Последние посты

Ethio-Chamber
22 сент., 14:23
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፤ ንግድና ኢንቨስትመንትን የማስተዋወቅ፣ ግልጽና ተወዳዳሪ የንግድ ስርዓት እንዲኖር የመደገፍ፣ ስነ-ምግባራዊ የንግድ አሠራርን የማጠናከርና በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ሆኖ የማገልገል ኃላፊነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ዛሬ ሕገወጥ ንግድን በመከላከል ዙሪያ የተካሄደው መድረክ ችግሮቹ ላይ በመወያየት የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ በመተለም ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል።ሕገ-ወጥ ንግድ ሕጋዊ የንግድ ድርጅቶችን ከማዳከሙም ባሻገር መንግሥት የሚሰበስበውን ገቢ ያሳጣል፣ የአገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንትን ያዳክማል እንዲሁም ሙስናን በማስፋፋት በንግድ ድርጅቶች መካከል የሚኖር ውድድርን የሚያዛባ ሲሆን ፤ የድንበር ቁጥጥርን በማዳከምም ሕዝቡ በተቋማት ላይ ያለውን አመኔታም እንዲያጣ ያደርጋል።ከዚህም ባሻገር የሕጋዊ ንግድ ተቋማትን ብቻ የሳይሆን ሸማቾችን፣ መንግሥትን፣ ሠራተኞችን፣ አምራቾችንና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን የሚነካ ጉዳይ ነው።በመሆኑም ፤ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማካሄድ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የኤክስፖርት ተወዳዳሪነትንና የኢንዱስትሪ ሽግግርን ለማጎልበት በትጋት በምትሠራበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ ሕገ-ወጥ ንግድ ለአገራዊ ልማት ከባድ ፈተና ሆኖ የዘለቀ በመሆኑ መከላከሉ ትኩረት ያሻዋል።በዚህ አጋጣሚም፤ ኮንትሮባንድ ወይም ሕገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት❇️❇️❇️❇️ የኢትTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
22 сент., 14:23



Ethio-Chamber
22 сент., 13:32
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ፣ በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ የንግድ አማካሪ ከሆኑት ከአይሃን ቡዩክቱርክ ጋር መክረዋል።በውይይቱም በሁለቱ ሀገራት መካከል አዳዲስ የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎችን መክፈት፣ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ማህበረሰብና ባለሀብቶች የቀረበ ግንኙነት መፍጠር፣ እንዲሁም የጋራ እድገትን የሚያፋጥኑ አበይት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ተመክሮበታል።❇️❇️❇️❇️Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations Secretary General, Dr. Kenenissa Lemie met with Mr. Ayhan Buyukturk, Commercial Counsellor at the Turkish Embassy in Ethiopia, to explore fresh avenues for economic collaboration.The meeting centered on unlocking new trade and investment opportunities, building stronger connections between business leaders from both nations, and accelerating joint initiatives to support mutual economic growth. ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/TelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
22 сент., 13:32





Ethio-Chamber
22 сент., 13:17изменён
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው በምስራቅ ኢትዮጵያ ኮሪደር ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ መከላከል ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ።በመድረኩም ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከአዲስ አበባ ፣ ከሶማሌ ክልል፣ ከሀረሪ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል የንግድ ቢሮዎች፣ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ ከጸጥታ ተቋማት፣ ከቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማኅበርና ከሌሎች ማኅበራትና ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ፣ ህገ-ወጥ ንግድ ህጋዊ ነጋዴውን ከገበያ በማስወጣት በሀገሪቱ የንግድ ስርዓት ላይ ከባድ ጫና ከማድረጉም ባሻገር በሀገር ደህንነት ላይ ስጋት የሚደቅን አደገኛ እንቅስቃሴ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የምስራቅ ኢትዮጵያ ኮሪደር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱበት ዋናው አካባቢ እንደመሆኑና ካለው የጠረፍ ስፋት አንጻር ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን የሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡ በውይይት መድረኩ እንደ ቶባኮ ምርቶች ህገ-ወጥ ዝውውርና ስርጭት ፣ ጎማ እንዲሁም ከቁም እንስሳት ንግድ ጋር በተያያዘ የመወያያ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱ በተለይም በጉዳዩ ዙሪያ ቀጥተኛ ባለቤት የሆኑ ተቋማትን ያሳተፈ ምክክር በማዘጋጀቱ ተሳታፊዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣TelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
22 сент., 13:17





