gram news
Аватар канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute

Ethiopian Artificial Intelligence Institute

@ethiopianaii

This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute.

ПроектыENНейросетиПодтверждён Telegram

21,200подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    23 сент., 10:14

    https://youtube.com/shorts/9VgPMs4c8KY
    YouTubeስለ ኤአይ እይታቸውን የቀየረው የክረምት ስልጠናስለ ኤአይ እይታቸውን የቀየረው የክረምት ስልጠናበዚህ የክረምት ስልጠና ተማሪዎች አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ...
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    23 сент., 04:28

    በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተባባሪነት የተዘጋጀው "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ።በቴክኖሎጂ አማካሪ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ የተጻፈውና "አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ" በሚል ርዕስ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀው መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። በሳይንስ ሙዚየም የተመረቀው መጽሐፉ ስለኤ.አይ ቴክኖሎጂ ምንነት ብሎም በተለያዩ ዘርፎች የሚኖረውን አበርክቶ እና ስጋቶች ዳሷል።በምርቃ መርኃግብሩ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) የኤ.አይ ቴክኖሎጂ የዘመኑ እውነታ መሆኑን ተረድቶ በተጠና መንገድ ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ይህ መጽሐፍ ሊነበብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።ስለ መጽሐፉ ገለጻ ያደረጉት ዶ/ር ምህረት ደበበ በኩላቸው መጽሐፉ ቴክኖሎጂውን በተለያዩ መነጽሮች ለማየት እንደሚያግዝ ገልጸው፤ ከሰው ልጆች አዕምሮና ማህበራዊ ህይወት ጋር ያለውን ቁርኝት አስረድተዋል።የመጽሐፉ ደራሲ ሰለሞን ሙሉጌታ ካሳ ለስኬቱ ድጋፍ ላደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና ለተባባሩት አካላት ምስጋናውን አቅርቧል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
    1,110611Открыть в Telegram
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    22 сент., 14:29

    https://youtube.com/shorts/yXpQ-wStOTo
    YouTubeኤአይን በተግባር ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትኤአይን በተግባር ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትልጆችዎ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የ...
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    22 сент., 08:51

    አሊባባ የኤአይ ውድድሩን አፋፍሟል፤ እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር የሚደርስ ሞዴል እያበለጸገ ነው።የቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አሊባባ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዕድገቱን ለማፋጠን አዲስ ቺፕ፣ ከፍተኛ አቅም ያለው የኤአይ ሞዴል እና ሰፊ የዳታ ማዕከል መሠረተ ልማት ለማስፋፋት የሚረዳ እቅድ ይፋ አድርጓል።ኩባንያው ከአሁኑ ዋና የኤአይ ሞዴሉ እስከ አራት እጥፍ የሚበልጥ አዲስ ሞዴል እያሰለጠነ ነው። የሞዴሉ መጠን ከ5 እስከ 10 ትሪሊዮን ፓራሜትር ሊደርስ እንደሚችል አስታውቋል። ይህም የኤአይ ሞዴሎች የማሰብ፣ የመተንበይ እና ውስብስብ ሥራዎችን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እየተደረገ ካለው ዓለም አቀፍ ውድድር ጋር የሚገናኝ እርምጃ ነው።አሊባባ የኤአይ መሠረተ ልማቱንም በስፋት ለማሳደግ እየሰራ ነው። የአሊባባ ክላውድ ዓለም አቀፍ የዳታ ማዕከላት አቅም ከ20 ጊጋዋት እንዲሻገር አቅዷል። ይህ ኤአይ ከሞዴል ልማት ባሻገር ቺፕ፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ዳታ ማዕከላትን ያካተተ ሙሉ የቴክኖሎጂ ሰንሰለት ለመገንባት የሚደረግ ኢንቨስትመንት መሆኑን ያሳያል።የኤአይ ቴክኖሎጂ መስፋፋት ለአሊባባ እንደ ኩባንያ የንግድ ዕድልን ከማስፋት ባሻገር፤ ለክላውድ ኮምፒውቲንግ፣ ለዳታ ማዕከላት፣ ለሴሚኮንዳክተር እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ የገበያ ፍላጎት እየፈጠረ ነው።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    22 сент., 04:33

