Последние посты

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
12 нояб., 13:57
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከ200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን ጥቃት መከላከል አልቻሉም ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከሰሰ‼️በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በደቡብ ሱዳን በምትገኝ አንዲት መንደር ውስጥ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመው ከ200 በላይ ሰዎችን ከመግደላቸው በፊት፣ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች እና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት የቀረቡላቸውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ተከትለው ተገቢውን እርምጃ አለመውሰዳቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሐሙስ ዕለት ይፋ ባደረገው አዲስ ሪፖርት፣ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው አቢየምኖም በተባለች አካባቢ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ ቀድሞ ያውቅ እንደነበር ገልጿል።የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲጌሬ ቻጉታህ "የሱዳን መንግስትም ሆነ የተባበሩት መንግስታት ባላቸው ተልእኮ የመከላከያ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል በቂ መረጃ እና ጊዜ ነበራቸው።ይሁን እንጂ ጠንካራ እርምጃ ባለመውሰዳቸው ምክንያት የሰዎች ሕይወት ጠፍቷል" ብለዋል።ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከአጎራባች ማዮም ግዛት የመጡ ከ1,000 እስከ 1,500 የሚገመቱ ታጣቂዎች ነዋሪዎችን በጥይት ገድለዋል።ባለስልጣናት በጥቃቱ 130 የከተማዋ ነዋሪዎች፣ 76 የጸጥታ አባላት እና ሰባት የውጭ ሀገር ዜጎችን ጨምሮ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።የሳተላይት ምስሎች ከ230 በላይ መኖሪያ ቤቶችና ተቋማት መቃጠላቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ተጎጂዎች በሁለት የጅምላ መቃብሮች ውስጥ መቀበራቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
10 нояб., 10:40
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የደረጃ «ሀ» ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገባቸውን እስከ ህዳር 2 እንዲያቀርቡ የቅጣት ዕድል ሰጠ‼️የ2018 የግብር ዘመን ማሳወቂያ ጊዜ ዛሬ ጥቅምት 30 መጠናቀቁን ተከትሎ፣ ቢሮው እስከ ረቡዕ ህዳር 2 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን የሚቀርቡ የሂሳብ መዝገቦችን በቅጣት ተቀብሎ እንደሚያስተናግድ አስታውቋል። ከህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሂሳብ መዝገብ ማቅረቢያው ሙሉ በሙሉ የሚዘጋ ሲሆን፣ ቢሮው ባለው መረጃ መሠረት ግምት በመስጠት ከከባድ ቅጣት ጋር ግብሩን እሰበስባለው ብሏል። ግብር ከፋዮች የተሰጣቸውን የሁለት ቀናት ተጨማሪ ዕድል በመጠቀም የሂሳብ መዝገባቸውን በኦንላይን እንዲያቀርቡ እና ያልተከፈሉ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
10 нояб., 10:39
📍ሲምሲ(CMC) /አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር/ አጠገብ🔥🔥35%እና 30%ልዩ ቅናሽ 🔥🔥 (የ3አመት ሳይት) 👉ባለ1መኝታ 73105,000=7,665,000 ቅድመ ክፍያ 20%=1,533,000 👉ባለ2መኝታ 112105,000=11,760,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,352,000 👉ባለ3መኝታ 125105,000=13,125,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,625,000 👉👉👉ለምሳሌ 100%ስትከፍሉ(አንዴ ስትከፍሉ) ባለ1መኝታ 7,665,000ብር የነበረው 5,365,500 ብር ይሆናል📍አዋሬ ቁጥር 240/60አከፋፈል 🔥ስቱዲዮ 42 እና 46 ካሬ 👉42 ካሬ 3.3 ሚሊየን 👉46 ካሬ 3.7 ሚሊየን 👉🏾 👉ባለ 1 መኝታ 80 እና 75 ካሬ 💥የ80ካሬ ➣ ሙሉ ክፍያ 9,200,000 ➣ 100% ክፍያ ለሚከፍል 30% ቅናሽ ሲደረግ ጠቅላላ ክፍያው 6.4 ሚሊዮን ብር ይሆናል።📍ቡልጋሪያ👉ስቲድዮ=40ካሬ 👉1መኝታ=62&70ካሬ 👉2መኝታ=110&113ካሬ 👉3መኝታ=152ካሬለበለጠ መረጃ 0978791342 ይደውሉ ቴምር ሪል እስቴት የህልምዎ ማረፊያ
