Последние посты

EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
18 сент., 14:25
#የህክምና #ሙከራ #ፈቃድና #ቁጥጥር #በኢትዮጵያ
EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
17 сент., 11:37



EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
17 сент., 07:07изменён
የአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል የባለሥልጣኑን የክትባት ደህንነት ቁጥጥር ለማጠናከር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡መስከረም 5/2019 ዓ.ም አዲስ አበባ፡- የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ የአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል የአለም አቀፍ የክትባት ክፍል ልዑካን ቡድን አባላትን ዛሬ ተቀብለው አነጋግርዋል፡፡ከክትባት በኋላ የሚከሰቱ የጎንዮሽ ጉዳቶች የቁጥጥር ስርዓትን ማጠናከር እና የመረጃ አስተዳደርን ለማሻሻል እንዲሁም በህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ወቅት ስራ ላይ የሚውሉ የክትባት ደህንነት ክስተቶች ምላሽ ማዘጋጀት እና ወደ ስራ ማስገባት ዙሪያ ማዕከሉ ባለፉት አመታት ለአከናወናቸው ተግባራት ምስጋና አቅርበው በክልሎች የመድኃኒትና የክትባት ደህንነት ክትትል መረጃን ቅብብሎሽን ለማጠናከር ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡የአሜሪካው የበሽታዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል የአለም አቀፍ የክትባት ክፍል ቡድን መሪ ዶ/ር ጄን ጊዱዱ በበኩላቸው የሀገሪቱን የክትባት ደህንነት መከታተያ ስርዓቶችን እና አሰራሮችን ለማጠናከር እንዲሁም ህብረተሰቡ በክትባቶች ደህንነት እና ውጤታማነት ላይ ያለው እምነት እንዲጎለብት ማዕከላቸው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡




EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
15 сент., 07:34



EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
11 сент., 04:19изменён
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ይላል!አዲሱ ዓመት የጤና፣ የሰላም፣ የፍቅርና የስኬት እንዲሆንልዎ በላቀ አክብሮት እንመኛለን። ባለሥልጣን መሥሪያ ቤታችን በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን ጤናና ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል።🌼 መልካም አዲስ ዓመት! 🌼


EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
10 сент., 07:42
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ተቋሙ ለሚያሳድጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የበዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።አዲስ አበባ (ጳጉሜን 5 ቀን)፦ የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ተቋሙ ኃላፊነት ወስዶ ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቁሳቁስ እና የእንቁጣጣሽ በዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።በድጋፍ ማስረከቢያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እና የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ በመገኘት ለተማሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት አስተላልፈዋል።የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልእክት፤ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት በትምህርታቸው ጎበዝ ሆነውና የተሻለ ደረጃ ደርሰው ማየት ትልቅ ደስታ እንደሆነ ገልጸዋል። ተማሪዎች የቤተሰቦቻቸውንና የሀገራቸውን ብልጽግና ለማረጋገጥ ጠንክረው መማር እንዳለባቸው በማሳሰብ፣ ተቋሙ ህልማቸውን ለማሳካት እንደሁልጊዜው ሁሉ ከጎናቸው እንደሚቆም አረጋግጠዋል።የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ በበኩላቸው፤ ባለሥልጣኑ አምስት ህፃናትን ኃላፊነት ወስዶ ማስተማሩ የሚወደስ ተግባር መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራ ገልጸዋል። አክለውም ለተማሪዎቹ የደብተር፣ የስክሪፕቶ፣ የእርሳስ እና የበዓል መዋያ ድጋፍ ያስረከቡ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ አዲሱን ዓመት በደስታ አከብረው ስኬታማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ "የምግብና መድኃኒት ደህንነት የጋራ ኃላፊነት ነው—የዛሬ


3,410Открыть в Telegram
EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
10 сент., 03:56



EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
10 сент., 03:54
ጳጉሜን-5 (የነገ ቀን) • የዛሬ የጋራ ጥረት ለነገ የተሻለ የደህንነትና ጥራት ቁጥጥር! • የምግብና መድኃኒት ደህንነት የጋራ ኃላፊነት ነው—የዛሬ ትብብራችን የነገ ጤናችን ነው!
EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
9 сент., 18:52изменён
የባለስልጣኑ የኮምቦልቻ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ከምስራቅ አማራ ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር በ527 ተቋማት ላይ ባከናወነው የገበያ ቅኝት ስራ ሕግና ሥርዓት ጠብቀው በማይሰሩ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡ ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም—የባለሥልጣኑ የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከምሥራቅ አማራ ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር ባካሄደው የገበያ ቅኝት፣ ሕግና ሥርዓት ሳይጠብቁ በተገኙ ተቋማት ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃዎችን መውሰዱን አስታወቋል። ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከደሴ፣ ወልዲያ፣ ከሚሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች የጤና መምሪያ ተቆጣጣሪዎች፣ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች እንዲሁም ከፖሊስ መምሪያ ጋር በመቀናጀት የበዓል የምግብ ገበያ ቅኝትና ቁጥጥር ማካሄዱን ገልጻል። በዚህም መሠረት በ527 የምግብ ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ መደብሮች፣ ሱፐርማርኬቶች እና ማከፋፈያዎች ላይ በተደረገው የቁጥጥርና ክትትል ሥራ ሕግና ሥርዓት ሳይከተሉ በተገኙ ተቋማት ላይ የተለያየ ደረጃ ያላቸው እርምጃዎች ተወስደዋል። ከተወሰዱት እርምጃዎች መካከል ለ127 ተቋማት የቃል ማስጠንቀቂያ፣ ለ16 ተቋማት የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን፣ 7 ተቋማት እንዲታሸጉ፣ በ33 ምርቶች ላይ የመወረስ እርምጃ እንዲወሰድ እና በአንድ ተቋም ኃላፊ ላይ ደግሞ የእስራት እርምጃ እንዲፈጸም ተደርጓል። ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ህብረተሰቡን ከጎጂና ጥራታቸውን ካጡ የምግብ ምርቶች ለመጠበቅ የሚያደርገውን የቁጥጥር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አሳውቋል።




EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
9 сент., 12:22
በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በርካታ ሕገወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።ጷጉሜ 4/2018 - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ነክ ጉዳዮች ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጤና መምሪያ እና ከአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ጋር በመተባበር ባካሄደው ሰርቬላንስን መሰረት ያደረገ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በርካታ ሕገወጥ መድኃኒቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቀ። በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኝ ሕገወጥ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው የተገኙት እነዚህ መድኃኒቶች ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እንዲሁም በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የገበያ ፈቃድ ያልተሰጣቸው ናቸው።በኦፕሬሽኑ ከተያዙት መድኃኒቶች መካከል እንደ Artesunate injection፣ Artemether/Lumefantrine tablet፣ Tramadol injection፣ Adrenaline injection እና Pethidine injection ያሉ ለሕክምና አገልግሎት ከፍተኛ አስፈላጊነት ያላቸውና ሌሎች መሠረታዊ መድኃኒቶች ይገኙበታል። እነዚህ ሕገወጥ መድኃኒቶች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው በህብረተሰቡ ጤና ላይ ሊደርስ የነበረውን ከፍተኛ አደጋ ለማስቀረት ያስቻለ ሲሆን፣ በቀጣይም በጥፋተኞቹ ላይ አስፈላጊው ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለዚህ ስኬታማ ኦፕሬሽን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የክልሉ ጤና ተቆጣጣሪዎች፣ የፖሊስ አባላትና የቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ ባለሙያዎች ምስጋናውን አቅርቧል። አያይዞም




EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
9 сент., 03:05изменён
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የአቅም ውስንነት ያላቸው ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡ተቋሙ በ2019 ዓ.ም ለተማሪዎች መማሪያ የሚሆኑ አጠቃላይ ግምቱ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን 500 ደርዘን ደብተር ፣ 500 እስክሪፕቶ እና 500 እርሳስ፣ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የበጎ አድራጎት አስተባባሪ ኮሚቴ በኩል ከሰራተኞችና ስራ አስፈጻሚዎች በተሰበሰበ ገንዘብ የመማሪያ ቁሳቁሶችን በመግዛት ለጤና ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡በጤና ሚኒስቴር የሴቶችና አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ፋጡማ ሰይድ እርዳታውን የተረከቡ ሲሆን ለተደረገው እርዳታ በሚኒስቴሩ ስም ተቋሙን አመስግነው የመማሪያ ቁሳቁሱ በወቅቱ ለችግር ተጋላጭ ተማሪዎች ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል፡፡




EFDA የኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ባለስልጣን
8 сент., 02:54изменён
የመድኃኒት፣ የምግብና ሕክምና መሣሪያዎች ተቆጣጣሪዎች—የህዝብ ጤና ደህንነት ጋሻ ናቸው !

