.2፥11 የሥጋንም ሰውነት በመገፈፍ፥ በክርስቶስ መገረዝ፥ በእጅ ባልተደረገ መገረዝ በእርሱ ሁናችሁ ደግሞ ተገረዛችሁ ይላል። ምን ማለት ነው?መልስ፦ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን የማምለክ ምልክት የነበረው ሥጋን መገረዝ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ትክክለኛው ግዝረት ኃጢአትን ከሰውነት ማስወገድ ነው ማለት ነው። ይህም በክርስቶስ አምነን በመጠመቅና በሕጉ በመኖር ስለሚፈጸም በክርስቶስ መገረዝ ተብሏል።🍊፯. እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ እነዚህ ነገሮች የኦሪት ሥርዓቶች ናቸው። ስለሆነም የኦሪት ሥርዓት አልፎ በሐዲስ በወንጌል ስለተተካ የኦሪትን ሥርዓት ካልጠበቃችሁ ብሎ ማንም አይፍረድባችሁ በሕገ ወንጌል ጸንታችሁ ኑሩ ማለቱ ነው።© በትረ ማርያም አበባው ካሣየዩቲይብ ቻናሌ ንሕነ ዘክርስቶስ We belong to Christ ወይም ሊንኩ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=GWc54SKTPg4RBlfNየፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw ወይም ሊንኩ https://www.facebook.com/betremariam.abebaw ነው።
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    22 сент., 16:45

    🌿🌿የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል 6🌿🌿 🍒ወደ ቈላስይስ ምዕራፍ 2🍒 ከቁጥር 1-8፦ ቅዱስ ጳውሎስ ስለምእመናን እንደሚያስብ ተናግሯል። በነገር ማታለል የሚያስታችሁ አይኑር። በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳመናችሁ በዚያው ጸንታችሁ ኑሩ። ወተሣረሩ ወተሐነጹ ቦቱ። በእርሱ በማመን ጸንታችሁ ለእርሱ ማደሪያ ሁኑ።ከቁጥር 9-23፦ [ክርስቶስ] ዘላዕሌሁ ኀደረ ኵሉ መለኮቱ በሥጋ ሰብእ። ፍጹም መለኮቱ በከዊን የተዋሐደው። በክርስቶስ በማመን ጸንታችሁ ኑሩ። እስመ ውእቱ ርእሱ ለኵሉ መኰንን ወለኵሉ መንግሥት። ገዢ ነኝ ለሚል ሰው ሁሉ ገዢ እርሱ ነውና። ንጉሥ ነኝ ለሚል ሁሉ ንጉሥ እርሱ ነውና። ወተቀበርክሙ ምስሌሁ በጥምቀት። ከእርሱ ጋራ ተዋሕዶ ለመኖር በጥምቀት መቃብርነት የተቀበራችሁበት። ወባቲ ተንሣእክሙ ምስሌሁ በሃይማኖት። ከእርሱ ጋር ተዋሕዶ ለመኖር በሃይማኖት ትንሣኤ ልቡና የተነሣችሁበት። ክርስቶስ ኃጢአታችሁን ይቅር እንዳላችሁ ዕወቁ። ወደምሰሰ ለነ መጽሐፈ ዕዳነ። ፍዳችንን አጠፋልን። ክርስቶስ ዲያብሎስን በመስቀሉ ቸነከረው። ኦሪት ለወንጌል አምሳል ናት። 🍋Ancient Christian Commentary🍋 Christ is the way to the father; by no means may angles play that role [John Chrysostom]. True religion consists of these two elements: pious doctrines and virtuous actions. All person will rise through the resurrection of Christ from the dead.
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    21 сент., 14:24

