Последние посты

Dashen Bank
23 сент., 12:19
ዝም ብሎ አይከፈትም!ማንኛውንም ማስፈንጠሪያ ወይም ሊንክ ከመክፈትዎ በፊት ላኪውን እና ሊንኩን በትኩረት ያረጋግጡ። የኦንላይን ደህንነትዎን በመጠበቅ ደህንነቱ የተጠበቀ የባንክ አገልግሎት ያግኙ።#DashenBank #CyberSecurity #OnlineSafety #DigitalBanking #Ethiopia #SecurityFirst


Dashen Bank
23 сент., 05:28
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም)👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል።#𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲


Dashen Bank
23 сент., 04:39
የካርድዎን የግብይት ገደብ እርስዎ ይወስኑ!ወደ ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግዎ የዳሸን ሱፐር አፕን በመጠቀም የኤቲኤም ካርድዎን ዕለታዊ የክፍያ እና የመገበያያ ገደብ በቀላሉ ማስተካከል እንደሚችሉ ያውቃሉ?የካርድዎን ገደብ ለማስተካከል እነዚህን ቀላል መንገዶች ይከተሉ፦1. የዳሸን ሱፐር አፕን ይክፈቱ፤ ከመነሻ ገጹ ላይ My Cardsየሚለውን ይ ጫኑ።2. በመቀጠል Local ATMCards የሚለውን ይምረጡ።3. ከ Quick Actionsዝርዝር ውስጥ Card Limit የሚለውን ይጫኑ።4. ለገንዘብ ማውጫ (WithdrawalLimit) ወይምለክፍያ መፈጸሚያ (POS Payment Limit) ማስተካከል የሚፈልጉትን መርጠው Set Limit የሚለውን ይጫኑ።5. የሚፈልጉትን አዲስ የገንዘብ መጠን ያስገቡ፡፡ (ያስታውሱ፡ የሚያስገቡት መጠን ከተፈቀደው አጠቃላይ የክፍያ ገደብ ዎ መብለጥ የለበትም)።6. በመጨረሻም Continueየሚለውን ተጭነው፣ የሚስጥር ቁጥርዎን (PIN) በማስገባት ሂደቱን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቁ።የካርድ አጠቃቀምዎን ይበልጥ ቀላል እና ምቹ ያድርጉ!👉 ስለ አገልግሎቱ የበለጠ ለማወቅ ይህን ሊንክ ይጎብኙ፦ https://dashenbanksc.com/customer-knowledge-cent er/


Dashen Bank
22 сент., 08:51изменён
🎊ግማሽ ትሪሊየን ብር!ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ ከ50 ሚሊዮን በላይ ግብይቶችን በማስተናገድ አጠቃላይ የግብይት መጠኑ ከ ግማሽ ትሪሊየን ብር በላይ ደርሷል።የዲጂታል ፋይናንስ ጉዞአችን አካል ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!#DashenBank #DashenSuperApp #milestone #HalfTrillion


Dashen Bank
22 сент., 07:26изменён
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን መጀመር አስመልክቶ ዳሸን ባንክ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።የዳሸን ባንክ ሰሜን አዲስ አበባ ፣ ምስራቅ አዲስ አበባ እና ሐዋሳ ቀጠና ጽ/ቤቶች ለተማሪዎች የደብተር፣ የቦርሳ፣ እስክሪፕቶና እርሳስ ድጋፍ አደርገዋል።ዳሸን ባንክ የተማሪዎችን የትምህርት ጉዞ በማገዝ በትምህርት ዘርፍ ያለውን ማህበራዊ ኃላፊነት ለመወጣት በማለም ድጋፉን አበርክቷል።ድጋፉን የተቀበሉ ወገኖችም ዳሸን ባንክ የትምህርት መጀመሪያ ወቅትን አስቦ ድጋፍ በማድረጉ የተሰማቸውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል።ከዚህ ቀደም መሰል ድጋፎች በ 11 የዳሸን ባንክ ቀጠና ጽ/ቤቶች ላይ መካሄዱ ይታወሳል፡፡




Dashen Bank
22 сент., 05:23
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም)👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል።#𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲


Dashen Bank
22 сент., 04:52
𝐕𝐚𝐜𝐚𝐧𝐭 𝐏𝐨𝐬𝐢𝐭𝐢𝐨𝐧𝐬· Branch Business Manager I-Dalocha IFBBranch · Branch Business Manager I for Nekemte DistrictFor application and more information, please follow this link: https://dashenbanksc.com/careers/


Dashen Bank
21 сент., 08:18
የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 6ተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን በዳሸን ባንክ ዋና መስሪያ ቤት አካሄደየኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር 6ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የማህበሩ ፕሬዝደንት አቶ አብዱልቃድር ወለላ "ዳሸን ባንክ ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ላደረገው ትብብር እናመሰግናለን" ብለዋል።አቶ አብዱልቃድር የማህበሩን የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።በሪፓርታቸው ማህበሩ በአቅም ግንባታ ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መታየታቸውን ያመላከቱ ሲሆን ለማህበሩ አባላት በርካታ ወርክሾፕ እና ስልጠናዎች ከዓለም አቀፍና ሐገር በቀል ተቋማት ጋር በመተባበር መሰጠታቸውን ተናግረዋል።በ2013 ዓ.ም በዘርፉ የረጅም ጊዜ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎች የተመሰረተው የኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር እና ዳሸን ባንክ የተለያዩ ስራዎችን በትብብር ይሰራሉ። በዚህም ለባለሙያዎች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉባቸው ስልጠናዎችን እንዲያገኙ ይደረጋል።ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ባለሙያዎች ማህበር ቋሚ አባል በመሆን እየሰራ ሲሆን ዘርፉ እንዲያድግ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።




Dashen Bank
21 сент., 05:53изменён
ATM Card ሳልይዝ፣ ካሽም የለኝም ድሮ ቀረ!➡️ ሱፐር አፕን ይክፈቱ ➔ See More ➔ Cardless Withdrawal ይምረጡ። ➡️Generate Voucher የሚለውን ይጫኑ። ➡️ተቀባይ ይምረጡ፦ -Self (ለራስዎ ከሆነ) -Others (ለሌላ ሰው ከሆነ የስልክ ቁጥራቸውን ያስገቡ) ➡️የገንዘብ መጠኑን እና ብር የሚቀነስበትን የሂሳብ ቁጥር (Account) ይምረጡ። ➡️Confirm የሚለውን ተጭነው የምስጢር ቁጥርዎን (PIN) ያስገቡ።በስልክዎ የደረሰዎትን ባለ 6 ዲጂት የቫውቸር ቁጥር (Voucher Code) በመጠቀም ከማንኛውም የዳሸን ኤቲኤም ገንዘብዎን ያውጡ። (ማስታወሻ፦ የቫውቸር ቁጥሩ የሚያገለግለው ለ72 ሰዓታት ብቻ ነው!)📱ካርድዎን ከአንድ ቦታ በቀላሉ ያስተዳድሩ https://www.dashensuperapp.com/download#dashenbank #dashensuperapp #ዳሸንባንክ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #CardlessWithdrawal #ATM


Dashen Bank
21 сент., 05:28
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም)👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል።#𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲


Dashen Bank
19 сент., 06:32
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀን ሐሙስ እለት በወዳጅነት አደባባይ በድምቀት መከበሩ ይታወሳል።በዚህ መርሐ-ግብር ላይ የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ በክብር እንግድነት ተገኝተው መልእክት አስተላልፈዋል።ተቋሙ ያስመዘገበው የላቀ ስኬት ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ልባዊ ምኞታችንን ለመግለጽ እንወዳለን።ለመላው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሠራተኞች ዳሸን ባንክ እንኳን ለዓመታዊው የቤተሰብ ቀን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።መልካም የሥራ ዘመን።
Dashen Bank
19 сент., 05:34
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም)👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል።#𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲


Dashen Bank
18 сент., 05:51
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በያዝነው ሳምንት መጀመሩ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶ ዳሸን ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል።ባንካችን እያከናወነ ያለው የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሎ በትላንትናው እለት የመቀሌ እና ደቡብ አዲስ አበባ ቀጠና ጽ/ቤቶች ለተማሪዎች የደብተር፣ የቦርሳ፣ እስክሪፕቶና እርሳስ ድጋፍ አድርገዋል።በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ካበረከቱት ድጋፍ ባሻገር የዳሸን ባንክ ድሬዳዋ ቀጠና ጽ/ቤት በጅግጅጋ ከተማ እንዲሁም የወላይታ ቀጠና ጽ/ቤት በሶዶ ከተማ ላይ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደርገዋል።




Dashen Bank
18 сент., 05:20
የእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን (መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም)👉👉👉 በዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊዎች ገንዘብ ሲላክልዎ ዳሸን ባንክ በእለቱ የምንዛሪ ተመን የሚሰላ የ10% የማበረታቻ ቦነስ ያበረክትልዎታል።#𝐭𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 #𝐛𝐚𝐧𝐤 #𝐝𝐚𝐢𝐥𝐲 #𝐜𝐮𝐫𝐫𝐞𝐧𝐜𝐲


Dashen Bank
18 сент., 03:56
የ5% ተመላሽ ተጠቃሚ ይሁኑ!ከነሐሴ 26 እስከ መስከረም 30/ 2019 ድረስ ማንኛውንም ግብይትዎን ከዳሸን ባንክ ጋር በጋራ ከሚሰሩ ተቋማት በሸሪክ እና አን-ኒሳእ ካርድዎ፣ በፖዝ ማሽን እንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሱፐር አፕ ተጠቃሚዎች ኪውአር ኮድን ተጠቅመው ክፍያ በመፈጸም የ5% ተመላሽ ተጠቃሚ ይሁኑ።ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ።#Ethiopia #ኢትዮጵያ #cashback #DashenBank #Sharik #IFB


Dashen Bank
17 сент., 13:22изменён
ዳሸን ባንክ ከ25 ቢሊየን ብር በላይ በቴሌብር የብድር አገልግሎት አቀረበ!ዳሸን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በነበረው ስራቴጂካዊ አጋርነት ባለፉት አራት ዓመታት ከ25 ቢሊየን ብር በላይ የብድር አገልግሎት በቴሌብር በኩል ማቅረቡን ስንገልጽ ታላቅ ደስታ ይሰማናል።እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም በቴሌብር ላይ በሚገኙት መላና እንደኪሴ ከ3.2 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የብድር አገልግሎት ባንካችን ያቀረበ ሲሆን ከ15.7 ሚሊየን በላይ የብድር ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል።በዚህ አጋጣሚ የፋይናንስ አካታችነትን ለማረጋገጥ የምናከናውናቸውን ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ይበልጥ አጠናክረን እንደምንቀጥል ለመግለጽ እንወዳለን።#FinancialInclusion #ኢትዮጵያ #DigitalBanking #DashenBank #Telebirr #EthioTelecom #Fintech #Ethiopia #Innovation


Dashen Bank
17 сент., 09:17
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን መጀመር አስመልክቶ ዳሸን ባንክ እያከናወነ ያለው የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።የዳሸን ባንክ ወላይታ እና ምዕራብ አዲስ አበባ ቀጠና ጽ/ቤቶች ለተማሪዎች የደብተር፣ የቦርሳ፣ እስክሪፕቶና እርሳስ ድጋፍ አድርገዋል።ከዚህ ቀደም መሰል ድጋፎች በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ድጋፎች የተከናወኑ ሲሆን በቀሪዎቹም የባንኩ ቀጠና ጽ/ቤቶች ድጋፉ ይቀጥላል።



