Последние посты

Dn Abel Kassahun Mekuria
22 сент., 09:39



Dn Abel Kassahun Mekuria
21 сент., 04:33
"አሁንም አሁንም ወደቅሁ ብሎ የሚያዝን (ተስፋ የሚቆርጥ) አይኑር። ንስሐ የሞተን (በኃጢአት) እንኳን ከመቃብር ታነሣለችና” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Dn Abel Kassahun Mekuria
19 сент., 08:35
“ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል” ዕን 3:19
Dn Abel Kassahun Mekuria
11 сент., 08:40
የጌታውን እናት የሰላምታ ድምጽ ሰምቶ በማኅጸን በደስታ የዘለለውን (የሰገደውን) ጽንስ፣ በንጉሡ ፊት በክፉት የደነሰችው ልጅ አንገቱን አስቆረጠችው።ጽንሱ ስለ ሕይወት መምጣት በጠባቡ አዳራሽ በማኅጸን ሲያመሰግን፣ የሄሮድያዳ ልጅ ግን የነቢዩን ሕይወት ስለ ማስጠፋት በሰፊው የንጉሡ አዳራሽ ዘፈነች።አዲሱ ዓመት የኢትዮጵያ ልጆች በሄሮድያዳ ምክር የማይሄዱበት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተማሩ ሆነው የሚያድጉበት በጎ ዘመን ያድርግልን!!!ዲያቆን አቤል ካሳሁን https://t.me/Dnabel https://youtube.com/channel/UCRvatZyeFOJtXnAjZSOdrZg


Dn Abel Kassahun Mekuria
10 сент., 10:18изменён
+++ የአዲስ ዓመት ስለት +++በኖኅ ዘመን የነበሩት ሰዎች አመጸኞች ሆኑ። የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ እምቢ ብለው መንገዳቸውን በፊታቸው አበላሹ። ምድሪቱንም በግፋቸው ሞሏት። ስለዚህም እግዚአብሔር ከትውልዱ ጻድቅ የነበረው ኖኅና ቤተሰቡን አስቀርቶ ሌሎቹን ከምድር ጋር ያጠፋቸው ዘንድ የጥፋት ውኃን አዘነመ። የታላላቅ ቀላያት ምንጮች ሁሉ ተነደሉ። የሰማይ መስኮቶችም ከፈቱ። ምድር በአምላክ የቁጣ ውኃ ተጥለቀለቀች። በመርከቢቱ ከነበሩት በቀር ምድር አንዲት ነፍስ አልቀረላትም።እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ቁጣ በኋላ በመርከቡ የነበሩትን ኖኅንና እንስሳት አራዊቱን አሰበ። በምድርም ላይ ነፋስን አሳለፈ። የቀላያቱን ምንጮች የሰማዩንም መስኮቶች ደፈነ። ዝናሙንም ከሰማይ ከለከለ። ሞልቶ የነበረውም ውኃ ቀስ በቀስ እየጎደለ መጣ። በመጽሐፈ ኩፋሌ እንደ ተቀመጠው በውኃ ተጥለቅልቃ የነበረችው ምድር ግልጥ ሆና የታየችው በመጀመሪያው ወር መባቻ ላይ ነበር።(ኩፋ 7፥1)ባለ ዘመኖቹ እኛ ልክ በኖኅ ጊዜ እንደ ነበሩት የቀድሞ ሰዎች ክፋታችን ተካክሏል። መንገዳችንን በእግዚአብሔር ፊት አበላሽተናል። ምድርን በግፋችን ሞልተናታል። ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ያወረደው የጥፋት ውኃ ለእኛም ይገባን ነበር። እኛ ግን እርሱ እስኪቀጣንም አልጠበቅንም። እርስ በእርሳችን እየተጋደልን ምድራችንን በጥፋት ደም አጥለቀለቅናት። ወንድም ወንድሙን በጥይት ነደለ፣ በስለትም ሰውነቱን ከፈተ። የቁጣው ደም ከሰው እየመነጨ ምድርን ሸፈነ።ታዲያ በዚህች ጎስቋላ ምድራችን ላይ የፈሰሰውን ደም የሚያደርቅ የይቅርታ ነፋስ መቼ ይነፍሳል?
