Последние посты

dinel_islam
22 сент., 19:00
የመኝታ አደብና ዚክሮች
dinel_islam
22 сент., 17:38
በእያንዳንዱ ሳቅህ ፈጣሪን ካላመሰገንክ...ስለ እንባህ አትውቀሰው!
dinel_islam
22 сент., 17:12
በየቤቱ ሁሉ፣ ጨዋ፣ ጥብቅ፣ ሐላልን ናፋቂ ፣ አላህን ፈሪ የሆኑ ወጣት ሴቶች አሉ።መልካም ትዳር ይመኛሉ ፣ ጥሩ ቤተሰብ ያልማሉ፣በመልካሙ ሥምህ እና በላቁ ባህርያትህ ለመንህ፣ አላህ ሆይ አሳካላቸው።
dinel_islam
21 сент., 19:00
ደህናነኝ ብለህ ማለፍ እየቻልክ ብዙ አውርተህ አትገመት. ...🤝
dinel_islam
21 сент., 18:58
አስቸጋሪ የሚሆነው ምን መሰለህ? … እንደክፍት መፅሃፍ መሆን። የቀረበህ ሁሉ ፣ አላፊ አግዳሚው ሁሉ የሚያነብህ አይነት ሰው መሆን። አንዳንዱ አየር ላይ አንብቦህ ቦታ አይሰጥህም፣ አንዳንዱ በተሳሳተ መንገድ ይረዳዋል… እና የህይወትህን አንድ ፊደል እንኳን ማንበብ የማይገባቸውም ሰዎች ሀሳብ ሊሰጡብህ ይመጣሉ። … እና ክፍት መሆን ጥሩ አይመስለኝም።
dinel_islam
21 сент., 18:57
"በጨለማ ወደ መስጂድ የሚሄዱን ሰዎችን የቂያማ ቀን ሙሉ በሆነ ብርሃን አበስራቸዉ"ረሱልﷺ
dinel_islam
21 сент., 18:43
ሸይኽ ዐዲልን (ሐፊዘሁላህ) የተወሰኑ ፈትዋ አዘል ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ሞክሬ አውቃለሁ። አንድም ቀን ፈትዋን በፍጥነት ሲመልሱ ገጥሞኝ አያውቅም። ባሳለፍነው አመት አንድ መድረክ አሰናድቼ በወረቀት ከመጡላቸው ጥያቄዎች ውስጥ የፈትዋ አዘል ጥያቄዎችን የሚመልሱበት አግባብ ይገርመኛል። ከልጅነት ጀምሮ በዒልም ማዕድ ላይ ኖረው፣ የሐጂ ዘይኔ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ዱዓ አግኝተው። ከውጭ ሐገራት መሻኢኾች ብዙ ተምረው መጥተው ለፈትዋ በፍጹም አይቸኩሉም። ፈትዋ አዘል ጥያቄዎችንም ሲሰጡ የታላላቅ የሻፍዒያ ሊቃውንቶች ያሉትን ያስደግፋሉ። የራሳቸው Bias አለያ የቡድንተኝነት ተጽዕኖ እንዳይኖረው የዒልም አደብን (አደራን) ይጠብቃሉ። ይህ ሲፋቸው ቀደምት የሐበሻ ሊቃውንቶችን ያስታውሰኛል። አቴንሽን ለመፈለግ ዛሬ ካሜራ ላይ በሁለትና በሦስት ደቂቃ ፈትዋ ያከፋፍላሉ። አንዳንዴ ፈትዋ ከኪሳቸው ኹላ የሚያወጡ ይመስላሉ።ያ አኺ ከዒልም በፊት አደብ ቅራ!አላህ አደብ ይስጠን ♥


dinel_islam
21 сент., 12:38
በእያንዳንዱ ሳቅህ ፈጣሪን ካላመሰገንክ...ስለ እንባህ አትውቀሰው!
dinel_islam
19 сент., 16:02
አስተውል…« ቀናቸውን በሙሉ በሥራ ተጠምደው የሚያሳልፉ፣ ነገር ግን ብዙም ወደ ግቦቻቸው የማይቀርቡ ሰዎች አሉ። ምክንያቱም የእንቅስቃሴ መብዛት በትክክለኛ አቅጣጫ ለመጓዝ ማረጋገጫ አይደለምና ።»(ዶ/ር ዐብደልከሪም በካ፟ር)በሥራዎች መወጠር ሁሉ እድገት አይደለም፤ እንቅስቃሴም ሁሉ መድረስ አይደለም።
dinel_islam
19 сент., 03:13
የሐጅ ተመን ዋጋ - 98,000 (2012) - በሙፍቲ ዘመን (ራዐ) የሐጅ ተመን ዋጋ - በኮቪድ አልተደረገም (2013) - በሙፍቲ ዘመን (ራዐ) የሐጅ ተመን ዋጋ - በኮቪድ አልተደረገም (2014) - በሙፍቲ ዘመን (ራዐ) የሐጅ ተመን ዋጋ - 241,0000 (2015) - በሙፍቲ ዘመን (ራዐ) የሐጅ ተመን ዋጋ - 465,000 (2016) - በፈንቃዩ ዘመን የሐጅ ተመን ዋጋ - 625,000 (2017) - በፈንቃዩ ዘመን የሐጅ ተመን ዋጋ - ለመደበኛ 740,000 / አንደኛ ደረጃ ቪአይፒ 1,315,000 / ሁለተኛ ደረጃ ቪአይፒ 1,015,000 - (2018) - በፈንቃዩ ዘመንአባታችን ላይ ዶላር ምንዛሬ እስማስከልከል እና ሙሰኞች በሕግ ይጠየቁ ዘመቻ አፋቸው የከፈቱ ሁሉ ዛሬ ተለጉመዋል ጆተኒ መሆናቸውን እናውቃለን።


dinel_islam
17 сент., 18:40
[ በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ አንዲት ጉንዳን « እናንተ ጉንዳኖች ሆይ! ወደ መኖሪያችሁ ግቡ። ሱለይማንና ሠራዊቱ እነርሱ የማያውቁ ሲኾኑ አይሰባብሩዋችሁ።» አለች።] አንነምል፤18አላህ በመጽሐፉ ውስጥ የዚህችን ጉንዳንን ፍርሃት እና ስጋት መዝግቧል! ታዲያ አላህ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የእኔንና የእናንተን ስጋትና ፍርሃት የማያውቅ ይመስለናል?!በፍጹም!በተለያየ ጉዳትና እንግልት ላይ ካለን እርሱን ደጋግመን እንድንጠራው ስለፈለገ ነውና። የሰ^ይጣንን ማሳሳቻ ትተን ወደርሱ ደጃፍ ባርነትን እንከጅልበት። በክፉ አመል፣ እንደፈለገን ስንኾንም የአዛኙን አላህ ኢስቲድራጅ እንጠንቀቅ።አልላሁመ ሰሊ ወሰሊም ዐላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመዲን ወዓላ አሊ ሙሐመድ!


dinel_islam
17 сент., 17:54
ሁሉም ነገር ባለበት ይቀጥላል ብለህ አታስብ… የወጣ ሁሉ ይወርዳል … የኖረ ሁሉ ይሞታል… የማይነጋ ጨለማም አይኖርም… የሆነ ቀን ፀሃይ ራሱ ህጉን ጥሶ፣ ፍፃሜን ለመግለፅ ከምዕራብ የሚወጣበት ጊዜ አለ። የሰዎች ህይወትና የግንኙነት ሂደት ባልታሰበ ሁኔታ ሊለወጥ ይችላል። በጣም የወደደህ በመጨረሻ በጣም ይጠላህ ይሆናል። በጣም የጠላህ ደግሞ በጣም ይወድህ ይሆናል።
dinel_islam
16 сент., 18:56
እድሜ እየጨመራችሁ በመጣችሁ ቁጥር ምን እያስጠላችሁ እና እየቀነሳችሁ መጣችሁ?
dinel_islam
16 сент., 18:06изменён
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ “መልካም ስራ ማለት ከዱኒያ ቆይታህ እየተለየህ ምላስህ በዚክር (አላህን በማውሳት ነው እስቲ ምላሳቹን ሁሌ የምትጠቀሙት ዚክር ምንድነው?
dinel_islam
15 сент., 18:18
መጀመሪያ ሲታዩ ጓደኛሞች ሊመስሉ ይችላሉ ነገር ግን አይደሉም አባትና ልጅ ናቸው..💝አልጀዚራ እንዲህ ሲል ዘግቦታል “መጀመሪያ ሲያዩዋቸው እርስ በርስ የሚመሳሰሉ ጓደኛሞች ይመስላሉነገር ግን የኡምራ ስነ-ስርዓት አብረው ሲፈጽሙ ቪዲዮ የተቀረጹ አባትና ልጅ ናቸው” በማለት አውጥቶታል...💝ማሻአሏህ ማሻአሏህ


dinel_islam
14 сент., 19:57
ዳመናዎች ባይኖሩ የሰማይን ጥራት ባልተረዳን ነበር! ጭንቀቶች ባይኖሩ የውስጥ መረጋጋትን ፀጋ ባላወቅን ነበር! ውድቀቶች ባይኖሩ አብረውን የሚቆሙ እውነተኛ ጓደኞችን ደረጃ ባልተገነዘብን ነበር!
dinel_islam
14 сент., 19:30
«አላህ በሲሳይህ (በሪዝቅህ) ምሎልሃል፤ ስለዚህ አብዝተህ ጭንቀት አትሸከም፤ በተረጋጋ ልብ ጥረት አድርግ።»ይህ ዐቂዳ ነው፤ ይህ ተውሒድ ነው። ይህ ገብቶት የኖረ እምነቱ ብርቱ ነው። በዚህ ውስጥ በእርሱ እርግጠኛ መኾን (የቂን) አልለ፣ በረረጋጋ መንገድ ሰበብ ማድረስ አልለ፣ ከመረበሽና ከውጥረት በእርሱ መጠበቅ አለ፣ ከሌሎች ጋር አለመፎካከርና አላህ የሰጠንን ማወቅና መቀበል አልለ።አላህ ያስረዳና ♥


dinel_islam
14 сент., 15:08
እራሳችንንም ሆነ ልጆቻችንን ከሶሻል ሚዲያ ሸር መጠበቅ አለብን!! ኡስታዝ ሙሀመድ ዚያድ ዳሩል አርቀም የምርቃት ፕሮግራም ላይ የቀረበ
dinel_islam
12 сент., 20:26
ሰዎችን የመናቅ እና አሳንሶ የማየት ክፉ በሽታ ልቦና ውስጥ ከተደበቀ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አንድ ቀን አንደበትን አፈትልኮ አደባባይ ላይ ገሀድ መውጣቱ አይቀሬ ነው። አንድ ሰው በዕውቀትም ሆነ በተከታይ ከፍ ሲል ይበልጥ ትህትናን ሊላበስ ሲገባው በተቃራኒው እብሪት እና ንቀት ውስጥ ሲዘፈቅ ማየት በእጅጉ ያሳዝናል።ኡስታዝ ያውም የመስጂድ ሚንበር ላይ ኸጥብ ሆኖ «አስቀይምሃለሁ» ብሎ መዛቱ በራሱ ምን ያህል ስነ-ምግባር የጎደለው አባባል በመሆኑን ስንገረም ጭራሽ ይሄ አልበቃ ብሎት በእድሜ ብያንስ በ10 ወይም በ15 ዓመት የሚበልጠውን ታላቅ ወንድሙን «አያቴ ትሆናለህ» ብሎ መናገሩ የትዕቢቱን ጥግ በግልፅ የሚያሳይ ነው።ሰው እንዴት ራሱን ሰማይ ላይ ሰቅሎ ሌላውን እንደዚህ አሳንሶ ያያል? «አያቴ ትሆናለህ» ሲል እኮ ራሱን እንደ ትንሽ ልጅ ኡስታዝ መሀመድ ኸድርን ደግሞ ዘመኑ እንዳለፈበት አዛውንት አድርጎ መሳሉ ነው።😁አላሁ ሙስተዐን 💔


dinel_islam
12 сент., 20:05
ዱኒያን "በቃህ" እንጂ "በቃኝ " ተብሎ የተሠናበተ የለም
