Последние посты

Brook News ብሩክ ኒዉስ
26 сент., 12:49
ለተመሪዎች የተሰማው የምስራች! የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት 11 ተጨማሪ የሥልጠና ዘርፎችን በማካተት ምዝገባ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።ኢንስቲትዩት እነዚህን ተጨማሪ የስልጠና መስኮች ያስተዋወቀው ከመስከረም 14/2019 ዓም ጀምሮ ክፍት የሚሆን የመረጃ ሳምንትን ይፋ ባደረገበት መርሃ ግብር ላይ ነው።ተቋሙ ላለፉት ከ15 ዓመታት በላይ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብቸኛው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት• በመጀመሪያ ዲግሪ (ደረጃ 6) በ29 ፕሮግራሞች፣• በሁለተኛ ዲግሪ (ደረጃ 7) በ23 ፕሮግራሞች እንዲሁም• በሦስተኛ ዲግሪ (ደረጃ 8 / ፒኤች.ዲ) በ2 ፕሮግራሞች ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።በተለይም በ2018 ዓ.ም ደግሞ የዓለም ገበያ የክህሎት ፍላጎትን ያገናዘቡ ናቸው የተባሉትን 11 መስኮች ማለትም :-- ባዮሜዲካል ቴክኖሎጂ፣ - የሳይበር ደህንነት፣ - አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ - ኢንተለጀንት ሮቦቲክስ፣ - ፕላስቲክ ቴክኖሎጂ - ሆርቲካልቸር - ኢንቴሪየር ዲዛይን እና ፊኒሺንግ - ሌዘር ፕሮዳክት - በTVET ሊደርሺፕ እና ማኔጅመንት - በማኑፋክቸሪንግ - ፋሽን ዲዛይን እና በአዳዲስ ኢነርጂ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራና የወደፊት የሥልጠና መስኮች (Emerging Skills) ተቀርጸው ወደ ተግባር መግባታቸው ተገልጿል።ሥልጠናው 50 በመቶ የንድፈ-ሀሳብ እና 50 በመቶ የተግባር ልምምድ እንዲሆን በተሟሉ ወርክሾፖች የተደገፈ ነው የተባለ ሲሆን ተቋሙ በ16 ሳተላይት ካምፓሶችና በ2 ማዕከላት አማካኝነት ከ 10 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።ኢንስቲትዩቱ ከቻይና እና አልጄሪያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጥምረት የዲግሪ ፕሮግራሞችን ከመስጠት ባሻገር፣ በየዓመቱ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሌሎች የጎረቤት ሀገራት ዜጎች ነፃ የሥልጠና ዕድል እየሰጠ መሆኑን አሳውቋል።የተቋሙን መስፈርት የሚያሟሉ የመደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም 25/2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ይፋ አድርጓል።




Brook News ብሩክ ኒዉስ
26 сент., 10:22
በ ላስታ ወረዳ የተፈፀመ ጥቃት!በዚህ ቪዲዮ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ፣ በትግራይ ክልል የተከሰተውን የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጥ፣ በሰሜን ወሎ ያለውን የትራንስፖርትና የባንክ ሁኔታ እንዲሁም የኢሰመኮንና የዓለም አቀፍ አካላትን ምላሽ በጥልቀት የምንዳስስ ሲሆን፤ ከከባድ የህይወት ፈተናና ከሱስ ተላቆ በአንድ ጊዜ የ4 መንታ ልጆች አባት በመሆን ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን የሰበረውን የ27 ዓመቱ ወጣት ፋሲልና ባለቤቱ ፅዮንን ልብ የሚነካና አነቃቂ እውነተኛ የህይወት ታሪክ ይዘንላችሁ ቀርበናል https://youtu.be/UIq0O55umMoYouTubeበላስታ ወረዳ የተፈጸመው ጥቃት!በዚህ ቪዲዮ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ፣ በትግራይ ክልል የተከሰተውን የኢንተርኔትና የስልክ አገልግሎት መቋረጥ፣ በሰሜን ወሎ ያለውን የትራንስፖርትና የባንክ ሁኔታ እንዲሁም የኢሰመኮንና የዓለም አቀፍ አካላትን ምላሽ በጥልቀት የምንዳስስ ሲሆን፤ ከከባድ የህይወት ፈተናና ከሱስ ተላቆ በአንድ ጊዜ የ4 መንታ ልጆች አባት በመሆን ማህበረሰባዊ አስተሳሰቦችን የሰበረውን የ27 ዓመቱ ወጣት…
Brook News ብሩክ ኒዉስ
25 сент., 15:03
ከማንነት ፉክክር ወደ......ቪዲዮው ኢትዮጵያ በብዝሃነት የተገነባች የጋራ ሀገር መሆኗን በማስታወስ፣ የክልል ድንበሮች የዜጎችን የመዘዋወር፣ የመሥራት እና በኢኮኖሚ የመሳተፍ መብት ሊገድቡ እንደማይገባቸው፣ እንዲሁም እውነተኛ ሰላም እና አንድነት የሚገነባው ከማንነት ፉክክር ይልቅ ልዩነቶችን በማክበር፣ የዜግነት እኩልነትን በማረጋገጥ እና የሕግ የበላይነትን በማስቀደም መሆኑን በጥልቀት ያስረዳል! https://youtu.be/tpZGsmeOsZ0?si=YFMcUZKX3SP8aZZgYouTubeከማንነት ፉክክር ወደ...#ethiovistanewsቪዲዮው ኢትዮጵያ በብዝሃነት የተገነባች የጋራ ሀገር መሆኗን በማስታወስ፣ የክልል ድንበሮች የዜጎችን የመዘዋወር፣ የመሥራት እና በኢኮኖሚ የመሳተፍ መብት (በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 32፣ 41(1) እና 25 መሠረት) ሊገድቡ እንደማይገባቸው፣ እንዲሁም እውነተኛ ሰላም እና አንድነት የሚገነባው ከማንነት ፉክክር ይልቅ ልዩነቶችን በማክበር፣ የዜግነት እኩልነትን በማረጋገጥ እና የሕግ የበላይነትን በማስቀደም መሆኑን…
Brook News ብሩክ ኒዉስ
25 сент., 14:07
🇪🇹ኢትዮጵያዊዉ አትሌት ልዩ ክብር በአዲዳስ ተሰጠው❗️🏃🏾 የጀርመኑ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ በ2026 ለንደን ማራቶን አስደናቂ ታሪክ ላስመዘገቡት ለኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ እና ለኬንያዊው ሴባስቲያን ሳዌ በዋና መሥሪያ ቤቱ ልዩ ዕውቅና እና ክብር ሰጥቷል።አዲዳስ ለሁለቱ አትሌቶች ክብር በዋና መሥሪያ ቤቱ ስማቸውን እና የእግራቸውን ዐሻራ በክብር አስቀምጧል።🇪🇹 በ2026ቱ የለንደን ማራቶን ዮሚፍ ቀጄል በ1:59:41 እንዲሁም ሴባስቲያን ሳዌ በ1:59:30 ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች በመጨረስ ታሪክ መሥራታቸው ይታወሳል።



Brook News ብሩክ ኒዉስ
25 сент., 12:29
📢 ማስታወቂያበ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦ 👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement 3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።ትምህርት ሚኒስቴር


Brook News ብሩክ ኒዉስ
25 сент., 08:03
ከዛሬ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ላልተወሰነ ጊዜ ተከለክሏል። ከኮድ 4 እና ከፖሊስ ሞተር ብስክሌቶች ውጭ ያሉ ሁሉንም ይመለከታል። የእገዳው ምክንያቶች፡ ሞተር ብስክሌቶችን ለቅሚያ፣ ለስርቆት እና የተሰረቁ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ መጠቀም በመበራከቱ። ቀይ መብራት መጣስ፣ ገጭቶ ማምለጥ፣ ሄልሜት አለመጠቀም እና የሰሌዳ ቁጥር ማደብዘዝ የመሳሰሉ የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች በመብዛታቸው ነው ሲል የ አዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል::


Brook News ብሩክ ኒዉስ
25 сент., 07:40изменён
🛰ራሺያን ለመምታት ኤለን መስክ ድጋፍ ተጠየቀ❗️👉ዘ ጋርዲያን እና ሮይተርስ እንደዘገቡት፣ የፊንላንዱ ፕሬዝዳንት ስተብ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከኢሎን ማስክ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት በሩሲያ ግዛት ውስጥም እንዲሠራ እና ዩክሬን እንድትጠቀምበት ጠይቀዋል። ዝርዝር ዘገባውን በዚህ ገብተው ይመልከቱ https://www.brook.news/article/untitled-2kw35q


