Последние посты

Dr. Eyob Mamo
22 сент., 12:59
ከቤትዎ ሆነው ስራዎትንወደ ገቢ ይቀይሩ! Upwork Freelancing Full Course Upwork ላይ ፕሮፋይል ማዘጋጀት፣ ስራ መፈለግ፣ Proposal መጻፍ እና ደንበኛ ማግኘት ይማሩ። 15 Videos + PDF ክህሎትዎን ወደ ዶላር ገቢ ይቀይሩ!ተጨማሪ ስጦታ! በዳውንሎዱ ውስጥ ሙሉ የግራፊክስ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠናዎች በአማርኛ ተካትተዋል! አሁኑኑ ይጀምሩ!https://ye-buna.com/penielterefe?ref=product_detail&product=6aae1ef33e5d8_penielterefeሌሎች የወርክሾፕ ስልጠናዎች።1.ለግራፊክ ዲዛይነሮች እና content creator የተዘጋጀ የ AI ስልጠና፤ በ 2 ሰዓት ውስጥ የፈጠራ ችሎታዎን ከፍ ያድርጉ።2.Web Design in WordPress፤ ከ 6 እስከ 8 ሳምንት በባለሙያ የታገዘ፤ plus mentorship.የተወሰኑ ቦታዎች ብቻ ስለቀሩ እንዳያመልጥዎት አሁኑኑ ይመዝገቡ! 📞 ስልክ: 0906556409 / 0777893589
Dr. Eyob Mamo
22 сент., 09:20изменён
የ2019 ዓመት የጅማሬ ስልጠና!የስልጠናው ርእስ፡-“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (ውጤታማ የምክር አሰጣጥ ተግባራዊ መመሪያ)Counseling Skills and Techniques (A Practical Guide to Effective Counseling)ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)የስልጠናው ቀናት፡- ጥቅምት 05/2019፣ ጥቅምት 12/2019፣ ጥቅምት 19/2019 እና ጥቅምት 26/2019 (አራት ኃሙሶች)የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)ስልጠናው ለማን ይጠቅማል?-💡 በማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ለተሰማሩና የሕብረተሰቡን የስነ-ልቦና ሁኔታ ለመፍታት ለሚፈልጉ!
Dr. Eyob Mamo
22 сент., 02:01
የ2 ደቂቃ ሕግ (The 2-Minute Rule)የ2 ደቂቃ ሕግ ቀላል የሥራ አመራር መርህ ነው።አንድ ሥራ ከ2 ደቂቃ በታች የሚወስድ ከሆነ፣ ለወደፊት አታስተላልፉት፤ ወዲያውኑ አድርጉት!የዚህ ሕግ ጥቅሙ!✔️ ትንንሽ ሥራዎች እንዳይከማቹ ይከላከላል✔️ ትንንሽ ሥራዎችን እያስተላለፍን ስናዘገያቸው፣ በመጨረሻ ብዙ ሥራ ይሆናሉ።✔️ የአእምሮ ጫናን ይቀንሳል✔️ ያልተጠናቀቁ ትንንሽ ሥራዎች በአእምሮአችን ቦታ ይይዛሉ። ወዲያውኑ ማጠናቀቃቸው ነፃ ያደርገናል።✔️ የእርምጃ ልምድን ይገነባል✔️ “በኋላ አደርገዋለሁ” ከማለት ይልቅ “አሁን አደርገዋለሁ” የሚል አመለካከት ይገነባል።
Dr. Eyob Mamo
21 сент., 14:59
ከቤትዎ ሆነው ስራዎትን ወደ ገቢ ይቀይሩ! Upwork Freelancing Full Course Upwork ላይ ፕሮፋይል ማዘጋጀት፣ ስራ መፈለግ፣ Proposal መጻፍ እና ደንበኛ ማግኘት ይማሩ። 15 Videos + PDF ክህሎትዎን ወደ ዶላር ገቢ ይቀይሩ!ተጨማሪ ስጦታ! በዳውንሎዱ ውስጥ ሙሉ የግራፊክስ ዲዛይን እና የቪዲዮ ኤዲቲንግ ስልጠናዎች በአማርኛ ተካትተዋል! አሁኑኑ ይጀምሩ! ለማንኛውም ጥያቄዎች: በ+251 90 655 6409 ይደውሉhttps://ye-buna.com/penielterefe?ref=product_detail&product=6aae1ef33e5d8_penielterefe
Dr. Eyob Mamo
21 сент., 12:04
የ2019 ዓመት የጅማሬ ስልጠና!የስልጠናው ርእስ፡-“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (ውጤታማ የምክር አሰጣጥ ተግባራዊ መመሪያ)Counseling Skills and Techniques (A Practical Guide to Effective Counseling)ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)የስልጠናው ቀናት፡- ጥቅምት 05/2019፣ ጥቅምት 12/2019፣ ጥቅምት 19/2019 እና ጥቅምት 26/2019 (አራት ኃሙሶች)የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)ስልጠናው ለማን ይጠቅማል?-💡 በማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ለተሰማሩና የሕብረተሰቡን የስነ-ልቦና ሁኔታ ለመፍታት ለሚፈልጉ!
