gram news
Аватар канала እንማር

እንማር

@enmare1988

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን 🎯 መፅሀፎች 🎯ተከታታይ ልቦለድ 🎯ግጥም 🎯ፍልስፍና 🎯ምክር የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ Ads - @Kiya988 https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

122,000подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • እንማር

    23 сент., 18:03изменён

    ሀጭር ቀሚስ መልበስ የምትወዳዋ የሃይስኩ'ሏ ፍቅሬ ከረጅም ገዜ በኋላ ድንገት ፃፈችልኝ ግን ለመመለስ ግራ ተጋባው !! ሀይስኩል 12 ተኛ ክፍል ፍቅረኛ ነበረችኝ ። ፅገሬዳ ትባል ነበረ ። ነጭናጫም : ጨቅጫቃም ነበረች ። ነገር ግን ልቧ ንፁህ ነበረ ።ልክ እንደ ስሟ ግብር መአዛዋ የሚስብ እሾክዎቿ የሚያደሙ ልክ እሾክ የበዛባት ፅገሬዳ ተብላ የምትገለፅ አይነት የሆነች ሴት ነበረች። እኔ ዩኒቨርስቲ ስገባ የስልክ ጭቅጭቋ ምክንያት ሆ'ኖን ተለያየን ። በመሀል ሰፊ ክፍተት ተፈጠረ ። ሁለት : 3ቴ ስልክ ቁጥር ቀያየርኩ ። ትምህርት : ስራ እና ክረምቱን እንዳልመለስ እናቴ እና እህቴ እዚሁ አዲስ አበባ ገቡ እና የሚያስቀረኝ ነገር ተፈጠረ ።ከ6 አመት በኋላ ዳግም ያንን ስሜት የሚያስታውሰኝ ነገር ዛሬ : አሁን ተፈጠረ።አሁን ስልኬ ላይ ቴክስት ገባ ።...እሷ ነበረች !! ......ፅ ገ ሬ ዳ....." Hi አዳም እንዴት ነህልኝ? ፅገሬዳ' ህ ነኝ ስልክህን በመጨረሻም አገኘሁት ። "ይላል ይቀጥላል" አንድ ነገር ብቻ ልነግርህ ነው የፃፍኩልህ ። ወደ ህይወቴ ከአንተ በኋላ መተው ከቀሩትም ትቻቸው ከሄድኩትም ደግሞም ዛሬም በዙርያዬ አጅበውኝ ካሉትም ወንዶች ይልቅ ፥ መጣለሁ ብለህ የቀረህው አንተ ነው የምትናፍቀኝ : አንተን ነው ልረሳህ ያልቻልኩት !! እንዴት ነበረ ከአንተ ጋር ያሳለፍኩት?? ምን ተአምር ነበረ ያህ ግዜ?? የማይረሳ : በታወሰ ቁጥር ሁሉ አሁን አሁን የሚመስል : የመጣም የሄደ የማይሽሩት ምን ጉድ ነበረ ?? ለዚህም ነው ደግሜ ይህንን የምልህ ወደ ህይወቴ ከአንተ በኋላ መተው ከቀሩትም ትቻቸው ከሄድኩትም ዛሬም በዙርያዬ አጅበውኝ ካሉትም ወንዶች ይልቅ ፥ መጣለሁ ብለህ የቀረህው አንተ ነው የምትናፍቀኝ : አንተን ነው ልረሳህ ያልቻልኩት !! "ፅሁፉ አለቀ ረጅም ደቂቃ ግን እኔ ፅሁፉ ላይ እንዳፈጠጥኩ ዝ ም !!ምን ልመልስ?? ምን ልበላት?? እንዴትስ ይሰማኝ ?? የማላውቀው ስሜት መጥቶ ወረረኝ !!"ያለፈ" ሁሉ ቀላል አይደለም !!!
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    3,1309123152Открыть в Telegram
  • እንማር

    23 сент., 12:06

    👩‍🎓ሁሉም የኢትዮጵያ 🇪🇹 ተማሪዎች ሊኖሯቸው የሚገቡ ምርጥ 10 የትምህርት ቻነሎች!™️ Ministry of Education | 250K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ English for Ethiopia | 194K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ እንማር | 121K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ Learn English | 116K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ Bemnet Library | 100K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ ቀሰም አካዳሚ | 85K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ MOE | 77K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ™️ Temari News | 127K ᴊᴏɪɴ ᴄʜᴀɴɴᴇʟ
  • እንማር