Brook News ብሩክ ኒዉስ
24 сент., 17:49изменён
🇪🇹⚔️የህውሀት ከፍተኛ አመራሮች እየተለቀሙ ነው❗️🛡የቀድሞው የትግራይ ጸጥታ ኃይሎች ወታደራዊ መረጃ ኃላፊ ኮሎኔል ተወልደ እንበብ እና የትግራይ ኃይሎች የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊና የቀድሞው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ኢሳያስ ታደሠ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተሰምቷል።🛡ግለሰቦቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ ለፌደራል መንግሥቱ ወታደራዊ መረጃ ያቀብላሉ በሚል ተጠርጥረው መሆኑን ምንጮች ነግረውናል። ሌሎች ሦስት የጸጥታ ኃይሉ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችም እንዲታሠሩ ትዕዛዝ መተላለፉን ምንጮቹ የገለጡ ሲኾን፣ የወታደራዊ አዛዦቹን ማንነት ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡🛡የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሠ ወረደም መኖሪያ ቤታቸው ከረቡእ ምሽት ጀምሮ በአዳዲስ የጸጥታ ኃይል አባላት እየተጠበቀ እንደሚገኝ ተሠምቷል። 👉 የጀነራሉ ቤተሠቦችም ሆኑ የቅርብ ወዳጆቻቸው ከቤታቸው መውጣትም ሆነ መግባት እንደተከለከሉም በኋላም ዛሬ አመሻሹን ከቤታቸው ተወስደው መታሰራቸው ከቤተሰቦቻቸው በተገኘ ምንጭ ተዘግቧል።


Brook News ብሩክ ኒዉስ
22 сент., 17:47
🇪🇹 ኢትዮጵያ አንድ ደረጃ አሻሻለች❗️🕊ኢትዮጵያ በተያዘው የአውሮፓዊያን ዓመት የዓለም አገራት የሰላም አመላካቾች ከ163 አገራት 138ኛ ደረጃ ተሠጣት። ኢትዮጵያ፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር፣ ዘንድሮ አንድ ደረጃ አሻሽላለች።🕊 ለአገራት የሰላም ጠቋሚ ደረጃ የሚያወጣው ዓለማቀፉ የኢኮኖሚክስና ሰላም ኢንስቲትዩት፣ ከ5 ከያዘው ነጥብ ለኢትዮጵያ 2 ነጥብ 6 ነጥብ ሠጥቷታል። አገሪቱ ዝቅተኛ ነጥብ ያገኘችባቸው ጠቋሚዎች፣ ፖለቲካዊ ሽብር፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ ከጎረቤት አገራት ጋር ያላት ግንኙነት፣ ውስጣዊ ግጭቶች፣ የውስጣዊ ግጭቶች አስከፊነት እና የአነስተኛ ጦር መሳሪያዎች ተደራሽነት ናቸው።🕊ኢትዮጵያ በደረጃው ከተካተቱ 44 የአፍሪካ አገራት ያገኘችው 35ኛ ደረጃ ነው።👉በሌላ በኩል ተመድ፣ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልፅዋል። የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቲፋኒ ዱጃሪክ፣ በአገሪቱ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች አዲስ ጥምረት መፍጠራቸውን፣ የድሮን ጥቃቶች መደጋገማቸውንና የጸጥታ ችግሮች መቀጠላቸውን ጠቅሠው፣ ድርጅቱ የአገሪቱ የጸጥታ ሁኔታ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ትናንት ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። ዱጃሪክ፣ የአገሪቱ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የጸጥታ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ ከሚያደርጉ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል።ወታደራዊ ርምጃ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን ወይም ነባር ቅራታዎችን አይፈታም በማለት ጭምር ዱጃሪክ አጽንዖት ሠጥተዋል።በተያይዘ፣ በኢትዮጵያ የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ኦዞኒያ ኦጄሎ፣ በኢትዮጵያ ሰላም፣ መተማመንና


