Последние посты

4-3-3 World News
14 нояб., 10:49
በትግራይ አፈሳን የሸሹ “800 ሺህ ወጣቶች” ወደሌሎች ኢትዮጵያ አካባቢዎች መሸሻቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ‼️ትግራይ ውስጥ በነበረው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ምክንያት “እስከ 800 ሺህ" የሚደርሱ ወጣት የክልሉ ነዋሪዎች ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች መሸሻቸውን የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ይህንን የተናገሩት ሰሞነኛው የፌደራል መንግሥት እና የትግራይ ኃይሎች ግጭት በድጋሚ ከተነሳ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት አርብ ኅዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም. በክልሉ መዲና መቀለ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።ኢታማዦር ሹሙ በቆይታቸው በክልሉ ከሚገኙ ከሠራዊት አዛዦች ጋር ግምገማ ማድረጋቸውን እንዲሁም “ወደ ሠራዊቱ አንዳንድ አሀዶች” በመሄድ ወታደሮችን ማግኘታቸውን ገልጸዋል።በመቀጠል ክልሉን የማስተዳደር ጊዜያዊ ኃላፊነትን ከተረከበው የባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር መወያየታቸውን አክለዋል።ከመቀለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በ2013 ዓ.ም. ከተነሳው ደም አፋሳሹ የሁለት ዓመት ጦርነት አንስቶ የነበሩ ክስተቶችን አንስተዋል።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
14 нояб., 04:14
የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብር ካባና የምስጋና ሽልማት አበረከተአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ አስተዳደር ለጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የክብር ካባና የምስጋና ሽልማት አበርክቷል።ሽልማቱ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በመቐለ ከተማ ተገኝተው ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍል ተወካዮች ጋር ሕዝባዊ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው የተበረከተላቸው።የክብር ካባውንና የምስጋና ሽልማቱን ያበረከቱት የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) ናቸው።በዚህ የእውቅና ሥነ ስርዓት ወቅት የሕዝባዊ ውይይቱን አስፈላጊነትና የማኅበረሰቡን ድምፅ በቀጥታ የማዳመጥ ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።በግዛቸው ግርማዬ@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
13 нояб., 13:51
የየመን መልዕክተኛ የሶሪያ ወታደሮች ወደ የመን ሊሰማሩ ነው የሚሉ ዘገባዎችን አስተባበሉደማስቆ እና ሰንዓ ይበልጥ የጠበቀ ግንኙነት ለመመስረት ፍላጎት እንዳላቸው ቢያሳዩም፤ የሶሪያ ኃይሎች በየመን ወታደራዊ ዘመቻዎች ለመሳተፍ እየተዘጋጁ ነው የሚሉ ዘገባዎችን ሁለቱም ወገኖች ውድቅ አድርገዋል።በሶሪያ የየመን ተጠባባቂ አምባሳደር መሐመድ አዚ ባክር ለሶሪያ የዜና አገልግሎት እንደገለጹት፤ወታደሮችን ስለማሰማራት የሚወጣ ዘገባ በመሬት ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ አያንጸባርቅም።እንዲህ ዓይነት ውሳኔዎች ሕጋዊ ሂደቶችን ተከትለው በይፋዊ ተቋማት በኩል ብቻ የሚገለጹ እና የሁለቱንም አገራት ጥቅም የሚያስከብሩ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።አምባሳደሩ፤የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሳድ ሀሰን አል ሻይባኒ የሁቲ ታጣቂዎች በሲቪሎች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ማውገዛቸውን እና ለየመን መንግሥት የሰጡትን ድጋፍ አድንቀዋል።በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነትም በተለያዩ ዘርፎች ወደ ላቀ ትብብር እየተሸጋገረ መሆኑን ገልጸዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አል ሻይባኒ በበኩላቸው ከዮርዳኖስ አቻቸው ጋር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤የሶሪያ ኃይሎች በየመን እንደማይገኙና ወታደሮችን የመላክ የቅርብ ጊዜ ዕቅድ አለመኖሩን አረጋግጠዋል።ማንኛውም የሶሪያ ወታደራዊ ስምሪት በድብቅ ሳይሆን በይፋ የሚታወጅ መሆኑንም ገልጸዋል።ሳራ ዮሐንስ@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
13 нояб., 11:50
የሰላም ድርድሮች ሰፊ ማዕቀፍ በሚሹበት ወቅት ሩሲያ እና ዩክሬን ጥቃቶች መድረሳቸውን ሪፖርት አደረጉሞስኮ እና ኪቭ በቀጣዩ የድርድር ዙር የአውሮፓ አጋሮችን ለማሳተፍ በተስማሙበት ወቅት፤ በሁለቱም አገሮች በተፈጸሙ ጥቃቶች ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ዋና ከተማ አቡዳቢ በአሜሪካ አደራዳሪነት የተካሄደው የሁለት ቀናት የሰላም ድርድር ከተጠናቀቀ ከሁለት ቀናት በኋላ፣ በሌሊት በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ዙሪያ ሩሲያ እና ዩክሬን እርስ በርስ በተወነጃጀሉበት ወቅት ቢያንስ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል።ሁለቱ ወገኖች በትልቅ ደረጃ የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ ተስማምተዋል፤ ዝርዝር ጉዳዮቹ ግን አሁንም በድርድር ላይ ናቸው።የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጃሬድ ኩሽነር ውይይቶቹ ‹‹የሁለቱንም ወገኖች ስጋቶች በመረዳት ሊሆኑ የሚችሉ መፍትሄዎችን በመለየት እና ወደፊት የሚኬድበትን መንገድ በመዘርጋት ረገድ ትርጉም ያለው መሻሻል አሳይተዋል››ብለዋል።አክለውም ሁለቱ ወገኖች በቀጣዩ የድርድር ዙር የአውሮፓ አጋሮችን ለማካተት መስማማታቸውን ገልጸው፤ይህም ከግዛት ጉዳዮች ጎን ለጎን ከጦርነቱ በኋላ በሚኖሩ ሰፊ የአውሮፓ የጸጥታ ዝግጅቶች ላይ ውይይት ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።ሳራ ዮሐንስ@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
13 нояб., 10:23
በፊት ቆዳ ላይ የቡና ዉህድን መጠቀም ለከፍተኛ የቆዳ ጉዳት እንደሚዳርግ ተገለፀበማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚለቀቁ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ምክሮች አብዛኛውን ጊዜ የሰዎችን ትኩረት የሚስቡ ቢሆንም ከሳይንሳዊ ትንተና ውጭ የሚደረጉ አሰራሮች ግን በቆዳ ላይ የማይተካ ጉዳት እንደሚያስትሉ ተጠቁሟል።የቆዳ እና የአባላዘር ስፔሻሊስት ሀኪም ዶክተር ደረጄ በዬቻ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ከሆነ በፊት ቆዳ ላይ መጠቀም ከማይገቡ ነገሮች መካከል የቡና ዉህድ ወይም ስክራብ ዋነኛዉ ነዉ ።የተወሰኑ ሰዎች የቡና ስክራብ ሲጠቀሙ ፊታቸዉ እያማረ ሊሄድ እና ምንም አይነት ጉዳትን በፊታቸው ቆዳ ላይ ላይመለከቱ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ቡና በሚወቀጥበት ወቅት በደንብ ስለማይደቅ በዉስጡ የሚይዛቸዉ የሚሻክሩ ነገሮች ከቆዳ ጋር ሲገናኙ በፊት ላይ ጉዳት እንደሚያደርሱ ተነግሯል ።ይህም ሳይንሳዊ ባልሆነ መንገድ ሲከናወን በአይን የማይታዩ ጥቃቅን የቆዳ ስንጥቆችን ወይም ማይክሮ ትራማን እንደሚያስከትል ዶክተር ደረጄ አስገንዝበዋል ።በተጨማሪም የቆዳ መላጥ ፣ መድረቅ እና መቆጣትን ስለሚያስከትል እነዚህ ትናንሽ ጉዳቶች የቆዳን ተፈጥሯዊ የመከላከል አቅም በማዳከም ለተለያዩ አለርጂዎች እና ለቆዳ ምቾት ማጣት ሊዳርጉ እንደሚችሉ ስፔሻሊስቱ ገልፀዋል ።የቡና ስክራብን የሚመርጡ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ የሚጠቀሟቸዉ የቆዳ ማለስለሻ ቅባቶች ለቆዳቸው ተስማሚ ካልሆኑ መንስኤው ስክራብን የመጠቀም ዉጤት ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል ።በመሆኑም እነዚህ ዉህዶች ለአንዱ ቢስማሙም ሌላው ሰው ላይ ተመሳሳይ ውጤት ስለማያመጡ ሰዎች ከመጠቀማቸው አስቀድሞ የባለሙያ ምክርን ማግኘት እና የፊታቸውን የቆዳ ዓይነት ማወቅ እንደሚገባቸው ስፔሻሊስቱ አሳስበዋል ።በመባ ወርቅነህ@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