    https://youtube.com/shorts/5MarXW9iAsI
    YouTubeትርጉም ባለው መልኩ ያለፈው የክረምት ጊዜትርጉም ባለው መልኩ ያለፈው የክረምት ጊዜየክረምቱ የኢንስቲትዩታችን ስልጠና (AI Summer Camp) በ...
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    21 сент., 14:51

    ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ የ11 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለንዋይ ሊያፈስ ነዉ።የጃፓኑ ሶፍትባንክ ኩባንያ በኦፕን ኤ.አይ ያለውን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ቦንድ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ኩባንያው 10 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዶላር እንዲሁም 1 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዩሮ ለመሸጥ እየተዘጋጀ ነው። ከቦንድ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ ፈሰስ ለሚያደርገዉ መዋዕለንዋይ የሚዉል መሆኑ ተነግሯል።የቦንድ ሽያጩ በታቀደው መጠን ከተጠናቀቀ 7 ኢለቨን (7-Eleven) የተሰኘዉ ኩባንያ በአዉሮፓዊያኑ 2021 ይዞት የቆየውን የ10.93 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል።የተዘጋጀዉ ቦንድ በተያዘዉ መስከረም የመጨረሻ ቀናት ለሽያጭ ለማቅረብ መታቀዱም ተገልጿል።ሶፍትባንክ እና ኦፕን ኤ.አይ ከዚህ በፊት በጃፓን በኤ.አይ የታገዙ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ብሎም በአሜሪካዉ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት (ስታርጌት ) ላይ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    21 сент., 10:57

    የሰው ሰራሽ አስተውሎት እያስመዘገበ ባለው አስደናቂ እምርታ የጤናው ዘርፍ ከምንጊዜውም በላይ በታካሚ ላይ ያተኮረ እና ይበልጥ ቀልጣፋ ለውጥ እያስተናገደ ይገኛል።6 የጤና ፈጠራዎች፤ በሽታዎችን በቅድመ ማስጠንቀቂያ ለመለየት፣ ሕክምናዎችን ለግል የተስማሙ ለማድረግ እና የሕብረ ሕዋሳትን ጥገና በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን የሚያስችሉ የለውጥ ምዕራፎች ናቸው።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    21 сент., 06:52

    https://youtu.be/74Vc7mDysHw
    YouTubeየፈጠራው ንጉሥ ሹንፔ ያማዛኪበታሪክ ከፍታ ላይ ያለውን የሳይንስ እና የፈጠራ ሰውን የሚያውቁት ይመስልዎታል? ዛሬ በዝግጅታችን ከ20,000 በላይ ፓተንቶችን በማስመዝገብ የዓለማችን አቻ የማይገኝለት የጃፓናዊውን ሳይንቲስት የሹንፔ ያማዛኪን አስደናቂ የሕይወት እና የፈጠራ ጉዞ እንቃኛለን በቪዲዮው የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ ሹንፔ ያማዛኪ ማን ናቸው? ከ20 ሺህ በላይ ፓተንቶች ባለቤት የመሆን ሚስጥር በቴክኖሎጂው ዓለም ላይ ያበረከቱት…
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    21 сент., 04:22

    https://youtube.com/shorts/wS3D2eYpOxs
    YouTubeበኤአይ ሰመር ካምፕ የሰለጠኑ ተማሪዎች ምን አገኙ?ከንድፈ ሀሳብ እስከ ፕሮጀክት የ5ኛው ዙር የኤአይ ሰመር ካምፕ ጉዞበኤአይ ሰመር ካምፕ የሰለጠኑ ተማሪዎች...
    2,090611Открыть в Telegram
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    19 сент., 06:03

    https://youtube.com/shorts/beNDapEb1DI
    YouTubeለታዳጊዎች ምቹ እና አጓጊ የሆነው የ Summer Camp 2026ለታዳጊዎች ምቹ እና አጓጊ የሆነው የ Summer Camp 2026የተማሪዎችን ፍላጎት፣ ምርጫ እና የትምህር...
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    18 сент., 14:41

    https://youtu.be/scwcZNQVE34
    YouTubeመረጃዎቻችን የት አሉ?መረጃዎቻችን የት አሉ? ዓለም የቁሳቁስን ወሰን ተሻግራ ወደ መረጃው ህዋ በተቀላቀለችበት በዚህ ዘመን ፎቶዎቻችን፣ የንግድ ምስጢሮቻችን እና ግዙፍ ዳታዎች የት ይከማቻሉ? በዚህ ቪዲዮ ስለ ክላውድ ኮምፒውቲንግ (Cloud Computing) ቴክኖሎጂ ምንነት፣ ጥቅሞች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስለሚጠቀሱ ግዙፍ ኩባንያዎች እንቃኛለን። እንዲሁም የኢትዮጵያ እርምጃ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት…
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    18 сент., 11:05

    ጣሊያን ለአፍሪካ የኤአይ መሠረተ ልማት መጠናከር የገንዘብ ድጋፍ አቀረበች፤ ኢትዮጵያም የዚህ ማዕቀፍ አካል ናትጣሊያን በ14 የአፍሪካ ሀገራት የሰው ሠራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለማጠናከር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቷ ተገለጸ። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ፣ አልጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ጋና የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ ከሆኑ 14 ሀገሮች መካከል ይጠቀሳሉ። በጣሊያን መንግሥት እና በዓለም አቀፍ ተቋማት ትብብር የሚከናወነው ይህ የ“ማቴኢ ፕላን” አካል የሆነው ተግባር በአፍሪካ የኤአይ አቅምን በማሳደግ ሀገራቱ በፈጣን ለውጥ ላይ ካለው የቴክኖሎጂ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።ይህ የጣሊያን ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14ቱ የአፍሪካ ሀገራት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አቅምን ለማጎልበት፣ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማትን ለማስፋፋት እና ሀገራቱ በኤአይ ዘርፍ የራሳቸውን ሉዓላዊ አቅም እንዲገነቡ የሚያግዝ መሆኑ ታውቋል። በተለይም አፍሪካ በኤአይ ቴክኖሎጂ ከውጭ አቅራቢዎች ብቻ ጥገኛ እንዳትሆን የአህጉሩን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ የድጋፉ ዋነኛ ዓላማ ነው። ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር አጋርነት ካላቸው 14 አፍሪካ አገራት መካከል አንዷ ስትሆን፤ በሰፊው እየተተገበረ ባለው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂዋ መሠረት የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ማዕከል ለመሆን ወሳኝ ርምጃዎችን እየወሰደች ነው።ድጋፉ አፍሪካ በጤና፣ በግብርና፣ በትምህርት እና በፋይናንስ ዘርፎች የራሷን የኤአይ መፍትሔዎች እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ከኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት ግቦች ጋር በቀጥታ የሚጣጣም ነው። ይህ ድጋፍ ሀገራችን
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    18 сент., 04:58

    የኤአይ ተደራሽነት ክፍተትን ለማጥበብ 3 ቢሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ፈንድ ጥሪ ቀረበየተባበሩት መንግሥታት ታዳጊ ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በፍትሃዊነት እንዲጠቀሙና የራሳቸውን የቴክኖሎጂ አቅም እንዲገነቡ የሚያግዝ 3 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ ፈንድ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርቧል።የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እንደገለጹት፤ የኤአይ ቴክኖሎጂ እጅግ ፈጣን እድገት በጥቂት አገራት ብቻ ተወስኖ መቅረት የለበትም።በመሆኑም በታዳጊ አገራት የሚስተዋሉ የቴክኖሎጂና የአቅም ክፍተቶችን ለመሙላት የተቀናጀ ዓለም አቀፍ ድጋፍ ማድረግ አስገዳጅ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።ለዚህ ዓላማም ሥራ ይጀምራል ተብሎ በሚጠበቀው የመጀመሪያዎቹ ከ2 እስከ 4 ዓመታት ውስጥ 3 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ለመሰብሰብ ታቅዷል።የተሰበሰበው ገንዘብ በታዳጊ አገራት የኤአይ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር፣ የሰው ኃይልን ለማሰልጠን እንዲሁም የዲጂታልና ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያገለግል ይሆናል።የፈንዱ የመጨረሻ ግብ የቴክኖሎጂ ልማት በጥቂት የበለጸጉ ሀገራት ብቻ እንዳይወሰን ማድረግ ሲሆን፤ ይህም ታዳጊ ሀገራት የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የወደፊት የኤአይ ዕድገት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያስችል ወሳኝ ዕድል ይፈጥራል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
    2,660721Открыть в Telegram
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    17 сент., 10:44

    ማይክሮሶፍት ለሰው ልጅ ደህንነትና ክብር ቅድሚያ የሚሰጥ አዲስ የኤ.አይ የሥነ-ምግባር መመሪያ ሊያወጣ ነው።ማይክሮሶፍት በቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ምርምር እና ልማት በትክክለኛው አቅጣጫ ለመምራት የሚያስችል አዲስ የሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።በረቂቅ መመሪያው መሠረት የማይክሮሶፍት የኤ.አይ ሥርዓቶች ከሰዎች የሚሰጣቸውን ማስተካከያዎች መቀበል፣ ለሰዎች ሊገባ በሚችል መንገድ መግባባት እንዲሁም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ተግባራቸው በሰዎች ቁጥጥር ሥር መሆን የሚችሉበትን አቅጣጫ ማካተት ዋና ትኩረቱ ነው።ኩባንያው ይህንን መመሪያ ለማዘጋጀት የዘርፉ ባለሙያዎችን ያሳተፈ የብዙ ወራት የጥናት እና የውይይት ጊዜያት እንደወሰደ ገልጿል። የሕዝብ አስተያየትንም የሚያካትተው መመሪያ ኩባንያው በቀጣይ የሚያበለጽጋቸውን የኤ.አይ ሞዴሎች ለማሠልጠን እንደ መሠረታዊ አቅጣጫ ይውላል።የማይክሮሶፍት ኤ.አይ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሙስጠፋ ሱሌይማን መመሪያው ኩባንያው ለሚያለማቸው የኤ.አይ ሥርዓቶች ሁሉ መሰረት እንደሚሆን ተናግረዋል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    17 сент., 04:36

    ቻይና ብሪክስን በክፍት ምንጭ(open source) ኤአይ ለማገናኘት ሀሳብ አቀረበችየቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በኒው ዴልሂ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ላይ ሀገራቸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከአባል ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል አዲስ እቅድ አቅርበዋል።በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በጋራ ለማልማት እና ለመጠቀም የክፍት ምንጭ ኤአይ ማህበረሰብ እንዲቋቋም ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ቻይና በዚህ የጋራ የኤአይ ትብብር መድረክ የአንበሳውን ድርሻ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።የታቀደው ማህበረሰብ ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎችን በጋራ ለማልማትና ለመተግበር፣ የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ እና የቴክኖሎጂ ልውውጥን ለማሳደግ ያለመ ነው። ከዚህ የኤአይ ትብብር ባሻገር ቻይና የብሪክስ ዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለማጠናከር የክላውድ መድረክ እንዲቋቋም፣ የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲሰጥ፣ በስማርት ፋብሪካዎች ልማት ላይ ትብብር እንዲጎለብት እና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን አጋርነት እንዲመሰረት ፍላጎት አላት፡፡በጉባኤው ላይ የብሪክስ ሙሉ አባላት ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን የክፍት ምንጭ ኤአይ ትብብሩ በተለይ የአባል ሀገራቱን የኤአይ ምርምር፣ የሰው ኃይል አቅም እና የቴክኖሎጂ ትብብር ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተገልጿል። በተጨማሪም ቻይና የብሪክስ ሀገራት የኢንዱስትሪና የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማጠናከር እንዲሁም የተቀናጀ ገበያ ለመገንባት ጥሪ አቅርባለች።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
    3,290821Открыть в Telegram
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    16 сент., 08:42

    ኤአይ ለሁሉም፤ ጌትስ ፋውንዴሽን ለ ኤአይ ልማት አንድ ቢሊዮን ዶላር ሊያውል ነው።የጌትስ ፋውንዴሽን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂና መፍትሄዎች በዓለም ዙሪያ ተደራሽ እንዲሆኑ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት አንድ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሊያውል መሆኑን አስታውቋል። ፋውንዴሽኑ የ2026 ዓመታዊ Goalkeepers Reportን በማስተዋወቅ ላይ ሲሆን የኤአይ ቴክኖሎጂ ለሁሉም በፍትሃዊነት ተደራሽ እንዲሆን የዛሬ ውሳኔዎችና ኢንቨስትመንቶች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጿል።ፋውንዴሽኑ ሦስት ዋና ነጥቦችን አስቀምጧል። ኤአይ በተለያዩ የዓለም ቋንቋዎች እንዲሰራ፣ የሚጠቀመው ማህበረሰብ ፍላጎትና መረጃ ታሳቢ እንዲደረግ እና ሰዎች ቴክኖሎጂውን በብቃት መጠቀምና መገምገም እንዲችሉ በእውቀትና ተደራሽነት ላይ መስራት ናቸው።ከሚመደበው አንድ ቢሊዮን ዶላር 40 በመቶ ለትምህርት፣ 40 በመቶ ለጤና፣ 10 በመቶ ለግብርና እና 10 በመቶ ለዲጂታል መሠረተ ልማት እንደሚውል ተገልጿል። በትምህርት ዘርፍ የኤአይ የትምህርት መሳሪያዎችን ለማስፋፋት፣ በጤና ዘርፍ የበሽታ ምርመራና የሕክምና ውሳኔ ድጋፍን ለማጠናከር፣ በግብርና ዘርፍ ደግሞ አርሶ አደሮች ከአፈር፣ ከአየር ሁኔታና ከሰብል ይዞታ ጋር የተጣጣመ የኤአይ ምክር እንዲያገኙ ለማስቻል ይውላል።የጌትስ ፋውንዴሽን ሊቀመንበር ቢል ጌትስ ኤአይ ለሰው ልጆች ጥቅም እንዲውል ኩባንያዎች፣ መንግስታት እና የበጎ አድራጎት ተቋማት በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
    3,000821Открыть в Telegram
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    16 сент., 06:08

    የወደፊቱን ዓለም የሚቀይሩ 5ቱ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ቴክኖሎጂ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።የነገን ዓለም ቅርጽ ከሚያስይዙ እና የምንኖርበትን ምድር ከሚጠብቁ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂዎች አምስቱን እነሆ!ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    15 сент., 13:57

