gram news
Аватар канала መጽሐፍ ቤት Bookstores

መጽሐፍ ቤት Bookstores

@bookstoresaz

Ask any materials @Books_storebot @Books_storebot

ПроектыENКниги

3,970подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    19 сент., 12:03

    ሲጃራ ለወሲብ ሊቀሰቅሰኝ ይገባ ነበር? ሲጃራ የያዘ ጣቱ ጭኔ ስር እንዲገባ ተመኘሁ!ሰውዬው ካኪ ሱሪ እና ጥቁር ሸሚዝ ለብሷል። መጀመሪያ የሳበኝ ልብሱ ነበር። ከዚያ ጠይም ፊቱ፣ ከዚያ ሽበቱ። በተለይ የሽበቱ ንጣት...አወይ ሽበቱ... አወይ የፀጉሩ ንጣት...ነጫጭ ፀጉሩ የረሳሁትን አስታወሰኝ።ሲጃራ አወጣ። በከንፈሩ መካከል አድርጎ አቀጣጠለው። የእሳቱ ብርሃን ለቅጽበት ፊቱን አበራው፤ ከዚያም ጢሱ የፊቱን ከፊል ሸፈነው።የሲጃራው ሽታ እንደ መልካም መዓዛ አወደኝ።የሲጃራውን ጢስ በአይኔ ለመከተል ሞከርኩ። ሰውነቴ በድንገት ራሱን ከአእምሮዬ ለይቶ የራሱን ምላሽ ሰጠ። ስስ ሙቀት ተሰማኝ።አፈርኩ።ሰውዬው አላየኝም። እኔ ግን እሱን ከማየት ወደ መመኘት ተሸጋገርኩ። እድሜው ሃምሳ ይሆናል። የእኔን እጥፍ ዕድሜ ኖሯል።
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    6 сент., 20:05

    ታስሬ ነበር💔የሚያዉቁኝ ሰዎች ሁሉ "ታስሮ ስላልጠየቅነው ነው የተቀየረብን" ይላሉ::እውነታቸውን ነው ተቀይሬያለሁ....... ተቀይሜያቸው ግን አይመስለኝምህይወቴ ውክብክብ ያለ ነበር ። የጓደኞቼ ብዛት የትየለሌ የሚባል አይነት ነው። ስልክ ሳወራ ነው የምውለው ።ሁሉም የማወራው ስልክ አንገብጋቢ፣ አስፈላጊ ይመስለኝ ነበር ....የሚሰማኝን የምነገራቸው፣ የሚሰማቸውን የሚነግሩኝ ፣ ተባበሩኝ የምላቸው ፣ ተባበረኝ የሚሉኝ ፣ ቀልድ የምናወራ፣ በርታ በርታ የምንባባል፣ አጀንዳዎችን የምንተነትን ፣ የማባብላቸው ፣ ያልፋል የሚሉኝ ሰዎች ጋ ስደዋወል የምውል ሰው ነበርኩ ።እቅድ በየቀኑ አወጣለሁ......
    1,170981Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    4 сент., 10:43

    ርዕስ:-አንድሮ ሜዳ 👤ደራሲ:-ሮዳስ ታደሰ &ጌትነት ፈለቀ 📅አ.ም:-2011 📑ገፅ:-1-59Share and join 👇👇👇👇👇👇 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👆👆👆👆👆👆
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    2 сент., 15:28

    ሚስቱን የገደለው ማን እንደሆነ ሁሉም ሰው ያውቃል፤ የማያውቀው ባሏ ብቻ ነበር። ሚስቱ በሞተች ሌሊት ማንም ሌላ ገዳይ አልፈልገም፤ ሁሉም ጣቶች ወደ እርሱ ተዘረጉ።"እሱ ነው የገ^ደላት። ከእሱ ሌላ ማንም ሊሆን አይችልም" አሉ። በአንድ ለሊት ባልነቱ ተሰርዞ የሚስት ገዳይ ሆነ።ባል የእስር ቤቱን ቀዝቃዛ ግድግዳ ተደግፎ፣ "እኔ አልገ^ደልኳትም" አለ ለራሱ። ከአንደበቱ የወጣው ቃል ከግድግዳው እየተላተመ ወደእርሱ የሚመለስ መሰለው።"ሚስቱን እየደበደበ ሲያሰቃያት እናውቃለን" ይላሉ ጎረቤቶች"እኔ አልገደልኳትም"ማንም አልሰማውም። የሰሙትም ሊያምኑት አልፈለጉም። የሟች ባል ሰካራም ነበር፣ ከነብሱ ይልቅ ቁማርን የሚያፈቅር ቆማሪ ነበር። ቁጣ ሲያሳብደው የሚስቱ ፊት ላይ ቡጢ ያሳርፋል።ጎረቤቶቿ ከባሏ ቡጢ በየጊዜው ያድኗት ነበር።"ለምን አትፈቺውም?" ይሏታል በዱላ የደቀቀ ሰውነቷን እያዩ
    1,2109332Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    24 авг., 04:24