Brook News ብሩክ ኒዉስ
22 сент., 15:07
ጃዋር ለምን ደነገጠ?የጃል መሮ አነጋጋሪ ኢንተርቪው ቅስሙን ከሰበረው በኋላ ጃዋር መሐመድ ይዞት የመጣው አዲስ መግለጫ ምን ይላል? በዚህ አጓጊ ቪዲዮ ጃዋር ስለ አብይ አህመድ ወታደራዊ ጡንቻ መፈረጥ፣ የድሮን አጠቃቀም እና የውጭ አጋሮች ሚና ያነሳቸውን አከራካሪ ነጥቦች እንፈትሻለን፤ እንዲሁም አዲሱ «ትብብር ለህልውና» ከሕወሓትና ከአብይ ውጪ ማንን ይጠቅማል ብሎ የደምደመበትን ጥልቅ ትንተና እንቃኛለን! https://youtu.be/G6L_xZlestE?si=s3DsoLJQw3oMfoeAYouTubeጃዋር ለምን ደነገጠ?#EthioVistaየጃል መሮ አነጋጋሪ ኢንተርቪው ቅስሙን ከሰበረው በኋላ ጃዋር መሐመድ ይዞት የመጣው አዲስ መግለጫ ምን ይላል? በዚህ አጓጊ ቪዲዮ ጃዋር ስለ አብይ አህመድ ወታደራዊ ጡንቻ መፈረጥ፣ የድሮን አጠቃቀም እና የውጭ አጋሮች ሚና ያነሳቸውን አከራካሪ ነጥቦች እንፈትሻለን፤ እንዲሁም አዲሱ «ትብብር ለህልውና» ከሕወሓትና ከአብይ ውጪ ማንን ይጠቅማል ብሎ የደምደመበትን ጥልቅ ትንተና እንቃኛለን! 👍 ይህንን ቪዲዮ…
Brook News ብሩክ ኒዉስ
22 сент., 13:52
⚽️አርቴታ ውላቸውን ሊያራዝሙ ነው🏐 ስፔናዊው የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በክለቡ ያላቸውን ኮንትራት ለማራዘም ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብሏል።🏐አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ቤት ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ከስምምነት ደርሰዋል።🏐አዲሱ ውል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአርሰናል ከአስር ዓመት በላይ እንዲቆዩ ያስችላቸዋል ተብሏል።


Brook News ብሩክ ኒዉስ
22 сент., 13:48
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በፍጥነት እየተባባሰ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ትኩረት ነፍገዋል” ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የዴሞክራቶች ተወካይ ግሪጎሪ ሚክስ ነቀፉ። በኢትዮጵያ ባለው የሰብአዊ ሁኔታዎች እና የሰብአዊ መብቶች ቀውስ ምክንያት፤ አሜሪካ ጥላው የነበረው ማዕቀብ አለመራዘሙን የኮንግረስ አባሉ ተችተዋል።በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ አሜሪካ በኤርትራ ላይ ጥላው የነበረው ማዕቀብ የመጨረሻ ቀነ ገደብ አርብ መስከረም 8፤ 2019 ነበር። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ማዕቀቡ እንዲጣል በመስከረም 2014 ዓ.ም. ትዕዛዝ ያስተላለፉት፤ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎችን ባዳረሰው ጦርነት የተፈጸሙ ጥሰቶች ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ “ያልተለመደ እና ልዩ ስጋት ፈጥረዋል” በሚል ነበር።ማዕቀቡ ሳይራዘም የቀረበት አካሄድ በ72 ዓመቱ የኒውዮርክ የኮንግረስ አባል ግሪጎሪ ሚክስ ትችት ገጥሞታል። ሚክስ የማዕቀቡን ማብቃት በማስመልከት ትላንት ሰኞ መስከረም 11፤ 2019 ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ “በከፍተኛ የግጭት ስጋት” ውስጥ እንደሚገኙ አስጠንቅቀዋል።“ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሁለቱም ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ቀጠናዊ ሰላም እና መረጋጋትን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል” የሚሉት ዴሞክራቱ የኮንግረስ ተመራጭ፤ ማዕቀቡ እንዲያበቃ መደረጉን ኮንነዋል። “እነዚህን ማዕቀቦች አሁን ማንሳት የተሳሳተ መልዕክት በተሳሳተ ጊዜ ያስተላልፋል” ሲሉም አስገንዝበዋል። ምንጭ_ኢትዮኢንሳይ