12 нояб., 22:02изменён
'የታክሲ የለኝም እባክህ ልጄን ይዘሃት ሂድ....😥;«እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!»ዛሬ ጠዋት ታክሲ ውስጥ ሙሉ ተሳፋሪውን በእንባ ያራጨ፣ እስከ አሁን ድረስ ውስጤን እያደማው ያለ ልብ ሰባሪ ክስተት...ጠዋት ወደ ስራ ለመሄድ ታክሲ ተሰልፌ ገባሁ። በመስኮት በኩል ሳስተውል አንዲት እናት በጣም ቆንጆ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ትንሽ ልጇን እጅ ይዛ ቆማለች። ታክሲው ሊሞላ ጥቂት ሰው ብቻ ነው የቀረው፤ «ይቺ እናት ለምን አትገባም? ልጇ አረፈደች እኮ...» እያልኩ በልቤ ሳስብ...እናትየው ድንገት ወደ መጀመሪያው ወንበር ተጠግታ መስኮቱን አንኳኳች። የፊት ወንበር ላይ የተቀመጠው ሰውዬ መስኮቱን ሲከፍተው በለዘበ፣ በሀፍረትና በጭንቀት በተሰበረ ድምፅ እንዲህ አለችው፦«ወንድሜ... እባክህ ልጄን ይዘህልኝ ትሄዳለህ? እኔ የታክሲ ገንዘብ የለኝም... እቀፋት ንፁህ ናት!»ይሄን ስትል የታክሲው ድባብ ድንገት ፀጥ አለ፤ ልቤ ተንሰፈሰፈ! «እቀፋት ንፁህ ናት» የሚለው ቃሏ እንደ ጦር ልቤ ውስጥ ተሰካብኝ። ድህነት እንዲህ ያሳንሳል? የገዛ ልጇን ሰው እንዲሸከምላት ስትለምን እንኳ «ንፁህ ናት» ብላ ይቅርታ እንድትጠይቅ ያስገድዳል?የፊት ወንበር የተቀመጠው ጨዋ ሰው ያለምንም ማመንታት «ኧረ በደስታ እህቴ! ምንም ችግር የለውም፤ ችግር አይንካሽ አምጪያት» ብሎ ልጅቷን በክብር ተቀብሎ አቀፋት። ረዳቱም «የትምህርት ቤቱን በር አውቀዋለሁ እዛው አወርዳታለሁ አትጨነቂ» አለ።እናት ግን ልቧ አልቻለም... የልቧ ጭንቀት እረፍት ነሳትና ዐይኖቿ በእንባ ተሞልተው «እባክህ ስልክህን ጻፍልኝ?» አለችው፤ የእናት አንጀት አይደል! ስልኩን ተቀበለች። ድህነት አይኑ ይጥፋ ወላሂ! ይሄን ያየው ተሳፋሪ በሙሉ ልቡ ተነካ። ሁሉም ኪሱን ፈትሾ ለነገዋ፣ ለቀጣዩ ቀኗ የታክሲ የሚሆናትን ብር አዋጥቶ ሰጣት።ታክሲው ተነስቶ መንቀሳቀስ ሲጀምር... ያቺ ምስኪን እናት ታክሲው እይታዋ እስኪሰወር ድረስ እዛው ቆማ፣ በልጇ ላይ ያፈጠጠውን የፍቅርና የጭንቀት ዐይኗን ሳትነቅል እያየችን ቀረች።እናት ማለት ይቺ ናት... ለልጇ ትምህርት ስትል ክብሯን ጥላ የምትለምን፣ ራሷ በባዶ እግሯ ቆማ ልጇን ወደ ከፍታ የምትሸኝ! ፈጣሪ ለደጉ ተሳፋሪም፣ ለምስኪኗ እናትም ይድረስላቸው።(መረጃው የአሃዱ ሚዲያ ነው/Afi Natilus)@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
12 нояб., 13:19
ከሞት በኃላ የአይን ብሌን መለገስን የሚፈቅድ ዉሳኔ መስጠቱን የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ገለፀበጤና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አማካኝነት ከሞት በኃላ የአይን ብሌንን ስለመለገስ ኃይማኖታዊ ውሳኔ ፈትዋ ለማግኘት በምክር ቤቱ የዑለማ ጉባኤ ለከፍተኛ የፈትዋ ኮሚቴ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም ላይ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ተገልጿል ።ይህንንም ተከትሎ የሸሪዓን መሠረታዊ ዓላማዎች ወይም መቃዲሶች ከግምት ዉስጥ በማስገባት በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር ተደርጎ ጥቅምት 25 ቀን በተካሄደዉ ስብሰባ ከሞት በኃላ የአይን ብሌንን መለገስ እንደሚፈቀድ ውሳኔ መሰጠቱን የገለፁት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጠቅላይ ጸሐፊ ሃጂ መሱድ አደም ናቸዉ ።ይህም የሚሆነዉ የለጋሹ ሞት ከተረጋገጠ ፣ኑዛዜዉ ከመሞቱ በፊት የተደረገ ከሆነ ፣ያለምንም ቁሳዊ ወይም የገንዘብ ክፍያ በበጎ ፈቃደኝነት የተደረገ ፣የዓይን ብርሃን ለሚፈልገዉ አካል እዉነተኛ ጥቅም የሚሰጥ መሆኑ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን የገለፁት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክርቤት የኡለማ ጉባኤ ፀሀፊ ሼህ መሀመድ ዘይኑ ናቸዉ ።በተጨማሪም የሟቹን አካል መቆራረጥ ወይም የሰዉነት ቅርፅ ማበላሸት የማይፈቀድ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ድርጊቱም ህጋዊ በሆነ የህክምና ተቋም እና በባለሙያ በኩል መከናወን እንዳለበት ተጠቁሟል።በመባ ወርቅነህ@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