    ባለትዳር ሴት አባለግኩ፤ "አወጣሻለሁ" አልኳት። እንደተናገርኩት አደረግኩ።እንዳሸነፍኳት ተሰምቶኝ ነበር። ከቤቴ ወጥታ በሩን ስትዘጋ የድሉ ድምፅ አብሮ ጠፋ።ለጥቂት ቆሜ ቀረሁ። በቤቱ ውስጥ የሽቶ መዓዛ ትታ ሄዳለች።አልጋው ላይ የተጨማደደውን ሸሚዜን አየሁ፤ ወለሉ ላይ የፀጉሯ አንድ ዘለላ ወድቋል።አሸንፌያታለሁ።ድሉ ደስ ሊያሰኝ ይገባ ነበር። ነገር ግን ውስጤ ባዶ ሆነመስታወቱ ፊት ቆምኩ። መስታወቱን እያየሁ አባቴን አሰብኩ።አባቴ እናቴ ከከዳችው በኋላ ሌላ ሰው ሆነ፤ አዘውትሮ መስታወት ይመለከት ጀመረ።እናቴ ክፉ ናት!... ከአባቴ ጓደኛጋ አንሶላ በመጋፈፍ አባቴን ሰበረችው!... ቤታችን በአንድ ቀን አልፈረሰም። በቀስታ ዘመመ፣ በዝግታ ወደቀ። ቤታችን ፈረሰ፣ የአባቴ አለም ተገንዶሶ ወደቀ።
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    24 авг., 04:23

    እርቃኔን ሻወር ቤት አይኖቼን ጨፍኜ ቆሜያለሁ። ውሃው ከጸጉሬ ጫፍ ተንሸራቶ ጡቴን ተሻግሮ ይወርዳል።... ሰውነቴን እየታጠብኩ ሃጢያቴን አስባለሁ። የሚወርደው ውሃ የውስጤን ቆሻሻ እንዲያፀዳ እመኛለሁ። .... ዓይኖቼን ጠረግሁ። ከውሃ የተቀላቀለ እንባ ከአይኔ አበስኩ። "እንዴት ይህ ሁሉ ሆነ? ባሌን እወደደው አይደል?" በቀላሉ አመነዘርኩ? ከባላቸው ውጭ ለሌላ ወንድ የሚሽኮረመሙ ሴቶችን እፀየፍ
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    23 авг., 16:19

    እርቃኔን ሻወር ቤት አይኖቼን ጨፍኜ ቆሜያለሁ። ውሃው ከጸጉሬ ጫፍ ተንሸራቶ ጡቴን ተሻግሮ ይወርዳል።... ሰውነቴን እየታጠብኩ ሃጢያቴን አስባለሁ። የሚወርደው ውሃ የውስጤን ቆሻሻ እንዲያፀዳ እመኛለሁ።.... ዓይኖቼን ጠረግሁ። ከውሃ የተቀላቀለ እንባ ከአይኔ አበስኩ።"እንዴት ይህ ሁሉ ሆነ? ባሌን እወደደው አይደል?"በቀላሉ አመነዘርኩ? ከባላቸው ውጭ ለሌላ ወንድ የሚሽኮረመሙ ሴቶችን እፀየፍ አልነበር? ምንድነው ያገኘኝ?ባሌ ይወደኛል። የሚወደኝን ባሌን አስብኩ። ስቆጣ ዝም የሚለውን፣ የምፈልገውን ሳልጠይቅ የሚያደርግልኝን...ባሌን አሰብኩ።ለምንድነው የማይቆጣኝ? ለምን አይታገለኝም? ላጣው እንደምችል የማያሳየኝ ለምንድየው?ሳለቅስ የምፈልገው መታቀፍ ነው ፤ እርሱ ግን "አይዞሽ ሁሉም ይስተካከላል" ይለኛል። ቀዝቃዛ ነው። የለቅሶዬን ችግር ከማስወገዱ በላይ በእንባዬ ወቅት መታቀፍ መፈለጌ አይገባውም።
    1,510103111Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    22 авг., 11:47

    📚ርዕስ:-አልተዘዋወረችም 📝ደራሲ:-አሌክስ አብርሃምShare and join 👇👇👇👇👇👇 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👉📔 @BookstoresAZ 📔👈 👆👆👆👆👆👆Ask any materials @Books_storebot @Books_storebot
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    22 авг., 10:57

    "መሞቴን ሰምተሃል፤ ነገር ግን የእኔ ሞት እንደምታስበው አይደለም። ከዚህ በኋላም የምትሰማውን ሁሉ አትመን"የጽሁፍ መልእክቱን ደግሜ አነበብኩት። በስልኩ ስክሪን ላይ የሚታየውን ቁጥር ማመን አልቻልኩም።የሟች ቁጥር ነው። መልክቱ የተላከልኝ ከሟች ጓደኛዬ ነው። ግራ ገብቶኝ ዝም አልኩ። በዚያ ቅጽበት የስልኩ ብርሃን እንኳን የሚሰልለኝ መሰለኝ።መልክቱን ማን ላከው? በሟች ጓደኛዬ ስልክ የጽሁፍ መልክት የላከልኝ ማን ይሆን?ሟች አብሮ አደጌ ነው። አንድ እንጀራ ተካፍለን በልተናል። ያስተሳሰረን እንጀራ ተካፍሎ መብላት ብቻ አይደለም። ሌላ አስተሳሳሪ ነገር ፈጠርን። የወንጀል እንጀራን በጋራ ጋገርን!በጥቂት አቅም የሽርክና ንግድ ጀምረን ነበር፤ በኋላ ተያይዘን ወደ ሌላ ዓለም ገባን። ከወንጀል ትርፍ የምናጋብስ ሆንን። ከሟች ጋር የጦር መሣሪያ እንሸጣለን፣ አደንዛዥ ዕፅ እንነግዳለን።... አንድ ጊዜ ወደዚያ ዓለም ከገባን በኋላ መውጣት ከበደን። የጦር መሳሪያ ዝውውርና አደንዛዥ እጽ ንግድ መግቢያ በር እንጂ መውጫ የለውም።ወደዚያ አለም ከገባህ በኋላ የገባህበት በር ከጀርባህ ይዘጋል።"እስካልተያዝን ድረስ..." ይለኝ ነበር ሟቹ ባልደረባዬ።የቀድሞ ወንጀላችን እንደሚከተለን ይሰማኝ ነበር። ወንጀላችንን ሁለታችንም አንረሳውም፤ ነገር ግን ስለ ወንጀላችን አንነጋገርም። እንዳልተከሰተ አስመስለን እንኖራለን።
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    14 авг., 18:03изменён

    ፍቅር በአንድ ጀምበር አይሞትም። እንደ ሻማ እየቀለጠ በዝግታ ይደክማል፤ እሳቱ እያለ ብርሃኑ ይደበዝዛል።ሳራ ከባሏ ጋር ከተጋቡ ሰባት ዓመታት አልፈዋል። የመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንደ ጸደይ ነበሩ፤ ትንሽ ቤታቸው በሳቅ፣ በህልምና በተስፋ የተሞላ ነበር።ዛሬ ግን ልባቸው ተራርቋል። ለእራት ሲቀመጡ ውይይታቸው ከሁለት አሊያም ሦስት ሐረጎች አያልፍም።"ውሃ አቀብዪኝ""እሺ።""ማታ አመሻለሁ።""እሺ።"ከዚያ ዝምታ።ሳራ ሙዚቃን ትወዳለች። ሙዚቃ የልቧ ቋንቋ ነው። ስትደሰት ትዘፍናለች፣ ስታዝን ዘፈን ታዳምጣለች።ባሏ ሙዚቃ አይወድም። "ይህ ጫጫታ ምንድነው?" ይላል ሙዚቃ ሲሰማ
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    13 авг., 15:58изменён

    ጎዳና አዳሪ ነበርኩ። አስፓልት ጥግ ከቦይ አጠገብ ማዳበሪያ ለብሼ ተኝቻለሁ፤ መንገድ ዳር ኖሬያለሁ።ብድግ ብዬ ከቤት ወጣሁ። እግሬ እንደ መራኝ በዘፈቀደ ሄድኩ። በ14 አመቴ የቤተሰቦቼን ቤት ትቼ ተሰደድኩ።ከቤት የወጣሁባት የመጀመሪያ ቀን የዘላለም ያህል ረጅም ነበረች። ከተማውን ሳካልል ዋልኩ። ሲመሽ አስፓልት ጥግ ተቀመጥኩ። የለበስኳት ነጭ ትሽረት በአንድ ቀን ነተበች። ብርዱ አጥንቴን ሰረሰረው። ጥርሶቼ ተፏጩ ፥ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ።"ያዝ" አለኝ አስፈሪ ገፅ ያለው ጎረምሳ። ቀና ብዬ አየሁት። ማዳበሪያ አቀበለኝ። ማዳበሪያውን ይዤ ፈዘዝኩ። "ልበሰው" አለኝ። ልታዘዘው ሞከርኩ። ነገር ግን አቃተኝ። ማዳበሪያ እንዴት እንደሚለበስ ግራ ገባኝ። እየሳቀ አስተካክሎ አለበሰኝ።"ምግብ በልተሃል?" "አይ" ትራፊ ሰጠኝ። ምግቡን ብፀየፍም ረሃቡ በለጠብኝ። እየፈራሁ ጥቂት ቀመስኩ፣ ሲያቅለሸልሸኝ ተውኩት። ሲጃራ አቀበለኝ "አልፈልግም" አልኩ። ማስቲሽ ሰጠኝ እሱንም አልፈልግም አልኩ።"ትለምደዋለህ። ከሳምንት በኋላ ሱሰኛ መሆንህ አይቀርም" አለኝ እየሳቀ።ማዳበሪያው ብርዱን አላሸነፈውም። ሰውነቴ ወባ እንደያዘው ሰው ይንቀጠቀጣል።"ከቤት ተጣልተህ ነው?" አለኝ እየሳቀ። እንባዬ ገነፈለ። ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያለቀስኩት በረሃብና ብርዱ ምክኒያት ነበረ።"ምን ሆነሃል?" አለኝ
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    6 авг., 19:37

    ስላመንኩት፥ ለሰጠኝ ፍቅር ዋጋ ስለሰጠሁ፥ እየተመቸኝ አልችልም ስለማልል፥ ስለሚወዱኝና ደጅ ስለሚጠኑ ወንዶች አያወራሁ ስለማልመጻደቅበት ...እኔን የማግኘት መጓጓቱ ቀነሰጥፋቱ ላይ ስለማላተኩር፥ ቅሬታዬን ስለማላሳየው፥ በልቤ ከሌሎች ጋ ስለማላወዳድረው...የማይገባኝ መሰለው!ቅር ይለዋል ብዬ የማስበውን ስለማላደርግ፥ ቅድሚያ ስለምሰጠው፥ ስለምወደው ዋጋዬ አልገባውም።እየተወኝ ሁኔታው ሁሉ ውለታ እንደዋለ ነው። እየበደለ ውለታ ዋልኩ እንደሚል ሰው ክፉ የለም!ክፉ አለመሆኔን እንዴት እንዳለማወቅ መቁጠር ተቻለው?!ረስቶት ነው..!? እንዴት አድርጎ ቀልቤን ለመግዛት እንደደከመ። ረስቶት ነው እንዴት አድርጎ ደጅ ጠንቶ እንደቀረበኝ። ረስቶት ነው እንዴት አንቆለጳጵሶ እጁ እንዳስገባኝ...ሲያገኘኝ እና ሳገኘው የነበረውን ሁኔታውን ሁሉ ዘንግቶታል!ሰነፍ እንዲህ ነው....በእጁ የያዘው ውድ አይመስለውም !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... የሚደረግለት ካልተነገረው አይገባውም !! ሰነፍ እንዲህ ነው ... ሲቆጠርበት አያይም !! ሰነፍ አንዲህ ነው ... የሚፈልገውን ሲይዘው ያንስበታል !!
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    24 июл., 06:41

    “ምነው አምና በሞትኩ፥ እንዲያ እንዳማረብኝ!?”ዝምታ ይረብሸኛል።ለዚያም ነው፥ መንገድ ስሔድ መጽሐፍ ይዤ የምዞረው፣ ሁሌም ጆሮዬ ውስጥ ‘ኤርፎን’ የምወትፈው፣ ልተኛ ስል፥ ያለችውን ፀጥታ እንኳን ላለማስተናገድ፥ የኾነ ነገር ከፍቼ ነው የምተኛው ...በዝምታ ውስጥ ከመኾን፥ ዝም ብሎ ከሚቀደደው ቱሪናፋው ከቤ ጋር ብውል እመርጣለሁ። ዝምታ ሽሽት የማልደውልበት፣ የማላነበው፣ የማልሰማው ዜና የለም።ዝምታ እፈራለሁ!መንገድ ስሔድ… ስቀመጥ! የማነበው መጽሐፍ ካልያዝኩ፣ ስራመድ የምሰማበት ኤርፎን ካልወተፍኩ…. ፖሊሶች አቻኩለው ከቤት አስወጥተውኝ ነው የሚሆነው!ዝምታ እፈራለሁ!አስታውሳለሁ፤ 12ኛ ክፍል ነበርኩ። ሙዚቃ ከፍቼ እያጠናሁ፥ የአጎቴን የለቅሶ ሳግ ሰምቼ ደንግጬ “ምነው አመመህ?” አልኩት፤ እሱ ሙዚቃ እየተጫወተበት ያለውን ‘ቴፕ’ ዐየት አድርጎ፥ ወደ ጣርያው አፍጥጦ፣ እምባው ቁልቁል ወረደ!አሞት መስሎኝ ነበር… ከዚህ በፊት ሲያመው ያቃስታል፤ ሲብስበትም ማስታገሻ ይውጣል እንጂ አያለቅስም ነበር።አጎቴ ጥቁር ነው፤ ፊቱ ክስክስ ያለ… ሲያወራ ግን እንደሚታየው ኮስተር ያለ ማንነት እንደሌለው የሚያስታውቅበት፥ ቁጥብ፣ ደስ የሚል ሰው ነው።
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    23 июл., 18:19

    ወጣቶች ነበርን በእውቀቱ ስዩምጊዜ ሲራመድ ኮቴው ድምጥ አልባ ከየት ተነስቶ ወደ የት ገባ ከየት ተነስቶ ወዴት ደረሰ ጠጉር መንጥሮ፣ ፊት እያረሰ፤ወጣቶች ነበርን ቅጽር የሰራን ፤ አምባ የሰበርን ኮካ ኮላውን ባሲድ በርዘን ብንጎነጨው፤ የማይመርዘን፤ በራዱን ያጋልን፣ ሙት ልብ ያስነሳን ግራዋ በልተን ፤ ሎሚ ያገሳን፤ተስፋችን ብዙ፤ እድሚያችን ለጋ ስንሰማራ፣ ትርጉም ፍለጋገላችን አይፈዝ፣ ጭቃ ቢለሰን የማናስቀይም፤ ቡትቶ ለብሰን
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    18 июл., 06:57

    "ለምንድነው ድንገት የተውከኝ አለቺኝ ?""እኔ'ንጃ ምን አልባት ፈርቼሽ ይሆናል"።በአይኗ እየተቅለሰለሰች "ምኔ አስፈራህ ትባ'ላለች አሉህ ወይ "ጥቁረቷ የዐይኗን ውበት ጨምሮታል ጥቁረቷ ጥርሷን ጥርሰ በረዶ ናት እንድትባል ያደረጋት ይመስለኛል።ስታምር !ትክ ብዬ እያየኋት"የመወደድ ርኃብ ያለብሽ ይመስላል "አልኳትምን ማለት ነው ??"የሚወደኝ አጥቼ ማለት ነው? " ሳቀች አሳሳቋ ፌዝ አዝሏልአይምሰልሽ የአንዳንድ ርሃብ ምንጭ እኮ የአቅርቦት እጥረት አይደለም የአስተዳደግ ጠባሳም ሊሆን ይችላል።
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    12 июл., 06:43