Brook News ብሩክ ኒዉስ
22 сент., 09:36
«ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር» - ሮዛበማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተለቀቀውንና ውዝግብ ያስነሳውን የሃይማኖት አባት ፀያፍ ቪዲዮ እውነተኛነት አስመልክቶ «ተበዳይ ነኝ» ያለችው ግለሰብ ምስክርነት ሰጠች። የግንኙነቱ መጀመር፦ አክሱም ከተማ ውስጥ ሆቴል በአስተናጋጅነት የምታገለግለው ሮዛ የተባለችው ግለሰብ፤ ከዓመት በፊት የትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቡነ አረጋዊ ጋር መተዋወቋን እና ቆይቶም ግንኙነታቸው ወደ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተናግራለች።የቪዲዮው መቅረጽ እና የቀረበው ጉቦ፦ ጳጳሱ ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት በመግለጽ፣ መግቻ ይሆን ዘንድ በድብቅ ቪዲዮ መቅረጿን የገለጸች ሲሆን፤ ቪዲዮውን እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላት ገልጻለች።የዛቻና የደህንነት ስጋት፦ ብር ከመቀበል ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ጸያፍ ተግባር እንድትላቀቅ ባላት አቋም እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባትና ቪዲዮው ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ መለቀቁን አብራርታለች።ተጨማሪ ጥቆማዎች፦ ሮዛ እሷን ጨምሮ በአክሱምና ከአክሱም ውጪ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።የአሁኑ ሁኔታ፦ ጳጳሱም ሆኑ በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን የሌለ ሲሆን፤ ሮዛ በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ ትገኛለች።


Brook News ብሩክ ኒዉስ
21 сент., 15:06изменён
የ አንዱን ዜጋ መብት ለማክበር የሌላውን ዜግነት መብት መንጠቅ!?አገር በድንገት አትፈርስም፤ ውድቀቷ የሚጀምረው በትንንሽ የጥርጣሬ ቃላትና በ«እኔ እና እነሱ» ፖለቲካ ነው።አዲስ አበባን በተመለከተ የሚወሰን ውሳኔ በዜጎች ማንነት እና በጋራ ማዕከልነት ላይ ሊያስከትለውን አደገኛ የ«ጠፋው ዜጋ» (Lost Citizen) ቀውስ ከዩጎዝላቪያ ታሪክ ጋር በማያያዝ በአስገራሚ ሁኔታ ይዳስሰዋል። የአንዱን መብት ለማክበር የሌላውን ዜግነት መቀነስ የሚያስከትለውን እጅግ አሳሳቢ የዜሮ-ሰም ጨዋታ እ ለመረዳት ቪዲዮውን ይመልከቱ!https://youtu.be/8NWthl95QH8YouTubeየአንዱን መብት ለማክበር የሌላውን ዜግነት መቀነስ?!#EthioVistaአገር በድንገት አትፈርስም፤ ውድቀቷ የሚጀምረው በትንንሽ የጥርጣሬ ቃላትና በ«እኔ እና እነሱ» ፖለቲካ ነው።አዲስ አበባን በተመለከተ የሚወሰን ውሳኔ በዜጎች ማንነት እና በጋራ ማዕከልነት ላይ ሊያስከትለውን አደገኛ የ«ጠፋው ዜጋ» (Lost Citizen) ቀውስ ከዩጎዝላቪያ ታሪክ ጋር በማያያዝ በአስገራሚ ሁኔታ ይዳስሰዋል። የአንዱን መብት ለማክበር የሌላውን ዜግነት መቀነስ የሚያስከትለውን እጅግ አሳሳቢ…
Brook News ብሩክ ኒዉስ
20 сент., 15:59
#NewsAlert ❗️ሰባት አማፅያን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት አስወግደው የሽግግር መንግስት ለመመስረት ያስችለናል ያሉትን አዲስ ጥምረት "ትብብር" ይፋ አድረጉ።በትግራይ ክልል በሚገኙ የሚዲያ አውታሮች በኩል የተሰራጨውን የ"ትብብር" መመስረት ይፋ ያደረጉት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሰብሳቢ አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው። አቶ ዘመነ የትብብሩ ሰብሳቢ መሆናቸውም ተገልጿል።አፋብን፣ ሕወሓት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ህዝብ ነፃነት ግንባርና የአፋር ብሄራዊ አንድነት ግንባር የ"ትብብሩ" አባላት መሆናቸው በመግለጫው ላይ ተነግሯል። "ትብብሩ" በስልጣን ላይ ያለውን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ መንግስት በመጣል "ሁሉን አቀፍ የሽግግር መንግስት" ለማቋቋም ትልም እንዳለውም አቶ ዘመነ ካሴ በመግለጫው አብራርተዋል።


Brook News ብሩክ ኒዉስ
20 сент., 15:29
ታግደዉ የነበሩት የስፖርት ውርርድ እና ዲጂታል ሎተሪዎች በአዲስ እና ጥብቅ ማዕቀፍ ሊጀምሩ ነዉየኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ጥብቅ የቁጥጥር ማዕቀፍ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የስፖርት ውርርድ እና ዲጂታል ሎተሪ አገልግሎቶችን በአዲስ መልክ ለማስጀመር አጠቃላይ ዝግጅቶችን እያደረገ ይገኛል።ምንጭ _ካፒታል