    22 сент., 17:07изменён

    እናቴ ሁሌ እንዲህ ትለኝ ነበር፦“አባትህ ወደ ቤቱ ሲመለስ ፊትህን ፈገግ አድርግለት፤ ውጭ ያለው አለም ልብ በሚሰብሩ አውሬዎች የተሞላ ነው!።”―ዶይስቶቭስኪ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    7,490171171633Открыть в Telegram
  • እንማር

    21 сент., 17:33изменён

    " ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት::“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ….. አንዱ ይኖርበታል፡፡ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባሕሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በስተቀር ንጹሕ፣ ቅን እና ሁኔታ እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው ሕይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል። አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም። "ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    9,79072129Открыть в Telegram
  • እንማር

    21 сент., 14:41изменён

    " ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ ….. ብቻ አንዱ ይኖርበታል፡፡ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎን ካልተገለጠ በስተቀር ንፁህ፣ ቅን እና ፍፁም እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ "ጠበኛ እውነቶች በሜሪ ፈለቀ@Enmare1988 @Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    9,57074377Открыть в Telegram
  • እንማር

    20 сент., 17:56изменён

    📚ርዕስ :- ኦሪጅን (Origin ✔️ደራሲ :- Dan Brown 👤ትርጉም:- ሃኒም ኤልያስ 📖የገፅ ብዛት:- 468እኛ ማን ነን? ከወዴት መጣን? ወደፊትስ ወዴት እንሄዳለን?"​ለሺህ ዓመታት የሰው ልጅን ሲያወዛግብና ሃይማኖቶችን ሲያንቀጠቅጥ የኖረው ታላቁ ሚስጥር... በመጨረሻ ምላሽ ሊያገኝ ነው!​በስፔን ቢልቦ ሙዚየም፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የዓለም ህዝቦች በቀጥታ ስርጭት በሚከታተሉት ታሪካዊ ምሽት... ታዋቂው የነገሮች ተንባይ ኤድመንድ ኪርሽ የሰው ልጅን አመጣጥና እጣ-ፈንታ የሚቀይረውን ግኝት ይፋ ሊያደርግ ሰከንዶች ሲቀሩት… የጥይት ድምፅ ተሰማ!​ደም በረበበበት መድረክ ላይ ሚስጥሩ ከሬሳው ጋር አብሮ ሊቀበር ሲል፣ የኪርሽ መምህር—የምልክቶች ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሮበርት ላንግደን—እና የሙዚየሙ ዳይሬክተር ውቧ አምብራ ቪዳል፣ የይለፍ ቃሉን ለመክፈት ከጊዜ ጋር አደገኛ የሞትና የሽረት እሽቅድድም ውስጥ ይገባሉ። ​ነገር ግን ጠላታቸው ጊዜ ብቻ አይደለም!የሃይማኖት መሪዎች ጥቁር ጥላ፣ የስፔን ንጉሳዊ ቤተሰብ ሚስጥሮች፣ እና ጨካኝ አደኖች በየመጠምዘዣው ደብቀው ይጠብቋቸዋል። በዚህ አስፈሪ ፍልሚያ
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    9,980272132Открыть в Telegram
  • እንማር

    20 сент., 11:06

    ምን መማር ይፈልጋሉ👍ፎሬክስ ትሬዲንግ 👍Adobe Photoshop 👍ዲጂታል ማርኬቲንግ👍Website አሰራር 👍 የሞባይል ጥገና 👍 Computer ጥገና👍Gaming አሰራር 👍Hacking 👍 Graphics design👍 YouTube masterclass 👍Logo design 👍ድሮፕሺፒንግሁሉንም ኮርስ አንድ ላይ Telegram Channel ይቀላቀላሉ
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
  • እንማር

    20 сент., 09:38изменён

    ርዕስ:- አልገባኝም ደራሲ:- ዮናስ ዘውዴ (የፍልስፍና መምህር)የገፅ ብዛት:- 135 ባለማውቅ ጨለማ ስትኖሩ ነፍሳችሁ ትጨነቃለች ሁሉ ነገር ያስፈራችሁ ዐይኖቻችሁ እየተጠበረበሩ የሚያዩትን አይምኑም ።ዋሻ ውስጥ የአንድ ክብሪት ብርሃን በላይ የምትፈልጉት አይኖረም ።ማንነትን መረዳት ዙሪያችሁን በውል መለየት ነወ። መማር ብርሃን ነው ፤በአለማወቅ ዋሻው ውስጥ ለተጣለ ሰው እውቀት ይገልጥለታል። አብዛኛ ሰው ይማራል የሚማረው ግን በማወቅ የሚገኘውን ሐሴት ፍለጋ አይደለም መማራቸውን የሚገለፅ ወረቀት ለመፈለግ ነው ።📔አልገባኝም ዬናስ ዘውዴ@Enmare1988 @Enmare1988
    8,700файл38421Открыть в Telegram
  • እንማር

