Последние посты

ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 13:24
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ⌚️20'🇸🇩 ሱዳን 0-0 ኢትዮጵያ 🇪🇹🏟 ጁባ ብሔራዊ ስታዲየምTelegram T.me/Dagu_Sport Telegram T.me/DaguLive




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 12:55
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሟሙቆ ወደ መልበሻ ክፍል ተመልሷል።




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 12:07изменён
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ ሱዳንን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመርያ አሰላለፍጨዋታው 10፡00 ይጀምራል።


ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 11:12
የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር በጨዋታ ቀንና ሰዓት!የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዕጣ ማውጣት መስከረም 10/2019 ዓ.ም መከናወኑ ይታወቃል። በዕጣ ማወጣቱ በተገለጸው መሰረት የመጫወቻ ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት የተካተተበት የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብር ይፋ ሆኗል።መስከረም 29/2019 የሚጀምረው የመጀመሪያ ዙር ጥር 9/2019 ይጠናቀቃል። አህጉር አቀፍ ጨዋታ ያለባቸው ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2ተኛው፣ የ3ተኛው እና 4ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሃ ግብር የሚደረጉ ይሆናል።የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 10:40
переслано из @wanawsportwear
ውድ ኢትዮጵያውያን፣ ይህ የእኛ አንድነት የሚደምቅበት ጊዜ ነው!ብሄራዊ ቡድናችን የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 19 🇪🇹 በባህር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ያደርጋል ለዚህም ድል ለዋልያዎቹ! እንመኛለን።ሀገራችንን የምንወድ ሁሉ በአንድ ቀለም በአንድ መንፈስ ፍቅራችንን እና ድጋፋችንን እናሳይ!📍 አዳማ ፍራንኮ ሳራ ሞል 1ኛ ፎቅ 📍ድሬደዋ ሳቢያን ፣ ድሬ ሞል ፊት ለፊት ቢራ ሞል 1ኛ ፎቅ። 📍 ቦሌ ሸዋ ዳቦ ወደ ደንበል አደባባይ ከኦሜዳድ ህንጻ ፊት ለፊት። 📍 ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።


ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
25 сент., 05:22изменён
የጨዋታ ቀን !የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የመጀመሪያ ምድብ ጨዋታ በደቡብ ሱዳን⌚️10፡00 ሰዓት !🇸🇩 ሱዳን ከ ኢትዮጵያ 🇪🇹🏟 ጁባ ብሔራዊ ስታዲየምTelegram T.me/Dagu_Sport Telegram T.me/DaguLive


ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
24 сент., 18:18
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ነገ ከሱዳን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን ከቀኑ 10፡00 በጁባ ብሔራዊ ስታዲየም አከናውኗል። ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት ልምምዳቸውን ማከናውንም ችለዋል።ነገ 10፡00 ላይ በሚደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ፤ የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ሙሉ ነጭ መለያ ለብሰው ወደ ሜዳ ይገባሉ።




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
24 сент., 18:16
ደሴ ከተማ ተጨማሪ ተጨዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል !ከዝህ ቀደም በፉሪ ክ/ከተማ ያለፉትን ዓመታትን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው የመስመር አጥቂው አብዱሰላም አወል ፣ ከዝህ ቀደም በደሴ ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈውና ከዛም ወደ ወላይታ ድቻ በማምራት አንድ ዓመት ከተጫወተ በኃላ ወደ ደሴ ከተማ የተመለሰ የግራ መስመር ተከላካዩ ስንታየሁ ሰለሞን ፣ ከዝህ ቀደም በሱሉልታ ክ/ከተማ ተጫውቶ ካሳለፈ በኃላ ያለፉትን ዓመታትን አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ተጫውቶ ያሳለፈው አማካዩ ሀብታሙ ታደሰ ፣ ከዝህ ቀደም በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ከተጫወተ በኃላ ሀላባ ከተማ እንድሁም ሸገር ከተማ እና አዲስ ከተማ ክ/ከተማ መጫወት የቻለው ተከላካዩ ሙባረክ ጅላሉ ፣ የመስመር አጥቂው አሸናፊ ተስፋዬ ከ ሶሎዳ ዓድዋ እና የቀኝ መስመር ተከላካይ አብዱሰላም አማን ደሴ ከተማን የተቀላቀሉ ተጨዋቾች ናቸው።Telegram T.me/Dagu_Sport Telegram T.me/DaguLive




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 18:20
переслано из @wanawsportwear
3ኛው_ዙር_ዋናው_የዶክተር_ብሩክ አማረ መታሰቢያ የእግር ኳስ ውድድር በአርባምንጭ ከተማ ዝግጅቱን በደማቅ ሁኔታ ተዘጋጅቷል።ከሶስት ዓመት በፊት መስከረም 10 ቀን በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ዶክተር ብሩክ አማረን ለማስታውስና መልካም ስራዎቹን ለመዘከር ቤተሰቡ ከዋናው ስፖርት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት "ዋናው የዶ/ር ብሩክ አማረ ሦስተኛ ዓመት መታሰቢያ የእግርኳስ ውድድር" ከመስከረም 8 እስከ 10 በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።✍️ ለአሸናፊዎች አጓጊ ሽልማቶች የሚበረከቱ ሲሆን፤ በየአንዳንዱ ጨዋታም የላቀ ብቃት ላሳዩ ተጫዋቾች የ Man of the Match ስጦታ ተዘጋጅቷል! 📍ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ። ⭐️ዋናው ወደፊት🔣🔣🔣




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 17:11
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሱዳን ጋር የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ የሚያደርግበት ደቡብ ሱዳን ጁባ በሰላም ደርሷል።




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 15:16
የትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የካፍ ሲ ላይሰንሲ (CAF C Liecence) አሰልጣኞች ስልጠና በመቐለ ከተማ የመጀመርያ ሞጁል መስከረም 07/2019 ተጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል።የመጀመሪያ ዙር በመስከረም 16/2019 የሚጠናቀቅ ሲሆን ሁለተኛ ሞጁል ስልጠና የሚጀምርበት በጥቅምት ወር መጀመርያ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።Telegram T.me/Dagu_Sport Telegram T.me/DaguLive




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 13:19
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል። የኢ/እ/ፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት የቡድኑ አባላትን አበረታተው ሽኝት አድርገዋል።




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 11:44
4ኛው ሚሻላ ካፕየሀላባ ቁሊቶ ከተማ የክረምት እግር ኳስ ሻምፒዮና ውድድር በቀይ ዛላ አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል !⌚️ የሙሉ ሰዓት ውጤት !ሀላባ ሸገር 1-1 ቀይ ዛላጨዋታ በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ቀይ ዛላ 5-4 ሀላባ ሸገርን በማሸነፍ የውድድሩ ሻምፒዮን ሆኗል።መለያ ምት 1⃣2⃣3⃣4⃣5⃣ ሀላባ ሸገር ✅❌✅✅✅ ቀይ ዛላ ✅✅✅✅✅Telegram T.me/Dagu_Sport Telegram T.me/DaguLive




ዳጉ ስፖርት DAGU SPORT
22 сент., 07:12
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ የተዘጋጀው የካፍ ሲ ዲፕሎማ የመጨረሻ ሞጁል ስልጠና ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ ስልጠናው ላለፉት ሦስት ወራት በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ለስልጠናው መሳካት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትልቅ አስተዎጽኦ አበርክቷል። በስልጠናው መዝጊያ ሥነስርዓት ላይ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አሰፈጻሚ እና የውድድር እና ሥነስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ኃይሉ የመዝጊያ ንግግር እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።