Dr. Eyob Mamo
21 сент., 01:59
መቋቋም (Coping) እና ችግርን መፍታት/መጋፈጥ (Dealing)አንዳንድ ችግሮች ሲገጥሙን ከእነዚህ አቀራረቦች መካከል የትኛውን መጠቀም እንዳለብን በጥንቃቄ መለየት አስፈላጊ ነው፡፡መቋቋም (Coping) ማለት ሁኔታውን ወዲያውኑ መቀየር ባንችልም፣ የሚያመጣውን ጭንቀትና ተፅዕኖ በጤናማ መንገድ መቆጣጠር ነው።መፍታት/መጋፈጥ (Dealing) ማለት ችግሩን በቀጥታ መመልከት፣ የሚቻለውን እርምጃ መውሰድና መፍትሔ መፈለግ ነው።የመቋቋምን መንገድ የምንጠቀምበት ጊዜ• ሁኔታውን ወዲያውኑ መቀየር ሳትችሉ ስትቀሩ • ከአቅማችሁ ውጭ የሆነ ነገር ሲሆን • ስሜታችሁን መጀመሪያ ማረጋጋት ሲያስፈልግ • ሁኔታው ጊዜያዊ ችግር ሲሆንምሳሌ፦ ስራችሁን በድንገት ብታጡ፣ መጀመሪያ ፍርሃትና ተስፋ መቁረጥን መቋቋም ያስፈልጋል፤ ከዚያ ሌላ ሥራ መፈለግ ይችላል።የመጋፈጥ/መፍታትን መንገድ የምንጠቀምበት ጊዜ• ችግሩን ለመቀየር ተፅዕኖ የማሳደር አቅም ሲኖራችሁTelegramDr. Eyob MamoLife skill development! You can contact me @DrEyobmamo
Dr. Eyob Mamo
21 сент., 01:58
መቋቋም (Coping) እና ችግርን መፍታት/መጋፈጥ (Dealing)
Dr. Eyob Mamo
20 сент., 14:56
ከቤትዎ ሆነው ስራዎትን ወደ ገቢ ይቀይሩ! Upwork Freelancing Full Course Upwork ላይ ፕሮፋይል ማዘጋጀት፣ ስራ መፈለግ፣ Proposal መጻፍ እና ደንበኛ ማግኘት ይማሩ። 15 Videos + PDF ክህሎትዎን ወደ ዶላር ገቢ ይቀይሩ! አሁኑኑ ይጀምሩ! https://ye-buna.com/penielterefe?ref=product_detail&product=6aae1ef33e5d8_penielterefe
Dr. Eyob Mamo
20 сент., 05:59
የ2019 ዓመት የጅማሬ ስልጠና!የስልጠናው ርእስ፡-“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (ውጤታማ የምክር አሰጣጥ ተግባራዊ መመሪያ)Counseling Skills and Techniques (A Practical Guide to Effective Counseling)ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)የስልጠናው ቀናት፡- ጥቅምት 05/2019፣ ጥቅምት 12/2019፣ ጥቅምት 19/2019 እና ጥቅምት 26/2019 (አራት ኃሙሶች)የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)ስልጠናው ለማን ይጠቅማል?-💡 በማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ለተሰማሩና የሕብረተሰቡን የስነ-ልቦና ሁኔታ ለመፍታት ለሚፈልጉ!
