gram news
Аватар канала EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

@ebcnewsnow

EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1 @ETVkidschannel @EBCWORLD1 @etventertainment1

ПроектыENНовостиПодтверждён Telegram

132,712подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    14 нояб., 06:45

    ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያመጣች ያለችው ተጨባጭ ስኬትየኢኮኖሚው ዋነኛ ምሰሶ የሆነው የግብርና ዘርፍ ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከፍተኛ ድርሻ የሚይዝ ሲሆን፣ አብላጫ ክፍል ለሚሆነው ሕዝብም ዋና የገቢ እና የመተዳደሪያ ምንጭ ነው::ባለፉት ዓመታት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማዕቀፍ ውስጥ በመነሳት ዘርፉን ከዕለት ፍላጎት ማሟያነት ወደ ዘመናዊና ገበያ ተኮር የንግድ እርሻ ለማሸጋገር ታላላቅ የሪፎርም እርምጃዎች ተወስደዋል
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    14 нояб., 06:44

    ኢትዮጵያ የፈነጠቀችው የተፈጥሮ ማደሻ ብርሃንምድራችን ዛሬ ከሰደድ እሳት እስከ ፈጣን የበረዶ መቅለጥ የደረሰ ከባድ የአየር ንብረት ቀውስ ገጥሟታል::የዓለም ሜትሮሎጂ ድርጅት መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ የዓለም ሙቀት መጠን ማሻቀብ እና የሙቀት አማቂ ጋዞች ክምችት ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የምድራችንን ሕልውና እየፈታተነ ይገኛል
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    14 нояб., 06:43

    በሴኔጋል ዳካር የወጣቶች ኦሊምፒክ በአትሌቲክስ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል ተደረገበአፍሪካ ምድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሴኔጋል መዲና ዳካር በተካሄደው አራተኛው የወጣቶች ኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ወጣቶች አትሌቲክስ ልዑክ አዲስ አበባ ገብቷል::ልዑኩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር አክሊሉ ታደሰ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን፣ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የፌዴሬሽኖች አመራሮች በተገኙበት አቀባበል አድርገውላቸዋል
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    13 нояб., 18:18

    የኢትዮጵያና የትግራይ ዋነኛ የጸጥታ ችግር የውጭ ጠላቶች የረጅም ጊዜ እቅድ ውጤት ነው - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመቐለ ከተማ ከኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የትግራይም ሆነ የኢትዮጵያ ዋነኛ የጸጥታ ችግር የዴሞክራሲ ጥያቄ ሳይሆን ኢትዮጵያን በውስጥ ግጭት የማዳከም የረጅም ጊዜ የሻዕቢያ እና ከጀርባው ያሉ ታሪካዊ ጠላቶች እቅድ ውጤት ነው ብለዋል::የመከላከያ ሠራዊት ከ2013 ዓ.ም ግጭት በፊት በትግራይ ክልል እንቅስቃሴው ተገድቦ፣ አመራሮቹ ከመቐለ አውሮፕላን ማረፊያ እስከመባረር የደረሰ ተጽዕኖ ሲደርስበት መቆየቱን አስታውሰዋል
    4,0501544Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    13 нояб., 16:35

    በኅብረት የጸናችው ኢትዮጵያየዲፕሎማሲ ስኬት፣ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እና ዓለም አቀፍ ተደማጭነት ከሜዳ የሚገኝ ሳይሆን፣ በሀገር ውስጥ በሚኖረው በኅብረት የጸና ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ነው::ኢትዮጵያ ዛሬ በአፍሪካ ቀንድና በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በኮፕ32 ዝግጅት እና በባሕር በር ዲፕሎማሲ ላይ እየተጫወተች ያለው ሚና እና ስኬት ከኅብረ ብሔራዊ አንድነቷ ጥንካሬ ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ነው
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    13 нояб., 16:17

    "በጣም ብዙ ሊፈርሱ የሚገባቸው ከሰው የመኖር ደረጃ በታች የሆኑ ቤቶች አሉ፤ አቅም በፈቀደ መጠን እሱን እያሻሻልን እየሠራን እንሄዳለን" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    13 нояб., 16:06

    ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ሥራ አስፈፃሚ ክሪስቶፍ ለኩርቲየር ጋር ተወያዩየኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በቱርክዬ አንታሊያ እየተካሄደ ካለው የኮፕ 31 ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ ስራ አስፈፃሚ ክሪስቶፍ ለኩርቲየር ጋር ተወያይተዋል::ውይይታቸውም ከኢትዮጵያ ጋር ያለ አጋርነትን ይበልጥ ለማጠናከር እና የCOP32 ጉዳዮች ላይ በቀጣይ ለመሥራት መሆኑን ከኮፕ32 ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    13 нояб., 16:01

    የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የሞዛምቢክ አቻውን 1 ለ 0 አሸነፈበ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድብ አስር ሦስተኛ መርኃ ግብር ማፑቶ ላይ በዚምፔቶ ስታዲየም ሞዛምቢክን የገጠመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1 ለ 0 አሸንፏል::የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ48 የማጣሪያው ተሳታፊ ቡድኖች ብቸኛ ያደረገውን ግብ ያለማስቆጠር ችግር በቀረፈበት ጨዋታ፣ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ 87ኛው ደቂቃ ላይ ከነዓን ማርክነህ አስቆጥሯል
    3,6801451Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 17:17

    የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ እና ፅናት የሚያንፀባርቀው "ድል ቁርሱ" መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመረቀ::መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሬዋ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው
    3,110391410Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 16:51изменён

    የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ እና ፅናት የሚያንፀባርቀው "ድል ቁርሱ" መጽሐፍ ተመረቀየኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሕይወት ታሪክ፣ ልምድ፣ አመራር እና ጀግንነት ላይ የሚያጠነጥነው "ድል ቁርሱ" የተሰኘው መጽሐፍ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተመረቀ::መጽሐፉ የግለሰብ ታሪክ ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ክፍል ተነስቶ የወታደራዊ ሕይወትን በመቀላቀል ሀገር በፈተና ማዕበል በተናጠችበት ወቅት በፅናት የቆመ ታላቅ መሪን መንፈስ የሚያሳይ እና የሕይወት ውጣ ውረድን በጥልቀት የሚያስቃኝ ነው
    3,600241882Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 16:06

    በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ነው“መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን መፍጠር” በሚል መሪ ሐሳብ በኒውዮርክ እየተካሄደ የሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ልዑክ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡በልዑክ ቡድኑ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተሳትፈዋል፡፡ኢትዮጵያ በጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሟን እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅም በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በሚደረጉ ውይይቶች በንቃት እንደምትሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል::ኢትዮጵያ ከዋናው ጉባኤ ጎን ለጎን በሚደረጉ በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ስብሰባዎች ላይ እንደምትሳተፍም ተገልጿል
    3,76011322Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 15:57

    "የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የልማትና የትራንስፖርት ትስስር የሕዝቦችን ሕይወት የመቀየር አቅሙ ከፍተኛ ነው"፦ የተባበሩት መንግሥታትየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ኻሊሉር ረህማን ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሀብት ድልድሉንና አጠቃቀሙን በአግባቡ ማስተካከል እንዳለበት ጥሪ አቀረቡ::ፕሬዚዳንቱ እንዳመለከቱት ልማትን ለማፋጠንና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የልማት እርዳታዎችን ማሳደግ፣ የዕዳ ጫናዎችን ማቃለል እንዲሁም የዓለም አቀፉን የፋይናንስ መዋቅር ማሻሻል ወሳኝና አስቸኳይ ጉዳይ ነው
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 14:44

    "አፍሪካ ለመላው ዓለም ውይይት እና እርምጃ አስተዋጽኦ ማበርከት የምትችልባቸው ቋሚ መቀመጫዎች በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ውስጥ ሊኖሯት ይገባል።" አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 07:04

    ቀይ ባሕር ኢትዮጵያን ለምን ይፈልጋል?የኢትዮጵያ የባሕር በር መዳረሻ ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚነሳው ከአንድ ሀገር የኢኮኖሚና የንግድ ፍላጎት አንጻር ብቻ ነው::ሆኖም ጉዳዩን በጥልቀት ለሚመረምር አካል፣ የኢትዮጵያ ቀይ ባሕር ላይ መገኘት ለአንድ ወገን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ለአጠቃላይ የቀይ ባሕር ቀጣና እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ መሠረታዊ ጉዳይ ነው
    6,1202611Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    22 сент., 06:55

    ተመድ ሲፈተን፦ የኢትዮጵያ ፍትሐዊ የፖለቲካ ጥሪ፣ የማድረግ አቅም ልዕልና እና የዓለም አቀፍ ተፈላጊነት አዲስ ምዕራፍበኒውዮርክ በሚካሄደው የዓመቱ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የዓለም መሪዎች በተሰበሰቡበት በዚህ ወቅት፣ ድርጅቱ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ ሁለንተናዊ ፈተና ውስጥ ይገኛል::የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚያስጠነቅቁት የዓለማችን ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እየከፋ የመጣው በኃያላን ሀገራት መካከል ያለው የጂኦ-ፖለቲካ ክፍፍል የጸጥታው ምክር ቤቱን ውሳኔ መስጠት እንዳይችል "ሽባ" በማድረጉ ነው
    5,790652Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    21 сент., 18:17

    ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የተሻገረ ትርጉም ያለው የኩርሙክ ወርቅ ፋብሪካየማዕድን ክፍለ-ኢኮኖሚ ከጥሬ ሀብት ሻጭነት ወጥቶ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዋና ምሰሶ የሚሆንበት ታሪካዊ መዋቅራዊ ሽግግር በተጨባጭ እየተረጋገጠ ይገኛል::በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ዞን የሚገኘው የኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፕሮጀክት የዘመናዊ እና ግዙፍ የኢንዱስትሪ ደረጃ የወርቅ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ግንባታን በማጠናቀቅ ወደ ምርት ምዕራፍ መሸጋገሩ በዘርፉ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል
    6,5201714101Открыть в Telegram
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    21 сент., 17:54

    ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የታዳሽ ኃይል ትኩረቱን ከማመንጨት ወደ ኤሌክትሪክ ተደራሽነት ሊያሸጋግር ይገባል - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የኢትዮጵያን ከፍተኛ ልዑካን በመምራት በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው የዓለም አቀፍ ታዳሽ ኃይል ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የታዳሽ ኃይል ትኩረቱን ኃይል ከማመንጨት ባሻገር ኤሌክትሪክን ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለማዋል ወደሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች ሊያሸጋግር እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች፣ የኃይል ማከማቻዎች እና ጠንካራ የኤሌክትሪክ አቅርቦት አቅም ሳይኖሩ ማመንጨት ብቻውን የኢኮኖሚ ሽግግርን ስለማያመጣ አዳጊ ሀገራት እምቅ አቅማቸውን ወደ አስተማማኝ ተደራሽነት እና የኢንዱስትሪ ዕድገት እንዲቀይሩ ጠንካራ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ካላት 9 ሺህ 761 ሜጋ ዋት አቅም ውስጥ ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ከታዳሽ ኃይል የሚገኝ መሆኑን ያብራሩት ፕሬዚዳንቱ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎች የኃይል ማመንጫዎች ለኤሌክትሪክ ተደራሽነት እና ኢንዱስትሪ ልማት መሠረት መሆናቸውን አስገንዝበዋል፡፡ ግድቡ በሀገር ውስጥ አቅም እና በሰፊ የሕዝብ ተሳትፎ መገንባቱ የሀገር በቀል ባለቤትነት ማሳያ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም መንግሥት በአሁኑ ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠር ሜጋ ዋት እምቅ አቅምን ለመጠቀም ሦስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ እያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይኸውም በፈረንጆቹ 2030 የማመንጨት አቅምን
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    21 сент., 17:50

    የአተካና ምሽት በመሳላ ዋዜማየከምባታ ብሔር የዘመን መለወጫ ‘መሳላ’ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል::በአካባቢው ባህል መሠረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው "የአተካና ምሽት" ወይም "የእናቶች መሳላ" በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ሥነ-ሥርዓት በዱራሜ ከተማ፣ በኡቱቢ ወጋ አደባባይ እየተካሄደ ይገኛል
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    21 сент., 17:25

    የማይበጠሰው የዳገታ ሰንሰለት፡ የፍቅር እና የይቅርታ ጥበብ“ዳገታ” በወላይታ ባህላዊ ሥርዓት ውስጥ ሁለት ሰዎችን “ከወንድማማችነት በላይ” በሆነ ፍጹም ታማኝነት ስና ፍቅር የሚያስተሳስር፣ እስከ ዕለተ ሞት የሚዘልቅ የማይፈርስ የፍቅር እና የአብሮነት ቃል-ኪዳን ነው::በጊፋታ በዓል ወቅት ሁለት ሰዎች በጋራ በመሆን የጊፋታ ልዩ ባህላዊ መጠጥ የሆነውን “ቦርዴ” በአንድ ቅል ይጋራሉ
  • EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

    21 сент., 17:04

    የትግራይ ሕዝብ የሚፈልገው ሰላምን እና ልማትን እንጂ የቡድኖችን የፖለቲካ ሴራ አይደለም - ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያየትግራይ ሕዝብ ዘላቂ ጥቅም እና ሰላም እውን ሊሆን የሚችለው በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ ብቻ መሆኑን ጋዜጠኛ ዳሞራ ያህያ ተናግሯል::ጋዜጠኛው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት እና በተለያዩ ከተሞች እየተተገበሩ የሚገኙት የኮሪደር ልማቶች፣ ኢትዮጵያውያን በጋራ ሲሠሩ የሚያመጡትን የላቀ ለውጥ እንደሚያሳዩ ገልጿል
    5,110641Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота