Последние посты

Dn. HaileRaguel
19 сент., 06:32
переслано из @dnhaileraguel
በነገራችን ላይ ሁለቱን (ሥዕሏንና መስቀልን) የጋራ የሚያደርጋቸው ነገር አለ፤ መስቀል የክርስቲያኖች መለያ ምልክት ነው። ይኸውም ነቢዩ ዳዊት:- ❝ለሚፈሩህ ምልክት ሰጠኻቸው፡፡❞ ብሎ ነግሮናል፡፡ መዝ ፶፱፥፬። በአንጻሩ ደግሞ እመቤታችንም የክርስቲያኖች መለያ ምልክት ናት፤ ነቢዩ ኢሳይያስ:- ❝እነሆ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።❞በማለት ነግሮናል:: ኢሳ ፯፥፲፬።(አንድም): መስቀል ዙፋኑ እንደሆነ እመቤታችንም ዙፋኑ ናት፤ በመስቀል ካሣ እንደተፈጸመ በእመቤታችንም ካሣ ተፈጽሟልና። መስቀሉ የቃል ኪዳን ማጽኛ እንደሆነ እመቤታችንም የቃል ኪዳን ማጽኛ ናትና።(አንድም): መስቀል፣ ኪሩቤልና ማርያም ወዳጅ ቃላት ናቸው። ለምን ቢሉ:-- ፫ቱም የፊደላቸው ብዛት ፬ ነው። - ፫ቱም አምላክን ተሸክመዋል። መስቀሉ በተሰቀለ ጊዜ፣ ኪሩቤል መንበሩን በመሸከማቸው፣ ድንግልም በጸነሰችው ጊዜ። - የእመቤታችን ግን ይለያል፤ ፪ቱ በኅድረት (በማደር/አድሮባቸው) ሲሸከሙት፣ የእርሷ ግን በኩነት (በመሆን፣ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ በመንሳት) ነው። ለዚህም ነው ከቅዱስ ኤፍሬም ጋር ሆነን በእሑድ ውዳሴ ማርያም:- ❝ ... አንቺ ከኪሩቤል ትበልጫለሽ...❞ የምንላት።- አባ ጽጌ ድንግልም ❝ዝንቱ መስቀል መንበረ ነበልባል ለኪሩቤል ቢፅ — መስቀል የእሳት (የመለኮት) መንበር የኪሩቤልም ወዳጅ ነው❞ ይላል።(፪/፪)


Dn. HaileRaguel
19 сент., 06:32
переслано из @dnhaileraguel
ጼዴንያ ማርያምመስከረም ፲ ጼዴንያ በምትባል ሀገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ላይ ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር የተገለጠበት ቀን ነው:: ይህቺን ሥዕል የሣላት ወንጌላዊ ሉቃስ ነው:: ስንክሣሩ እንደ መዘገበው ወደ ጼዴንያ ሀገርም የመጣችበት ምክንያት ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች ስሟ ማርታ የምትባል አንዲት ደግ ሴት ነበረች። እመቤታችን ድንግል ማርያምን እጅግ ትወዳት ነበር በሚቻላትም ሁሉ ታገለግላት ነበር:: ከዕለታት አንድ ቀን ስሙ ቴዎድሮስ የሚባል መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አደረ፤ በመልካም አቀባበልም ተቀበለችው በማግስቱም ስትሸኘው:-❝አባት ሆይ የምትሔደው ወዴት ነው?❞ አለችው፤እርሱም:-❝ልሰግድ ወደ ቅድስቲቱ ሀገር ወደ ኢየሩሳሌም❞ አላት።እርሷም:-❝ከእኔ ገንዘብ ወስደህ የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተህ አምጣልኝ❞ አለችው፡፡እርሱም:-❝በራሴ ገንዘብ ገዝቼ በአመጣሁልሽ ጊዜ ገንዘቡን ትለጪኛለሽ❞


Dn. HaileRaguel
11 сент., 07:00
переслано из @dnhaileraguel
ርእሰ ዐውደ ዓመትና ቅዱስ ዮሐንስየቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል ከርእሰ ዐውደ ዓመት በዓል ጋር በአንድ ቀን እንዲከበር የተደረገበት ምክንያት የርእሰ ዐውደ ዓመት ወይም የዘመን መለወጫ በዓል ለአሮጌው ዓመት ጨረሻ፣ ለአዲሱ ዓመት መነሻ በመሆን ለጊዜ አቆጣጠር የሚያገለግል ስለሆነ ነው:: ከዚህ መሠረታዊ ተግባር የተነሣ የቅዱስ ዮሐንስ ታሪክ ከዘመን መለወጫ ጋር በንጽጽራዊ ምሥጢር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር ስላለ ነው። ጥቂቶቹ ስንመለከት ...ቅዱስ ዮሐንስ የተፀነሰው መስከረም ወር ውስጥ መሆኑ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ :- ❝በስድስተኛው ወር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ማርያም ተላከ❞ — ብሎ ነግሮናል - ሉቃስ ፩፥፳፩።ቅዱስ ገብርኤል መጋቢት ፳፱ ቀን ድንግል ማርያም በድንግልና እንደምትፀንስ ባበሠራት ጊዜ እመቤታችን ❝እንደምን ይሆንልኛል?❞ ባለችው ሰዓት :- ❝ኤልሳቤጥ እንኳ ካረጀች ከሸመገለች በኋላ ከፀነሰች ፮ ወር ሆኗታል❞ በማለት ዮሐንስ በተፀነሰ በስድስት ወሩ እመቤታችንን እንዳበሠራት እንረዳለን:: ይህ ከሆነ ከመጋቢት ፳፱ ቀን ጀምረን ወደ ኋላ ብንቆጥር ፮ኛው ወር መስከረም ስለሆነ ዮሐንስ የተፀነሰው በመስከረም ወር እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ከዚህ በመነሣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም ፩ ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም ፰ ቀን የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ ብላ ስታከብር የዮሐንስ መፀነስ በወርኃ መስከረም መሆኑን ለማስገንዘብ መስከረም ፰ ቀን የወላጆቹን የካህኑ ዘካርያስና የቅድስት ኤልሳቤጥን በዓል ከዕንሰተ ዮሐንስ ጋር በማስተባበር ታከብራለች። ስለዚህ


Dn. HaileRaguel
10 сент., 04:28
переслано из @dnhaileraguel
❝እልኸኛ አትሁን ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣልና ይህን ብትይዝ ከዚያም ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው።❞ በማለት እልኸኝነት በእግዚአብሔር ኅሊና ከተፈቀደልን የዕድሜ ገደብ በታች ዘመናችንን በአጭሩ እንደሚያስቀርተናግሯል:: መክ ፯፥፲፰ ። ይህም በንጉሡ በሕዝቅያስ ሕይወት ይታወቃል፡፡ንጉሥ ሕዝቅያስ በትዕቢቱ ዕድሜው ሊያጥር ነበር፣ ሆኖም ግን ብልህ ንጉሥ በመሆኑ ወዲያው ንስሐ ገብቶ ያጠረውን ዕድሜውን ለማራዘም ችሏል:: ዕድሚያችን ለሰው ሁሉ ከተስጠው የዕድሜ ገደብ በታች እንዳይሆን ወይም በአጭሩ እንዳይቀጭ የዕድሜ ማራዘሚያ ቀመሩ ምን እንደሆነ ጥበበኛው ሰሎሞን እንዲህ ሲል ይጠቁመናል:- ❝ፈሪሃ እግዚአብሔር ያነውን መዋዕለ ወዓመተ ረሲዓንስ ይውኅድ — እግዚአብሔር መፍራት ዘመንን ታረዝማለች፥ የኀጥአን ዕድሜ ግን ታጥራለች ታንሳለች።❞ — ምሳ ፲፥፳፯ በማለት እግዚአብሔር የሚወዳቸውን እንዲያመሰግኑት በዘመናቸው እንዲመለክበት ረጅም ዕድሜ እንደሚሰጣቸው፤ የኀጥአን ዕድሜ ግን ለብዙዎች የመኖር ጠንቅ ስለሆነ ጤነኞች የክፋታቸው ሰለባ እንዳይሆኑ ዘመናቸውን እንደሚያሳጥረው ተናግሯል::በመሠረቱ የጥንት ሰዎች በምድር ላይ እስከ ዘጠኝ መቶ ዓመት የመኖር እድል ተሰጥቷቸው ነበር፤ የሰው ልጅ ግን ኀጢአቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎሽ እያገረሽ ምድርን እያበላሽ በመሄዱ እግዚአብሔር የሰው ዕድሜ መርዘሙ ትርጉም ስላጣበት ከዘጠኝ መቶ ወደ መቶ ኻያ፤ ከመቶ ኻያ ወደ ሰማንያ ለመቀነስ ተገዷል፡፡ ዘፍጥ ፮፥፭ ፣ መዝ ፹፱፦፱ነገር ግን ይህ ሕግና መመሪያ በዘመናቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩ፤


Dn. HaileRaguel
10 сент., 04:27
переслано из @dnhaileraguel
ዓመትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ❝ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ፥ ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም — በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።❞ — መዝሙረ ዳዊት ፷፭፥፲፩ዘመን የሚለወጥበት የመስከረም ወር ዘር ዘርተው ተክል ተክለው የሚኖሩ ሐረስተ ምድር በክረምት የዘሩትን ዘር አሽቶ አፍርቶ ምድርም በልምላሜ ተጊጣ እንስሳትም ለምለሙን ሣርግጠው የጠራ ውኃ ተጎንጭተው ጠግበው አምረው የሚታዩበት የልምላሜና የፍሬ ወር ነው። ነቢዩ ዳዊት ❝ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፣ የእግዚአብሔርን ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ እንዲሁ ታሰናዳለህና። ትልምዋን ታረካለህ ቦይዋንም ታስተካክላለህ፤ በነጠብጣብ ታለሰልላታለህ ቡቃያዋንም ትባርካለህ፡ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል:: የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ፡፡ ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፣ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም” ብሎ እንደዘመረው እግዚአብሔር ዓመታትን በቸርነቱ እየለወጠ፤ የበረከት እጁን ሳያጥፍ እየመገበ፤ የሰዎችን ማንነት ሳይለይ ለክፉም ለደጉም፤ ለኀጥኡም ለጻድቁም፣ ለድሀውም ለሀብታሙም፣ ለአሕዛብም ለሕዝቡም የምሕረት ዝናቡን እያወረደ ፍጥረትን በሙሉ የሚያረካ አምላክ እርሱ ብቻ መሆኑን ያስገነዝበናል:: እንዲሁም ሥነ ፍጥረትን ብንመረምርየበጋና የክረምት መፈራረቅ፤ ተራሮች በዝናብ መርካታቸው፤ ከድርቀት (ከፀሐይ) ወራት በኋላ የሚመጡት የበረከት ጊዜያት እንዴት ባለ በሚያስደንቅ ሁኔታ የምድሪቱን ገጽታ እንደሚቀይር እንገነዘባለን፡፡


Dn. HaileRaguel
7 сент., 07:05
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክትነገ ጳጉሜ ፫ ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሩፋኤል በዓሉ ነው፡፡ እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው። ደግሞም ከእስክንድርያ ውጪ በደሴት የታነጸች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጠባት የከበረችበት ነው።ልዑል እግዚአብሔር በዕለተ እሑድ ሰባቱን ሰማያት ከፈጠረ በኋላ ሊቁ በአክሲማሮስ እንደገለጸው ከቅዱሳን መላእክት መካከል፦❝ወእምዝ ነሥአ እግዚአብሔር እምሠራዊተ ሩፋኤል ፳ወ፬ተ ሊቃናተ ወአቀሞሙ ዐውደ መንበሩ፤ ወሰመዮሙ ለእሙንቱ ካህናተ ስማይ ወወሀቦሙ ማዕጠንታተ ዘእምወርቀ እሳት ወአክሊላተ ብርሃን ዘእምጳዝዮን ወአብትረ ዘከተማሆን መስቀል ወአልበሶሙ አልባሰ ክህነት — ከሠራዊተ ሩፋኤል ፳፬ ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አቁሟቸዋል። ቍጥራቸውን ሃያ አራት ማድረጉ በኻያ አራቱ ጊዜያት ጸልየው ሌላውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ዋጋቸውን ተቀብለው የሚኖሩ በመኾናቸው ሲሆን እነዚህንም መላእክት «ካህናተ ሰማይ» ሲላቸው የእሳት የወርቅ ጽና ሲያሲዛቸው የብርሃን አክሊል ጳዝዮን የሚባል የብርሃን ዘውድ ደፍቶላቸዋል፤ የብርሃን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የሆነ ሲያስይዛቸው የብርሃን ካባ ላንቃ ሕብሩ መብረቅ የመሰለ አልብሷቸዋል❞ — ሕዝ ፩፥፲፩ይህ መልአክ ጦቢትን የተራዳ መልአክ ነው፤ ይህ ጦቢት ዐሥሩ ነገድ በ፯፻፳ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ሲማረኩ ዐብሮ የተማረከ ጻድቅ ሰው ነው፤ ይህ ሰውን በመርዳት በደግነቱ የታወቀው ጦቢት ከመንገድ ወድቆ የተገኘ በድን ቀብሮ፤ በዚያው ሌሊት
Dn. HaileRaguel
6 сент., 16:05
переслано из @dnhaileraguel
❝ወደ ተቀደሰችው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ስፍራ ይገቡ ዘንድ አሕዛብን ዝም አላላቸውም፡፡ በሕንፃዋ ላይ ቢሆን በሠራዊቱ ላይም ቢሆን ጻድቅና የዋህ በሆነ በንጉሥ አኖሬዎስ ሕዝብ ላይም ምንም ምን ክፉ ነገር ሳያደርጉ መለሳቸው እንጂ❞ እንዳለ ድርሳነ ሩፋኤል ዘታኅሣሥ፡፡ቅዱስ ሩፋኤል የተጨነቁትን ከጭንቀት የሚያድን መልአክ ነው፡፡ በነሐሴ የሚነበበው የድርሳነ ሩፋኤል ተአምር ላይ ቴዎፍሎስ ለሚባል ሊቀ ጳጳስ ከጭንቀቱ እንደደረስለት ያስረዳናል፦ ይህ ቴዎፍሎስ የሚባል ደግ ጳጳስ እውነትን ስላስተማረ በሮም ሀገር የንጉሡ የወታደር አለቃ ጕድጓድ ቆፈረና በዕንጨት ሳጥን አድርጎ ከጕድጓዱ ውስጥ ጣለው፡፡ ጳጳሱም ምንም ሳይሆን ከሦስት ቀን በኋላ በአራተኛ ቀኑ ቅዱስ ሩፋኤል በአደረገለት ተአምር ከተጣለበት ጕድጓድ በሰላም ወጥቷል፡፡❝አስተርእየኒ ሩፋኤል መልአከ ጥዒና ወፈውስ በራብዕት ዕለት ለአሕይዎ እምአመ ኀተሞ ንጉሥ በንፍቀ ዚአሁ አስተርአይኮ ለብእሲ ቀሲስ — ንጉሥ በራሱ ሳጥን ቆልፎ ከጣለው በኋላ በአራተኛ ቀኑ ልታድነው ለቀሲሱ የተገለጥክለት ፈጣን የማዳንና የሕይወት መልአክ ሩፋኤል ሆይ ለኔም ተገለጥልኝ❞ እንዳለ ደራሲ።የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የበዓሉ መታሰቢያየቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የመታሰቢያው ዕለት ጳጕሜን ሦስት ቀንና ታኅሣሥ ዐሥራ ሦስት ቀን ነው ፤ ታኅሣሥ ዐሥራ ሦስት ቀን አንደኛ በዓለ ሢመቱ ነው:: ሁለተኛ በቴዎዶስዮስ ልጅ በንጉሥ አኖሬዎስ ትእዛዝ ንጉሡ አኖሬዎስ ራሱም ከሠራተኞች ጋር አብሮ እየሠራ በቊስጥንጥንያ ሀገር ቤተ ክርስቲያኗን ከፈጸመ በኋላ ቅዳሴ ቤቱ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን ተከብሯል። ስለ


Dn. HaileRaguel
6 сент., 16:04
переслано из @dnhaileraguel
ዻጉሜንና ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ-መላእክትቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ-መላእክት አንዱ ነው። ሊቀ-መላእክትነቱም ❝መናብርት❞ በሚባሉ መላእክት ላይ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊትም ለማማለድና ትእዛዝ ለመቀበል ከሚቆሙት ሰባቱ መላእክት ሦስተኛው መልአክ ሩፋኤል ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ለሰውና ለእንስሳት ርኅሩኅ መልአክ ነው፡፡ በርኅራኄውም የሰው ልጆች ምሕረትን፣ ብዕልና ክብርን ያገኙ ዘንድ ይልቁንም የመካኖችን ማኅፀናቸውን ይፈታ ዘንድ ወላጆችም ያለ ጽኑ ምጥ ይወልዱ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ቀርቦ እንደሚለምን በቅዱሳን ዘንድ በስፋት የታወቀ መልአክ ነው፡፡በዕብራይስጥ ቋንቋ ❝ሩፋ❞ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት፣ መስተፍሥሒ፣ ድንቅ ማለት ነው፡፡ ❝ኤል❞ ማለትም አምላክ ማለት ስለ ሆነ ሁለቱ ቃላት ሲጣመሩ ሩፋኤል የሚል ይሆናል፡፡ ይህም ከአምላክ የተሰጠ ድንቅ ፈውስ ማለት ነው፡፡❝ስሙሂ ብሂለ ሩፋኤል መስተፍሥሒ ወመድምም ብሂል ወትርጓሜሁ ፈውሰ አምላክ ውእቱ — ሩፋኤል የተባለ ስሙ ደስ የሚያሰኝ ትርጓሜውም ድንቅ የአምላክ ፈውስ❞ — እንዳለ (ድርሳነ ሩፋኤል ዘጥር) እርሱም የሰዎች ነፍሳትን በምልጃው ለማዳን የተሾመ የዋህ መልአክ እንደ ሆነ ነቢዩ ሄኖክ:- ❝ሩፋኤል ፩ዱ እመላእክት ቅዱሳን ዘመናፍስተ ሰብእ — ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ሩፋኤል በሰዎች ነፍሳት ላይ የተሾመ ነው❞ — (ሄኖ፮÷፫) ካለ በኋላ በሌላ አንቀጽ ሁለተኛውም በበሽታው ሁሉ ላይና በሰው ልጆች ቊስል ላይ የተሾመ ❝ቅዱስ ሩፋኤል ነው❞ በማለት ያስረዳናል (ሄኖ፲፥፲፫)።የነፍሳት ጠባቂ ለመሆኑ መጽሐፈ ሜላድ ነፍሳትን ለመጠበቅ በሰዎች


Dn. HaileRaguel
5 сент., 06:00
ጳጉሜ «ጳጉሜ» ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ ጳጕሜን በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ ቅበላ ስድስት ቀን ትሆናለች። በዚህም ሃገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ (Thirteen months of sunshine) በመባል ትታወቃለች፡፡ ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ
Dn. HaileRaguel
5 сент., 05:10
переслано из @dnhaileraguel
ጳጉሜ«ጳጉሜ» ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ ይህም በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን የምትመጣ ናት፡፡ ጳጕሜን በአራት ዓመት አንዴ ማለትም በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ በዘመነ ዮሐንስ ቅበላ ስድስት ቀን ትሆናለች። በዚህም ሃገራችን ኢትዮጵያ የአስራ ሦስት ወራት ጸጋ (Thirteen months of sunshine) በመባል ትታወቃለች፡፡ጳጉሜ በዘመነ ዮሐንስ ስድስት በምትሆንበት ጊዜ ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ህዳር ፲፬ ቀን ይገባና ታህሳስ ፳፰ ቀን ጾሙ ተፈትቶ የልደት በዓል ይከበራል፡፡በቅድስት ቤተክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜ ወር የምንጾመው የፈቃድ ጾም ነው፡፡ ይህም «ጾመ ዮዲት» በመባል ይታወቃል፡፡ ይህ ግን እንደ አንደኛው የፈቃድ ጾም (የጽጌ ጾም) በብዙዋኑ ዘንድ የታወቀ አይደለም፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ እዚህ ላይ ዮዲት ተብላ የተጠቀሰችው በቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ላይ በጥፋት ሥራዋ በተደጋጋሚ የምትጠቀሰው ዮዲት ጉዲት አይደለችም፡፡ወደ ታሪኩ ስንመለስ የፋርስ ንጉስ ናቡከደነጾር በሠራዊቱ ተመክቶ ሹም ጠላት አጥፋ ድንበር አስፋ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበልህ ያላመነውን እያሳመንህ ና ብሎ ለጦር አበጋዙ ለሆሎፎርኒስ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ መጽሐፈ ዮዲት ፪፥፪-፯፡፡ እርሱም እንደታዘዘው በኃይላቸው የታመኑ ፲፪ሺህ እግረኞችንና በፈረስ የተቀመጡ ፲፪ሺህ ጦረኞችን እየመራ ዘምቶ ካመነው እጅ መንሻ እየተቀበለ ያላመነውን እያሳመነ ብዙ ሀገሮችን እያጠፋ ሲሔድ ከአይሁድ ከተማ ደረሰ በዚህም ብዙ ጥፋ በመድረሱ የእስራኤል
Dn. HaileRaguel
29 авг., 17:26
переслано из @dnhaileraguel
ቅዱሳን ጻድቃን በሕይወተ ሥጋ እያሉም በዐጸደ ነፍስ ሆነው በጸሎታቸው ለምንታመን፤ በቃል ኪዳናቸው ለምንማፀን ለእኛ ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነት ነፍስን የምናገኝባቸው ምክንያቶች ናቸው፡፡አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲፪፻፲፪ ዓ.ም በቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ (ቦታው በአሁኑ ሰዓት ደብረ ጽላልሽ ኢቲሳ ተክለ ሃይማኖት ተብሎ ይጠራል)፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው :- ❝አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ — አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው❞ — በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡በተወለዱ በ፲፭ ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፤ በ፳፪ ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ጌርሎስ (ቄርሎስ) ተቀብለዋል፡፡ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም ❝ፍሥሐ ጽዮን❞ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን ሔዱ፡፡ በዚያች ዕለት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ከአውሬ አዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደ ተመረጡ፤ አጋንንትን የማውጣት፣ ተአምራትን የማድረግ ሥልጣን እንደ ተሰጣቸው፤ስማቸውም ❝ተክለ ሃይማኖት❞ እንደሚባል፤ ትርጓሜውም


Dn. HaileRaguel
27 авг., 13:05
አኮቴተ ቁርባን በሁለተኛው ምእት ዓመት መጨረሻ ላይ ጸረ ኑፋቄያት (መድፍነ ኑፋቄያት) በሆነው ድንቅ ሥራው ውስጥ ሄሬኔዎስ ካነሣቸው የተለያዩ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች መካካል፥ የሥርዓተ አምልኮ ሊቃውንት እንደ መመሪያ የሚጠቀሙበት ፅንሰ-አሳብ ይገኝበታል። ኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት የተመሠረተው በቅዱስ ቍርባን ላይ ባለን እምነት መሆኑን በአጽንኦት ሲገልጽ፦ ❝የምናምነው [በትምህርተ] ቍርባን
Dn. HaileRaguel
27 авг., 13:03изменён
አኮቴተ ቁርባንበሁለተኛው ምእት ዓመት መጨረሻ ላይ ጸረ ኑፋቄያት (መድፍነ ኑፋቄያት) በሆነው ድንቅ ሥራው ውስጥ ሄሬኔዎስ ካነሣቸው የተለያዩ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶች መካካል፥ የሥርዓተ አምልኮ ሊቃውንት እንደ መመሪያ የሚጠቀሙበት ፅንሰ-አሳብ ይገኝበታል። ኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት የተመሠረተው በቅዱስ ቍርባን ላይ ባለን እምነት መሆኑን በአጽንኦት ሲገልጽ፦❝የምናምነው [በትምህርተ] ቍርባን ላይ የተመሠረተ ነው። ቅዱስ ቍርባን ደግሞ እምነታችንን ያጸናዋል❞ — ይላል። የቅዱስ ሄሬኔዎስንና የሌሎች ኦርቶዶክሳውያን አባቶችን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በዓለም ያለችው ኦርቶዶከሳዊት ቤተክርስቲያን፥ ቅዱስ ቍርባን የሚከብርበትን የቅዳሴ አገልግሎት የሕልውናዋ መሠረት አድርጋዋለች። በቅዳሴ አምልኮዋን የማትገልጽ ቤተክርስቲያን በፍጹም ኦርቶዶክሳዊት ልትባል አትችልም። ለኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቅዳሴ የልምድ ሥራ ሳይሆን የእግዚአብሔርን መንግሥት በዚህ ምድር የምትለማመድበት ሰማያዊ አምልኮዋ ነው። ስለዚህ መሠረታዊ ትምህርቶችዋ በሙሉ በመጽሐፈ ቅዳሴዋ ይገኛል። ከቅዱስ ሄሬኔዎስ የተማሩ የሥርዓተ አምልኮ ሊቃውንትም በላቲን ቋንቋ፦❝ሌክስ ኦራንዲ፥ ሌክስ ከሪዴንዲ❞ — ብለዋል፣ ይህም የምንጸልየውን እናምነዋለን፥ የምናምነው የምንጸልየው ነው ማለት ሲሆን የቤተክርስቲያን መሠረቱ ሰማያዊው ማዕድ (ቅዱስ ቁርባን) የሚከብርበት ጸሎተ ቅዳሴዋ እንደሆነ ያስረዳል። እያለ ይቀጥላል ... (ገጽ ፹፪-፷፫)የዚህን ወርቅ መጽሐፍ pdf እንደዋዛ ሲዘዋወር ማግኘቴ በጣም ገርሞኛል። ለማንኛውም በተለያየ ምክንያት
Dn. HaileRaguel
27 авг., 06:09изменён
❝ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወአስተበርክ ክሡተ ቅድመ ማኅበራንኪ እሉ እንዘ እቀውም ድርገተ ፈጻሚተ መፍቅድ ማርያም እስእለኪ ስእለተ ጸግውኒ እግዝእትየ ለዓለመ ዓለም ሕይወተ እምእደ እኩያን አጽራርየ አድኅንኒ ሊተ❞ ... .. .[በእነዚህ የአንቺ ማኅበር በሚሆኑ ጉባኤያተኞችሽ መካከል በአንድነት እየቆምኩ በሥዕልሽ ፊት እሰግዳለሁ፤ በግልጽም እንበረከካለሁ፡፡ የልቤን መሻት የምትፈጽሚልኝ ማርያም ሆይ እለምንሻለሁ፤ እመቤቴ ሆይ፥ ለዘለዓለሙ ሕይወትን ስጪኝ፥ ከክፉ ጠላቶቼ እጅም አድኚኝ።]


Dn. HaileRaguel
21 авг., 14:42изменён
ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ❝ይሥዕሉ ሥዕሎ ምስለ ሥዕላ ከመ ይኩን መርሶ መድኃኒት ለእለ ይትነሐፀኑ — ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ። በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ❞— ስንክሳር ዘነሐሴ ፲፮ነሐሴ ፲፮ የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ ሃገር ወደ ሃገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበትም ዕለት ነው። ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እመቤታችንን ዕረፍተ ሞቴን በዕረፍተ ዕለትሽ አድርጊልኝ ይህም ባይሆን በዚህ አሕዛብ ሃገር ተቀብሬ አልቅር ከሚያምኑት ሃገር እቀበር ዘንድ ፍልሰተ ሥጋዬን ከፍልሰተ ሥጋሽ ዕለት አገናኝልኝ ብሎ ተማጽኗት ነበር።ይህም የዕለቱ አርኬ ላይ፦❝ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ፥ እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል ዘተቶስሓ ፍልስተ ዐፅሙ፥ እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ ኀቤሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ❞ — ተብሎ ተገልጿል።የጊዮርጊስ ልመናውንም ተሰምቶለት የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሁኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ ጽኑዕ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።[ዝርዝር ታሪኩን ለጽጌ ማኅሌት ትርጓሜ ከዚህ ቀደም ከጻፍኩት ከዚህኛው ጽሑፍ ማግኘት ይችላሉ (👉🏿) https://t.me/DnHaileRaguel/231]


Dn. HaileRaguel
21 авг., 06:00изменён
( ... ከላይኛው የቀጠለ - ክፍል ፪)ንጉሥ ሰሎሞን እናቱ ቤርሳቤህ ወደ ቤተ መንግሥቱ በመጣች ጊዜ ያደረገውን እዚህች ጋር ላስታውስ፦❝ንጉሡም ሊቀበላት ተነሣ ሳማትም በዙፋኑም ተቀመጠ ለእናቱም ወንበር አስመጣላት በቀኙም ተቀመጠች፡፡ እርሷም አንዲት ታናሽ ልመና እለምንሃለሁ አታሳፍረኝ አለች። ንጉሡም እናቴ ሆይ አላሳፍርሽምና ለምኚኝ አላት❞ — ተብሎ ተጽፏል (፩ኛ ነገ ፪፥፲፱)። «ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ» ተብሎ ደግሞ በወንጌል ተጽፏል (ማቴ ፲፪፥፵፪) ክርስቶስ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከሆነ የክርስቶስ እናትም ከስሎሞን እናት በብዙ እጥፍ ትበልጣለች፡፡ ሰሎሞን ለእናቱ ከስጣት ክብርም በላይ ክርስቶስ ለእናቱ የሰጣት ክብር በእጅጉ ይበልጣል። የሰሎሞን ቤተ መንግሥት በምድር ነው፤ የክርስቶስ ቤተ መንግሥት ግን በሰማይ፡፡መድኀኔዓለም ግን ወደ ሰማያዊው መንግሥቱ እናቱን በጠራት ጊዜ እንደምን ተቀብሏት ይሆን?