Dr. Eyob Mamo
20 сент., 04:33
ሁለቱ ስህተቶችብዙ ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚፈልጉና በውስጣቸው የሚያነሳሳቸውን ነገር የማወቅ ችግር የለባቸውም፡፡ ነገር ግን ያንን ሳያደርጉት ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ ይህ የሚሆንበት ምንክንያት ብዙ ሊሆን ቢችልም፣ ዋና ዋናዎቹ ግን ሁለት ናቸው፡፡1. ለማድረግ ለምንፈልገው መልካም ነገር ገና ጊዜው አይደለም ብሎ መዘናጋት፡፡መፍትሄው፡- ማድረግ የፈለግነው ነገር በእርግጥም ትክክለኛ እና ያመንንበት እንደሆነ ካረጋገጥን በኋላ በትንሹ መጀመር፡፡2. ለማድረግ ለምንፈልገው መልካም ነገር ጊዜው አልፏል ብሎ ተስፋ መቁረጥ፡፡መፍትሄው፡- ማድረግ የምንፈልገው ነገር አሁንም በውስጣችን የመኖሩ ሁኔታ የሚጠቁመን አሁንም ለማከናወን ጊዜው እንዳላለፈ መሆኑን በማወቅ ግራ እና ቀኝ ሳይሉ መጀመር፡፡ዓላማችንን የመጀመርና የማሳካት ጉዞ 80 በመቶ የውስጥ ቁርጠኝነት፣ 20 በመቶው ደግሞ የሁኔታዎች መመቻችት እንደሆነ አትዘንጉ፡፡እችላለሁ ብላችሁ ከወሰናችሁ 80 በመቶውን ጉዞ እንደተጓችሁ አስታውሱ፡፡ 20 በመቶው ቀስ በቀስ ይመጣል፡፡መልካም እሁድ!https://t.me/Dreyob
Dr. Eyob Mamo
19 сент., 08:09изменён
የ2019 ዓመት የጅማሬ ስልጠና!የስልጠናው ርእስ፡-“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (ውጤታማ የምክር አሰጣጥ ተግባራዊ መመሪያ)Counseling Skills and Techniques (A Practical Guide to Effective Counseling)ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)የስልጠናው ቀናት፡- ጥቅምት 05/2019፣ ጥቅምት 12/2019፣ ጥቅምት 19/2019 እና ጥቅምት 26/2019 (አራት ኃሙሶች)የስልጠናው ሰዓት፡- ለአራቱም ኃሙስ ምሽቶች ከ3፡00 እስከ 4፡30 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)ስልጠናው ለማን ይጠቅማል?-💡 በማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ለተሰማሩና የሕብረተሰቡን የስነ-ልቦና ሁኔታ ለመፍታት ለሚፈልጉ!
Dr. Eyob Mamo
18 сент., 16:20
በዚህ አመት ደስተኛነታችሁን አስመልሱ“ደስተኛችሁና ፈገግተኛነታችሁ በዙሪያችሁ ያሉትን ሁኔታዎች ይለውጡ እንጂ በዙሪያችሁ ያሉ ሁኔታዎች ደስተኛችሁንና ፈገግተኛነታችሁን እንዲለውጠው በፍጹም አትፍቀዱ” (ካልታወቀ ምንጭ)ምን ያህል ደስተኛ እና በፈገግታ የተሞላችሁ እንደነበራችሁ አስቡት እስቲ፡፡ ከአንዳንድ ሰዎች እና ሁኔታዎች የተነሳ ይህ ደስተኛነትና ፈገግታ ጠፍቶባችሁ ከሆነ የድሮ ማንነታችሁን አስመልሱ፡፡https://t.me/Dreyobhttps://m.youtube.com/user/naeleyob623https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
Dr. Eyob Mamo
18 сент., 02:01
የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል አምስት)ከውድቀት በኋላ ተነስቶ የመቀጠል መርሆች!በያዝነው አዲስ ዓመት የጀመራችሁት አዲስ ጉዞ ምንም እንኳን የሚያጓጓ ቢሆንም እንቅፋት የለውም ማለት አይደለም፡፡ ጉዞው አዲስ እና መንገዱም ያልተለመደ መሆኑን አስታውሱ፡፡ እንቅፋት የሚያጋጥመው ሰው የሚራመድ ሰው ነው፡፡ የሚወድቅ ሰው የቆመና የሚንቀሳቀስ ሰው ነው፡፡ በመሆኑም ወደ አዲሱ የሕይወት ዘይቤ ስትራመዱ እንቅፋት ማጋጠሙ አይቀርምና ራስን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው፡፡ይህንን አድርጉ . . .1. ውድቀታችሁ ማንነታችሁን እንዲወክል አትፍቀዱበአንድ ነገር ወደቃችሁ ማለት እናንተ ውዳቂ ናችሁ ማለት አይደለም፡፡ ውድቀት የአንድ ጊዜ ክስተት እንጂ የማንነታችሁ መመዘኛ እንደሆነ ከማሰብ ራሳችሁን ጠብቁ፡፡2. ትምህርቱን ውሰድየመውደቅ ውበቱ ከልምምዱ የምታገኙት ትምህርት መሆኑ ይታወሳችሁ፡፡ “ከዚህ ልምድ ምን መማር እችላለሁ?” ብላችሁ መጠየቅን የዘወትር ልምምዳችሁ አድርጉት፡፡3. ተነሱና እንደገና ሞክሩመውደቃችሁ ምንም ችግር የለበትም፡፡ ችግር ያለበት ከወደቃችሁ በኋላ ካልተነሳችሁ ነው፡፡ ከእያንዳንዱ ውድቀታችሁ በኋላ ትምህርታችሁን በመያዝ እንደገና መነሳት ጠንካራ ያደርጋችኋል፡፡
Dr. Eyob Mamo
17 сент., 08:20
አሁንም የመስከረምን ወር የንበብ Challenge መቀላቀል ይቻላል ወይ በማለት ለምትጠይቁ!!!አዎን!!! አሁንም በመቀላቀልና ያለፈውን በማንበብ መቀጠል ትችላላችሁ፡፡“የመስከረምን ወር ንባብ አሁን መቀላቀል ይቻላል?” ብላችሁ ለምትጠይቁ . . .መልሱ፣ “አዎን ይቻላል!” የሚል ነው፡፡ዛሬን ጨምሮ ያለፏሁን የሶስት ቀን ንባቦች አንብባችሁ በማስተካከል ከነገ ጀምሮ ያለውን በየቀኑ መቀጠል ትችላላችሁ፡፡የንባብ ወር - መስከረም / 2019ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ትኩረት”ንባቡ የተጀመረበት ቀን - መስከረም 1 / 2019ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - መስከረም 30 / 2019ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡
Dr. Eyob Mamo
17 сент., 02:03
የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል አራት)አዲሱ ጅማሬ አስቸጋሪ ሲሆን የመቀጠል መርሆች!በያዝነው አዲስ ዓመት በያዛችሁት አዲስ አመለካከት፣ በወሰናችሁት ውሳኔ እና በጀመራችሁት አዲስ ጅማሬ ላይ እንቅፋት ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይህንን እውነታ አምናችሁ ስትቀበሉ በምንም ነገር አትደናገጡም፡፡አዲሱን ጅማሬያችሁን አስቸጋሪ የሚያደርጉት ሁኔታዎች ከውስጥም ከውጮም ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በውስጥ ያላችሁ ስሜት ሲሆን፣ በውጪ ደግሞ የሰዎችና የሁኔታዎች አጉል ተጽእኖ ነው፡፡ይህንን አድርጉ . . .1. በሚገጥማችሁ ችግር አትናወጡበአዲስ ጅማሬ ወቅት አስቸጋሪ ልምምድ መጣ ማለት የተሳሳተ ውሳኔ አድርጋችኋል ማለት አይደለም። የጀመራችሁት ጉዞ አሁን ዋጋ እንደሚያስከፍልና ወደፊት ደግሞ ዋጋ እንደሚከፍላችሁ ምልክቱ ነው፡፡2. በትንሹ መጀመር አትፍሩትልልቅ እድገቶችና ውጤቶች የሚጀመሩትም ሆነ የሚገነቡት በየጊዜው በሚደረጉ ትንንሽ እርምጃዎች ነው፡፡ እነዚህ ትንንሽ እርማጀዎች ግን በቀጣይነት ሊገነቡ ያስፈልጋል፡፡3. ጊዜ ስጡት
Dr. Eyob Mamo
16 сент., 02:03
የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል ሶስት)ያለፈው ልማድ እንዳይመለስ የመከልከል መርሆዎች!በያዝነው አዲስ ዓመት አልፋችሁት የመጣችሁት ለመመለስ ሙከራ ማድረጉ አይቀርም፡፡ ይህ እንዳይሆን የከራረመን ልማድ አልፎ መሄድን መቀጠልና በአዲሱ ዓመት የአሮጌ ልማድ በሮች እንደገና እንዳይከፈት መቋቋም አስፈላጊ ነው፡፡ያለፈው ልማዳችሁ ወደኋላ ከሚጎትታችሁ በበለጠ ሁኔታ የወደፊቱ ጉጉታችሁ እንዲስባችሁ ፍቀዱለት፡፡ ይህ ልምምድ ከባድ ቢሆንም የሚቻል እና የግድም ነው፡፡ይህንን አድርጉ . . .1. ያለፈውን ለምን እንደለቀቃችሁት አስታውሱያለፈው ትውስታ እንደገና ለመመለስ ሲያገረሽ፣ መጀመሪያውኑ ለምን ትታችሁት ወደ አዲሱ መራመድ እንደጀመራችሁ ለማስታወስ ሞክሩ፡፡ አሮጌውና ጊዜያዊው ስሜት ከወደፊቱን ዘላቂ ጉዙ እንዲያዘናጋችሁ አትፍቀዱ።2. እድገትን ከአጉል ልማድ አስቀድሙአሁን በጀመራችሁት አዲስ ጎዳና ላይ በፊታችሁ እድገት አለ፡፡ ይህ እድገት የወደፊታችሁን ውብ የሚያደርግ ጉዳይ ነው፡፡ ከጀርባችሁ ደግሞ የቀድሞው ልማድ አለ፡፡ ይህ የለመዳችሁት ሁሉ ለወደፊታችሁ ጥሩ ስላልሆነ እድገታችሁ ይቅደም፡፡3. ዓይናችሁን ወደፊት አድርጉ
Dr. Eyob Mamo
15 сент., 02:02
የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል ሁለት)ከትክክለኛ ሰዎችና ነገሮች ጋር የመተሳሰር መርሆዎች!በያዝነው አዲስ ዓመት፣ የተሻለ ግንኙነት ለመመስረት ወስኑ! ባለፈው ዓመት የነበራችሁን ጎጂ ግንኙነት ስታቆሙ፣ ውስጣችሁ ባዶነት ሊሰማው መቻሉ ተፈጥሯዊ ሂደት ነውና ተቀበሉት፡፡የተዋችሁትና ከውስጣችሁ ያስወጣችሁት ነገር ይዞት የነበረው ቦታ ባዶ ስለሚሆን ከትክክለኛ ሰዎች ጋር ጤናማ ግንኙነትን የመመስረትን እና አዳዲስና ጤናማ ሁኔታዎችን የመልመድ ጉዙ ጀምሩ፡፡ይህንን አድርጉ . . .1. የሚያሳድጓችሁን ሰዎች ምረጡሰዎች ስለቀረቧችሁ ብቻ አትቅረቡ፣ ትኩረት ስለሰጧችሁ ብቻ ራሳችሁን ክፍት አታድርጉ፡፡ ከዓላማችሁ እና ለማደግ ከምትፈልጉት ከፈታ አንጻር እድገትን፣ ጥበብንና መልካም ባህሪን የሚያበረታቱ ሰዎችን ቅረቡ።2. ለአስፈላጊው ነገር ቁርጠኛ ሁኑከአንድ ነገር ተለይቶ ወደ ሌላ ነገር መጓዝ ቁርጠኝነት ይፈልጋል፡፡ ጊዜያችሁንና ኃይላችሁን ለዓላማችሁና ቅድሚያ ለምትሰጡት ነገሮች ስጡ እንጂ ለጊዜው ጥሩ ስሜት የሰጣችሁን ነገር ብቻ አትከተሉ፡፡3. መልካሙን ልምምድ አሳድጉ
Dr. Eyob Mamo
14 сент., 02:05
የአዲስ ዓመት ጅማሬ ! (ክፍል አንድ)ከተሳሳቱ ሰዎችና ነገሮች የመለየት መርሆዎች!በያዝነው አዲስ ዓመት፣ አዲስ የቀይ መስመር ይኑራችሁ!ባለፈው ዓመት በሕወታችሁ ጎጂ የነበሩ የሰው-ለሰው ግንኙነቶችና እና ሁኔታዎች በዚህ ዓመት መስመር ይበጅላቸው፡፡ምናልባት ቀይ መስመር እንዳታሰምሩ የሚያደርጋችሁ፣ አንድ ነገር ይደርስብኛል፣ ወይም አንድ ነገር አጣለሁ ብላችሁ ይሆናል፡፡ ሆኖም፣ ለትክክለኛ ነገር ቀይ መስመር በማስመር የሚመጣ ጉዳት ጊዜያዊና ወደፊት የሚያራምድ ጉዳት ነው፡፡ይህንን አድርጉ . . .1. የሚጎዳችሁን ለዩአንድን ነገር ስለለመዳችሁት ብቻ አታቆዩት፡፡ ጥቅሙና ጉዳቱን በሚገባ አስቡ፡፡ የለመዳችት ነገር ሁሉ ለወደፊትህ የሚጠቅም እንዳልሆነ አስታውሱ፡፡2. ያለ ጥፋተኝነት ስሜት ልቀቁበተለይም ክፉ መስሎ የመታየት ሁኔታ የሚያሳስባችሁ ከሆነ የቀይ መስመር በማበጀታችሁ ምክንያት ጥፋተኝነት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ሆኖም፣ የተሳሳቱ ሰዎችን፣ ልማዶችንና አካባቢዎችን መተው ለእድገት ቦታ እንደሚፈጥር አስቡ።
Dr. Eyob Mamo
13 сент., 16:40
“የመስከረምን ወር ንባብ አሁን መቀላቀል ይቻላል?” ብላችሁ ለምትጠይቁ . . .መልሱ፣ “አዎን ይቻላል!” የሚል ነው፡፡ዛሬን ጨምሮ ያለፏሁን የሶስት ቀን ንባቦች አንብባችሁ በማስተካከል ከነገ ጀምሮ ያለውን በየቀኑ መቀጠል ትችላላችሁ፡፡የንባብ ወር - መስከረም / 2019ለንባብ የተመረጠው መጽሐፍ - “ትኩረት”ንባቡ የሚጀመርበት ቀን - መስከረም 1 / 2019ንባቡ የሚጠናቀቅበት ቀን - መስከረም 30 / 2019ይህንን Book Club ለመቀላቀል፡- በዚህ 👉 @DrEyobmamo የቴሌግራም አድራሻ (user name) inbox በማድረግ ፍላጎታችሁን ስትገልጹ ሙሉ መረጃ ይላክላችኋል፡፡Join now!!!
Dr. Eyob Mamo
13 сент., 04:02
2019 New Year’s Kickoff Training!የ2019 ዓመት የጅማሬ ስልጠና!የስልጠናው ርእስ፡-“የምክር አሰጣጥ ክህሎቶች እና ዘዴዎች” (ውጤታማ የምክር አሰጣጥ ተግባራዊ መመሪያ)COUNSELING SKILLS AND TECHNICS (A Practical Guide to Effective Counseling)ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በ online (telegram live)ስልጠናው ለማን ይጠቅማል?-💡 በማንኛውም ማሕበራዊ ዘርፍ ለተሰማሩና የሕብረተሰቡን የስነ-ልቦና ሁኔታ ለመፍታት ለሚፈልጉ!
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →