Последние посты

Daily Injera
22 сент., 04:02
እግዚአብሔርን አስቆጥቶ ከሚጠፋ ሕዝብ ጋራ ተነጻጽሮ ጻድቅ ሆኖ መገኘት አንድ ነገር ነው። በእግዚአብሔር መለኪያ ላይ ከፍ ብሎ መገኘት ደግሞ ሌላ፤ “ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት ሰው ነበር፤ አካሄዱንም ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ” (ዘፍ 6፥9)። ኖህ፣ ተለክቶና ተለይቶ የተገኘ ብቻ ሳይሆን፣ የልኬቱን ደረጃ አምላኩን በመከተል ያጸና ነበር። ዓለምን የኮነነው እምነቱ ባካሄዱ ታየ። አካሄዱም መርከቡ ላይ አውጥቶ ሸሸገው።Genesis 6:9 ... Noah was a righteous man, blameless among the people of his time, and he walked faithfully with God.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
21 сент., 04:00
ሔኖክ የኖረው ዕድሜ ጥቂት ነበር። አባቱ ያሬድ 962፣ ልጁ ማቱሣላ ደግሞ 969 ዓመታት ኖረዋል። በንጽጽር ጥቂት በሆነው ዓመቱ ግን መንገዱን ጠበቀ፤ "ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ አደረገ፤ እግዚአብሔር ስለ ወሰደውም አልተገኘም" (ዘፍ 5፥24)። 300 ዓመታት ከእግዚአብሔር ጋራ ሕብረት እያደረገ ኖረ። ያም 'አንሶ' እግዚአብሔር ወሰደው፤ በምድር ያቀረበውን ሰው፣ ይበልጥ እንዲጠጋጋው ወደ ሰማይ ወሰደው። ይህ ሕብረት፣ ከጊዜያዊው ሰው በላይ በዘላለማዊው አምላክ ስንቅ (አቅርቦተ-ማንነት) ላይ ይመሠረታል።Genesis 5:24 Enoch walked faithfully with God; then he was no more, because God took him away.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
20 сент., 04:04
ቃል በእውነት ሲሞላ መልካም ፍሬ ይታያል። በጥበብ ሲሟሽ ደግሞ መድኀኒት (ፍቱን) ይሆናል። ይህም ቃል እንደየአድማጩ ሲቃኝ ነው፤ "ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ በጨው እንደ ተቀመመ ሁልጊዜ በጸጋ የተሞላ ይሁን" (ቈላ 4፥6)። "እያንዳንዱ" እና "ሁልጊዜ" የሚሉት ቃላት ትኩረት የሚደረግባቸው፣ ለቃል መጠንቀቅም ፈጽሞ ቸል ሊባል የማይችል ለመሆኑ አመልካች ነው። ቃል በጸጋ ሲሞላም፣ ከውጤት አይጎድልም።Colossians 4:6 Let your conversation be always full of grace, seasoned with salt, so that you may know how to answer everyone.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
19 сент., 07:27
#ArtSaturdaysቃል ኅይል አለው። ሰዎች በንግግራቸው ይወከላሉ፤ ከዚያም አልፈው ግን ይወሰናሉ፤ የሚናግሩትን ይሆናሉና። ጠቢቡ ሰሎሞን፣ በጥበብ ንግግሩ መካከል እንዲህ አለ፤ "አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ" (ምሳ 18፥21)። ሔዋን በቃል ተሳበች፤ በቃሏም ተያዘች። 'በልብ የሞላ በአፍ' እንደ ተባለ፣ ቃል ልብን እያስከተለና ሕይወትና ሞትን እያማረጠ ኖሯል። አንደበተቻቸውን የሚወድዱም ዝግጅቷን ይከታተላሉ፤ መልካም እርሻ እንደሚታረም ቃላቸውን 'ከአጨዳ' (ከንግግር) በፊት ያርማሉ። የገዛ ቃላቸውን ከቆይታ በኋላ የሚጠሉ እንዳሉ ሁሉ፣ በአንደበታቸው ፍሬ ደስ የሚሰኙ ብዙ ናቸው።Proverbs 18:21 The tongue has the power of life and death, and those who love it will eat its fruit.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
18 сент., 06:17
ጴጥሮስ በእምነታቸው አማካኝነት የተበተኑትን እያጽናና በመልካም አኗኗር እንዲኖሩ ያበረታታል። ቀጥሎም ከመዝሙር በመጥቀስ ያሳስባል፤ “ሕይወትን የሚወድድ፣ መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ፣ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል" (1ጴጥ 3፥10)። መከራ ቢኖርም ተስፋ አለ፤ ስለዚህ ጥንቃቄ ያለበት ዝግጅት ያስፈልጋል። ክፉ ንግግር መልካም ቀንን (ብርሃንን) አያመጣም። የተሻለውን የሚፈልጉም፣ የቀለለውን በመተው ይታወቃሉ።1 Peter 3:10 For, Whoever would love life and see good days must keep their tongue from evil and their lips from deceitful speech.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
17 сент., 04:04
የሰው ቃል በእግዚአብሔር ቃል ላይ ሲያርፍ፣ በቃሉ ይገራል፤ ይሟሻል፤ ይበለጽጋልም—ያፈራል። የቆሬ ልጆች እንዲህ ብለው ተቀኙ፤ "አፌ የጥበብን ቃል ይናገራል፤ የልቤም ሐሳብ ማስተዋልን ይሰጣል" (መዝ 49፥3)። በከበባ መካከል ቢሆኑም፣ በእግዚአብሔር ስለ ታመኑ ልባቸው አስተዋለ፣ ቃላቸውም ጥበብን ገለጠ። ሕይወት አጭር፣ ባለጠግነትም አላፊ እንደ ሆነ ተቀኙ፤ እግዚአብሔር ደግሞ ከሲዖል የሚታደግ ስለ መሆኑ መሰከሩ። ሰዎች በእግዚአብሔር ካልታመኑ በቀር ልባቸው ይከብዳል፤ ዑደቱ ይቀንሳል፤ አቅም ይከዳል። ያረፈ ልብ ግን ጥበብን ያመነጫል። ልብም ለአንደበት ይቀርባል፤ እርስ በርስ ይስማማል።Psalms 49:3 My mouth will speak words of wisdom; the meditation of my heart will give you understanding.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
16 сент., 04:20
አንዳንድ ጸሎት የብዙ ጊዜ ጥረትን ይከተላል። ሞክረው ያልቻሉትን እገዛ ይጠይቁበታል። ዘማሪው የገዛ አንደበትን መቆጣጠር እንደማይቻል ሲገነዘብ፣ አምላኩን ተማጸነ፤ "ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን" (መዝ 19፥14)። ልብ አንደበትን ይገራል። ሐሳብ ሲጠል ነገር ያጥራል፤ ይጠላልም። እግዚአብሔር ደግሞ በተጠራበት ሁሉ ይገኛል። ለሚማጸኑትም ዐለትና ረዳት ነው። እነርሱም ባማረላቸው አንደበት ያከብሩታል።Psalms 19:14 May these words of my mouth and this meditation of my heart be pleasing in your sight, Lord, my Rock and my Redeemer.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
15 сент., 06:53
ቃልና ምራቅ አንድ ነው፤ ወይ ይዋጣል፣ አልያም ይወጣል። በእግዚአብሔር ወይም ስለ አግዚአብሔር የተናገሩት ሲሆን ደግሞ ወዲያው ይሰማል፤ (ሳይወጣ ገና ታውቋልና፤) ኢዮብ ከጥልቅና ሰፊው መከራ የተነሣ ብዙ ተናገረ፤ የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ገለጠ። መስማቱ የማይታወቀውና ሩቅ የሚመስለው እግዚአብሔርም 'ተራው ሲደርስ' መናገር ጀመረ። ከፍጥረቱና ከሥራው አንሥቶም ኅይሉንና ጥበቡን ገለጠ። ኢዮብም እንዲህ አለ፤ "እኔ ከንቱ ሰው፣ ምን እመልስልሃለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ። አንድ ጊዜ ተናገርሁ፤ የምመልሰው የለኝም፤ ሁለተኛም ተናገርሁ፤ ከእንግዲህ አንዳች አልጨምርም" (40፥4-5)። ይህ ከንቱነት ከማጣት—ያለውን ሁሉ ስላጣ—ወይም ከጤና ጉድለት የመጣ አይደለም፤ ካለማወቅ፣ ፈጥኖ ከመናገርና ሳይለዩ ከማውራት የሚመጣ እን። ሰው ሁሉም ለዚህ ከንቱነት ተዳርጓል፤ ካልሰማና ካልተማራ ብዙ ይናገራል፤ ያለ ዕውቀትም ቃላት ያበዛል። በእግዚአብሔር ፊት ዝም ማለትም ኩርፊያ አይደለም፤ አዋቂ አድማጭ መሆን፣ አልፎም መቅረብ ነው።Job 40:4-5 I am unworthy—how can I reply to you? I put my hand over my mouth. I spoke once, but I have no answer— twice, but I will say no more.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
14 сент., 04:01
የሕጉ ርዝመት ከጆሮ እስከ አንደበት ነው። የሰሙትን የሚያምኑም የሚናገሩትን ይኖራሉ። እግዚአብሔር ብርቱውን ጦረኛ ኢያሱን እንዲህ አለው፤ "ይህ የሕግ መጽሐፍ ከአፍህ አይለይ" (1፥8)። ጌታ አምላክ ቃሉ ላይ አለ። ቃሉን የሚጠሩም የስሙን ያህል በሕልውናው ይገናኙታል። ይህን ቃል 'ከሐሳባቸው የማይለዩም' ክንውናቸውን የሚጀምሩ ብቻ ሳይሆን፣ የሚጨርሱም ናቸው።Joshua 1:8 Keep this Book of the Law always on your lips; meditate on it day and night, so that you may be careful to do everything written in it. Then you will be prosperous and successful.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
13 сент., 04:04
ዘመን ይቆጠራል፣ ይቆጥራልም። ዓመታትን ስንቆጥርና ዘመን ለመለወጥ ስንዘጋጅ የእኛንም መቍጠር መማር አለብን። ሙሴ በመዝሙሩ የሚጸልየው ይህንኑ ነው፤ "ጥበብን የተሞላ ልብ ይኖረን ዘንድ፣ ዕድሜያችንን መቍጠር አስተምረን" (መዝ 90፥12)። እንዳሳለፍነው ሁሉ የቀረንን ስናስብ፣ የዘመንን ባለቤት፣ ለሕይወታችን ያለውን ዐላማና ግብ ማሰብ እንጀምራለን። ይህም እንድናስተውል ያደርጋል። በዘመን ግልቢያ ጥበብን የሚማሩም ለጊዜው ለውጥ ልጓም፣ ለዕድሉ ደግሞ አቅምን ይወስዳሉ።Psalms 90:12 Teach us to number our days, that we may gain a heart of wisdom.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
12 сент., 09:42
ዘመን ሲጨመር፣ የጨመረልንን ጌታ ዘመናችን ውስጥ እናስገባለን። ጊዜ ሁሉ የርሱ ቢሆንም ሕይወታችንና ጉዳያችን ውስጥ እርሱን ማስገባት ግን የኛ ፈንታ ነው። ስለዚህም "ዛሬ" ሁሉ እርሱን የምናይበትና ከርሱ ጋራ የምንሠራበት ሊሆን ይገባል። እርሱ፣ "በተወደደ ጊዜ ሰማሁህ፤ በድነት ቀን ረዳሁህ" ብሏልና፤ "እነሆ፤ የተወደደው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳንም ቀን አሁን ነው" (2ቆሮ 6፥2)። ድነት "አሁን" ከሆነ፣ ሥራ ለነገ አይቀጠርም። የዘመን ፍሬ ከዛሬ ይጀምራል።2 Corinthians 6:2 For he says, 'In the time of my favor I heard you, and in the day of salvation I helped you.' I tell you, now is the time of God’s favor, now is the day of salvation.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
11 сент., 04:03
ሰው ወደ አዲስ ዓመት በብዙ ተስፋ ይገባል። የዘላለሙ አምላክ ደግሞ በጎነቱን ይዞ ጊዜን —ዓመትን— ይሞላል፤ በረከቱን ያትረፈርፋል። ዘመኑ ተስፋችሁን በማንነቱና በበጎነቱ የሚሞላበት የተባረከ ዘመን ያድርግላችሁ!መልካም አዲስ ዓመት 🌼Psalms 65:11 You crown the year with your bounty, and your carts overflow with abundance.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
10 сент., 04:00
ጌታ አምላክ ለብዙዎች የተዘነጋ (የማይታሰብ)፣ ለግማሹ ከስንት አንዴ የሚፈለግ፣ ጥቂት ለሚባሉ (አናሳዎች) ደግሞ እንደሌለ የሚቆጠር ነው። ለዘማሪውና ከእርሱም ጋር ለሚቀኙ ግን የዘወትር አለኝታ፣ የማይነቃነቅም ድጋፍ ነው፤ "ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል" (መዝ 94፥22)። አምላካቸውን የሚያውቁ ኀይሉን የተረዱ፣ በጽኑ ዐለትነቱም የታመኑ ናቸው። ለእነርሱ ማወቅ መታመንንና መደገፍን ያተርፍላቸዋል።Psalms 94:22 But the Lord has become my fortress, and my God the rock in whom I take refuge.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
9 сент., 06:17изменён
የተጨነቀ ሰው ጸሎት፣ መልክ (ውበት) ላይኖረው ይችላል፤ መከራም የተዋቡና የሰከኑ ቃላት ተሰካክተው እንዳይወጡ ያደርጋል። ዳዊት በመከራው መካከል ግሩም የሆኑ ቅኔዎችን—መዝሙሮችን—ተቀኝቷል፤ ያም የሆነው እግዚአብሔር ስለ ረዳው ነው። እርሱ መከራውን ገና ሳይነካ (ሳያስወግድ) በመከራ ውስጥ ያሉትን ይነካል፤ ራሱንም ይገልጣል። በአንዱ መዝሙሩም፣ "ጆሮህን ወደ እኔ መልሰህ ስማኝ፤ ፈጥነህ አድነኝ፤ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ" (መዝ 31፥2) ያለበት ተማጽኖ ስለ አምላኩ የገባውን እውነት ይገልጣል። አምላኩም እንደ መረዳቱ እንዲሆንለት ይማጸናል፤ "ዐለት ሁነኝ" በማለት። እግዚአብሔር እንጠራው ዘንድ እየረዳን፣ ስንጠራው የሚመልስልን፣ ተገንና ዕረፍት የሚሆነንም አምላክ ነው።Psalms 31:2 Turn your ear to me, come quickly to my rescue; be my rock of refuge, a strong fortress to save me.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
8 сент., 04:01
ዘዳግም 32 ጸሐፊ ሰማይንና ምድርን ምስክር በመጥራት ይጀምራል። የእግዚአብሔር ስም ስለሚታወጅ "ሰማያት" እና "ምድር" ያደምጡ ዘንድ ተጋብዘዋል፤ የሚነገረው ስለ እግዚአብሔር ነውና። ጸሐፊው (ሙሴ) ቀጠለ፤ "እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው" (ዘዳ 32፥4)። እግዚአብሔር "ዐለት" ነው ሲል፣ እርሱ ፍጹም መመኪያ፣ የማይነቃነቅ መታመኚያና የማይነካ ማረፊያ ነው ማለት ነው። የእርሱ መንገድ—ሐሳብ—ሁልጊዜ "ትክክል" ስለሆነ የሚደገፉበት ከማረፍ አልፈው ይደነቁበታል። Deuteronomy 32:4 He is the Rock, his works are perfect, and all his ways are just. A faithful God who does no wrong, upright and just is he.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
7 сент., 07:33
እግዚአብሔር በመከራ ጊዜ መሸሸጊያ፣ የዘወትርም ማረፊያ ዐለት ነው። ዮሴፍ ገና ከወጣትነቱ የቅናትና ክፋት፣ እንዲሁም የውንድሞች ሴራ ሰለባ (ተጠቂ) ሆኖ ነበር፤ ቀድሞ አብሮነቱን—በሕልም በመገለጥ—ያረጋገጠለት እግዚአብሔር ን አልተለየውም ነበር። ከብዙ ውጣ ውረድ፣ ባርነትና እስራት በኋላ ግን ጌታ አምላክ ከፍ ከፍ አደረገው። ሞቷል ብሎ እርም ያወጣለት አባቱም ካገኘው በኋላ ልጆቹን በየተራ ሲባርክ እንዲህ ብሎለታል፤ "ነገር ግን በያዕቆብ ኀያል አምላክ ክንድ፣ እረኛው በሆነው በእስራኤል ዐለት፣ ቀስቱ ጸና፤ ጠንካራ ክንዱም ቀለጠፈ" (ዘፍ 49፥24)። ቀደም ብሎ "ቀስተኞች በጭካኔ አጠቁት፤ በጥላቻም ነደፉት" ብሎ ነበር። ዮሴፍም በዚያ ሁሉ ጥቃት መካከል ባርነትና እስር ቢገጥመውና ቢወረወርም ያረፈው ይከተለው በነበረው "ዐለት" ላይ ነበር። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርቱ ዐለትና ሕያው እረኛ ስለሆነ፣ የሚታመኑበት መውደቂያ ሳይሆን ማረፊያ ነው ያላቸው።Genesis 49:24 But his bow remained steady, his strong arms stayed limber, because of the hand of the Mighty One of Jacob, because of the Shepherd, the Rock of Israel@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
6 сент., 04:02
እግዚአብሔር ለክብር ጎድሎ የማያውቅ ባለትልቅ ግርማ አምላክ ነው። ክብሩንም ለሕዝቡ ያካፍላል፤ ግርማው በሕዝቡ ላይ፣ ኅይሉም ከደመናት በላይ ነው። ዐይኖቻቸው የተከፈተላቸውም እንደ ዘማሪው ይህንኑ ይመሰክራሉ፦ “ግርማው በእስራኤል ላይ፣ ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣ እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት” (መዝ 68፥34)። ብዙ ነገሮች፣ ያም ችግር፣ መከራ፣ ዕጦት፣ ግራ መጋባት የሰው ልጆችን ይገጥማሉ። የማይነጥፍ (የማይቀንስ) ብርታት ደግሞ የእግዚአብሔር ነው፤ ከእግዚአብሔርም ነው። እርሱ ለሚፈልጉት ይገኛል፤ ብርታታቸውም ይሆናል።Psalms 68:34 Proclaim the power of God, whose majesty is over Israel, whose power is in the heavens.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
5 сент., 05:58
#ArtSaturdaysበመጨረሻ የሚናገሩት ነገር እጅግ አስፈላጊና ሊረሳ የማይገባው ነው። ጳውሎስም ለቆሮንቶስ አማኞች በደብዳቤው ማጠቃለያ “በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ” አላቸው።ድካምና ማመንታት፣ ዝለትና ግራ መጋባት ትልቅ ስፍራም ሆነ የተራዘመ ጊዜ ሊሰጣቸው አይገባም፤ በቶሎ የምናወልቃቸው፣ የምንወጣባቸውም አጋጣሚዎች መሆን አለባቸው። በዚያ ፈንታ ግን በሚያበረታው እየበረታን፣ በሚያግዘው ልንጠነክር ይገባል። የተሰጠንን እምነት ተግተን የምንይዘው ከሆነ ዘወትር ጽናትን ያጎናጽፈናል!1 Corinthians 16:13 Be on your guard; stand firm in the faith; be courageous; be strong.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
4 сент., 05:01
እምነት ከፍ ባደረጓት ጻድቃን ትደምቃለች። የእምነት እምነታቸው የተመሰከረላቸውም የእምነት አባቶች ተብለዋል። የዕብራውያን ጸሐፊ ከአቤል ጀምሮ የተወሰኑትን በስም ከዘረዘረ በኋላ፣ የተቀሩትን በጥቅሉ ጠቀሳቸው፤ "እነዚህ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ...የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀያል ሆኑ፤ ባዕዳን ወታደሮችን አባረሩ" (11፥33-34)። እምነታቸው ታላቅ ለውጥን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ ብዙ አቅምና ኀይል አደረገላቸው። ማመን መበርታት የሚሆነውም "የምድርን መሠረቶች" የያዘው የሰማይ አምላክ የእምነታችን ማረፊያ ሲሆን ነው። ያመኑም ተስፋቸው ጋር ለመድረስ አቅም የሚያገኙ ናቸው።Hebrews 11:33-34 who through faith conquered kingdoms... quenched the fury of the flames, and escaped the edge of the sword; whose weakness was turned to strength; and who became powerful in battle and routed foreign armies.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest


Daily Injera
3 сент., 07:48
አቅምና ብርታት መመሪያን (ሕግን) ሲከተል መታዘዝ ከባድ አይሆንም። ጳውሎስ በኤፌሶን ለነበሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች—ባሎች፣ ሚስቶች፣ ልጆች፣ አሠሪዎችና ሠራተኞች (ባሮች)—ምክር የሰጣል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለሁሉም የሚሆን ማሳሰቢያ ያስቀምጣል፤ "በተረፈ በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ ጠንክሩ" (6፥10)። የሚጠበቅባቸውን ለመሆን፣ የሚፈለግባቸውን ለመፈጸምና ሊደርሱ የሚገባቸው ላይ ለመድረስ በጌታ ሊበረቱ ይገባል። በእርሱ መበርታትም ግሩም ከሆነው ኀይሉ መካፈል ነው። ክፉውን መቋቋም የሚቻለው ከጌታ የተነሳ ብቻ ነው። እርሱ—ማንነቱ—ለተወሰነ ችግር፣ ኀይሉም ለተወሰነ ችግር ወይም ጥቃት ብቻ የሚፈለግ አይደለም፤ ለመሆን እንፈልገዋለን፤ ለማድረግ እንፈልገዋለን፤ እንዲሳካልንም እንፈልገዋለን። ለመጀመር መነሻ እንደ ሆነንም፣ ለመቀጠል እንዲሁ ምክንያታችን እርሱ ነው። እርሱ በደካማ መካከል ልዩነት አያደርግም፤ ሁሉን ግን እኩል ያግዛል።Ephesians 6:10 Finally, be strong in the Lord and in his mighty power.@ethbiblicaTelegram | Facebook | Instagram | Twitter | LinkedIn | Pinterest

Ссылки