    19 сент., 15:50изменён

    📚ርዕስ:- አልገባኝም 👍ደራሲ:- ዮናስ ዘውዴ (የፍልስፍና መምህር) 👍የገፅ ብዛት:- 135 👍አቅራቢ:- ነቢል እንድሪስ====-----ከመጽሐፉ የተወሰደ -----==== የተሳሳተ አረዳድ ውስጥ የሚታዘዘው ታማኝ ተደርጎ ይወሰዳል። 'አይ" የሚለው ደግሞ ከአመጸኞች ጎራ ተፈርጆ ይገፋል። ተለጣፊ ስም በመፍራት ያላመኑበትን ነገር አድርጉ ሲባሉ ሰዎች ያደርጋሉ። አሮጌ ልብና የበሬ ወለደ ትርክት ማንንም አያራምድም ባለበት የሚረግጥ ትውልድ አዲስ ብሔራዊ ጀግና አይፈጥርምስኬታማ ሰዎች አዕምሯቸውን የመቆጣጠር አቅም ያላቸው ናቸው ከአንደበታችሁ ይልቅ ጆሮዎቻችሁ ክፍት መሆንን መልመድ አለባቸው። በሰማችሁት ሳይሆን በተናገራችሁት ነገር ሰውን ታስቀይማላችሁ። የልቡና ስፋት ሳይሆን የምላስ መርዘም አገር ያጠፋል። ሁሉም ሲናገር ያን ጊዜ ዝም በሉ። በጸጥታችሁ ሰላም ይፈጠራል፩. ገባኝ' የሚጀምረው ከ'አልገባኝም' ነው።፪.እምነት የሚጀምረው ከመጠራጠር ነው፫. የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ ማሰብን መፍራት ሳይሆን ማሰብ መጀመር ነው( አልገባኝም...ከተለያዩ ገጽ የተወሰደ )
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    9,610711041Открыть в Telegram
  • እንማር

    18 сент., 06:13

    "ምን እያሰብሽ ነው?""ጊዜን ስለማቆም ስለምንፈለገው ስለምንወደው ምቾት በሚሰጠን ስፍራ ሁሉ!""ሃሳብሽ ማነው ጋር ነው?"ከቡና ወዝ ፡ ከመፅሃፍት ሽታ፤ እንደ ድካም እንቅልፍ ፡ እንደ እናት እቅፍ፤ ባዶ እግርን እንደመጓዝ ፡ ዕፅ እንደመጠብዘዝ፤ በአስቴር ዘፈን ፍሰት ፡ እንደ አዳም ድርሰት፤ አላውቅም አላውቅም መንፈሱን አልርቅም።"ሃሳብሽ ስለምንድነው?"እርጋታን በዝምታ ከቀይ ሰማይ ስር ማጥለል .. በፀዐይ መውጣትና መጥለቅ ያለህ እድሜ እንደ መኖር ..@Enmare1988 @Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    13,3006650551Открыть в Telegram
  • እንማር

    17 сент., 06:24

    ⇲⇲ ✘ የውበት ወጥመድ ✘ ⇲ ⇲ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ❏ ❐ ❑ ❒ ❏ ❐ ደራሲ ፦ ከርታ ክሌይ ትርጉም ፦ ዮሐንስ ገ/ጻድቅ📖 ✈️@Enmare1988 ✈️@Enmare1988
    14,300файл1693332Открыть в Telegram
  • እንማር