Ethio-Chamber
22 сент., 13:17





Ethio-Chamber
21 сент., 10:28
❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in


1,140Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
21 сент., 07:07
Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA), Business Leadership Academy (BLA), invites the private sector to participate in: Import/Export Procedures and Documentation Record and Archives Management Additional information can be found in the promotional poster. ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
1,190Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
18 сент., 18:01
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የግሉ ዘርፍን አቅም ለማጠናከር ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ የሆነው የአራት ቀናት የሴቶች አመራርነት (Women in Leadership) ስልጠና ተጠናቋል።የሴቶች የአመራር ክህሎትን በማጎልበት አቅማቸውን እንዲጠቀሙ በማስቻል፤ ጠንካራ ተቋማትን፣ ውጤታማ አመራርን እና የበለጠ ተወዳዳሪ የግሉ ዘርፍን መገንባት ይጠበቅብናል።ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ❇️❇️❇️ We are pleased to have successfully concluded the four-day Women in Leadership training programme, which is part of ECCSA’s ongoing efforts to strengthen the capacity of the private sector.By investing in women’s leadership skills and enabling them to realise their full potential, we are contributing to stronger institutions, more effective leadership and a more competitive private sector.Sebsib Abafira AbajobirPresident, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 PTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers1,650Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
18 сент., 18:01

1,210Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
18 сент., 14:41
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በሴቶች አመራርነት (Women in Leadership) ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡ለአራት ተከታታይ ቀናት የተሰጠው ስልጠና ሴቶች ያላቸውን አቅም በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና በአመራርነት ውጤት ማምጣት እንዲችሉ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል ።በስልጠናው ማጠቃለያ ወቅት የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ወይዘሮ ሔለን ረታ፣ ምክር ቤቱ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች ለግሉ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። ለሴቶች አመራሮች የሚሰጠው ስልጠናም የሴቶችን ውጤታማነትና የአመራር አቅም በማሳደግ ለላቀ ውጤታማነት እንደሚያበቃ ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ በቢዝነስ አመራር አካዳሚው የግሉን ዘርፍ የስልጠና ፍላጎት ለማርካት በበርካታ የቢዝነስ ዘርፎች ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/inTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers1,330Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
18 сент., 14:41



1,250Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
16 сент., 12:41
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓይናለም አባይነህ በኢትዮጵያ የስሪላንካ ኤምባሲ ሁለተኛ ጸሐፊ ፑርኒማ አበይጉናሴካራ ጋር በሁለቱ አገራት የንግድና የኢንቨስትመንት ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።ለሁለቱም አገራት የጋራ ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክቱ የትብብር መስኮችን ማስፋት፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስሮችን ማጠናከር እንዲሁም በሁለቱ አገራት የሚገኙ ኩባንያዎች የንግድ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ስለሚያስፈልጉ ጉዳዮች ሀሳብ ተለዋውጠዋል። ሚስ ፑርኒማ አበይጉናሴካራ የስሪላንካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለይም በማዕድን፣ በመድኃኒት፣ በጨርቃጨርቅና በሌሎች ዘርፎች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፤ አንዳንድ የስሪላንካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ አሁንም እየሠሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ምክትል ፕሬዚደንቱ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለስሪላንካ ኩባንያዎች ምቹ የንግድና የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን አብራርተውላቸዋል፡፡ በሁለቱ አገራት የሚዘጋጁ ኤግዚቢሽኖች፣ የንግድ ትርዒቶችና ትልልቅ የንግድ ዝግጅቶች ኩባንያዎች የገበያ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ፣ አዳዲስ የንግድ አጋሮችን እንዲያፈሩና የንግድ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ ጠቃሚ መድረኮች መሆናቸውን ዶ/ር አይናለም ገልጸዋል። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ኩባንያዎች የፊታችን ጥር አጋማሽ በስሪላንካ በሚካሄደው International Sri Lanka Expo 2027 እንዲሳተፉ ግብዣ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር አይናለም በበኩላቸው የስሪላንካ ኩባንያዎች እኤአ ጥር መጨረሻ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 16ኛውTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers1,720Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
16 сент., 12:40



1,520Открыть в Telegram
Ethio-Chamber
12 сент., 20:50изменён
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በBRICS ቢዝነስ ፎረም ላይ ተሳትፎ እያደረገ ሲሆን፤ በፎረሙ መሳተፋችን የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ ተደራሽነት በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ በማጉላት ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስሮችን ለማስፋት እና ተጨባጭ የገበያና የትብብር እድሎችን ለመፍጠር ያስችለናል።ምክር ቤታችን ጠቅላይ ሚንስትራችን በሚገኙበት ዓለም አቀፍ የንግድ መድረኮች ላይ የሚያደርገው ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ንግዶች የገበያ፣ የቴክኖሎጂ፣ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ አጋርነት እድሎችን ወደ ተጨባጭ የንግድ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል በመሆኑ በቁርጠኝነትም የጎላ ተሳትፎ እያደረገ ነው ።ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ The Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations is participating in the BRICS Business Forum. Our participation in the Forum enables us to amplify the voice and visibility of Ethiopia’s private sector on the global business stage, expand trade and investment linkages, and create tangible market and cooperation opportunities.ECCSA is also actively and firmly engaging in international business forums attended by the Prime Minister of Ethiopia.Such participation provides an important platform for connecting Ethiopian businesses with opportunities in markets, technology, investment, and economic partnerships, and for translating these opportunities into tangible business outcomes.Sebsib Abafira AbajobirPresident, Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/inTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
12 сент., 20:39
ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል። በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ ናት። በተጨማሪም በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ይኖርብናል። የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። ❇️❇️❇️❇️❇️ Yaa'ii BRICS 18ffa yaada ijoo cichoomina, kalaqa, walta'insaafi waaromina ijaaruu jedhuun Indiyaa, Niiwu Deeliitti taa'amaa jiru irratti hirmaachuukoof gammachuutu natti dhagahama.Biyyoota miseensota BRICS biratti qabeenya, teknooloojiifi gabaa bal'aatu jira. Carraa gaariin amma jiru humnoota kanneen walitti hidhuudhaan sona olaanaa uumuufi sonni kunimmoo bakka qabeenyichi argamutti homishamuu akka danda'u taasisuudha. Itoophiyaan misooma albuudaa, humna haarawuufi bu'ura indaastiriishee guddataa jiru irratti michummaa kanneen ijaaruuf qophooftuudha.Dabalataanis, sirnoota hojimaataa keenya keessatti cichoomina ijaaruu, hubannoo nam-tolcheen ardii keenya akka tajaajilu gochuu, adeemsa aaragalfii liqii amansiisaa guddisuu, akkasumas hojiiwwan eegumsa haala qilleenaa cehumsa dinagdee waliin walqabsiisuutu nurra jira.Waltajjiin BRICS walta'insa waloo gara duudhaa waloo, cichoominaafi guddina waaraatti jijjiiruuf humna bal'aafi murannoo qaba. ❇️❇️❇️❇️❇️❇️ I am pleased to participate in the 18th BRICS Summit in India, under the theme of building for resilience, innovation, cooperation and sustainability.Across BRICS, we have capital, technology and markets. The opportunity is to bring them together, create more value, and ensure that value is generated where resources are found. Ethiopia is ready to build these partnerships across minerals, renewable energy and our growing industrial base.We must also build resilience into our systems, ensure AI serves the needs of our continent, advance predictable debt resolution, and link climate action with economic transformation.Together, BRICS can turn cooperation into shared value, resilience and sustainable growth.ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/inTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
12 сент., 02:36
እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ!መልካም በዓልሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ❇️❇️❇️❇️❇️ Baga bara haara 2019 naggaafi gamachuudhaan geesan.Ayaana gaarii Sebsib Abafira prezdantii mana mare daldalaafi wolda sektera etiyopiyaa❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in


Ethio-Chamber
11 сент., 15:19
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው በብሪክስ የንግድ ፎረም፤ በአባል አገራት መካከል የአገልግሎት ንግድን ለማሳለጥ በሚያስችሉ አዳዲስ የትብብር ማዕቀፎች ላይ ውይይት ተካሂዷል።የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸኃፊ ዶ/ር ቀነኒሳ ለሚ፣ በፎረሙ ላይ “Unlocking Intra-BRICS Trade in Services: New Pathways for Growth and Cooperation” በሚል ርዕስ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ በፓናሊስትነት ተሳትፈዋል።በመድረኩም ዶ/ር ቀነኒሳ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች (MSMEs) በብሪክስ (BRICS) አገራት መካከል በሚካሄደው የአገልግሎት ንግድ ውስጥ የበለጠ ንቁ ተሳትፎ ሊኖራቸው እንደሚገባ አስገንዝበዋል።የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የሚፈጥሩትን የሥራ ዕድል፣ የፈጠራ አቅም እና ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክቱትን ሚና በመጥቀስ፤ እነዚህ ድርጅቶች ከBRICS የንግድ ዕድሎች ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ በአገልግሎት ንግድ የእሴት ሰንሰለቶች ውስጥ ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ መደረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል ።አክለውም፤ በአገራት መካከል ያለውን ትስስር ብቻ ከማጠናከር ባለፈ በኩባንያዎች መካከል የቀጥታ የንግድ ትስስርን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በBRICS አገራት መካከል ለንግድ ድርጅቶች ተጨባጭ የንግድ ዕድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል በገለፃቸው አመልክተዋል።ዋና ጸኃፊው ካነሷቸው ቁልፍ የትኩረት መስኮች መካከልም የዲጂታልና የመሠረተ ልማት ክፍተቶችን መቀነስ፣ የBRICS MSME Digital Gateways ማቋቋም፣ ለMSMEs የንግድ ፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋፋት፣ ክህሎትና ፈጠራን ማጠናከር እንዲሁም የንግድ አቅምን ማሳደግ ይገኙበታል።በተጨማሪም የቁጥጥርና የገበያ ተደራሽነት እንቅፋቶችን ለመቀነስ የሚደረጉ ጥረቶች የእያንዳንዱን አገር ብሔራዊ ጥቅም በማክበር መከናወን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።በመንግሥታት፣ በንግድ ምክር ቤቶች፣ በንግድ ማኅበራት፣ በፋይናንስ ተቋማትና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚደረግ የተቀናጀ ትብብር እነዚህን ቅድሚያ የተሰጣቸውን ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ የንግድ ዕድሎች ለመቀየር ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ❇️❇️❇️❇️❇️❇️The second day of the BRICS Business Forum has focused on strengthening trade in services among BRICS economies, with the Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) calling for greater participation by micro, small and medium-sized enterprises (MSMEs).ECCSA Secretary General Dr. Kenenisa Lemi, who participated as a panelist in a session titled “Unlocking Intra-BRICS Trade in Services: New Pathways for Growth and Cooperation”, said MSMEs should be at the centre of efforts to expand services trade within BRICS.The Secretary General said MSMEs should not only benefit from emerging opportunities but also become active participants in intra-BRICS services trade value chains. He highlighted their contribution to employment, innovation, entrepreneurship and broader economic development.He also stressed the importance of moving beyond connectivity between countries towards stronger connectivity between companies, arguing that closer business-to-business links could create practical opportunities for enterprises across BRICS economies.Among the priorities highlighted by Dr. Kenenisa were addressing gaps in digital and physical infrastructure, establishing BRICS MSME Digital Gateways, expanding access to trade finance, strengthening skills and innovation, and improving the business capabilities of MSMEs.He also called for efforts to reduce regulatory and market-access barriers while taking account of the national priorities of individual countries. Dr Kenenisa said closer cooperation among governments, chambers of commerce, business associations, financial institutions and private-sector actors would be essential to turning these priorities into concrete business opportunities.Representing ECCSA, he said Ethiopia’s private-sector perspective was focused on promoting more inclusive, connected and mutually beneficial economic cooperation among BRICS economies.The BRICS Business Forum brings together business leaders and representatives of governments, chambers, business associations and other economic institutions to discuss opportunities for deeper commercial cooperation among participating economies. ❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.comTelegramEthio-ChamberThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
Ethio-Chamber
10 сент., 13:15
እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በደስታ አደረሳችሁ!ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
1,050Открыть в Telegram
Ссылки