Dn Abel Kassahun Mekuria
4 сент., 13:51
“እግዚአብሔርን በመውደድ፣ በመንፈሳዊ ንቃት እና በንስሐ ራስህን ካላዘጋጀህበት፤ በትንሣኤ እና ከሞት በኋላ ባለ ዘላለማዊ ሕይወት ማመንህ ምን ጥቅም አለው?”አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
Dn Abel Kassahun Mekuria
3 сент., 10:54изменён
ሰይጣን መንፈሳዊ ሕይወትን ለመኖር ወስነህ ስትጀምር በእነዚህ ሁለት ሐሳቦች ይዋጋሃል።1. አንተ ለዚህ ሕይወት እንደማትሆን እና መቼም እንደማትለወጥ ሹክ ይልሃል። ይህን የሚያደርገው ተስፋ ቆርጠህ የያዝከውን ሩጫ እንድታቆም ነው። የሚገርመው ግን መለወጥ ባትጀምር ኖሮ ሰይጣን “አልተለወጥህም” አይልህም።2. ገና ከመጀመርህ የደረስህ እና ለመፈጸም ጥቂት የቀረህ አስመስሎ ያሳይሃል። ብዙ ርቀህ እንደ ሄድህ አስበህ ልክ እንደ ጥንቸሏ ተዘናግተህ እንድትተኛ እና የጽድቅ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው ትዕቢት እስረኛ እንድትሆን ያደርግሃል። አሁንም ሰይጣን “ደርሰሃል” እያለ ሲክብህ ገና እግርህን ለማንሣት የምትጣጣር እንደ ሆንህ አቅምህን በደንብ ያውቀዋል።ጀማሪ ስትሆን ሰይጣን “አትችልም” ብሎ ተስፋ በማስቆረጥ ወይም “ደርሰሃል” እያለ ያለ ልክ በማመስገን ወጥመዱ ውስጥ ሊጥልህ ይሞክራል።“በሰይጣን እንዳንታለል፤ የእርሱን አሳብ አንስተውምና” 2ኛ ቆሮ 2:11ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelmekuria2@gmail.com
Dn Abel Kassahun Mekuria
1 сент., 06:17
ዝምታ ራሳችንን የምናይበት ጥሩ መጽሔት(መስታወት) ነው። አብዛኛውን ሰዓት በወሬ ተጠምዶ የሚውል ሰው ራሱን የሚመለከትበት እድል አይኖረውም። በሌሎች ኃጢአት ሲፈርድ፣ ሲተችና ሲያማ ስለሚውል የራሱን ስህተትና ውድቀት ለማወቅ ይቸገራል። ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲያወራ የሚውል ሰው የሚያሳዝነው ዝም አለማለቱ ብቻ ሳይሆን የሚጠቅም ነገር የማይናገር መሆኑም ጭምር ነው። ነገር ግን ማር ይስሐቅ እንደሚለው "አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ብዙ ማውራት ባቆመ ጊዜ ወደ ራሱ ይመለሳል። በእግዚአብሔርም ፊት ምግባሩን ማቅናት ይጀምራል"የሥጋ አንደበታችንን መቆጣጠርና ዝም ማስባል ስንችል የነፍስ ጆሮአችን ንቁህ መሆን ይጀምራል። ስለዚህም ነፍሳችን ሳይሰለች ከልባችን ደጅ ቆሞ የሚያንኳኳውን የመልካሙን እረኛ ድምጽ ትሰማለች። ደጇንም ከፍታ ታስገባዋለች። ከእርሱም ጋር ለእራት ትሰየማለች።(ራእይ 3፥20) በእውነት ይህ እንደ ምን ያለ መታደል ነው? ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር "የዝምተኛ ሰው ጆሮ የእግዚአብሔርን ድንቆች ትሰማለች" ያለው ለዚህ ይሆን?!ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelzebahiran@gmail.com
Dn Abel Kassahun Mekuria
30 авг., 19:06
https://youtu.be/ECS9qUjWWyk?si=sH1QwxBfi5Y-txEMYouTubeእንዴት እንግባባ / መምህር አቤል ካሳሁን“አዲሱን ዓመት ለመቀበል ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል…” ዓመት አልፏል። ወጥተናል… ወርደናል… ነግደናል… አትርፈናል… ተምረናል… ሰርተናል… ብዙ ነገር አድርገናል። ግን… ለነፍሳችንስ? እኛ አዲሱን ዓመት በተስፋ ልንቀበል ስንዘጋጅ… መነኮሳትና መነኮሳያትስ የገጠር አብያተክርስትያናትስ ምናልባት… የእርስዎን ትንሽ ልግስና ብቻ። አንድ … ጧፍ…እጣን ዘቢብ…ዕሱም ከበዛ መርፌና ክርም ቢሆን ለእነሱ ትልቅ…