    16 сент., 15:58

    ዳያን ትባላለች። በመንደሩ አለች የተባለች ውብ ነበረች። ያገባችው ወዳ ፈቅዳ አይደለም። ውበቷ አንድ ገበሬ አጥምዶ እንጂ። ትዳሩ ከጅምሩ አላቻ ጋብቻ ነበር። ዳያን በትዳር ህይወቷ ደስተኛ ባትሆንም አንድ ልጅ ወለደች። ይህ ልጅ የመኖሯ ምክንያት ሆነ።ነገር ግን ይህ ልጅ ታመመ ፤ በጠና ታመመ። በመጨረሻ ሞተ―ወይም ለዳያን የሞተ መሰላት። አሁን ዳያን እዚህ የምትኖርለት ምክንያት ሞቷል። ስለዚህ ማቄን ፣ ጨርቄን ሳትል ወደ ለንደን ተሰደደች።ብዙ አመታት አለፉ። ዳያን አሁን ከትልቅ ሰው ጋር ግንኙነት መስርታለች። ይህ ሰው ያለፈ ታሪኳን አያውቅም። ዳያን ከምታዘወትርበት የስእል ጋለሪ አንድ ልጅ እግር ሰአሊ ጋር ተግባባች። ከብዙ ምልልስ በኋላ ይህ ከፊቷ ቆሞ የምታየው የ19 አመት ወጣት ልጇ ፣ መሆኑን ተረዳች። ተደሰተች ፣ ደነገጠች። ልጇን በተደጋጋሚ ለማየት ወደ ስእል ጋለሪው መመላለስ አዘወተረች።በአንድ የተረገመ ቀን ግን ከቀድሞ ባሏ ብሩኖ ጋር በመንገድ ተገጣጠሙ። ብሩኖ የቀድሞ ሚስቴን አገኘሁ ብሎ ሲንሰፈሰፍ ፣ ዳያን ጭራሽ አላውቅህም ብላ ካደች።ብሩኖ ዳያንን ፍርድ ቤት ከሰሳት። ምስኪን ዳያን! መስካሪዎች አንድ በአንድ እየቀረቡ ሀሰተኝነቷን አረጋገጡባት። በመጨረሻ እራሷም አመነች። ጓደኛዋ የዋህነቷን እና ድንቁርናዋን ይቅር
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    16,800105117432Открыть в Telegram
  • እንማር

    15 сент., 17:36изменён

    «ፍቅረኛዬ ልደቷ ደርሷል። ምን ልስጣት » አለኝ«ለምን አትነቀስላትም» አልኩት።«ምን ልነቀስ? ስሟን? »«አይ እሱማ የተለመደ ነው። »«የተወለደችበትን ቀን? ወይ የተገናኘንበትን?»«እሱም አዲስ ነገር አይደለም!»«ታዲያ?»«ለየት ያለ ነገር። መጀመሪያ ከተገናኛችሁበት ቦታ... ወይ አብራችሁ ካደራችሁበት ጋር የተያያዘ ነገር ካለህ... » አልኩት...«ምርጥ ሀሳብ ! መጀመሪያ አብረን ያደርንበትን እንደውም!» ተቻኩሎ ሳይነግረኝ ጥሎኝ ሄደ። በሳምንቱ ጥቁርቁር ብሎ አገኘሁት።«ምነው?» አልኩት።
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    16,70046763551494Открыть в Telegram
  • እንማር

    14 сент., 16:55изменён

    ዶይስቶይቭስኪ አንድ እውነት ልንገራችሁ ብሎ ይጀምራል፦‹‹ዓለም እንደ እናታችሁ አይደለችም ንዴታችሁን የመታገስ አመል የላትም፤ ቢርባችሁ ደርቃችሁ ትቀራላችሁ እንጂ ማንም ግድ አይሰጠውም!። እናት ግን ቀን ላይ ተናዳችሁ ትጮኹባታላችሁ፤ እናም ማታ በቀኑ መጨረሻ ሁሉንም እረስታ እራት ታቀርብላችኋለች..›› ❤‍🩹💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    16,10035843252165Открыть в Telegram
  • እንማር

    14 сент., 13:34

    📢በ 2019 ህይወቴን እቀይራለውተረጋጋ Brooooooo 🤣🎉 yango ላይ ተመዝገበህ ስራ ካልጀመርክ አይቀየረም🌻 አዲሱን ዓመት ከYango ጋር በበለጠ ገቢ ይጀምሩ!🎉 የYango አጋር ሹፌር ይሁኑ ብዙ ተሳፋሪዎችን ያግኙ ብዙ ጉዞዎችን ያድርጉ ገቢዎንም ያሳድጉ!🎉 2019 ከያንጎ ጋር ልዩ የስኬት ዓመት ነው🌻 መልካም አዲስ ዐመት 2019የያንጎ ፕሮ መተግበርያን ለማውረድ ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇https://ya.cc/t/3nVOkmT99fvrCa
    17,000532Открыть в Telegram
  • እንማር

    14 сент., 13:34

  • እንማር

    14 сент., 05:09изменён

    እንደምን አደራችሁ!⭐️ የዛሬዋ ቀን ውብ ቀን ትሁንላችሁ! ሰላማችሁ የበዛ ይሁን! እናንተና የእናንተ የሆነው ሁሉ ይጠበቅ! ለምልሙ! አብቡ! ይመርባችሁ! ያቀዳችሁት ይሳካላችሁ! ምንም ክፉ አጠገባችሁ አይቅረብ!⭐️ ይህንን ሁሉ ፈጣሪ ያድርግላችሁ! እነዚህና ሌሎችም መልካም ነገሮች ሁሉ ሲሆኑላችሁ ግን ሞልቶ ለሌሎች መትረፉንና ማካፈላችሁን አትዘንጉ!ዶክተር Eyob-Mamo💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    19,000824536531Открыть в Telegram
  • እንማር

    13 сент., 18:02изменён

    ድሮ... ቆንጆ ስለሆነች ብቻ ነበር የወደድኳት ። ስቀርባት አራዳ ናት! አንድ ቀን በፀሃይ ተገናኝተን ስንቃደድ፥ ስንጫወት አስተናጋጇ መጥታ ይቅርታ ልወጣ ነው ሂሳብ አለችን ...ፈረቃዋን ጨርሳ ልትሄድ መስሎን ነበር፤ ለካ መሽቶ ሊዘጋ ነው። የምንወደው ሰው እንደኛው መለክያ ስናገኘው ሰዓቱ አልመጎተቱ ነው አይደል?ያልተመቸን ቦታ ሁሉ ሰዓቱ አይበርም!! ተፈጥሮ እንደ ምላስ We had an amazing time!! ብሎ አይዋሽም!!ስቀርባት መልኳን ትበልጠዋለች ...!ከሚሰማት 'ርቃ አታስመስልም፤ ጥላቻ አያሳድዳትም ፣ የበታቾቿ ላይ አትቀማጠልም። የወደቀ ላይ አትንጠራራም... ደስታዋ ቁስ ላይ አልተንጠለጠለም...።ትወጂኛለሽ እላታለሁ...?አስከሰማይ ነው የምወድህ ትላለች...አንገቴ ስር እየተወሸቀች። አወዳደዷ ስር አለው...ድንገት ተገንብሮ ውድቅ ሊል ይችላል የሚባል አይነት አይደለም።እዚህ ጋ...መዋደድ ባይኖር መኖር ይሰለቻል ብለን መኖርን እናበሽቀዋለን!!💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    17,200148141231Открыть в Telegram
  • እንማር

    13 сент., 07:42изменён

    አንድ ቀን አንድ ታዳጊ ለፋርማሲስቱ እንዲህ አለው፦“መዳኒቶች ውጤት አላመጡም የእናቴን ጣቶች ስጠኝ!”ፋርማሲስቱ፡- የእናትህ ጣቶች ምንድናቸው?ታዳጊው፡-“ለብዙ ዓመታት እንቅልፍ ማጣት ነበረብኝ፤ እናቴ ድንገት ተነስታ ካየችኝ ጭንቅላቴን መዳበስ ትጀምራለች። በዚህ እጅ ውስጥ ምን አይነት ተአምር እንዳለ ባላውቅም የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ”💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    17,60023955211743Открыть в Telegram
  • እንማር

    12 сент., 15:35изменён

    ያዘዝነው ቡና ከፊታችን ተቀምጧል፤ እና ጥቂት ቀመስንለት ስኳር የለውም። አስተናጋጁን ጠርተን ለመውቀስ ግን ድፍረቱ የለንም። በራስ መተማመናችን ጠፍቷል፤ ጠንክሮ የመከራከር ኃይላችን ሞቷል።ስኳሩ የእኛ መብት አይደለም። ምንአልባት ስኬታማ ሰዎች ብቻ ናቸው ቡና ውስጥ ስኳር ለማድረግ የተፈቀደላቸው።እናንተ ግን አንድ ጊዜ ላይ ስኬታማ ነበራችሁ። በክፍል ውስጥ ጎበዝ ተማሪ ነበራችሁ። አፋችሁን ከፍታችሁ ማውራት ስትጀምሩ አስተማሪዎቻችሁ በዝምታ ነበር የሚያዳምጧችሁ።ታድያ ምንድነው የተከሰተው?፤ ምን እየተካሄደ ነው?። የሕይወት መንገዳችን በድንገት ለምን ቆመ?። ለነገሮች ያለን ጉጉት እና ፍላጎት በጠቅላላ ወዴት ተሰወሩ?።—ዶ/ር አሕመድ ካሊድ ታውፊቅ💬💬@Enmare1988 💬💬@Enmare1988
    Иллюстрация к посту канала እንማርИллюстрация к посту канала እንማር
    17,900109503525126Открыть в Telegram