    🌴🌴ቈላስይስ ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ክፍል 1🌴🌴🍊፩. በቈላስይስ ለሚኖሩ ቅዱሳን እና በክርስቶስ ለታመኑ ወንድሞች፣ ከአባታችን እግዚአብሔር እና ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይሁን ይላል (ቈላ.1፥2)። ቅዱሳን ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ ቅዱሳን የሚላቸው ምእመናንን ነው። ምእመን ማለት ኀሊናው መልካም የሆነ [ሠናየ ኅሊና] ማለት ነው [ዮሐንስ አፈወርቅ]። ከሌሎች ሰዎች ተለይተው በክርስቶስ አምነው በክርስቶስ መንገድ ስለሚሄዱ ቅዱሳን ይባላሉ።🍊፪. ቈላ.1፥15 እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ ምሳሌ ሁለት ዓይነት ነው። አንጻራዊ መመሳሰልን የሚገልጽና ፍጹም መመሳሰልን የሚገልጹ ናቸው። አንጻራዊ መመሳሰል በራሱ በሁለት ይከፈላል። አንደኛው ለምሳሌ ፎቷችን እኛን ይመስላል። ነገር ግን ፎቶ አይናገርም፣ አያይም፣ አይሰማም፣ አይንቀሳቀስም። ሁለተኛው ልጅ ወላጅ አባቱን ይመስላል። በዚህ ጊዜም መመሳሰሉ አንጻራዊ ነው። ልጅ በኋላ የሚመጣ አባት ቀድሞ የነበረ ነው። የመልክ ልዩነትም አለ። ሦስተኛው መመሳሰል ፍጹም መመሳሰል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ ምሳሌ ነው ሲባል በመልክም፣ በዘመንም፣ በመጠንም፣ በርቀትም፣ በችሎታም፣ በፈቃድም፣ በጠቅላላው በሁሉም ነገር ተመሳሳይ ስለሆነ ነው።🍊፫. ቈላ.1፥24 በአሁን ጊዜ በመከራዬ ምክንያት ስለ እናንተ ደስ ይለኛል። በአካሉም በሥጋዬ በክርስቶስ የተጋለጠውን መከራ እፈጽማለሁ። ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ ሐዋርያት ክርስቶስ መከራ መቀበሉን መሠረት አድርገው እነርሱም ስለእውነት መከራን
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    19 сент., 18:15

    🍒🍒የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል 5🍒🍒 🍃ወደ ቈላስይስ🍃 ቈላስይስ በሶርያ አጠገብና በፊልጵስዩስ አጠገብ ያለች ሀገር ናት። በውስጧም አይሁድና ዮናናውያን ይኖሩባት ነበር። በኤጳፍራስና በአክርጶስ ስብከት አምነዋል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቢጽ ሐሳውያን ወንጌል እንበለ ኦሪት፣ ጥምቀት እንበለ ግዝረት አይጠቅምም፤ እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ንጹሕ ያልሆነ ርኩስ ነገር ሁሉ እንዳይነኩ አዘዟቸው። ጳውሎስ ይህንን ሰምቶ ለቈላስይስ ሰዎች መልእክት ላከላቸው። በሮም በመጀመሪያ እስራቱ ጊዜ ጽፎ በቲኪቆስ እጅ ላከላቸው። 🌱ምዕራፍ 1🌱 ከቁጥር 3-14፦ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አባቱን እግዚአብሔር አብን እናመሰግነዋለን። በፍጹም ደስታ ሆናችሁ ቅዱሳን ለሚወርሷት ለመንግሥተ ሰማያት እንድንበቃ ያደረገንን እግዚአብሔር አብን አመስግኑት። በዕውቀት ከድንቁርና ከመገዛት በወንጌል ከኦሪት ከመገዛት በልጅነት ለሰይጣን ከመገዛት ያዳነን ልጁ ወዳጁ ነው።ከቁጥር 15-19፦ [ኢየሱስ ክርስቶስ] ዘውእቱ አምሳሊሁ ለእግዚአብሔር ዘኢያስተርኢ። የማይመረመር እግዚአብሔርን በመልክ የሚመስለው በባሕርይ የሚተካከለው። በሰማይም በምድርም ያለውን የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠረበት ነው። ሁሉ በእርሱ ሥልጣን የተፈጠረበት ነው። ወውእቱ ህልው እምቅድመ ኵሉ። ከሁሉ አስቀድሞ የነበረ ነው። ወውእቱ ርእሳ ለቤተክርስቲያን። የምእመን ገዥዋ ጌታዋ የሆነ እርሱ ነው። በኵር እርሱ አስቀድሞ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና።ከቁጥር 20፦ ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ ለዘበሰማይ ወለዘበምድር። ተሰቅሎ ባፈሰሰው ደሙ በሰማይ ያሉ መላእክትንና
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    19 сент., 17:48

    🌺🌺ቲቶ ምዕራፍ 3 ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው🌺🌺🍊፩. ቲቶ 3፥15 በሃይማኖት የሚወደንን ሁሉ ሰላም በል ሲል ምን ለማለት ነው? በሃይማኖት ለማይወዱት ወይም ለማይመስሉትስ?መልስ፦ ቅድሚያ በሃይማኖት የሚመስልን ሰላም ማለት ይገባል። ቀጥሎ ሌላውንም ሰላም ማለት ይገባል። ጳውሎስ መልእክት የሚልክ ነውና መልእክቱን የላከላቸው ደግሞ ለጊዜው ላመኑ ሰዎች ስለሆነ በሃይማኖት የሚወደንን ሁሉ ሰላም በል ብሏል።🍊፪. ቲቶ 3፥3 እስመ ንሕነሂ ትካት አበድነ ዘእንበለ አእምሮ (እኛም ቀድሞ ባለውቀት ሰንፈን ነበር) ትካት ብሎ የዘረዘራቸው የአዳም እና የሔዋንን ነው ወይስ እርሱ እስካመነ ድረስ ያደረጋቸው ነው?መልስ፦ ለሁሉም ይሆናል። በተጨማሪ ለአሕዛብ ይሆናል። ራሱ ጳውሎስም ቀድሞ ክርስቲያኖችን ያሳድድ ስለነበረ ይህንን ዕበድ ብሎታል። አሕዛብም ቀድመው ጣዖት በማምለክ ታላቅ ስንፍና ውስጥ ስለነበረ ዕበድ ተብሏል።© በትረ ማርያም አበባው ካሣየዩቲይብ ቻናሌ ንሕነ ዘክርስቶስ We belong to Christ ወይም ሊንኩ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=GWc54SKTPg4RBlfNየፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw ወይም ሊንኩ https://www.facebook.com/betremariam.abebaw ነው።
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    17 сент., 06:00изменён

    🌾🌾የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል 4🌾🌾 🎋ቲቶ ምዕራፍ 3🎋 ከቁጥር 1-8፦ በበጎ ምግባር ሁሉ ጸንተው ይታዘዙ ዘንድ ዲያቆናትን ቀሳውስትን ምከራቸው። እንዳይበሳጩ፣ እንዳይጣሉ፣ እንዳይከራከሩ፣ የዋሃንና መሓርያን እንዲሆኑ ምከራቸው። እኛም በድለን ነበር። ቸር ሰው ወዳጅ የሚሆን እግዚአብሔር በቸርነት በተገለጠ ጊዜ ግን በሙያችን በጉልበታችን ሳይሆን በቸርነቱ ከዚህ ሁሉ በጥምቀት አዳነን።ከቁጥር 9-15፦ የጸብ የክርክርን ነገር፣ የስንፍናን ነገር፣ የተረትን ነገር፣ የዋዛ ፈዛዛ ነገርን የሚናገሩትን ተለያቸው። ከንቱ ነውና። አይረባም አይጠቅምምና። ተከራካሪን ሰው አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜ ከረታኸው በኋላ አልመለስም ቢል ተወው። ሌሎችን እንዳያስት አስታውቅበት። ምእመናን በጎውን ትምህርት ይማሩ። 🥀Ancient Christian Commentary🥀 If what the emperor or leader orders is good, follow the will of him who orders. But if it is evil and is contrary to God, answer to it from the words of the Acts of the Apostles, "it is more important to obey God than men [Jerome]. Every kind of help comes to our souls through Christ [Basil the great]. It is from his side, that Christ formed his church, just as he formed Eve from the side of Adam. 🌹Fr. Tadros Y.
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    15 сент., 12:03

    🌻🌻የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል 3🌻🌻 🍎ወደ ቲቶ ምዕራፍ 2🍎 ከቁጥር 1-8፦ ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ሥራውን እየሠራህ አስተምር። ሽማግሌዎች ከዝሙት ንጹሓን፣ ከንዋመ ሐኬት የነቁ፣ ጠቢባን፣ ሃይማኖትን የማይጠራጠሩ፣ ፍቅርን የያዙ፣ የሚያስተውሉ፣ የሚታገሡ ይሁኑ። ባልቴቶች ንጹሓት፣ ነገር የማያዋስዱ፣ ለመጠጥ የማይገዙ፣ የማይሰክሩ፣ በጎውን ትምህርት ለሕፃናቱ ለሴቶቹ የሚያስተምሩ ይሁኑ። ወጣት ሴቶችም ባሎቻቸውን ልጆቻቸውን ይውደዱ፣ ከሌላ አይሂዱባቸው፣ በጎውን ሁሉ ይሥሩ፣ ቤተሰቦቻቸውን በሚገባ ያስተዳድሩ፣ ለባሎቻቸው ይገዙ። ወጣት ወንዶችም ሰውነታቸውን ከኃጢአት ይለዩ ዘንድ ምከራቸው አስተምራቸው፣ በበጎው ሥራ ሁሉ አብነት ሁናቸው። የምትናገረው ነገር የምታስተምረው ትምህርት በንጽሕና ይሁን። ዲያብሎስ በእኛ ላይ የሚናገረው ክፉ ነገር እንዳያገኝ እንሁን።ከቁጥር 9-15፦ ቤተሰቦች ለጌቶቻቸው ይገዙ በሥራው ሁሉም ደስ ያሰኟቸው። በንጽሕና ሆነው ግብራቸውን ያከናውኑ። ወንጌል ፍትወተ ዓለምንና ኃጢአትን እንለያት ዘንድ ታስተምረናለች። በዚህ ዓለም በፍቅር፣ በንጽሕና፣ በጽድቅ እንኖር ዘንድ ታስተምረናለች። ለእርሱ ማደሪያ የበቃን ሐዲስ ልጆች ያደርገን ዘንድና ከኃጢአት ይለየን ዘንድ ክርስቶስ ራሱን ስለእኛ አሳልፎ ለሕማም ለሞት ሰጠ። ትሕትናን ይዘህ ምከር አስተምር ዝለፍ። 🌺Ancient Christian Commentary🌺 When the soul is unclean, it thinks all things unclean. This is the chief point of all that is good in
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    15 сент., 08:20

    🌼🌼 ቲቶ ምዕራፍ 1 ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው🌼🌼🍊፩. ቲቶ.1፥1 ላይ «በእግዚአብሔር ለተመረጡት» የሚለውን ጥቅስ በመያዝ አንዳንዶች «መዳን እግዚአብሔር አስቀድሞ ለወሰናቸውና ለመረጣቸው የተወሰኑ ሰዎች ብቻ ነው፤ እግዚአብሔር ሌሎቹን ትቶ ጥቂቶችን ብቻ ነው የሚያድነው» ለሚለው የቅድመ-ውሳኔ (Predestination) ትምህርታቸው እንደ ማስረጃ ሲጠቀሙበት ይታያሉ። ይህ ጥቅስ በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት እንዴት ይታያል?መልስ፦ እግዚአብሔር የሚመርጥ በነጻ ፈቃዳችን በሠራነው ወይም በምንሠራው መልካም ሥራ መሠረትነት ነው። ስለዚህ በእግዚአብሔር ለተመረጡት የሚለው በአምላካዊ ዕውቀቱ ነጻ ፈቃዳቸውን ተጠቅመው መልካም የሚሠሩትን መምረጡን የሚያመለክት ነው። እንጂ እግዚአብሔር ያለነጻ ፈቃዳቸው አስገድዶ ማጽደቅ ወይም መፍረዱን የሚያመለክት አይደለም።🍊፪. ጳጳስ የአንዲት ሚስት ባል ይሁን የሚለው እንዴት ነው?መልስ፦ በሐዋርያት ዘመንና ከዚያም በኋላ ለጥቂት ዘመናት ጳጳስ ያገባ እንዲሆን ሥርዓት ተሠርቶ ስለነበር የአንዲት ሚስት ባል ይሁን ተብሏል። የኋላ ሊቃውንት ራሱ ጳውሎስ ካገባ ይልቅ ያላገባ የበለጠ እግዚአብሔርን ለማገልገል እንደሚመቼው ስለገለጸ ድንግል እንዲሆን ሥርዓት ሠርተዋል (1ኛ ቆሮ.7፥32-35)።🍊፫. ቲቶ 1፥11 ላይ "ቤቶችን ሁሉ ስለሚገለብጡ" ሲል ምን ማለት ነው?መልስ፦ የተገለበጠ ቤት በውስጡ ያለውን ንብረት መጠበቅ እንደማይችልና ሁሉ እንደሚዘርፈው የሰውን መልካም ልብ የሚለውጡም በዚህ ምሳሌነት ተነግረዋል። ቤቶች ያላቸው ልቦችን ነው።🍊፬. "ተረት
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    13 сент., 14:21изменён

    🍇🍇የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል2🍇🍇 🌼ወደ ቲቶ🌼 ጳውሎስ ቀድሞ በቀርጤስ አስተምሮ ብዙዎችን አሳምኗል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሌላ ቦታ ሲሔድ እንዲያስተምራቸው ቲቶን ትቶላቸው ሄዷል። ቲቶ የቀርጤስ ሰው ነው። እናቱም አባቱም አረማውያን ናቸው። ጳውሎስ የቀርጤስ ሰዎች የሠሩትን ክፋት ሁሉ ነገረው። እንዲገሥጻቸውና ካህናትን እንዲሾምላቸውና ካህናት ሊያደርጉት የሚገባውንም ለቲቶ ነገረው። ጳውሎስ ይህንን መልእክት የጻፈለት ናቆጽል በሚባል ቦታ ነው። አርጣማ በሚባል ደቀመዝሙሩ አማካኝነት ላከለት። ቲቶን የቀርጤስ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሹሞታል። 🍍ምዕራፍ ፩🍍 መልእክቱን የላከ፦ ጳውሎስ የእግዚአብሔር አገልጋይ፣ የኢየሱስ ሐዋርያ መሆኑን ገልጿል። መልእክቱ የተላከለት= ቲቶ ከቁጥር 6-14፦ ጳጳስ አንዲት ሚስት ያለችው፣ በክፉ ነገር የማያነሡት፣ ልጆቹን በበጎ ምግባር ያሳደገ፣ ፊት አይቶ የማያዳላ፣ ቁጡ ያልሆነ፣ ገራም፣ ወይን አብዝቶ የማይጠጣ፣ ኃላፊ ገንዘብን የማይወድ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ግብሩ ያማረ፣ ሰውነቱን ከኃጢአት የለየ፣ እውነተኛ፣ ቸር፣ ቅን፣ ትዕግሥት ያለው፣ ነገር አላፊ ልበ ሰፊ፣ የሃይማኖትን ነገር የተማረ፣ በወንጌል ትምህርት መምከር ማስተማር የሚችል፣ የሚከራከሩትን የሚረታ፣ቁጥር 15፦ የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ለንጹሓን ንጹሕ ነው። ላላመኑ ሰዎች ግን ንጹሕ ነው የሚሉት የላቸውም። ልቡናቸው ርኩስ ነውና።🍋Ancient Christian Commentary🍋 Nothing is impossible to God except to lie [Clement the Rome]. Commandments are
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    12 сент., 10:19

    🌴🌴 የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወደ ፊልሞና ላይ የተጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው🌴🌴🍊፩. ፊልሞ.1፥2 በቤትህ ላለች ቤተክርስቲያን የተባለች ማን ናት?መልስ፦ ፊልሞና ባለጸጋ እንደመሆኑ ከቤቱ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ። ብዙዎቹ ደግሞ እንደእርሱ በክርስቶስ አምነው የሚኖሩ ነበሩ። የምእመናን ሕብረት ቤተክርስቲያን ይባላል። ስለዚህ በቤትህ ለሚኖሩ ምእመናን ሰላም እላለሁ ለማለት የተነገረ ነው።🍊፪. "ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይኹን" ይላል (ፊልሞ.1፥3)። ከመንፈስ ቅዱስም የሚል ለምን አልተካተተም?መልስ፦ እግዚአብሔር በሚለው ስም አብም፣ ወልድም፣ መንፈስ ቅዱስም ይጠሩበታል። ስለዚህ እግዚአብሔር የሚለው አብንም መንፈስ ቅዱስንም የሚያመለክት ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ አልተካተተም አያሰኝም። ሌላውና ዋናው መሠረታዊ ጉዳይ ግን ሦስቱ አካላት በግብረ ባሕርይ አንድ ስለሆኑ በግብረ ባሕርይ ሁለቱ ብቻ የሚጠቀሱበት ጊዜ አለ፣ ሦስቱም የሚጠቀሱበት ጊዜ አለ፣ አንዱ ብቻ የሚጠቀስበት ጊዜም አለ። የሁሉም ግን ምስጢሩ አንድ ነው። አንዱ ቢጠቀስም ሁለቱንም የሚመለከት ነው። ሁለቱ ቢጠቀሱም አንዱንም የሚመለከት ነው (1ኛ ቆሮ.3፥16፤ 1ኛ ቆሮ.6፥11፤ ማቴ.28፥19)።🍊፫. ከእንግሊዘኛው commentary አናሲሞን (ለሰው ልጅ) ቅዱስ ጳውሎስን እንደ ክርስቶስ አማላጅነት እና ፊልሞናን እንደ አብ አርገውት የተረጎሙት አሉ። እንዴት ነው?መልስ፦ ብዙ ጊዜ ምሳሌ ሲነገር የተወሰነ ጉዳይን ለመግለጽ ይነገራል እንጂ ሙሉ ነገርን አይገልጽም። በመሆኑም ምሳሌ ዘየሐጽጽ
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    12 сент., 08:57изменён

    እስኪ ደግሞ "ሰትየ"ን እንግሠሠው። ሰትየ=ጠጣ [Drink/Drank] ይሰቲ=ይጠጣል [will drink] ይስተይ=ይጠጣ ዘንድ [to drink] ይስተይ=ይጠጣ [let him drink] ሰትይ/ሰትዮት=መጠጣት [drinking] ስቱይ/ሰታዪ=የጠጣ [drinker/Drunken] ስቱያን/ሰታይያን=የጠጡ [drinkers] ስትይት/ስቲት/ሰታዪት=የጠጣች ስቱያት/ሰታይያት=የጠጡ [ሴ] ሰትዮ=ጠጥቶ [having drunk] መስትይ/መስተስትይ/መስተሳትይ [ባ.ቅ] መስትያን/መስተስትያን/መስተሳትያን [በብዙ] መስትይት/መስተስትይት/መስተሳትይት [ለሴት] መስትያት/መስተስትያት/መስተሳትያት [ለብዙ] ሰተይት=መድበል=የጠጡ ስታይ=ዘመድ ዘር=መጠጥ ስቴ=ጥሬ ዘር=መጠጥ ምስታይ=ባዕድ ዘር=መጠጫ ስቴት=ሳቢ ዘር=መጠጣት
    Иллюстрация к посту канала በትረማርያም አበባው Betremariam AbebawИллюстрация к посту канала በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    12 сент., 03:38

    🍒የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ክፍል ፩🍒 🌻ወደ ፊልሞና🌻 መልእክቱን የላከው= ቅዱስ ጳውሎስ መልእክቱ የተላከለት= ፊልሞና የሚባል ሰው መልእክቱ የተጻፈበት=ሮም በመጀመሪያ እስራቱ ክታብ ወሳጅ=አናሲሞስ መልእክቱ የተላከበት ምክንያት= ለፊልሞና አናስሞስ የሚባል አገልጋይ ነበረው። ፊልሞና ከነቤተሰቡ በጳውሎስ ስብከት ያመነ ቢሆንም ይህ አናሲሞስ ግን ቀድሞ አረማዊ ነበረ። ፊልሞናን ሲያገለግለው ገንዘብ ጠፋበትና ከጌታዬ ማን ባስታረቀኝ እያለ ሲያስብ ጳውሎስን አስቦ ጳውሎስ ወደታሰረበት እስር ቤት ሄዷል። ጳውሎስም አናሲሞስን አስተምሮ አጥምቆታል። ካጠመቀው በኋላ ወደ ፊልሞና አናሲሞስን ይቅር እንዲለው ይህንን መልእክት ልኮለታል።ቁጥር 1፦ ላይ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስ ይላል። [ብዙዎች ወንጀል ሠርተው ይታሰራሉ። አንዳንዶች ግን ሰላም የሆነውን የክርስቶስን ወንጌል በማስተማራቸው ይታሰራሉ። የጳውሎስ መታሰር ወንጀል ሠርቶ የተደረገ ስላልሆነ የኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ተብሏል። ስለእውነት የሚታሰሩ ሰዎች ሁሉ የክርስቶስ እስረኛ ይባላሉ]። ቀጥሎ ከወንድማችን ከጢሞቴዎስም የተላከች ይላል። ጢሞቴዎስ ጳውሎስን ረድቶ ጽፎ ወይም ከጳውሎስ ጋር ጽፎ አይደለም። ስለትሕትና ከጢሞቴዎስም አለ እንጂ። ቀጥሎ መልእክቱ የተላከ ለፊልሞናና ለፊልሞና ሚስት አብፍምያ እንዲሁም ለፊልሞና ልጅ ለአክርጳ የተላከ መሆኑን ይገልጽልናል። ቅዱስ ጳውሎስ ስለፊልሞና ሲናገር ወንጌልን በማስተማር ከእኛ ጋር አንድ የሚሆን የምንወደው ወንድማችን ብሎታል። አብፍምያን እኅታችን ብሏታል። [ይህ የሚነግረን በሃይማኖት አንድ የሆኑ
    Telegramበትረማርያም አበባው Betremariam Abebawአቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር
  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53

  • በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

    10 сент., 16:53