Brook News ብሩክ ኒዉስ
20 сент., 08:58
አሜሪካ ለዜጎቿ ተጨንቃለች🇺🇸 አስቸኳይ መግለጫ ተሰቷል❗️ 👉የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ሪያድ፣ አቡ ዳቢ፣ ዶሃ፣ እየሩሳሌም እና ሌሎችም ከትናንት ጀምሮ ያወጡት የተቀናጀ የደህንነት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል። 🇺🇸 በየመኑ ሁቲዎች እና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ግጭትና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃቶች እንደገና ማሻቀባቸው። ከአንድ ቀን በፊት ወደ ሪያድ የተተኮሰ ሚሳይል መክሸፉ የተገለጸ ሲሆን፣ ግጭቱ በፍጥነት ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊስፋፋ እንደሚችል ተስጋቷል።👉 የሁቲ አማፂያን በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኙ የሲቪል አየር ማረፊያዎችን ጨምሮ መሠረተ ልማቶችን ኢላማ ማድረጋቸው ተጠቅሷል።🇺🇸 በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በመካከለኛው ምስራቅም ሆነ ከዚያ ውጭ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ተቋማትን፣ የንግድ ድርጅቶችን እና ዜጎችን ኢላማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ኤምባሲዎቹ አሳስበዋል።👉በአካባቢው የሚገኙ የአየር ክልሎች በድንገት ሊዘጋጉ ስለሚችሉ፣ የበረራ ሰረዛዎች እና ከፍተኛ የመንገድ መስተጓጎሎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።👉 በዱባይ፣ ዶሃ፣ አቡ ዳቢ፣ ሪያድ እና ጅዳ አየር ማረፊያዎች በኩል የሚያልፉ መንገደኞች ከቤት ከመውጣታቸው በፊት የበረራ ሁኔታቸውን ከአየር መንገዶቻቸው ጋር በቀጥታ እንዲያረጋግጡ ታዟል።👉 በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የሌሉ የአሜሪካ ዜጎች ወደ አካባቢውም ሆነ በአካባቢው አየር ክልል አቋርጠው የሚያደርጉትን ጉዞ "በድጋሚ እንዲያጤኑት" ምክር ተሰጥቷል።🇺🇸 አሜሪካውያን ከሆኑ ተቋማትና


Brook News ብሩክ ኒዉስ
19 сент., 15:57
አርሰናል በ ብራይተን አስደንጋጭ ሽንፈት ደርሶበታል!


Brook News ብሩክ ኒዉስ
19 сент., 15:21
በጉራጌ ዞን (በተለይም በአበሽጌ ወረዳ እና በወልቂጤ ከተማ) እየተባባሰ የመጣውን የደህንነት ስጋት፣ የወሰንና የአስተዳደር ውጥረቶች እንዲሁም ሰሞኑን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠውን ጠንካራ መግለጫ ዝርዝር ሁኔታ ይዳስሳል። https://youtu.be/nPYhoEBv6dU?si=w2ubtk17er9Pj4MiYouTubeበንጹሃን ላይ የተፈጸመው ጥቃት እና የአብን ጥሪ! #EthioVistaበጉራጌ ዞን (በተለይም በአበሽጌ ወረዳ እና በወልቂጤ ከተማ) እየተባባሰ የመጣውን የደህንነት ስጋት፣ የወሰንና የአስተዳደር ውጥረቶች እንዲሁም ሰሞኑን ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠውን ጠንካራ መግለጫ ዝርዝር ሁኔታ ይዳስሳል። በአካባቢው በሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ የንጹሃን ህይወት ማለፍ፣ እገታና መፈናቀል ምክንያት የተፈጠረውን ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ውጥረት በመተንተን፤ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄዎች…
Brook News ብሩክ ኒዉስ
18 сент., 18:16
✈️9ኛ ግዜ ተሸለመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ9ኛ ተከታታይ ዓመት ‘የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ’ ተባለ🌍✈️ ቀዳሚው የአፍሪካ አየር መንገድ በ2026ቱ የስካይትራክስ የዓለም አየር መንገዶች ሽልማት ክብሩን አስጠብቋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኛቸው ሽልማቶችበአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ፣ በአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክላስ የበረራ መስተንግዶ (የምግብ አቅርቦት)፣ በአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክላስ።