    ለ90 ዓመታት ሳይፈታ የቆየዉ የሂሳብ እንቆቅልሽ በ88 ሰዓታት ዉስጥ ተፈታ።ኦፕን ኤአይ አዲስ ሞዴል እና 10 ሺህ የሚጠጉ የኤ.አይ ኤጀንቶችን በመጠቀም ለ90 ዓመታት ያህል መፍትሔ ያልተገኘለትን የሂሳብ ስሌት በ88 ሰዓታት ውስጥ እንደፈታ ገልጿል። ኩባንያዉ ናቪዬ-ስቶክስ የተሰኘዉ ሂሳባዊ ስሌት ዉስጥ የሚገኘዉን የዘመናት ጥያቄ ነዉ መፍታት የቻለዉ።ናቪዬ-ስቶክስ ሂሳባዊ ስሌት(equation) እንደ ውኃ፣ አየር እና መሰል ነገሮች እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ለመረዳት የሚያስችል የሂሳብ ክፍል ነዉ። ኦፕን ኤአይ እንደገለጸው የኤ.አይ ኤጀንቶቹ ሂሳባዊ ስሌቱን ለመፍታት ሶስት ሚሊዮን የሚጠጉ መልዕክቶችን ተለዋውጠዋል።በተጨማሪም 130 ቢሊዮን የኤ.አይ ቶከኖችን ተጠቅመዋል። ኩባንያው እንዳስታወቀዉ ይህ ሥራ የ10 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ነው። ይህ ሂሳባዊ ግኝት በገለልተኛ የሂሳብ ባለሙያዎች ተጣርቶ ከተረጋገጠ ኦፕን ኤ.አይ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አሸናፊ ይሆናል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    15 сент., 08:34изменён

    የአፍሪካ የኤአይ መሠረተ ልማት በፍጥነት እየተስፋፋ ነውየአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረተ ልማት በአስደናቂ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተገለጸ። አፍሪካ በዓለም አቀፍ የኮምፒውቲንግ አቅም ውስጥ አነስተኛ ድርሻ ቢኖራትም በአህጉሪቱ የዳታ ማዕከላት ኢንቨስትመንት በፍጥነት እየጨመረ ነው። እንደ FurtherAfrica ገለጻ፤ በአሁኑ ወቅት የሚሠሩ የዳታ ማዕከላት አቅም ወደ 360 ሜጋዋት የሚጠጋ ሲሆን፤ በቅርቡ ወደ 656 ሜጋዋት የሚያህል ተጨማሪ አቅም እንደሚያድግ ይጠበቃል።በአህጉሪቱ የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንትም እየጨመረ ነው፡፡ አማኮ ኢነርጂ ግሩፕ በኬንያ ሞምባሳ 1.5 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት የኤአይ ዳታ ማዕከል ለመገንባት አቅዷል። ኤምቲኤን ግሩፕ ደግሞ የዳታ ማዕከል ላይ በስፋት እየሠራ ነው። በተጨማሪም ወደ 15 የሚጠጉ የአፍሪካ ሀገራት የኤአይ ማዕቀፍ ማዘጋጀታቸውና ከ20 በላይ ሀገራት ደግሞ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።የኤአይ መሠረተ ልማት ዕድገቱ ዘላቂ እንዲሆን ከዳታ ማዕከላት ግንባታ ባሻገር የኤሌክትሪክ፣ የፋይበር ኦፕቲክ መሠረተ ልማት፣ የሰው ኃይል ሥልጠናና ውጤታማ የኤአይ አስተዳደር ሥርዓት በተቀናጀ መልኩ ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
    Иллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence InstituteИллюстрация к посту канала Ethiopian Artificial Intelligence Institute
  • Ethiopian Artificial Intelligence Institute

    15 сент., 04:32

    https://youtube.com/shorts/pY1JaWizHyU
    YouTubeየሰመር ካምፕ ሰልጣኞቻችን የራሳቸውን ትናንሽ ቴክኖሎጂዎችና የሞዴል ሐሳቦች በተግባር እንዲያበለጽጉ መደረጉ የፈጠራ አቅማቸውን እንዲፈትሹ አስችሏቸዋል።የሰመር ካምፕ ሰልጣኞቻችን የራሳቸውን ትናንሽ ቴክኖሎጂዎችና የሞዴል ሐሳቦች በተግባር እንዲያበለጽጉ መደረጉ...

Ссылки