እንደ ሰሎሞን እናት ወንበር አስመጣላት እንዳንል በሰማይ መቆም መቀመጥ የለም፡፡ ነገር ግን፦❝የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች❞ — ተብሎ ድንግሊቱ ስለተሰጣት ክብር በዳዊት ተጽፏል፡፡ደግሞ ወርቅ መልበሷ ያንሳታል የሚል ካለ ደግሞ፦ «አሕዛብን በብረት በር የሚገዛቸውን» ወንድ ልጅ የወለደችው ድንግል፦❝ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃም ከእግሮችዋ በታች የሆነላት ዐሥራ ሁለትም ከዋክብት አክሊል የሆኑላት አንዲት ሴት ነበረች❞ — ተብሎም ተጽፎላታል (መዝ ፵፬፥፱ ፤ ራእ ፳፪፥፩)።በእውነት ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ድንግል ወደማያልፈው ዓለም ስትሸጋገር የነበራትን የክብር
Dn. HaileRaguel
21 авг., 06:00изменён
የትንሣኤ እናት ትንሣኤየእመቤታችን ትንሣኤ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ ነቢያት ከጥንት ጀምሮ የተገለጠ ነው፡፡ ከነቢያት አንዱ ቅዱስ ዳዊት፦❝አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት❞ — (መዝ ፻፴፩፥፰) ብሎ ዘምሯል፡፡ ፈጣሪዬ ሆይ ምዕመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ስማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሣ አለ፡፡ ታቦት የጽላት ማደሪያ እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም ለክርስቶስ ማደሪያ በመሆኗ «አማናዊት ታቦት» ትባላለች።ንጉሥ ሰሎሞንም፦❝ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ❞ — መኃ ፪፥፲ ብሎ ዘምሮላታል፡፡ እዚህ ላይ «ወዳጄና ውበቴ» የተባለች ነቢዩ ዳዊት፦❝ከክብሩ ውበት ከጽዮን እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል❞ — ብሎ የዘመረላት (መዝ ፵፱፥፪) የእግዚአብሔር የጌትነቱ ውበት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ምክንያቱም የሰው ዘር በሙሉ በሰይጣን ባርነት ተይዞ በጨለማ በነበረበት ጊዜ ብርሃን ክርስቶስን ያስገኘች የፀሐይ መውጫ በመሆኗ እርሷን «ወዳጄ» ይላታልና::ቅዱስ ያሬድ ስለእመቤታችን ትንሣኤ፦❝ዓመታቲሃ ለድንግል እመ ኮነ ስድሳ እምዝ ዓለም ሞት እምድኅረ አፍለሣ ካዕበ በሠረገላ መሠጠ ነፍሳ — የድንግል ዓመቶቿ ስድሳ ሲሆን ከዚህ ዓለም ሞት ካፈለሣት በኋላ ዳግመኛ ነፍሷን በሠረገላ አሳረገ❞ — ሲል ተቀኝቷል። እመቤታችን በውስጥ፥ በአፍአ፣ በነቢብ፣ በገቢር፣ በሐልዮ ፍጹም ነቅዕ የሌለባት ድንጋሌ ሥጋ ድንጋሌ ነፍስ ድንጋሌ ኅሊና የተባበሩላት በነፍስ በሥጋ በልቡና ንጽሕት ቅድስት ልዩ በመሆኗ
Dn. HaileRaguel
19 авг., 05:09изменён
ለማንም አትንገሩጌታችን በፊታቸው ሲለወጥና ከላይ ድምፅ ሲሰሙ ፫ቱ ደቀመዛሙርት በፊቱ ፍግም ብለው ወደቁ፥ በእጅጉም ፈርተው ነበርና የሚናገሩትንና የሚያደርጉትን ሁሉ አያውቁም ነበር። ከዚያ ጌታችን ሐዋርያቱን ዳሰሳቸውና «ተነሡ አትፍሩ» ብሎ አጽናናቸው፡፡ እነርሱም ተነሥተው ባዩ ጊዜ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስና ከእነርሱ በስተቀር ማንንም አላዩም፡፡ ጌታችንም እንዲህ አላቸው፦❝የሰው ልጅ ከሙታን ተለይቶ እስኪነሣ ድረስ ያያችሁትን ሁሉ ለማንም አትንገሩ❞ — ብሎ አስጠነቀቃቸው፡፡ጌታችን ስለምን 'ለማንም አትንገሩ' ብሎ አዘዛቸው? ቢሉ ውዳሴ ከንቱን የሚሻ አይደለምና (ለእኛ አብነት ለመሆን) ከፊቱ የሚቀበለውን መከራ ያውቃልና ከውርደት በኋላ ወደ ክብር መሄዱ የተሻለ መሆኑን ለእኛ ሲያስተምረን ነው፤ ተከብሮ ከመዋረድ ተዋርዶ መከበር ይሻላልና።ሌላው ምሥጢር መጠበቅን ለቅዱሳን ሐዋርያት ለማስተማርና ለማጽናት ነው። ምእመናን የሚነግሯችሁን ኀጢአት ወይም የሰዎችን ገመና በምሥጢር ያዙ፥ ለማንም አትንገሩ ሲል ነው፡፡ ምዕመናን የሠሩትን ኀጢአት ያለምንም ፍርሃት ለካህናት እንዲናገሩ የታዘዙት ካህናቱ ከፈጣሪያቸው ምሥጢር የመደበቅ መመሪያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ስለተቀበሉም ነው (ዛሬ ላይ ሁሉ አደባባይ በወጣበት ግልብ ዘመን የሰዉን ኀጥያት እያወጣ በየሜዳው ለሚያሰጣው ለዚያ ካህን ወየውለት!)፤ ምክንያቱም ለካህናት መናገር ለእግአብሔር መናገር ነውና፡፡ ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም በዜማው ለዚህ ጉዳይ አጽንዖት ሰጥቶበታል፦❝ወሪዶሙ እምደብር እምደብር አዘዞሙ ኢይንግሩ ዘርእዩ በደብር እስከ አመ ይትፌጸም


Dn. HaileRaguel
18 авг., 18:40
ደብረ ታቦርና እመቤታችንተራራ ከሁሉ ከፍ እንደሚል ሁሉ እመቤታችንም ከፍጥረት ሁሉ ከፍ ያለች ናት። በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት የእመቤታችን ደረጃዋ ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ነው። አባ ጽጌ ድንግል፦❝በከመ ይቤ መጽሐፍ ማዕከለ ፈጣሪ ወፍጡራን፥ ለዕረፍት ዘኮንኪ ትእምርተ ኪዳን፤ ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን፥ ብኪ ይትፌሥሑ ጻድቃን፥ ወብኪ ይወፅኡ ኀጥአን እምደይን — መጽሐፍ እንደተናገረው በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ምልክት የሆንሽ፤ የብርሃን ቀን ስንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ አበባ ባለበት ገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል❞ — ብሎ በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ያለች ብቸኛ ፍጥረት መሆኗን ከነምክንያቱ አስረድቶናል።አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ከፍጥረት ሁሉ ከፍ ያለች መሆኗን በረጅም ተራራ መስሎ በሰዓታቱ ሲያመሰግናት እንዲህ አለ፦❝ከረጅም ተራራ የሰው እጅ ሳይነካው የተፈነቀለው ይህ ድንጋይ አንድ ልጅሽ ነው፤ ባለሟልነትሽ የበዛ ድንግል ማርያም ሆይ ከቀዳማዊና ከደኀራዊ ትውልድ ሁሉ ለስምሽ አጠራር ስግደት ይገባል❞ — ሲል ጽኑዕ ዐለትን ያስገኘች ረጅም ተራራ መሆኗን ተናግሯል።ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ደግሞ ይህቺ ረጅም ተራራ የተገኘችው ከተቀደሱ ተራሮች እንደሆነ ሲናገር፦❝መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤ ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ የጽዮንን ደጃፎች ይወዳቸዋል፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል❞ — ሲል በዚች ተራራ እግዚአብሔር እንደከበረ ተናግሯል፡፡ «የተቀደሱ ተራሮች» የተባሉ ከአዳም ጀምሮ እስከ ኢያቄም ድረስ ያሉ
Dn. HaileRaguel
18 авг., 05:39изменён
ነገረ ቡሄ/ቡሔየደብረ ታቦር በዓል መንፈሳዊ ይዘት ያለው ብቻ ሳይሆን ባህላዊናም ይዘት ያለው ተወዳጅ በዓል ነው፤ ይህ ታላቅ በዓል ሲቃረብ ሕፃኑም ሽማግሌውም «ቦሄ ደረሰ» ይላል፡፡ መጀመሪያ ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው? ስንል ብዙ ትርጉም አለው፤ «ቡሄ» ተብሎ በሃሌታው «ሀ» ሲጻፍ የበራ የደመቀ የጎላ ብርሃን ማለት ነው፡፡ «ቡሄ በሉ ማለት ብርሃን ሆነ በሉ» ማለት ነው፡፡(አንድም)መገለጥ ነጭ መሆን ማለት ነው፤ ቡኸየ ተገለጠ ነጣ ማለት ነው። ይኸውም በደብረ ታቦር ቧ ብሎ የተገለጠውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የፊቱን ብርሃነ ጸዳል ልብሱ እንደ በረዶ ፀዐዳ ሆኖ የተገለጠበት የብርሃን ኀይል ነው፡፡(አንድም)ወቅቱን የሚያበሥር ነው፤ ከደብረ ታቦር በዓል በኋላ የከበደው አየር ንብረቱ ቀለል ብሎ መታየቱን ሰማይ እየጠራ ፈገግ እያለ መሄዱን፤ ጭጋጉ ተገፍፎ ጉሙ ተበትኖ ወጋገን መታየት የሚጀምርበት በመሆኑ በሰኔና በሐምሌ ወራት በእርጥበትና በካፊያ ስትናጥ በዶፉና በጎርፉ ስትዋልል የሰነበተችው መሬት የምትረጋጋበትና የምትጸናበት ወቅት መሆኑን የሚያበሥር ነው። አበው «ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት» በማለት የተረቱት ይህን በመገንዘብ ነበር።(አንድም)«ቡሔ» ተብሎ በሐመሩ «ሐ» ከተጻፈ ደስታ ፍስሐ ማለት ነው፡፡ «ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል» ተብሎ የተነገረው ትንቢት የተፈጸመበት ዕለት ነውና::(አንድም)በሓ በግእዝ ደግሞ የቡራኬና የሰላምታ ቃል ነው፤ ይኸውም ሰላም ማለት ነው፤ በታቦርና በአርሞንኤም መንጋዎቻቸውን አሰማርተው ሲያበሉ የነበሩ እረኞች
