Последние посты

Dilla University Official
26 сент., 13:09
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለደመራ እና ለመስቀል በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብ አባላት፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ፤ አደረሰን ማለት እወዳለሁ።የመስቀል በዓል ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ታላላቅ የአደባባይ በዓላት አንዱ ሲሆን፤ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ታሪካዊና መንፈሳዊ እሴት ነው። በዓሉ ከከፍተኛ ሃይማኖታዊ እሴትነቱ በተጨማሪ የሰላም፣ የመቻቻል፣ የይቅርታና የእውነተኛ አብሮነት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ድምቀቱ ከፍ ያለ ነው።በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ ቅርሶች አንዱ ሆኖ የተመዘገበው የደመራ በዓል፣ የሀገራችን ብቻ ሳይሆን የዓለም ሀብት ጭምር በመሆኑ፤ ሁላችንም ይህን ድንቅ እሴት ጠብቀንና ተንከባክበን ለተከታዩ ትውልድ የማስተላለፍ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት አለብን።በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመደገፍ፣ ያለንን ለሌላቸው በማካፈል እና አቅመ ደካማ ወገኖቻችንን በማስታወስ ሊሆን ይገባል።ደመራው የሰላማችን፣ የእድገታችን እና የአንድነታችን ማብሪያ እንዲሆንልን እየተመኘሁ፤ በዓሉ የሰላም፣ የጤና እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ!መልካም የደመራና የመስቀል በዓል!ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት===###===#ዲላ_ዩኒቨርሲቲ #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ


Dilla University Official
21 сент., 15:25
ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ነው =========================ዲ.ዩ: መስከረም 11/2019ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)ዲላ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎቹን እየተቀበለ ይገኛል።ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መደበኛ ተማሪዎችን እየተቀበለ የሚገኝ ሲሆን፣ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እስከ ነገ ድረስ የሚገቡ ይሆናል።ዩኒቨርሲቲው ለመላው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አዲሱ የትምህርት ዘመን የተሳካ እንዲሆን ይመኛል።===###===#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland
Dilla University Official
21 сент., 15:25





Dilla University Official
18 сент., 15:49изменён
📍አዲስ ማስታወቂያ📢በፖስት ቤዚክ የህክምናና የጤና ሳይንስ ፕሮግራሞች በመጀመሪያ ድግሪ መማር ለምትፈልጉ አመልካቾች በሙሉ፣ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ የትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁ መሆኑን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።🎯 የሚሰጡ የትምህርት ፕሮግራሞች📍Medical Laboratory 📍Midwifery 📍Nursing 📍Pharmacyበአካል መመዝገብ ለማትችሉ አመልካቾች ከስር የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙhtpps://portal.du.edu.et/Web/Announcementእንዳያመልጥዎ፣ መረጃውን ለጓደኞችዎ ያጋሩ!#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ


Dilla University Official
18 сент., 05:19
Dilla University Staff Receive Erasmus+ Project Writing Training =========================DU: Meskerem 07/2019EC (PIR)A delegation from the University of Turin, Italy, has provided intensive training to Dilla University staff on writing project proposals for Erasmus+ scholarship opportunities.The training was led by Professor Mauro Tusko and Dr. Valentina De Lacovo, who shared practical strategies for developing competitive proposals.Opening the session, Tamirat Beyene (PhD), Vice President for Academic Affairs, emphasized the importance of collective effort in strengthening international collaborations. “Staff must work in unity to bring such collaboration to the university,” he said, underscoring that project writing should be embraced as a shared responsibility.He further noted that recent policy initiatives and management support would help staff actively participate in
Dilla University Official
18 сент., 05:16





Dilla University Official
16 сент., 19:13
Turin University Delegation Holds High Level Talks at Dilla University ======================DU: Meskerem 06/2019EC (PIR)A delegation from Turin University held an official meeting with Dr. Tolossa Dadi, President of Dilla University, alongside senior management. The session featured presentations from both institutions highlighting areas of potential collaboration.In his remarks, Dr. Tolossa praised the initiative and expressed the University’s strong support for the initiative with Turin University. He emphasized that the agenda should be technically framed and backed by concrete action plans to ensure implementation at the grassroots level.Dr. Tolossa emphasized that joint programs and international mobility are key priorities for Dilla University, noting that the initiative launched now will play a vital role in advancing these objectives.Dr. Julia Bucoli, Officer of
Dilla University Official
16 сент., 19:13





Dilla University Official
16 сент., 14:01изменён
#MissitNot!Invitation to a Presentation on Writing a Research Project for Erasmus Mundus Scholarship Opportunities.We are pleased to cordially invite you to a presentation by Professor Mauro and Dr. Valentina.🎯 Date : September 7, 2019 EC 🎯 Time: 3:00 LT 🎯 Venue: Multipurpose HallYour punctual attendance will be highly appreciated.===###===#UniversityOfTheGreenland


Dilla University Official
13 сент., 20:00
Delegates from the University of Turin Welcomed at Dilla University =======================DU: Meskerem 03/2018EC (PIR)Delegates from Italy’s University of Turin received a warm welcome upon their arrival at Dilla University.Senior leaders of the institution, including Tamrat Beyene (PhD), Vice President for Academic Affairs, and other officials, greeted the Delegates.In his remarks, Tamrat Beyene (PhD)emphasized Dilla University’s commitment to strengthening cooperation with the University of Turin. He highlighted opportunities for joint initiatives, particularly in staff and student exchange programs, which he said would be facilitated under the partnership.Professor Mario Tusko, head of the Turin University's delegation, underscored that strategic collaboration between the two universities would maximize their shared potential and foster mutual growth.During their stay,
Dilla University Official
13 сент., 20:00





Dilla University Official
11 сент., 09:18
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ============ዲዩ: መስከረም 01/2019ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ የ2019ዓ.ም አዲስ ዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈዋል።ዋና ስራ አስፈፃሚው ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት፣ ለማስተማሪያ ሆስፒታሉ ሰራተኞች እና የህክምና ባለሙያዎች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።ዋና ስራ አስፈፃሚው "አዲሱ ዓመት የፍቅር፣ የብልጽግና እንዲሁም የበለጠ ስኬት የምንጎናጸፍበት እንዲሆን እመኛለው" ብለዋል።===###===#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenla


Dilla University Official
11 сент., 09:18
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ============ዲዩ: መስከረም 01/2019ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ማቲዎስ ሀብቴ (ዶ/ር) አዲሱ የ2019ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ለአስተዳደር ሰራተኞች፣ ለአከባቢው ነዋሪዎች እና ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ዶ/ር ማቲዎስ ዩኒቨርሲቲው በአዲሱ ዓመት አዳዲስ የለውጥ ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች መላው የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።ተቋሙ በሁሉም ዘርፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን በአዲሱ ዓመት፣ በአድስ ጉልበት እና በአዲስ አስተሳሰብ መላው የተቋሙ ሰራተኞች በጋራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የስኬት እንዲሆንም ተመኝተዋል።===###===#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland


Dilla University Official
11 сент., 09:18
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ============ዲዩ: መስከረም 01/2019ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚገኙ አጋር አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ምክትል ፕሬዝዳንቱ ያለፈው ዓመት በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ስራዎች በተሳካ መንገድ መከናወናቸውን ጠቁመው፣ የዩኒቨርሲቲው ጆርናሎች እውቅና እንድያገኙ መደረጉ፣ የዲጅታላይዜሽን ስራዎች፣ የቡና ትምህርትን በበይነ መረብ ለመስጠት የተጀመሩ ተግባራት ተጠቃሽ መሆናቸውን ገልፀዋል።የነበሩ መልካም ስራዎች በአዲሱ ዓመት ላይም የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መላው የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በጋራ እንዲሰለፉም ጥሪ አቅርበዋል።===###===#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland
2,029Открыть в TelegramDilla University Official pinned a photo
11 сент., 09:17

Dilla University Official
11 сент., 09:17
የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ============ዲዩ: መስከረም 01/2019ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ታምራት በየነ (ዶ/ር) ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ፣ ለመምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም በመላው ዓለም ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ምክትል ፕሬዝዳንቱ "አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ ሰርተን የምንለወጥበት፣ ከወትሮ በተለየ መልኩ ወደ ግቦቻችን የበለጠ የምንቀርብበት እንዲሆንልን እመኛለው" ብለዋል።አዲሱ ዓመት ላይ በመማር ማስተማር ዘርፍ የበለጠ ተደራሽ ለመሆን፣ ገበያው ላይ ተፈላጊ የሆኑ የቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለማስፋት የጀመርነውን እንቅስቃሴ የምናስቀጥልበት ይሆናል ብለዋል።ምክትል ፕሬዝዳንቱ አዲሱ ዓመት የስኬት፣ የአንድነት እና የፍቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል።===###===#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland


Dilla University Official
11 сент., 07:36
🌼እንኳን አደረሳችሁ🌼የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት!#የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ #UniversityOfTheGreenland