    "እናቴ ሦስቴ አግብታ ሦስቴ ፈታለች። ከእህቴ እና ከወንድሜ ጋር አባት እንደማንጋራ ታውቂያለሽ። እናቴ አዲስ ሕይወት በጀመረች ቁጥር በትዳሯ እንደምትፀና የምትወራረድ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕይወት ብዙም ሳይቆይ መዝመም ይጀምርና የመጠገን እድልን ሳያገኝ ይፈርሳል።ይህ እንዴት ሆነ?››‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››‹‹ወንድሜ ለትዳር ምንም አይነት መጓጓት እንዳልነበረው ታውቂያለሽ... እማማና ዘመዶቿ ወትውተውት ካገባ በኋላ በሦስት ዓመቱ ተፋታ። ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ለገዛ ልጁ እንኳን ግድ የለሽ ሆኖ የተገለለ ኑሮ እየገፋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።... ይህ እርግማን አይደለም?››‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››‹‹እህቴ ቁጥብ እና በራስ መተማመን ያላት ሴት እንደነበረች መመስከር እንደምትችይ አውቃለሁ። ስለ መልኳ ሁሉም ሰው ይናገራል። መብራት ከተማ ውስጥ የእህቴን ያህል ቆንጆ ማግኘት እንደማይቻል እወራረዳለሁ፡፡ ትዳር ከመሠረተች በኋላ ግን ሕይወቷ ተመሳቀለ። የወለደችው ልጅ ጡት ሳይጥል ትዳሯ ፈረሰ። በዚህ የተነሳ ማንንም ማመን የማትችል፣ በራስ መተማመኗን ያጣች ሆናለች። በሃዘኗ ብርታት የተነሳ ውበቷ ከድቷታል። የተሰበረች ሴት ነች... ይህ እርግማን አይደለም?››‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››‹‹የእኔን ታሪክ ታውቂዋለሽ። የፍቅር ሕይወቴ በመለየት ይደመደማል። ጀመርኩ ስል ይቋረጣል። የገነባው ሲመስለኝ ይፈርሳል። አንዴ አይደለም። በተደጋጋሚ እንጂ!.... ይህ እርግማን አይደለም?››‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል››‹‹ስለ አያቴ የትዳር ሕይወት ነግሬሽ አውቃለሁ?›› ‹‹ነግረሽኝ አታውቂም›› ‹‹የ
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    11 июл., 12:55

    ኦሮማን (በእውቀቱ ስዩም)ሰሞኑን እንደ አዲስ አስቴር አወቀን ሳደምጥ፣ በአሉ ግርማ ትዝ አለኝ፤ የበአሉን ኦሮማይ ታስታውሱታላችሁ ? ፀጋየ ሀይለማርያም ጋዜጠኛ ነው፤ ሮማን የተባለች ውብ ኩሩ እጮኛ አለችው፤ ሊጋቡ ጥቂት ወራት ሲቀራቸው በቀይ ኮከብ ጥሪ አስመራ ለግዳጅ ተላከ፤ በዚያም በዘመቻው መሀል ፊያሜታ የተባለች ያስመራ ሴት ተዋወቀ፤ ከባድ ፎንቃ ገባለት፤ ባስመራይቱና በሸገሪቱ ሴቶች ፍቅር መሀል ተወጥሮ በታሪካዊው ዘመቻ ላይ ተሳተፈ ፤ በመጨረሻ ሮማን አስመራ መጥታ ከሌላ ሴት ጋር ፍቅር አንደያዘው ተረዳች፤ ፊያሜታ ለሱ ብላ ህይወትዋን ትሰጣለች፤ በመጨረሻም ፊያሜታን በሞት ሮማንን በቅያሜ አጥቶ አጥቶ ብቻውን ሲቀር ልቦለዱ ይጠናቀቃል፤ሮማን አዲስአበባ ሆና የአስቴር አወቀን ክር ካሴት ልካለት ነበር፤፤ ፊያሜታ ሮማን የላከችውን ካሴት ሰባብራ ክሩን ጎልጉላ ፊቱ ላይ የምትነበትንበት ትእይንት አይረሳኝም፤አሁን ድንገት ጉደኛ ሀሳብ ብልጭ አለልኝ ፤ ኦሮማይን የደረሰው ስብሀት ቢሆን ኖሮ ብየ አሰብሁ፤ አንዲህ ነበር የሚሆነው፤ሮማን እና ፊያሜታ አስመራ ተገናኝተው እየተጨዋወቱ ነው፤-ስትገናኙ እጮኛው መሆኔን ነግሮሽ ነበር ? “አለች ሮማንፊያሜታ ራስዋን በአዎንታ ነቀነቀች፤“እና እጮኛ አንዳለው እያወቅሽ አፈቀርሽው?”ፊያሜታ ጸጉሯን ነስንሳ “አዝናለሁ፤ ነገሩ እዚህ ይደርሳል ብየ አላሰብኩም ነበር፤ ሕይወት አንደ ደራሽ ውሀ ገፍቶ የት አንደሚያደርሰን አናውቅም’ አለችና በስፕራይት ጠርሙስ የተቀዳ ቢራዋን ተጎነጨች፤ የቢራ ጠርሙሶች ተለቅመው ለምሽግ መስርያ ወደ ናቅፋ ስለተወሰዱ አስመራ
    1,82015531Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    18 июн., 06:36

    አንድ ልጅ አጣብሰኝ እስቲ አለችኝ ። ያን ወቅት አንድ ልጅ አጣብሰኝ ሲለኝ ስለነበር እና ማች ያደርጋሉ ስላልኩ ።አገናኘዋቸው ።ከመሃል ወጣው ። እሱ እንድወጣ አልፈለገም መሰለኝያሰበውን ሁሉ ይነግረኛል በተለይ ያደረጉትን ሲነግረኝ ልጎመጅ ይዳዳኛል ...."ምን አይነት አበባ ....ምን አይነት ቀሽት ልጅ ነው ያጣበስከኝ እንዴት እንደ ምትጣፍጥ .....ደሞ ሰውነቷ ደሞ ፍቅር ላይ አኳኃኗ "በሌላ ቀን ..."I think አስተዳደጓ ነው መሰለኝ ነፃ ነች ክላስ ይዛ ተሽሞንሙና ትጠብቀኛለች ...ደሞ ዋዛ እንዳመስልህ...ትሽከረከረዋለች ....OMG"በሌላ ቀን"አንተ እቺን መረቅ ልጅ አገናኝተኸኝ እኮ በቃ ኑሮዬ ሰመረ ....እንማጠጠዋለን ....OMG "ይላልI think ፀፀት ሊጀምረኝ ነው 😄
    2,5701655Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    12 июн., 17:09

    በአፍላነቴ በተፈጥሮ አስገዳጅነት ጭምር ብርቱ የሆነ የተቃራኒ ጾታ ፍላጎት የተፈጠረብኝ ቢሆንም 'ሰይጣን አለባት' በሚል ተልካሻ ምክንያት የሚንቁኝና የሚያገሉኝ በዙ፡፡በተገፋሁ ቁጥር ፍላጎቴ በእጥፍ አደገ፡፡ 'አንድ ወንድ አፈቅርሻለሁ ካለኝ ሳላቅማማ እኔም አፈቅርሃለሁ እለዋለሁ' ብዬ የነበረ ቢሆንም የፍቅር ጥያቄ የሚያቀርብልኝ ጠፋ፡፡ያኔ ለራሴ የፍቅር ደብዳቤ ፃፍኩ፡፡‹‹ጫሊ ጉድ ሰማሽ?›› አልኳት የክፍላችንን ፍልቅልቅ ተማሪ ‹‹የምን ጉድ?›› ‹‹ደብዳቤ ተፃፈልኝ›› ‹‹ከማን?›› ‹‹አላውቅም›› ‹‹እንዴት አታውቂም?›› ‹‹ስም የለውም፡፡ ግን ከዚህ በፊትም ጽፎልኝ ያውቃል›› ደብዳቤውን ከደብተሬ ውስጥ አውጥቼ ሰጠኋት፡፡ወሬው ተናፈሰ፡፡ የሆነ ሰው ማንነቱን ሳይገልፅልኝ ደብዳቤ እንደሚጽፍልኝ ተወራ፡፡ የክፍሌ ሴቶች በየቀኑ 'የሚጽፍልሽን ወንድ አወቅሽው?' በሚል ጥያቄ ያዋክቡኝ ጀመር። የሆነ ወንድ እንደሚያፈቅረኝ ተረጋገጠ፡፡ተፈቃሪነቴ በተማሪ ቤቱ በተወራ ወቅት አንድ ብጣሽ ወረቀት ደብተሬ ስር ተቀምጠ፤ ልቤ ዘለለች፡፡ 'እኔም እንደ እኩዮቼ አፍቃሪ አገኘሁ' ብዬ በደስታ ተሞላሁ፡፡ ተፈላጊ የመሆን ስሜት ሀሴትን ፈጠረብኝ፡፡ በደስታ ውስጥ ሆኜ አንድ አንቀጽ ጽሑፍ ብቻ ያለውን ደብዳቤ ማንበብ ጀመርኩ. . .‹‹ላንቺ የፍቅር ጥያቄ የሚፅፍልሽ ማን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የሚያፈቅርሽ ሰይጣን ነው፡፡ አንቺ ሴት ሰይጣን ነሽ፡፡ ወንዱ ሰይጣን ደግሞ ያፈቅርሻል፡፡ እሺ ካልሽው መውደቅሽ ይቆማል›› ይላል ደብዳቤው።ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ አለቀስኩ....
    2,6008333Открыть в Telegram
  • መጽሐፍ ቤት Bookstores

    11 июн., 17:10

    ምንገድ ላይ (በእውቀቱ ስዩም)በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ ኡራኤል ፊትለፊት ካለው አስፋልት ላይ ስደርስ የሚገርም ነገር ተከሰተ፤ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ ቡሌ በፌስታል, ሸክፎ አስፋልት እያቁዋረጠ ሳለ አንድ ሞተረኛ ከላይ ሲንደርደር መጥቶ ደንብቆ ጣለው ፤ የሸገር ሞተረኞች ለምን እንደሚካልቡ አይገባኝም፤ አለምን ከጥፋት የሚታደግ መልክት ለማድረስ የሚነዱ እንጂ የጠወለገ በለጨ የጫኑ አይመስሉም፤ሞተረኛው ከሞተሩ ተስፈንጥሮ አስፋልቱ ዳር ተዘረረ ፤ ሞተሩ ግን በራሱ ፈቃድ እየበረረ ሂዶ ባቅራቢያው ከሚገኝ ጋራጅ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ፤ የጎዳናው ሰውየ ተሽቀንጥሮ መንገዱ ጠርዝ ላይ ተገኘ፤ ወድያው ባካባቢው የነበረው ህዝብ ሞተረኛውን እና የጎዳናውን ሰውየ ተካፍለው ከበብ ከበብ አድርገው ቆሙ፤ ብብዙዎች ፊት ላይ ሀዘን በግልፅ ይነበባል ፤ ቢያንስ ከሁለት አንዱ አለመሞታቸው ብዙዎችን ያስደበረ ይመስለኛል ፤እኔ ሁሌም ከተጎጂው ጎን መሰለፍ ስለሚያስደስተኝ ፣ ከጎዳና ተዳዳሪው አጠገብ ቆምኩ፤ ተጎጂው ቀና ብሎ አየኝ፤ መላከ ሞትን ያባረረ ኡራኤል መስየ ታይቸው ይሆንን ብየ ራሴን ሸነገልሁ፤የጎዳናው ሰውየ የፈራሁትን ያህል አልተጎዳም፤ ደጋግሞ የመገጨት ልምድ ያካበተ ይመስላል፤ የቀኝ እግሩ መሀል አገዳ ላይ ብቻ የመድማትና የመጫጫር ምልክት አየሁ፤-አይዞህ ወንድም ጥላ! በዚች እግርህን ታይበት ‘ አልሁና ከቦርሳየ ውስጥ ሁለት መቶ ብር በማውጣት ዘረጋሁለት፤በልግስናየ ልቡ ተነክቶ ተጠምጥሞብኝ ያለቅሳል የሚል ግምት ነበረኝ፤‘እናትህ ትጎዳ ! (በትክክል ያለኝ እንኩዋ
    2,170631Открыть в Telegram