Dn Abel Kassahun Mekuria
25 авг., 11:05
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በግብጽ ስለ ተፈጸመ አንድ ታሪክ ላስታውሳችሁ። በላዕላይ ግብጽ ይኖር የነበረ አንድ ምስጉን ካህን በጊዜው የከተማው ከንቲባ ወደ ሆነው ባለሥልጣን ቢሮ ሄዶ ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት ለከንቲባው ጥያቄ ያቀርብለታል። ይሁን እንጂ ከንቲባው ግን በንቀት ያን የእግዚአብሔር ካህን እያመናጨቀ በጥፊ መትቶ ከቢሮው ያስወጣዋል። በዚህ ድርጊት እጅግ ልቡ ያዘነውም ካህን እንባውን እያፈሰሰ ለአገልግሎት ወደሚጠበቅበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የጸሎት ሥርዓቱን አስጀመረ። ካህኑ በቤተ ክርስቲያን ሆኖ ሲጸልይ ሳለ ያ ከንቲባ በመንገድ ሲሄድ ድንገት ዙሪያው ጨለመበት፣ በፈረስ የተቀመጠ አንድ ሰውም ከመንገዱ አስቁሞ "ለምን ካህኑን እንደዚያ አዋርደህ ሰደብህ?" ሲል ጠየቀው። ከንቲባውም ገና መልስ መስጠት ሳይጀምር ያ ፈረሰኛ ፊቱን በጥፊ ጸፋው። ከምቱ ጥንካሬም የተነሣ አንድ ዓይኑ ጠፋ። ይህ እንደ ሆነም ወዲያው ጨለማው ተገፈፈ። ያ ፈረሰኛ ማን ነው?ካህኑ ሄዶ እንባውን ካፈሰሰለት ከሰማዕቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ውጭ ማን ሊሆን ይችላል።ዲያቆን አቤል ካሳሁን abelmekuria2@gmail.com አዲስ አበባ
Dn Abel Kassahun Mekuria
24 авг., 11:08
አባ ረሳሁት 🙄


Dn Abel Kassahun Mekuria
22 авг., 09:19
በክንፎቻቸው ተሸፋፍነው በፊቱ የሚቆሙለት ቅዱሳን መላእክት፣ ፈጣሪያቸው "እኔ በምድር ወዳጅ አለኝ። እርሱም አብርሃም ነው" ብሎ በነገራቸው ጊዜ እጅግ በመደነቅ ወደ አብርሃም ሄደው "አብርሃም አርከ እግዚአብሔር"/"አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ"/ እያሉ ዘምረውለት ነበር። በእውነት እግዚአብሔር "ወዳጅ አለኝ" ስላላቸው እንዲህ የተደነቁ መላእክት፣ "እኔ በምድር እናት አለኝ" ሲላቸው ምን ያህል ተገርመው ይሆን? እመቤታችንንስ በምን ዓይነት ቃል አመስግነዋት ይሆን?በዛሬው እለት የአምላክን እናት ልዩ በሆነ ምስጋና እና እልልታ ያሳረጓት መላእክት፣ በምድር ሳለች "እይዋት የአምላክን እናት በምድር ትመላለሳለች" እያሉ በስስት የሚያይዋትና መምጣቷን የሚጠባበቁ እመቤታቸው ነበረች። ለዚህም ነው አባቶቻችን በሌሊት ማኅሌት "ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፣ ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ" እያሉ ሲወርቡ ያደሩት።እኛም ንግሥታችንን ወደ ልጇ እልፍኝ ለሸኘንበት፣ መላእክትም እርሷን በደስታ ለተቀበሉባት ለበዓለ ዕርገቷ እንኳን በሰላም አደረሰን!!!ዲያቆን አቤል ካሳሁን ነሐሴ 16፣ 2014 ዓ.ም. ኢየሩሳሌም፣ እስራኤል
Dn Abel Kassahun Mekuria
18 авг., 09:21