12 нояб., 12:23изменён
በደቡብ አፍሪካ በአንድ ግለሰብ ላይ ፆታዊ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ዋሉበደቡብ አፍሪካ ቴምቢሳ በተባለች ከተማ አንድ የ32 ዓመት ወጣት በሚኖርበት አካባቢ ከሚገኝ አንድ መጠጥ ቤት ውስጥ አብሯቸው ካመሸ በኋላ ፆታዊ ጥቃት ደርሶብኛል ማለቱን ተከትሎ ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለዋል።እንደ ዘገባዎች ገለጻ፣ ምሽቱን በመጠጥ ቤቱ ውስጥ ካሳለፋ በኋላ ሁለቱ ሴቶች ግለሰቡን ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንዲከተላቸው ጋብዘውታል።ግለሰቡ ጥቃቱ ከተፈጸመበት በኋላ አምልጦ በመውጣት የመኖሪያ ቤቱን ባለቤት እርዳታ የጠየቀ ሲሆን፣ ባለቤቱም ለፖሊስ ጥቆማ መስጠቱ ተገልጿል።ይህ ክስተት በደቡብ አፍሪካ ሰፊ ህዝባዊ ክርክር እና ውይይት ቀስቅሷል። የማህበራዊ ሚዲያዎች የተፈጸመውን ድርጊት በጽኑ ከመኮነን አንስቶ፣ ወንዶች የፆታዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።በፆታዊ ጥቃቶች ላይ የሚሰሩ ተሟጋቾች ይህ አጋጣሚ ማንኛውንም ፆታ ሊጎዳ እንደሚችል የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም ከወንድነት ባህሪ ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ዘንድ የተሳሳተ አመለካከት እና ጫና መኖሩን ጠቅሰዋል።እንዲህ ላሉ ጥቃቶች ሰለባ የሚሆኑ ወንዶች አቤቱታቸውን ለፖሊስ እንዳያቀርቡ ወይም እርዳታ እንዳይፈልጉ እንቅፋት እንደሚሆንባቸው ገልጸዋል።ድርጊቱ በቴምቢሳ ነዋሪዎች እና በተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ያስነሳ ሲሆን፣ የፆታዊ ጥቃት አቤቱታዎች እኩል ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል።ደቡብ አፍሪካ ከፆታዊ ጥቃቶች ጋር ተያይዘው የሚነሱ አጣዳፊ ችግሮችን ለመፍታት እየታገለች ትገኘለች ነው የተባለው።ተሟጋቾች የጥቃቱ ሰለባዎች የድጋፍ አገልግሎቶችን በቀላሉ የሚያገኙበት እድል እንዲመቻችላቸው እና የቅድመ መከላከል ስራዎች እንዲጠናከሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።የማህበረሰቡን የተሳሳተ አመለካከት መቅረፍ ተጎጂዎች ያለ ስጋት እርዳታ እንዲጠይቁ ለማድረግ ወሳኝ እንደሆነ አመልክተው በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለቱ ሴቶች በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተነግሯል።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
22 сент., 18:51
переслано из @tech_433et
በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰውና ቶቦት መካከል የተደረገ የ ቦክስ ፍልሚያ🙆♂️🙆♂️🥶https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy https://t.me/+5sCQf3Z1UUAxZDAy
4-3-3 World News
22 сент., 18:34