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
9 нояб., 13:19
በመቀሌ ከተማ ፈቃድ የሌላቸው የጦር መሳሪያዎች እንዲያስረከቡ ትዕዛዝ ተሰጠ‼️የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የኮማንድ ፖስት በመቀሌ ከተማ ፈቃድ የሌላቸውን የጦር መሳሪያዎች የያዙ ግለሰቦች ከህዳር 1 እስከ ህዳር 3 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ለመንግስት እንዲያስረክቡ አዘዘ።ትዕዛዙን ባለማክበር ፈቃድ የሌለው መሳሪያ ይዘው በተገኙ አካላት ላይ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ተመላክቷል።በከተማዋ ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ድረስ ጥብቅ የፍተሻ መርሃ ግብር የሚካሄድ ሲሆን፣ ማህበረሰቡ ለጸጥታ ኃይሎች ተገቢውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
9 нояб., 08:38
1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ‼️በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 584 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡ወደ ሀገራቸው የተመለሱት 1ሺህ 432 ወንዶች ፣ 131 ሴቶች እና 21 ህፃናት ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው።ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ እየተሰራ እንደሆነ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡እስካሁን ከ114 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
9 нояб., 08:38
📍ሲምሲ(CMC) /አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር/ አጠገብ🔥🔥35%እና 30%ልዩ ቅናሽ 🔥🔥 (የ3አመት ሳይት) 👉ባለ1መኝታ 73105,000=7,665,000 ቅድመ ክፍያ 20%=1,533,000 👉ባለ2መኝታ 112105,000=11,760,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,352,000 👉ባለ3መኝታ 125105,000=13,125,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,625,000 👉👉👉ለምሳሌ 100%ስትከፍሉ(አንዴ ስትከፍሉ) ባለ1መኝታ 7,665,000ብር የነበረው 5,365,500 ብር ይሆናል📍አዋሬ ቁጥር 240/60አከፋፈል 🔥ስቱዲዮ 42 እና 46 ካሬ 👉42 ካሬ 3.3 ሚሊየን 👉46 ካሬ 3.7 ሚሊየን 👉🏾 👉ባለ 1 መኝታ 80 እና 75 ካሬ 💥የ80ካሬ ➣ ሙሉ ክፍያ 9,200,000 ➣ 100% ክፍያ ለሚከፍል 30% ቅናሽ ሲደረግ ጠቅላላ ክፍያው 6.4 ሚሊዮን ብር ይሆናል።📍ቡልጋሪያ👉ስቲድዮ=40ካሬ 👉1መኝታ=62&70ካሬ 👉2መኝታ=110&113ካሬ 👉3መኝታ=152ካሬለበለጠ መረጃ 0978791342 ይደውሉ ቴምር ሪል እስቴት የህልምዎ ማረፊያ
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
8 нояб., 10:43
ሶማሊያ ለኢትዮጵያ ንግድ ወደብ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ አለች‼️ሶማሊያ ወደብ ለሌላት ኢትዮጵያ የንግድ ወደብ አገልግሎት ለመስጠት በሩን ክፍት ማድረጓን፣ ነገር ግን ከሀገሪቱ ሉአላዊነት ጋር በተያያዘ ምንም አይነት ድርድር እንደማታደርግ አስታወቀች።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ መሀመድ ኦማር እንደገለጹት፤ በቱርክ አሸማጋይነት ከተፈረመው የአንካራ ስምምነት በኋላ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረገው ውይይት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይገኛል ተብሏል። ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም፣ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ካደረጉት ይፋዊ ጉብኝት በመቀጠል እሳቸውም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመሩ ገልጸዋል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
8 нояб., 10:43
📍ሲምሲ(CMC) /አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር/ አጠገብ🔥🔥35%እና 30%ልዩ ቅናሽ 🔥🔥 (የ3አመት ሳይት) 👉ባለ1መኝታ 73105,000=7,665,000 ቅድመ ክፍያ 20%=1,533,000 👉ባለ2መኝታ 112105,000=11,760,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,352,000 👉ባለ3መኝታ 125105,000=13,125,000 ቅድመ ክፍያ20%=2,625,000 👉👉👉ለምሳሌ 100%ስትከፍሉ(አንዴ ስትከፍሉ) ባለ1መኝታ 7,665,000ብር የነበረው 5,365,500 ብር ይሆናል📍አዋሬ ቁጥር 240/60አከፋፈል 🔥ስቱዲዮ 42 እና 46 ካሬ 👉42 ካሬ 3.3 ሚሊየን 👉46 ካሬ 3.7 ሚሊየን 👉🏾 👉ባለ 1 መኝታ 80 እና 75 ካሬ 💥የ80ካሬ ➣ ሙሉ ክፍያ 9,200,000 ➣ 100% ክፍያ ለሚከፍል 30% ቅናሽ ሲደረግ ጠቅላላ ክፍያው 6.4 ሚሊዮን ብር ይሆናል።📍ቡልጋሪያ👉ስቲድዮ=40ካሬ 👉1መኝታ=62&70ካሬ 👉2መኝታ=110&113ካሬ 👉3መኝታ=152ካሬለበለጠ መረጃ 0978791342 ይደውሉ ቴምር ሪል እስቴት የህልምዎ ማረፊያ
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
22 сент., 11:40
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል‼️በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
22 сент., 04:17
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት ከነገ ጀምሮ “ሁሉም የኢራን አየር መንገዶች በረራ ማከናወን አይችሉም” ሲሉ አስታወቁ‼️ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ግምጃ ቤት 27 የኢራን አየር መንገዶች ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንግፒንግ ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ።የሁለቱ አገራት መሪዎች ኢራን ላይ ስለተጣለው ማዕቀብ እንዲወያዩ ለማመቻቸት የቻይና ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ይ እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።የአሜሪካ መንግሥት ኢራን ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና ለማሳደር ባንኮች፣ የንግድ ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ እና በረራ ዘርፎች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል ከሳምንታት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
21 сент., 09:07
በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ ሰባት ታጣቂ ቡድኖች ፀረ መንግሥት ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ‼️ሰባት ታጣቂ ቡድኖችን ያካተተ "ትብብር ለኅልውና" የተሰኘ ጥምረት መመስረቱን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመነ ካሴ በትግራይ መገናኛ ብዙኃን ቀርበው ተናገሩ።አቶ ዘመነ ካሴ ትናንት መስከረም 10/2019 ዓ.ም. አመሻሽ ላይ በትግራይ መገናኛ ብዙኀን ላይ ባነበቡት መግለጫ መሠረት ትብብሩ ህወሓትን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን እና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄን ጨምሮ ሰባት ታጣቂ ቡድኖችን ያካተተ ነው።የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዘመነ በትግራይ ቴሌቭዥን በሰጡት መግለጫ የብልጽግና አገዛዝ ከተወገደ በኋላ "አካታች የሽግግር መንግሥት" እንደሚመሰረት ተናግረዋል።ይፋ በሆነው ትብብር አፋብን፣ ህወሓት፣ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ፣ የጉሙዝ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ፣ የኦጋዴን ሕዝብ ነፃነት ግንባርና የአፋር ብሄራዊ አንድነት ግንባር አባላት መሆናቸው ተነግሯል።አቶ ዘመነ በመግለጫቸው ትብብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን መንግሥት ለመጣል እና "በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግሥት" ለመመስረት ዓላማ እንዳለውም አስረድተዋል።ትብብር ለኅልውናን በሰብሳቢነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ "አዲስ የሽግግር ምዕራፍ" ሲሉ በመግለጫቸው የጠሩት ይህ ሂደት፤ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች "ሳይሸራረፉ እንዲረጋግጡ የሚያስችል" እንደሆነም አስታውቀዋል።ይህ "አዲስ ምዕራፍ" የሚከፈተው፤
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
21 сент., 09:06
💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት ሽያጭ መረጃ;የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው👉 1መኝታ 69ካሬ =ሙሉ ክፍያ 8,280,000ብር ይሆናል። 👉40%=3,312,000ብር ይሆናል ሌላው 60% ቤቱን ሲረከቡ የሚከፈል 👉100%ሲከፈል=5,382,000ብር ይሆናል።👉 1መኝታ(73 ካሬ):ሙሉ ክፍያ 8,760,000ብር|20%ቅድመ ክፍያ 1,752,000ብር። 40% 3,504,000ብር ቀሪውን ሲረከቡ 100% ሲክፈሉ 35% ቅናሽ 5,694,000 ብር ይሆናል።2 መኝታ (90 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 11,700,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,340,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=7,605,000 ብር ይሆናል ።3 መኝታ (112 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 14,560,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,912,000 ብር። 100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ =9,464,000ብር።3 መኝት (123ካሬ);ሙሉ ክፍያ 14,760,000 ብር | 20% 2,952,000ብር። 100%ሲከፍሉ35%ቅናሽ=9,594,000 ብር ይሆናል ።
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
21 сент., 09:06
переслано из @esat_tv1
ለአዳማ ነዋሪዎች በሙሉ❗️ለልዩ ቀንዎ እና ለልዩ ዝግጅትዎ ውብና ማራኪ መሆን ይፈልጋሉ? 💕በሙያው ብቃት ባለው Makeup Artist የሚያምርና የሚመጥንዎትን Makeup በጥራት እንሰራለን። 💄✨✨ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦👉 Simple Makeup 👉 Bridal & Bridesmaid Makeup 👉 Full Wedding Package 👉 Special Events Touch-up 👉 Henna & Mesh (Eyebrow)🌸 ደንበኞቻችንን በፍቅርና በጥራት እናገለግላለን!📍 አድራሻ፦ አዳማ 💄 Makeup Artist፦ Neb 📞 ስልክ፦ 0920393924
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
20 сент., 14:56
ግብጽ በዓለም ላይ ደካማ የውሃ አስተዳደር ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት‼️አቶ ጌታቸው ረዳአቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፤ የግብጽ አቋም የወንዙን እውነተኛ ምንጭ ጨምሮ ፍጹም ሐቅን የሚክድ የድፍረት አካሄድ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ ደግሞ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም፡፡ግብጽ ሳይንስን በተቃረነ መልኩ በዓባይ አጠቃቀም ዙሪያ የምታራምደው የተሳሳተ አካሄድ ግብፃዊያን “ታሪካዊ መብቶች” በሚል የተሳሳተ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው አድርጓል ብለዋል።“ታሪካዊ መብት” የሚለው ሀሳብ ውሃውን ቀድሞ መጠቀም የጀመረ አካል ለዘላለም መቆጣጠር አለበት ከሚል ስግብግብ አስተሳሰብ የመነጨ መሆኑን አመልክተዋል።ግብጽ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምታራምደው የ“ውሃ ደህንነት” ጽንሰ ሀሳብ ጊዜ ያለፈበት የአንድ ወገን የበላይነት ፍላጎት አካል መሆኑንም አብራርተዋል።ግብጽ በዓለም ላይ ደካማ የውሃ አስተዳደር ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት ያሉት አቶ ጌታቸው በበረሃማ አካባቢዎች የሚገኙት እንደ ቱሽካ ያሉ ከፍተኛ የውሃ መጠን የሚጠይቁ ፕሮጀክቶች የዚሁ ብክነት የተሞላበት አጠቃቀም ማሳያ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።በግብጽ በሚገኘው የአስዋን ግድብ የሚከሰተው ዓመታዊ የውሃ ትነት መጠን፣ በኢትዮጵያ የውሃ ማከማቻዎች ውስጥ ከሚቀመጠው የውሃ መጠን በእጅጉ የሚበልጥ መሆኑንም ተናግረዋል።የዓባይ ወንዝ ዋና ምንጭ በሆነችው ኢትዮጵያ እና ሰፊ የመስኖ አቅም ያላት ሱዳን መካከል ሰላም እንዳይኖር ግብጽ ስትሰራ መቆየቷን አንስተው፤ በሱዳን ያለው ቀውስ ሀገሪቱ ውሃውን እንዳትጠቀም ለማድረግ ግብጽ የምታራምደው ስትራቴጂ
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
20 сент., 12:13
ሁቲዎች የሳዑዲ አረቢያን ዋና ከተማ በባሊስቲክ ሚሳይሎች ማጥቃታቸውን ተናገሩ‼️በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ ተዋጊዎች በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ላይ የድሮን እና የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃት መፈጸማቸውን ገለፁ።በተጨማሪም በአገሪቱ የቀይ ባሕር ዳርቻ ላይ ባሉ የኃይል ተቋማት ላይ መሰል ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፀዋል።የሳዑዲ ባለሥልጣናት ቅዳሜ ዕለት ወደ ሪያድ የተወነጨፈ አንድ ባሊስቲክ ሚሳይል ማክሸፋቸውን የተናገሩ ቢሆንም ሌሎች ጥቃቶች ወይም ጉዳቶች ስለመኖራቸው አላረጋገጡም።ባለሥልጣናቱ ይህን ከማለታቸው አስቀድሞ፣ ቅዳሜ ዕለት በሳዑዲ ዋና ከተማ አቅራቢያ ባለው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አካባቢ ካሉ የነዳጅ ማጠራቀሚያዎች ጥቁር ጭስ ሲነሳ ታይቷል። ይህም በረራዎች ለአጭር ጊዜ እንዲስተጓጎሉ አድርጓል።ሁቲዎች በሐምሌ ወር በሳዑዲ አረቢያላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ካጠናከሩ በኋላ፣ በሪያድ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሎች ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰምተዋል።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያሉ አሜሪካውያን “ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ሊኖሩ ለሚችሉ የበረራ ስረዛዎች እና ሌሎች የጉዞ መስተጓጎሎች ዝግጁ እንዲሆኑ” አሳስቧል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
19 сент., 06:26

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
19 сент., 06:24

ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
17 сент., 13:22
ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ተሰውሯል የተባለ ተጠርጣሪ በኢንተርፖል ትብብር በቁጥጥር ሥር ዋለ❗️ከ46.4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውን 12 የ«BYD Seagull» ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በውክልና ለመሸጥ ከተረከበ በኋላ ገንዘቡን ለተበዳይ ሳያስረክብ ከባድ የማታለል ወንጀል ፈጽሞ ከሀገር ተሰውሯል የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።ተጠርጣሪው ከግል ተበዳይ አቶ ዮናስ ገብረመስቀል ጋር በነበረው የውክልና ስምምነት ተሽከርካሪዎቹን ከተረከበ በኋላ፣ የተገኘውን ገንዘብ ይዞ ከሀገር በመውጣት በታይላንድ፣ በሲንጋፖር፣ በፊሊፒንስ እና በኢንዶኔዥያ ሀገራት ከሕግ ተጠያቂነት ለማምለጥ ሲዘዋወር ቆይቷል።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ኅብረት ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር ባደረገው የቅርብ ትብብር በግለሰቡ ላይ ዓለም አቀፍ የቀይ ማስታወቂያ (Red Notice) እንዲወጣበት አድርጓል። በዚህም መሠረት ተጠርጣሪው መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም በኢንዶኔዥያ ኢንተርፖል በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፣ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ ተጠቅሷል።ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች ሁለት ከባድ የማታለል ወንጀሎች ተጠርጥሮ ተጨማሪ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ አስታውቋል።የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በተለያዩ የሽብርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች የሚፈለጉ አካላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ለማቅረብ ከሀገራት የፖሊስ ተቋማትና
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
16 сент., 17:34
የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ‼️ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።@Esat_tv1 @Esat_tv1
ESAT (ኢሳት🇪🇹)®
16 сент., 06:09
በአበሽጌ 13 ሰዎች ተገደሉ ‼️በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና ልዩ ስሙ "ዋልጋ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፣ ትላንት መስከረም 4/2019 ዓ.ም ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች በከፈቱት አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 13 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ታጣቂዎቹ ንጹሃኑን ከመግደል ባለፈ 16 ያህል ሴቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ አፍነው ወስደዋል።ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንዳሉ እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ አልተቻለም።@Esat_tv1 @Esat_tv1
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →