Последние посты

Ethiopian Football Federation
25 сент., 19:45
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የካፍ ሲ ዲፕሎማ የመጨረሻ ሞጁል ስልጠና በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል።ስልጠናው ላለፉት ሦስት ወራት በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ለዚህ ስልጠና መሳካት የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ አስተዎጽኦ አበርክቷል።ስልጠናው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አሰፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ አንበሴ አበበ የመዝጊያ ንግግር እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።




Ethiopian Football Federation
25 сент., 19:42
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር በአዲስ አበበ ከተማ ለ10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የካፍ ኤ ዲፕሎማ ሦስተኛ ሞጁል ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል ፡፡የስልጠናው መጨረሻ ሞጁል በጥቅምት ወር በመስጠት የሚጠናቀቅ ይሆናል።




Ethiopian Football Federation
25 сент., 18:34
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የኦሊምፒክ ማጣርያ ዝግጅታቸውን ቀጥለው በዛሬው ዕለት የ6ኛ ቀን ልምምድ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ አከናውነዋል።




Ethiopian Football Federation
25 сент., 18:16
ድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ - ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ https://youtu.be/C-WEwN0imwMYouTubeድህረ ጨዋታ ጋዜጣዊ መግለጫ - ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Ethiopian Football Federation
25 сент., 17:47
ለመገናኛ ብዙሃን !በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከ ሴኔጋል የሚያደርጉት ጨዋታ ማክሰኞ መስከረም 19 በባህር ዳር ስታዲየም ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይካሄዳል።በዚህ ጨዋታ ላይ በአካል በስታዲየም በመገኘት የዘገባ ሽፋን መስጠት ለምትፈልጉ የሚዲያ አካላት (ጋዜጠኞች እና ካሜራ ባለሙያዎች) ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በመግባት እስከ ሰኞ መስከረም 18 ምሽት 6:00 ድረስ ምዝገባ ማከናወን የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።ከዚህ በፊት በዚህ ሲስተም ላይ ያልተመዘገባችሁ በቅድሚያ Sign up በማድረግ አዲስ ምዝገባ ማከናወን የሚኖርባችሁ ሲሆን ከዚህ ቀደም ምዝገባ አከናውናችሁ የነበራችሁ ግን Log in በማድረግ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።ሊንክ - https://accreditation.ethioff.com


Ethiopian Football Federation
25 сент., 15:01
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውጤት🇸🇩 ሱዳን 1-0 ኢትዮጵያ 🇪🇹 86' መሐመድ ማሞን (ፍ)


Ethiopian Football Federation
25 сент., 14:11
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ🇸🇩 ሱዳን 0-0 ኢትዮጵያ 🇪🇹




Ethiopian Football Federation
25 сент., 13:52
የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያእረፍት🇸🇩 ሱዳን 0-0 ኢትዮጵያ 🇪🇹




Ethiopian Football Federation
22 сент., 19:48
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ቆይታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ https://youtu.be/ifGE8qF4s8IYouTubeየኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ቆይታን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫEnjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
Ethiopian Football Federation
22 сент., 19:33
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፀደቁ ውሎችየኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪምየር ሊግማክሰኞ መስከረም 12 ቀን 2019




Ethiopian Football Federation
22 сент., 18:54
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የካፍ ሲ ዲፕሎማ የመጨረሻ ሞጁል ስልጠና በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል። ስልጠናው ላለፉት ሦስት ወራት በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ለስልጠና መሳካት የኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በስልጠናው መዝጊያ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ፍሮምሳ ለገሰ የመዝጊያ ንግግር እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።




Ethiopian Football Federation
22 сент., 17:10
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሱዳን ጋር የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ የሚያደርግበት ደቡብ ሱዳን ጁባ በሰላም ደርሷል።




Ethiopian Football Federation
22 сент., 13:00
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው የመጀመርያ የምድብ ጨዋታ ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ የሚያደርገውን ጉዞ ጀምሯል። የኢ/እ/ፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በቦሌ ዓለምአቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት የቡድኑ አባላትን አበረታተው ሽኝት አድርገዋል።




Ethiopian Football Federation
22 сент., 05:55
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ የተዘጋጀው የካፍ ሲ ዲፕሎማ የመጨረሻ ሞጁል ስልጠና ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ ስልጠናው ላለፉት ሦስት ወራት በተግባር እና በንድፈ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየ ሲሆን ለስልጠናው መሳካት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትልቅ አስተዎጽኦ አበርክቷል። በስልጠናው መዝጊያ ሥነስርዓት ላይ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አሰፈጻሚ እና የውድድር እና ሥነስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤርሚያስ ኃይሉ የመዝጊያ ንግግር እና የሥራ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል።




Ethiopian Football Federation
21 сент., 19:41
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፊፋ ጋር በመተባበር ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀው የተሰጥኦ ልየታ (Talent ID) ባለሙያዎች ስልጠና ተጠናቀቀ።በስልጠናው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ 31 ሰልጣኞች የተሳተፉ ሲሆን የፊፋ ከፍተኛ ብቃት ስፔሻሊስት ላይሰን ዙሉ፣ የፊፋ የታለንት ልየታ ባለሙያ ሚካኤል ሬንስችለር እንዲሁም የኢ/እ/ፌ ታለንት አሰልጣኝ ሲፕሪያን አሹ አማካኝነት ለአምስት ተከታታይ ቀናት የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ስልጠና ተሰጥቷል።በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ለአሰልጣኞች ምስጋና አቅርበው ሰልጣኞች የቀሰሙትን እውቀት በየአካባቢያቸው በተግባር እንዲያውሉ አሳስበዋል። አክለውም የሀገሪቱ ብሔራዊ ቡድኖች የወደፊት ጥንካሬ ዛሬ በሚለዩት ወጣት ተጫዋቾች ጥራት ላይ የተመሰረተ መሆኑን በመግለጽ ከስሜት በፀዳ መልኩ ያለ አድልኦ ምልመላ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል። በሚሰማሩበት አካባቢ ሁሉ የፌዴሬሽኑ ዓይን እና ጆሮ መሆናቸውን አውቀው መስራት እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።የኢ/እ/ፌ TDS ክፍል ኃላፊ አቶ ሸዋንግዛው አበበ በተሰጥኦ ልየታ አሰራር እና ሒደት ዙርያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ወጥ የሆነ የምልመላ እና ተሰጥኦ መለያ መስፈርቶች በፌዴሬሽኑ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። እያንዳንዱ የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያም ተጠሪነቱ ለፌዴሬሽኑ ሆኖ የመረጃ አሰባበሰብ እና ልውውጥ ስርዓቱ በተዘጋጀው ማንዋል መሠረት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።"ለእያንዳንዱ ታላንት እድል መስጠት" በሚል መሪ ቃል በፊፋ TDS ስር ከሚሰጡት ሶስት
Ethiopian Football Federation
21 сент., 19:41
የመጀመሪያው የተሰጥኦ ልየታ ባለሙያዎች ስልጠና ተጠናቀቀ