ሁለቱ ምስክሮች እንደ ተሰወሩም ወዲያው ቅዱስ ጴጥሮስ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ ሦስት ዳሶች እንሥራ ብሎ ጌታውን ጠየቀ። ሐዋርያው በዚህ ተራራ ላይ መቅረት የፈለገው ያለ ምክንያት አይደለም። መድኃኒታችን አስቀድሞ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ዘንድ ብዙ መከራ ይቀበልና ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲነግራቸው ቅዱስ ጴጥሮስ "አይሁንብህ፤ አይድረስብህ" ሲል ሊከላከለው ሞክሮ ነበር። ለዚህም በጊዜ "ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል" ተብሎ ተገስጾበታል።(ማር 9፥31-33) ይሁን እንጂ አሁንም ቅዱስ ጴጥሮስ ያለውን ሁሉ እድል ተጠቅሞ ጌታን ወደ ኢየሩሳሌም ከመሄድና በካህናት አለቆች እጅ ተላልፎ ከመሰጠት ማስቀረት ስለሚፈልግ "ጌታ ሆይ፦ በዚህ(በታቦር ተራራ) መሆን ለእኛ መልካም ነው" ብሎ ተናገረ።እርሱም ይህን ገና ሲናገር ሳለ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው። ከደመናው "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ። ሐዋርያቱ ይህን ድምጽ የሰሙት ሙሴ እና ኤልያስ ከክርስቶስ ተለይተው ከሄዱ፣ እነርሱም ወድቀው ከነበሩበት ከተነሡ በኋላ ነው። ይህም ከደመናው ውስጥ ሲወጣ ስለ ሰሙት ቃል "ለማን የተነገረ ይሆን?" ብለው እንዳይጠይቁና ምስክርነቱ ለክርስቶስ ብቻ የተሰጠ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ እንዲረዱ ነው። በዚሁም ላይ ደመናው ወርዶ የጋረደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሐዋርያቱንም ጭምር ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደሚነግረን ደመናው ጌታን ብቻ
Dn Abel Kassahun Mekuria
18 авг., 09:21
+++ "የምወደው ልጄ ይህ ነው" +++ጌታችን ከሐዋርያቱ መካከል "አዕማድ መስለው የሚታዩ ያዕቆብና ጴጥሮስ፣ ዮሐንስንም" ወደ ቅዱሱ የታቦር ተራራ ብቻቸውን ይዟቸው ወጣ።(ገላ 2፥9) ከተራራውም ጫፍ ሲደርሱ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የመምህራቸው ፊት እንደ ፀሐይ ሲያበራ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሲሆን ተመለከቱ። እነሆም ከቀደሙት ጻድቃን ታላላቆቹ ሙሴና ኤልያስ በታቦር ተገኝተው ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።እነዚህ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የትንቢታቸው ፍጻሜ ከሆነው ክርስቶስ ጋር ምን ተነጋገሩ? መቼም በጊዜው ከጌታ ጋር ውለው ያድሩ እንደ ነበሩት ተማሪዎቹ ሐዋርያት "አትሙትብን" አይሉትም። በሺህ ለሚቆጠሩ ዓመታት ሱባኤ የያዙለትና ደጅ የጠኑት የድኅነት ተስፋ እናዳይፈጸም "ይቅር አትሙት" እንዴት ይላሉ? ስለዚህ ከብሔረ ሕያዋን የመጣው ኤልያስና ከብሔረ ሙታን የመጣው ሙሴ በአንድ ላይ "በኢየሩሳሌም ሊፈጸም ስላለው ስለ መውጣቱ (ስለ መከራው፣ ሞቱ)" ያነጋግሩት ነበር።(ሉቃ 9፥31)በታቦር ተራራ ላይ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መልእክተኞች ተገናኙ። በባሕር ላይ በእግሩ የተራመደው ጴጥሮስ፣ የኤርትራን ባሕር እጁን ዘርግቶ የከፈለው ሙሴን አየው።(ማቴ 14፥29፣ ዘጸአ 14፥21) የሰማርያ ሰዎች በተቃወሙ ጊዜ "እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው" ያሉ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ከሰማይ እሳት አዝንሞ ሃምሳ አንዱን ወታደሮች ያስበላ ኤልያስን ተመለከቱት።(ሉቃ 9፥54፣ 2ኛ ነገ 1፥10) … ይቀጥላል


Dn Abel Kassahun Mekuria
16 авг., 23:06изменён
የኖኅ መርከብ ፍጥረታትን ሁሉ ከጥፋት ውኃ ከማዳኗ ጀርባ እንዴት እነዚያን ሁሉ ግዙፋን፣ ማዕከላውያን እና ቀሊላን የምድር ፍጥረታት የምትሸከም እና ለሁሉ የምትበቃ መርከብ ሆና ታነጸች የሚለው በጣም የሚያስደንቅ ነገር ነው።በእርግጥ የመርከቢቱን ርዝመት፣ ወርድ እና ከፍታዋን መጥኖ እንዲህ ሥራ ያለው፤ ከእጸዋትም መርጦ “ከጎፈር እንጨት” አዘጋጅ ብሎ ያዘዘው “የፈጠራቸው እና የሚያውቃቸው አምላክ ስለሆነ” መርከቡ ባይሸከማቸውና ባይበቃቸው ነበር የምንገረመው።ዛሬ ግን በኖኅና በልጆቹ ሳይሆን በመለኰት እጅ ስለ ታነጸችው ሕያው መርከብ፥ ወርድና ቁመቷ፣ ጎንና ስፋቷ በሰው መጠን ስለሆነው ስለምትናገረዋ ነባቢት ሐመር ድንግል ማርያም እያሰበ ኅሊናዬ ከመደነቅ አልፎ ተጨነቀ። የኖኅ መርከብ እነዚያን ፍጥረታት መሸከም እንድትችል በመጠንም፣ በስፋትም ትልቅ ሆና ነበር የታነጸችው። ድንግል ማርያም ግን ከዕብራውያን ሴቶች የተለየ ግዘፍ ሳይኖራት፣ በዓለም ያሉትን አንስት በአካል መጠን ሳትበልጣቸው በውስጧ ወርድ ቁመት፣ ላይ ታች፣ ግራ ቀኝ የሌለው፤ እንኳን የኖኅ መርከብ ዓለማት የማይወስኑትን አምላክ ተሸከመችው። ስለዚህ ድንቅ ነገር ከአባ ሕርያቆስ ጋር ሆኖ “ከስፋት ጋር የሆድ መጥበብ” እንደ ምን ያለ ነው? ብሎ ከመገረም በቀር ምን ልንል እንችላለን?የኖኅ መርከብ ምንም ሞገድ ባይሰባብራት ውኃ ባያሰጥማትም እሳት ግን በውስጧ አልያዘችም ነበር። ፊቱ እሳት፣ ልብሱ እሳት፣ ቀሚሱ እሳት የሆነ አምላክ ያደረባት፤ መለኰታዊ ነበልባል የተሳፈረባት የማትቃጠለው መርከብ ድንግል ማርያም ናት!!!ዲያቆን አቤል ካሣሁን የካቲት


Dn Abel Kassahun Mekuria
12 авг., 09:30
ፍርድ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ግን ወንድሞቻችን ላይ በመጨከን ስንት ጊዜ በክርስቶስ የፍርዱ ዙፋን ላይ ተቀመጥን? የሰውን ድካም ሳንረዳ ፈጥነን በመፍረድ ስንት ጊዜ ራሳችንን በእግዚአብሔር ቦታ አስገባን? እስኪ ዮሴፍን እናስበው፡፡ወደ ግብጽ ባሪያ አድርገው በግፍ የሸጡት ወንድሞቹ ከአባታቸው ሞት በኋላ እርሱ ወደ ተሾመበት ግብጽ መምጣት በፈለጉ ጊዜ፣ የክፋታችንን ብድራት ያስከፍለናል ብለው ስለፈሩ ‹‹በደላችንን ተውልን›› ሲሉ መልእክተኛ ልከውበት ነበር፡፡ የዋሁ ዮሴፍም ይህንን ሲሰማ እያለቀሰ እንዲህ አላቸው ‹‹አትፍሩ፤ እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?››፤ አይደለም ሳታውቀው ዐውቀኸው እንኳን በበደለህ ወገንህ ላይ ለመፍረድ ልብህ በከጀለህ ጊዜ ለራስህ የዮሴፍን ጥያቄ ጠይቀው፡፡‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፋንታ ነኝን?›› (ዘፍ 50፡19)ዲያቆን አቤል ካሣሁን abelmekuria2@gmail.com
Dn Abel Kassahun Mekuria
9 авг., 12:18
“የእግዚአብሔር ጆሮዎች ለመስማት ድምፅን የሚጠባበቁ ይመስላቸዋልን? እንዲህስ ካልሆነ ታዲያ የእነርሱ ጮኾ መጸለይ ጎረቤቶቻቸውን የሚያበሳጭ ነገር ከመሆን በቀር ሌላ ምን ጥቅም አለው?”ሊቁ ጠርጠሉስ፣ በእንተ ጸሎትhttps://t.me/Dnabel


Dn Abel Kassahun Mekuria
8 авг., 14:20
የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬበትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25)፣ 2024 ዓ. እ.የሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባል በመሆን በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ።ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሜዳልያ (Medal of St. Ephrem the Syrian) የተባለውን በክብር አበርክታለታለች።እነዚያን ወርቅ የሆኑ አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚወጉ የማር ኤፍሬምን ድርሳናት ከውጭ (በሃይማኖት) ሆኖ መተርጎሙ ሁሌ ያሳዝነኝ ነበር። ታምሞ ግን የሚድንበትን መድኃኒት ተሸክሞ እንደሚቸገር ምስኪን ሰው አድርጌም አስበው ነበር። ድርሳናቱ መቼ ነው ወደሚድንበት መርከብ እየመሩ የሚያስገቡት ብዬ ብዙ ጊዜ እጠይቅ ነበር።ያለፈው ቅዳሜ ግን ይህን ኀዘን የሚሽር የምሥራች ሰማሁ። ለካስ ቅዱሱ የቀጠረለት ቀን ነበር?! ይኸው የኤፍሬም ቀለም የበላውን (ያቃጠለውን) ምሁር ከኦርቶዶክሳዊው ካህን ስር በትሕትና በርከክ ብሎ አየሁት።ይህ መመለስ የቅዱሱ ምልጃ እና በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ያለቀሱ የብዙ የዋሃን ምእመናን እንባ ውጤት ነው።የአበው


Dn Abel Kassahun Mekuria
8 авг., 09:29
“ጉባኤ ኒቅያ” የመጨረሻ ክፍልhttps://youtu.be/pQOrLH_Jch0?si=EoDaeY0tNO0yHUZYYouTubeጉባኤ ኒቅያ ክፍል 3 | ዲያቆን አቤል ካሣሁንEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Dn Abel Kassahun Mekuria
7 авг., 03:47
+++ "እግዚአብሔር የጣላት እሳት" +++በደብተራ ኦሪት በመሠዊያው ላይ የሚነደውና መሥዋዕቱ ይቃጠልበት የነበረው እሳት ከሰማይ የወረደ ነበር። ይህም እሳት ዘወትር እንዳይጠፋ የአሮን ልጆች (ካህናቱ) ማለዳ ማለዳ እንጨት እየጨመሩ እንዲያቀጣጥሉና እንዲያነዱት እግዚአብሔር አዝዟቸዋል።(ዘሌዋ 6፥12) ከማዕጠንት ጀምሮ እስከ እንስሳት በድንኳኑ የሚቀርቡ ማናቸውም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ሁሉ የሚበሉት ከሰማይ በወረደው በዚህ "የእግዚአብሔር እሳት" ነው።ታዲያ ከእለታት በአንዱ ቀን የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እንዲህ አደረጉ። ለእግዚአብሔር የእጣን መሥዋዕት ማቅረብ ፈልገው ለየራሳው ጥናውን (ማዕጠንት) አነሡ። ነገር ግን በጥናው ውስጥ ያደረጉት ከሰማይ የወረደውን "የእግዚአብሔር እሳት" ሳይሆን፣ ከመንደር ጭረው ያመጡትን ወይም ራሳቸው ያቀጣጠሉትን "ሌላ እሳት" ነበር። በዚህም እግዚአብሔር ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት ስላቀረቡ አምላክ ተቆጣ። በፊቱም እሳት ወጥቶ እንዲበላቸው አደረገ። እነርሱም ወዲያው ሞቱ።(ዘሌ 10፥1-3) ሊቀ ካህናቱ አሮንን እየተከተሉ እንዲያገለግሉ የተመረጡት ሁለቱ ልጆቹ ገና አገልግሎታቸውን በቅጡ ሳይጀምሩ ተቀሰፋ። ለመሆኑ እነዚህ ሁለት የኦሪት ወጣት ካህናት የተቀጡበት "የሌላ እሳት" ታሪክ ለሐዲስ ኪዳኑ ዘመን ምን ምሳሌ ይኖረው ይሆን?እግዚአብሔር በኦሪቱ ድንኳን እሳትን እንዳወረደ፣ በሐዲስ ኪዳንም የሰውን ልጅ ለማዳን ከሰማይ ሲወርድ ይዞልን የመጣው እሳት አለ። "እሳተ አምጻእኩ ለብሔር፤ ወምንተ እፈቅድ ዘእንበለ አንድዶታ" - "በምድር ላይ እሳት ልጥል መጣሁ፥ አሁንም የነደደ