በሕይወት እያለ የራሱን የሐዘን ባነር ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ‼በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦካ ቀበሌ በሕይወት እያለ የራሱን ፎቶ በመጠቀም "ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" የሚል የሐሰት የሐዘን መግለጫ ባነር ያዘጋጀ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሽካ እንደገለጹት፡ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥንና አለመረጋጋትን የፈጠረ አሳዛኝ የስነ-ምግባር ግድፈት ነው። ህብረተሰቡ የሐሰት ወሬዎችን ሳያጣራ እንዳያምንና በጥንቃቄ እንዲመለከት አሳስበዋል።በማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ በሚቀልዱ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ይቀጥላል። በግለሰቡ ላይ የሚደረገው የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ህጋዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ክትትሉ እንደሚቀጥል ጠቅሶ መረጃውን የሰሜን ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን አጋርቷል።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
22 сент., 18:06
የጓደኛውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥር በመውሰድ 20ሺህ ብር ያወጣው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።ግለሰቡ ወንጀሉን የፈጸመው ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00 ሰዓት በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።ጉታ ገመዳ የተባለው ግለሰብ ከግል ተበዳይ ጋር በጓደኝነት አንድ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ የግል ተበዳይ ቤት ውስጥ ያስቀመጠውን የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥሩን በመውሰድ ከግል ተበዳይ የሂሳብ ደብተር ፊርማ ጋር በማመሳሰል በክ/ከተማው ወረዳ 7 ከሚገኝ ባንክ 20ሺህ ብር ወጪ አድርጓል፡፡ግለሰቡ ገንዘቡን ካወጣ በኋላ የግል ተበዳይ በደረሰው መልዕክት አማካኝነት ባንኩን በመሄድ ይጠይቃል።ገንዘቡ ወጪ መደረጉን ምላሽ የተሰጠው የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለአቅራቢያው ሙገር ፖሊስ መምሪያ አመልክቷል፡፡አቤቱታው የደረሰው ፖሊስም ምርመራውን በማጣራትና ባንኩ ውስጥ የነበረን ካሜራ በመጠቀም ወንጀል ፈጻሚውን በመለየት ከነ ኤግዚቢቱ ማስመለሱን የመምሪያው የወንጀል ምርመራ ምክትል መምሪያ ኃላፊ ኢ/ር ዮሴፍ ገረመው ተናግረዋል።ወንጀል ፈጻሚው ክስ እንደተመሰረተበትም ኃላፊው ገልፀዋል።ግለሰቦች የባንክ ደብተር የሂሳብ ቁጥራቸውን ከራሳቸው ውጪ ለየትኛውም አካል አሳልፈው መስጠት ወይም በግዴለሽነት ለወንጀል ተጋላጭ በሆነ ቦታ ማስቀመጥ እንደሌለባቸው የገለጹት ኃላፊው ደንበኞች ገንዘብ ለማውጣት ወደ ባንክ ሲሄዱም የባንክ ባለሙያዎች የሂሳብ ደብተሩ ባለቤት ትክክለኛ ማንነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡@Ethione
4-3-3 World News
22 сент., 15:57
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ተከፈተየዓለም መንግሥታት በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) 81ኛዉ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሰባስበዋል ። በጉባኤው ላይ ንግግር ያሰሙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፦ በላቲን አሜሪካ የጦር ኃይል የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም ሊያስጠብቅ ይችል ይሆናል ሲሉ ዝተዋል ። ፕሬዚደንቱ ተመድ ለተገኙ ጋዜጠኞች ሲናገሩም፦ ለሩስያ ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን መልእክታቸው «ጦርነቱን እንዲያበቁ» እንደነበር ገልጠዋል ። ከሳቸው በተጨማሪ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ኤማኑዌል ማክሮ እና የቱርክ አቻቸው ፕሬዚደንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃንን ጨምሮ ሌሎችም ንግግር ያሰማሉ ተብሏል ። 81ኛውን የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ በይፋ የከፈቱት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ናቸው ። በንግግራቸውም፦ ስለእራኤል እና ፍልስጥኤም ግጭትን በማንሳት በምዕራብ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ የአይሁድ የሰፋሪዎች መስፋፋት «የዘር ማጽዳት ሥጋቱን እያሰፋው ነው» ብለዋል ። የብራዚል ፕሬዚደንት ሉዊስ ኢናቺዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ተመድ ጦርነቶችን ለማስቆም አለመቻሉን ተችተዋል ።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
22 сент., 08:21
በቻይና ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስወገድ እንዲቧጨሩ የሚያደርግ ልዩ የቧጨራ ሳሎን ተከፈተበቻይና የ32 ዓመቱ ዣንግ ሺያኦቻኦ ሰዎች ጭንቀታቸውን ለማስታገስ በሰራተኞች በቀስታ የሚቧጨሩበትን ልዩ የአገልግሎት ሳሎን ከፍቶ በወር ወደ 100,000 ዩዋን ያህል ገቢ እያገኘ መሆኑ ተዘግቧል።ዣንግ ይህን ያልተለመደ የንግድ ሀሳብ ያገኘው በኢንተርኔት ላይ ባየው አጭር ቪዲዮ መሆኑን ገልጿል። በቪዲዮው ላይ አንዲት ሚስት የባለቤቷን ጀርባ በቀስታ ስትቧጭ ተመልክቶ አስተየየት ሰጪ የነበሩ ሰዎችም “እንዲህ ያለ አገልግሎት ቢኖር ገንዘብ እንከፍላለን” የሚሉ መልዕክቶቹን በመመልከቱ ወደዚህ ስራ መግባቱ ተናግሯል።የመጀመሪያው የቧጨራ ሳሎን ከተከፈተ ብዙም ሳይቆይ ሁለተኛ ሳሎን መክፈት ችሏል ሁለቱም ሳሎኖች በአጠቃላይ በወር ወደ 100,000 ዩዋን የሚጠጋ ገቢ እንደሚያገኝ ተነግሯል።ደንበኞች በጀርባቸው ተኝተው ሰራተኞች በልዩ የፕላስቲክ ጥፍሮች በመጠቀም ሰውነታቸውን በቀስታ ይቧጫሉ። ዣንግ ይህን ሥራ ለመጀመር ልዩ የቧጨራ ቴክኒኮችን ራሱ መመርመርና መፍጠር እንደነበረበት ገልጿል።አንድ ሰዓት የቧጨራ አገልግሎት 300 ዩዋን ያስከፍላል።የንግዱ ዋና ዓላማም ሰዎች የከተማ ሕይወት የሚያመጣውን ጭንቀት እንዲያስታግሱና የእንቅልፍ ጥራታቸውን ለማሻሻል ዘና የሚያደርግ ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ እየሰራ መሆኑ ተነግሯል።ዣንግ የከተማ ነዋሪዎች የጭንቀት ደረጃ ከፍ ያለ በመሆኑ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ፍላጎት እንዳለ በመግለጽ አንዳንድ ደንበኞችም አገልግሎቱ ከማሳጅ ይልቅ የበለጠ ዘና እንደሚያደርጋቸው እንደነገሩት ተናግሯል።
4-3-3 World News
22 сент., 07:10
" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል።በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም
4-3-3 World News
22 сент., 05:43
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት ከነገ ጀምሮ “ሁሉም የኢራን አየር መንገዶች በረራ ማከናወን አይችሉም” ሲሉ አስታወቁ...ከሁለት ሳምንት በፊት የአሜሪካ ግምጃ ቤት 27 የኢራን አየር መንገዶች ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንግፒንግ ከሁለት ቀናት በኋላ ወደ አሜሪካ ተጉዘው በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ይመክራሉ።የሁለቱ አገራት መሪዎች ኢራን ላይ ስለተጣለው ማዕቀብ እንዲወያዩ ለማመቻቸት የቻይና ምክትል ፕሬዝዳንት ዋንግ ይ እና የአሜሪካ ግምጃ ቤት ኃላፊ ስኮት ቤሳንት እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።የአሜሪካ መንግሥት ኢራን ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና ለማሳደር ባንኮች፣ የንግድ ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ እና በረራ ዘርፎች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል ከሳምንታት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
21 сент., 16:25
ሳይንቲስቶች ከ100 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ የዱር ድመት ዝርያ አገኙ ሳይንቲስቶች በቦሊቪያ በሚገኝ የዱር እንስሳት መጠለያ ውስጥ የሚኖር ቀደም ሲል ያልታወቀ የዱር ድመት ዝርያ አግኝተዋል።ይህች ትንሽ ድመት በመጠለያው ውስጥ ለብዙ ዓመታት የኖረች ሲሆን፣ የጄኔቲክ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ከ100 ዓመታት በላይ በሚሆን ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘች አዲስ የዱር ድመት ዝርያ መሆኗ ታውቋል።በከረንት ባዮሎጂ ሳይንሳዊ መፅሔት ላይ ሐሙስ ዕለት የተደረገው ይህ ግኝት፣ ሳይንቲስቶች በሕይወት ያለች የዱር ድመት ዝርያን የሰየሙበት እና ያብራሩበት አጋጣሚ ሆኗል።የናሽናል ጂኦግራፊክ አሳሽ እና የጥናቱ ዋና አዘጋጅ የሆኑት ቦሊቪያዊቷ የባዮሎጂ ባለሙያ ፓኦላ ኖጋሌስ-አስካሩንስ እንደተናገሩት፣ ድመቷ የተለየ መልክ እንዳላት ያስተዋለ አንድ የስራ ባልደረባቸው በአገሪቱ ዩንጋስ ክልል በሚገኘው መጠለያ ውስጥ በፈቃደኝነት በምትሰራበት ወቅት እንድትመረምራት ጠይቋት ነበር።ድመቷን በጫካ ውስጥ ያገኟት አንድ የአካባቢው ቤተሰብ በቤት ውስጥ ለማራባት ካጋጠማቸው ችግር በኋላ ወደ መጠለያው አምጥተዋት ነበር። ባለሙያዋን ያስገረማት የድመቷ መጠን እንደነበር ገልፃለች።ተራ ከሚባለው የቤት ድመት የሚያንስ መጠን እና የ10 ዓመት ገደማ እድሜ ያላት ይህች ድመት ከራሷ እስከ ጅራቷ መነሻ ድረስ ያለው ርቀት 46 ሴንቲሜትር ይረዝማል።ክብደቷም 1.4 ኪሎ ግራም ብቻ የሚመዝን መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፈካ ያለ ቡናማ ቀለም ያለው ፀጉሯ በነብር መሰል ጥቁር ነጠብጣቦች የተሸፈነ ነው።ሰላማዊ ነጋሲ@Eth
4-3-3 World News
21 сент., 12:47
ሚድሮክ ዝቅተኛውን የሰራተኞች ደመወዝ ወደ 10,000 ብር አሳደገሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2019 በጀት ዓመት አነስተኛ የወርሃዊ ደመወዝ ወለልን ከ6,000 ወደ 10,000 ብር ማሳደጉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ጀማል አህመድ አስታወቁ።ኩባንያው ለደመወዝ ጭማሪ ተጨማሪ 3.24 ቢሊዮን ብር የመደበ ሲሆን፣ ይህም ጠቅላላ ዓመታዊ የደመወዝ በጀቱን ወደ 13 ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል።በተጨማሪም ባለፈው የበጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር የቦነስ ክፍያ የተፈጸመ ሲሆን፣ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ 700 ሰራተኞች ከ100,000 እስከ 500,000 ብር የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል።ሚድሮክ ከትርፉ 10 በመቶ ለማህበራዊ ድጋፍ የዋለ ሲሆን፣ በዓመቱ 390 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም ገልጿል።ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 80,000 ሰራተኞች አሉት።@Ethionews433 @Ethionews433
4-3-3 World News
21 сент., 10:43
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ትግራይ ቴሌቪዥንን አገደትግራይ ቴሌቪዥን ባሳራጫቸው የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ በሚጥሉ መልዕክቶች ታግዷል አለ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፡፡ባለስልጣኑ ባወጣው መግለጫ በመንግሥት እና በሕወሓት መካከል በፕሬቶሪያ የተፈጸመውን የሰላም ስምምነት ተከተሎ፣ ባለስልጣኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ባደረገው ውይይት መሰረት ቀደም ሲል በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነስቶ ወደ ሥራ መመለሱን አስታውሷል፡፡ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ለትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች የሰላም ግንባታና የሙያ ብቃት ማሳደጊያ ሥልጠናዎችን በመስጠት ሚዲያው ወደ ሕገ መንግሥታዊና ሙያዊ መስመር እንዲመለስ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የትግራይ ቴሌቪዥን በተሰጠው ዕድል ተጠቅሞ እና የሙያ ሥነ-ምግባር አክብሮ አገልግሎት መስጠት ሲገባው፤ የሀገርንና የህዝብን ደህንነት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ጽንፈኝነት የሚያበረታቱ መልእክቶች በተከታታይ ማስተላለፉን አመልክቷል፡፡በመሆኑም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በህግ የተጣለበትን ኃላፊነት መሠረት በማድረግ፣ ከዛሬ ጀምሮ በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን አስታውቋል።ማንኛውም ዲጂታል፣ የብሮድካስትም ሆነ የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም የቴሌቪዥን ጣቢያው በህገወጥ መንገድ የሚያሰራጫቸውን ይዘቶች አሰራጭቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ መሁኑን ጠቁሟል፡፡
4-3-3 World News
21 сент., 05:27
የሩሲያ ፓርላማ ዱማ ምርጫ በሚጠናቀቅበት ወቅት ዩክሬን የድሮን ጥቃት ስትፈፅም ክሬሚሊን ደግሞ ምርጫው የጦርነቱን ህዝባዊ ድጋፍ ያሳየ ነው አለችየሩሲያ ገዢው ዩናይትድ ሩሲያ ፓርቲ የበላይነቱን እንደሚይዝ በተጠበቀበት እንዲሁም የፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስተዳደር የህዝብ ድጋፍ መለኪያ አድርጎ በወሰደበት የፓርላማ "ስቴት ዱማ" ምርጫ የሦስት ቀናት የድምፅ መስጠት ሂደት የተጠናቀቀ ሲሆን ዩክሬን በምርጫው ወቅት ከአንድ ሺህ በላይ ድሮኖችን ተጠቅማ ሞስኮን ደብድባለች ተባለ።በምርጫው የፑቲን ፓርቲ 57.5 በመቶ በቅደሚያ ውጤት እየመራ መሆኑ ታውቋል፡፡ይህ ምርጫ ሩሲያ እ.አ.አ የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ በሙሉ ወረራ ማለትም ሩሲያ የአንድ ሳምንት ዘመቻ ብላ ከከፈተችው ጦርነት ወዲህ የተካሄደ የመጀመሪያው የዱማ ምርጫ ሲሆን ክሬምሊን የምርጫውን ውጤት ህዝቡ ለፑቲን ፖሊሲዎች እና ለጦርነቱ ያለውን ድጋፍ ለማሳየት የሚጠቀምበት መሳሪያ ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከምርጫው በፊት አድርገውታል በተባለው ንግግር የምርጫው ውጤት ሚሊዮኖች የሩሲያ ህዝቦች በዩክሬን ውስጥ ለሚዋጉት ወታደሮች ያላቸውን ድጋፍ የሚያረጋግጥ እና ሀገሪቱ የተዋሃደች መሆኗን የሚያሳይ ነው ብለዋል።በዚህ ምርጫ ላይ ጦርነቱን የሚቃወሙ አብዛኞቹ እጩዎች ከምርጫው ውጪ የተደረጉ ሲሆን ተቺዎች እና ምዕራባውያን በበኩላቸው በሩሲያ ውስጥ እውነተኛ የፖለቲካ ተቃውሞ እንደማይቻል በመግለፅ ላይ ናቸው።በምርጫው የመጨረሻ ቀን ዩክሬን ያላትን አቅም ተጠቅማ በሞስኮ እና በዙሪያዋ ከፍተኛ የድሮን ጥቃት
4-3-3 World News
20 сент., 09:08изменён
መጋቢ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደስ እና ወ/ሪት ሳምራዊት መላኩ በዛሬው ዕለት የጋብቻ ሥነ-ሥርዓታቸውን ፈጸሙበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሚያቀርቧቸው መንፈሳዊና ሳይንሳዊ ምርመራዎች የሚታወቁት ተወዳጁ መጋቢ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደስ ከወይዘሪት ሳምራዊት መላኩ ጋር ጋብቻቸውን በዛሬው ዕለት መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ፈጽመዋል።የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ ቶታል ሰፈር ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በሃይማኖታዊ ሥርዓት መካሄዱ ታውቋል።በዕለቱም በርካታ ወዳጆች፣ አድናቂዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሥነ-ሥርዓቱ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።@Ethionews433 @Ethionews433
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →