Последние посты

Ewunet Media
22 сент., 12:57
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራል‼️በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል።የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ በሚገነባ መልኩ እንደሚከበር ተገልጿል፡፡
Ewunet Media
22 сент., 04:54
በወለጋ ታግተው የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ በሰላም መለቀቃቸው ተገለጸበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ "ቢላ" በተባለ አካባቢ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም በታጣቂዎች ተታግተው የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ ከእገታ መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አስታወቀ።በወቅቱ የነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ከተቃጠሉበት ጥቃት በኋላ ዘጠኝ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ጨምሮ እስከ 14 የሚደርሱ የኮንስትራክሽንና የሌሎች ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ተወስደው እንደነበር ይታወሳል።የማህበሩ አመራር እንደገለጹት፣ ታጋቾቹ ከቀናት በፊት በሰላም ተለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል።አሽከርካሪዎቹ የተለቀቁት ገንዘብ ተከፍሎ ስለመሆኑ ለተነሳው ጥያቄ የማህበሩ አመራር ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም፣ "ዋናው ነገር አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳይጎዳ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም መለቀቃቸው ነው" ሲሉ ተናግረዋል።ቲክቫህ
Ewunet Media
21 сент., 16:30
ሐሰተኛ ፖሊሶች ደሙ የፈሰሰን ሰው አፍነው ወሰዱበስፔን ባርሴሎና አቅራቢያ በሚገኝ አውራ ጎዳና ላይ ራሳቸውን እንደ ፖሊስ ያስመሰሉ አምስት ታጣቂዎች በአንድ መኪና ላይ ጥቃት በመሰንዘር አንድ መንገደኛን በኃይል አፍነው ወስደዋል።በቪዲዮ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተሰራጨው ይህ ድርጊት በአካባቢው አሽከርካሪዎች ላይ ትልቅ ድንጋጤን ፈጥሯል።አጋቾቹ የፖሊስ ምልከት ያለው ቬስት የለበሱና ፊታቸውን የሸፈኑ ሲሆን፣ ተጎጂውን ደሙ እየፈሰሰና ልብሱ የተገፈፈ ሆኖ ሳለ በግፍ እየጎተቱ ወደ ሌላ መኪና ሲከቱት ታይቷል።ድርጊቱ የተፈጸመው በነጭ ቀን በብዙ አሽከርካሪዎች ፊት በመሆኑ፣ አያሌ የዓይን እይታ ምስክሮች ወዲያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተዋል።
Ewunet Media
21 сент., 16:30
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እገዳ መጣሉን ገለፀባለሥልጣኑ ቀደም ሲል ከፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ተጥሎበት የነበረው እገዳ ተንስቶ ወደ ሥራ መመለሱን አውስታው፣ ለባለሙያዎቹም የሰላም ግንባታ ሥልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጿል።ሆኖም የይዘት ክትትል ግምገማው እንደሚያሳየው ጣቢያው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገርና ህዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ መልእክቶችን በተከታታይ ሲያስተላልፍ መቆየቱን አስታውቋል።በዚህም ምክንያት ከዛሬ ጀምሮ ጣቢያው መታገዱን የገለፀው ባለሥልጣኑ፣ ማንኛውም ዲጂታል፣ ብሮድካስት ወይም የሕትመት ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም ይዘቶቹን ማሰራጨት በጥብቅ መከልከሉን አሳስቧል።ይህንን መመሪያ በሚተላለፉ ሚዲያዎች ላይ አስፈላጊው ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስጠንቅቋል።2,160Открыть в Telegram
Ewunet Media
21 сент., 07:15
በኢትዮጵያ ስምንት የትጥቅና የፖለቲካ ድርጅቶች “የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና” የተሰኘ አዲስ ህብረት መመስረታቸውን ገለጹህወሓት፣ አፋብን፣ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት፣ ኦህነግ፣ አፋር፣ ቤንሻንጉል እና ጉሙዝን ያካተተው የጋራ ትብብር ሊቀመንበር አቶ ዘመነ ካሴ እንዳስታወቁት፣ የትብብሩ ዋና አላማ በሽግግር ቻርተር የሚመራ አካታች የሽግግር መንግስት ማቋቋም ነው።
Ewunet Media
20 сент., 16:36
በደቡብ አፍሪካ የዘጠኝ ሴቶች አስከሬን መገኘት ቅጥረኛ ገዳይ አለ የሚል ስጋት ፈጠረበደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኘው ኤኩርሁሌኒ ማዘጋጃ ቤት ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የዘጠኝ ሴቶች አስከሬን በግፍ ተገድለው መገኘቱ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃትና ስጋት ጥሏል።የመጨረሻዋ ተጎጂ ዕድሜዋ 30 ገደማ የሆነች ሴት አስከሬን በግንባታ ቦታ አቅራቢያ በላንቃዋ ታርዳና በወገቧ ላይ በቢላዋ ተወግታ ሆና መንገደኞች አግኝተዋታል።የፖሊስ መርማሪ ፍሬድ ኬካና እንደገለጹት፣ የወንጀሎቹ ተመሳሳይነት በአንድ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ የተፈፀሙ ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ጥርጣሬ አሳድሯል ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ጉዳዩን የሚያጣራ ልዩ የፖሊስ ቡድን የተዋቀረ ሲሆን፣ የጋውቴንግ ግዛት አስተዳዳሪ ፓንያዛ ሌሱፊ በምርመራው ላይ ተስፋ ሰጪ ፍንጮች መኖራቸውን ገልጸዋል።ፖሊስ ህዝቡ የፍርሃት ወሬዎችን ከመነዛት እንዲቆጠብና የተጠረጠሩ ሁኔታዎችን በፍጥነት እንዲጠቁም አሳስቧል።
Ewunet Media
18 сент., 14:50
ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ገለጸበጥቅምት ወር የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለአሐዱ አስታውቋል።በተለይም በሰሜን በሰሜን ምስራቅ በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ መጠን እንደሚኖር እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አሳምነው ተሾመ ተናግረዋል።በተለይም በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ አካባቢዎች በሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል፣ አርሶ አደሮች ሰብላቸውን በፍጥነት እንዲሰበስቡ እና የምርት ብክነት እንዳይከሰት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት። አክለውም የሚመለከታቸው አካላት የጎርፍ መውረጃ ቦዮችን በማጽዳት እና ማህበረሰቡን በማንቃት አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል።በደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሁለተኛ በጋ በመሆኑ ከመደበኛ በላይ የሆነ ዝናብ መኖሩ ለአርብቶ አደሩ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አንስተው ለግብርና እንቅስቃሴው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ እስከ 45 በመቶ የሚሆን የዝናብ መጠን ስርጭት በጉጂ እና ቦረና ዞን እንዲሁም ሲዳማ፤ ደቡብ የኢትዮጵያ የሀገሪቱ አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚጥለው የዝናብ መጠን ከፍተኛ መሆኑ ተጠቀሜታው ከፍተኛ እንደሆነ አስታውቀዋል።
Ewunet Media
18 сент., 10:36
የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩየቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ።ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም።በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም።በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል።በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
Ewunet Media
18 сент., 08:48
የፓርላማ አባል በሽንት ቤት ውስጥ ለ13 ሰዓታት ተቆልፎባቸው አደሩየቤልጂየም የፓርላማ አባል ፍሬደሪክ ኤረንስ በፓርላማው መጸዳጃ ቤት በር መቆለፊያ ብልሽት ምክንያት ተቆልፎባቸው ማደራቸው ተሰማ።ፓርላማ አባሉ ስልካቸውን ቢሯቸው ጠረጴዛ ላይ ትተው በመውጣታቸው እርዳታ ለመጠየቅ አልቻሉም።በሩን ቢደልቁም እና ቢጮሁም ድምፃቸውን የሚሰማቸው ሰው አልነበረም።በማግስቱ ጠዋት በጽዳት ሰራተኛ አማካኝነት የተገኙት ኤረንስ፣ ቦታው በቂ አየር የሌለው በመሆኑ የትንፋሽ እጥረት እና የማዞር ስሜት አጋጥሟቸዋል።በመሆኑም ከደረሰላቸው የህክምና እርዳታ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
Ewunet Media
17 сент., 09:00
በቀን 130 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚያስችል የከርሰ ምድር ውሃ የማልማት ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸበአዲስ አበባ ከተማ እያደገ የመጣውን የንጹህ መጠጥ ውሃ ፍላጎት እና ያለውን የአቅርቦት ክፍተት ለማሻሻል የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል።በ2018 በጀት ዓመት በቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በሌሎች አካባቢዎች 20 አዳዲስ ጉድጓዶች ተቆፍረው ስራ በመጀመራቸው በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዩብ ተጨማሪ ውሃ ወደ ሲስተም ማስገባት መቻሉን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል፡፡በ2019 በጀት ዓመት 130 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ መስጠት የሚያስችል የከርሰ ምድር ውሃ የማልማት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የጠቀሱት ዳይሬክተሯ፤ 100 ሺህ ሜትር ኪዩብ ያህሉ ባለፉት 2 ዓመታት ሲገነባ የቆየው የጨቋላ የውሃ ፕሮጀክት እንደሆነና ቀሪው 30 ሺህ ሜትር ኪዩብ ደግሞ በሌሎች አካባቢዎች ከሚቆፈሩ ጉድጓዶች የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በቀን ከ500 ሺህ እስከ 600 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የማመንጨት አቅም ያላቸው የሲቢሉ እና የአለልቱ ችዳሮቤ የገጸ ምድር ውሃ ፕሮጀክቶች ጥናት ተጠናቆ ገንዘብ የማፈላለግ ስራዎች በተጎዳኝ እየተከናወኑ መሆናቸውን ወ/ሮ ሰርካለም ገልጸዋል፡፡የከተማዋን የውሃ ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላት አዳዲስ ምንጮችን ከማልማት ጎን ለጎን የሚመረተው ውሃ እንዳይባክን የመጠበቅና የውሃ ሀብቱን በአግባቡ የመጠቀም ስራ በትኩረት ሊሰራበትEwunet Media pinned «በኢትዮጵያውያን ተጓዦች ላይ የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ መመሪያ ስራ ላይ ማዋሉን አሳወቀ በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከዚህ ቀደም ለበርካታ ሀገራት ይሰጥ የነበረው ያለቪዛ የመግባት እና የመዳረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አሰራር ድጋሚ ተከልሶ ለተወሰኑ ሀገራት ብቻ እንዲሆን ተደርጓል። በዚሁ መሰረት እስከ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረው…»
17 сент., 09:00

Ewunet Media
17 сент., 08:28
በኢትዮጵያውያን ተጓዦች ላይ የታይላንድ መንግስት አዲስ የቪዛ መመሪያ ስራ ላይ ማዋሉን አሳወቀበአዲሱ መመሪያ መሰረት ከዚህ ቀደም ለበርካታ ሀገራት ይሰጥ የነበረው ያለቪዛ የመግባት እና የመዳረሻ ቪዛ (Visa on Arrival) አሰራር ድጋሚ ተከልሶ ለተወሰኑ ሀገራት ብቻ እንዲሆን ተደርጓል።በዚሁ መሰረት እስከ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ታይላንድ ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ይሰጥ የነበረው የመዳረሻ ቪዛ የተሰረዘ ሲሆን፣ ከአሁን በኋላ ማናቸውም መንገደኞች ከሀገራቸው ከመነሳታቸው በፊት የኦንላይን ቪዛ (E-Visa) ማመልከት ይኖርባቸዋል።ተጓዦች thaievisa.go.th በተሰኘው ይፋዊ ድረ-ገጽ ላይ በማመልከት ፈቃድ ሲያገኙ ብቻ ወደ ሀገሪቱ መግባት እንደሚችሉ በኒው ዴልሂ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የታይላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አስታውቋል።
Ewunet Media
17 сент., 08:04
በጆርጂያ መዲና ትብሊሲ የ2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግበትና 62 ፎቆች ያሉት ግዙፍ የ'ትራምፕ ታወር' ህንፃ ሊገነባ ነው280 ሜትር ቁመት ያለው ይህ ሰማይ ጠቅስ ህንፃ፣ የከተማዋ "ዳውንታውን ትብሊሲ" ዘመናዊ የንግድና የመኖሪያ ግቢ አካል ሆኖ የሚገነባ ነው።ፕሮጀክቱ ከአሜሪካው 'ትራምፕ ኦርጋናይዜሽን' ጋር በመተባበር የሚከናወን ሲሆን፣ በካውካሰስ ቀጠና የመጀመሪያው በትራምፕ ስም የሚጠራ ግዙፍ ሀብት እንደሚያደርገው የጆርጂያ ቱዴይ ዘገባ አመልክቷል።ህንፃው የቅንጡ መኖሪያዎች፣ የሆቴል፣ የንግድ ማዕከላትና የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ ሆኖ ይገነባል።
Ewunet Media
16 сент., 06:50
ኤድ ሺራን እና ሜሲ፡ በቋንቋ መደናቀፍ የታጀበው የሶስት ደቂቃ አስቂኝ ገጠመኝእ.ኤ.አ. በ2023 በፍሎሪዳ በተካሄደ የሙዚቃ ኮንሰርት ወቅት በዓለም አቀፉ ድምፃዊ ኤድ ሺራን እና በእግር ኳስ ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲ መካከል የተከሰተው ያልተጠበቀ ገጠመኝ አሁንም ድረስ ይነሳል።ከኮንሰርቱ ማጠናቀቂያ በኋላ ኤድ ሺራን ከሜሲ ጋር በተገናኘበት ወቅት በታላቅ ደስታና ስሜት ለሶስት ደቂቃዎች ያህል በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሰፊ ንግግር አድርጎ ነበር።ሜሲም ምንም እንኳን የሚነገረው ቋንቋ ባይገባውም በጥሩ ስነ-ምግባር ፈገግታን በማሳየት እና ራሱን በመወዝወዝ በከፍተኛ ትህትና ሲያዳምጠው ቆይቷል።በመጨረሻም የሜሲ ረዳት ለሺራን ሹክ በማለት ሜሲ እንግሊዝኛ መናገር እንደማይችል ሲነግረው ድምፃዊው ለብቻው ሲናገር እንደነበር ተረድቶ ንግግሩን አቋርጧል።ኤድ ሺራን ይህን አጋጣሚ ከአጋጠሙት አስበላጭ እና አዝናኝ ገጠመኞች አንዱ እንደነበር ገልጾታል።
Ewunet Media
15 сент., 12:42
የፋይዳ መታወቂያን ከባንክ ሂሳብ ጋር ለማስተሳሰር የተሰጠው ጊዜ እስከ ጥቅምት 30 ተራዘመ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ደንበኞች ሂሳባቸውን ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ጋር የማስተሳሰሪያ ጊዜ ገደብን አራዝሟል።ባንኩ ከዚህ ቀደም በ27 የከተማ አስተዳደሮችና በሐረሪ ክልል ያሉ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6/ 2018 ዓ.ም፣ በቀሪው የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ደንበኞች ደግሞ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ሂሳባቸውን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ ጊዜ ሰጥቶ ነበር።በተሰጠው ቀነ-ገደብ ሂሳባቸውን ያላስተሳሰሩ ደንበኞች ሂሳባቸው እስኪያስተሳስሩ ድረስ ከሂሳቡ የሚወጣ ገንዘብ ወይም ተቀናሽ ግብይት እንዲታገድ የሚያደርገው "No Debit" እርምጃ ተግባራዊ ሆኖ ቆይቷል።አሁን ግን በሀገሪቱ የተከሰቱ የተለያዩ አበይት ሁነቶችንና የእርሻ ወቅቱን ታሳቢ በማድረግ፣ በ27ቱ ከተሞችና በሐረሪ ክልል ውጭ ላሉ ደንበኞች የነበረው የሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ቀነ-ገደብ ተራዝሟል።አዲሱ ቀነ-ገደብ እስከ ሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ሲሆን በ27ቱ የከተማ አስተዳደሮችና በሐረሪ ክልል የነበረው ቀነ-ገደብ ግን እንዳልተራዘመ ብሔራዊ ባንክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ካላወጡ እንዲያወጡና ከሂሳባቸው ጋር እንዲያስተሳስሩ እንዲያስታውሱና እንዲያበረታቱ መልዕክት አስተላልፏል።በተጨማሪም ባንኮች የፋይዳ መታወቂያን ጥቅምና ከባንክ ሂሳብ ጋር የማስተሳሰርን አስፈላጊነት በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንዲያካሂዱ ታዘዋል።ባንኮች ደንበኞች ያሏቸውን የተለያዩ
Ewunet Media
15 сент., 09:37изменён
ሁቲዎች በሳውዲ አረቢያ ላይ እንደገና ጥቃት ፈፀሙ፡፡አንድ የጦር ሰፈርን ለመምታት የታለመ ጥቃት መዳረሻው የሳዑዲ ከተሞችና ንጹሃን ነዋሪዎች ሆኗል።የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ከጦር ሜዳ አልፎ ወደ ዓለም የነዳጅ ገበያ እየተሻገረ ባለበት ሰዓት፣ የየመን ሁቲዎች በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ ላይ አዲስ የሚሳኤልና ድሮን ጥቃት ፈጽመዋል።ሁቲዎች ሰኞ ዕለት በደቡባዊ ሳዑዲ አረቢያ በሚገኘው ኻሚስ ሙሻይት የጦር አየር ማረፊያ ላይ በርካታ ሚሳኤሎችና ድሮኖችን መተኮሳቸውን ገልጸዋል። ቡድኑ የአየር ማረፊያውን የአውሮፕላን መጋዘኖች፣ የራዳር ስርዓቶች፣ የአውሮፕላን ማረፊያ መሮጫዎችና የጦር መሳሪያ ማከማቻዎችን ኢላማ እንዳደረጉ አስታውቀዋል።ነገር ግን ጥቃቱ የተወሰነው በጦር ሰፈር ዙሪያ ብቻ አልቀረም። የሳዑዲ ባለሥልጣናት በኻሚስ ሙሻይት፣ አብሃ እና ጣኢፍ ከተሞች ላይ ጥቃቶች መድረሳቸውን ገልጸዋል። በዚህም 13 ሰዎች በቀላልና መካከለኛ ደረጃ ቆስለዋል፤ 7 መኖሪያ ቤቶችና 2 ተሽከርካሪዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል።የሳዑዲ አረቢያ የሚመራው የየመን ጥምረት ኃይል ጥቃቱን አጥብቆ የኮነነ ሲሆን፣ በሁቲዎች ላይ “ጠንካራ ምላሽ” እንደሚሰጥ አስጠንቅቋል። ይህም በየመን የቆየው ግጭት እንደገና ወደ ከፍተኛ የጦርነት ደረጃ እየገባ መሆኑን ያሳያል።
Ewunet Media
15 сент., 07:46изменён
በ2018 በጀት አመት ከጥሬ ቆዳና ሌጦ 32.6 ሚሊዮን ምርት መመረቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀበሚኒስቴሩ የስጋ ፣ቆዳ እና ሌጦ ዴስክ ሀላፊ አቶ አስመላሽ በርሄ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በተጠናቀቀው የ2018 በጀት አመት ከበግ፣ ከፍየል እና ከዳልጋ ከብት 32.6 ሚሊዮን ምርት ማምረት ተችሏል።ይህም በእርድ ወቅት ከእንስሳቱ ላይ የተገፈፈ የቆዳና ሌጦ ምርት መሆኑን ገልፀዋል።ቆዳን በሚፈለገው ልክ ለፋብሪካዎች ለማቅረብ ምርቱ ከተለያዮ የኢትዮጵያ ክልሎች እንደሚሰበሰብ የገለፁት ሀላፊው በበጀት አመቱ ከእቅድ አኳያ ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።የእርድ እንስሳት መጠን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ በየአመቱ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ምርት እድገት እያሳየ መምጣቱ ተገልጿል።ምርቱ በአመት ከ2.5 እስከ 3 ሚሊዮን የሚደርስ ጭማሪን እንደሚያሳይ ነው የተነገረው።አንዳንድ ክልሎች ምርቱን በቶሎ ሰብስበው ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ረገድ ከታዮ ክፍተቶች በስተቀር ከታቀደው እቅድ አኳያ 98 በመቶ ያህሉን አፈፃፀም ማሳካት ተችሏል። ይሁን እንጂ በጥሬ ቆዳና ሌጦ ምርት ዙሪያ የግብይት ሰንሰለትን አስመልክቶ በርካታ ችግሮች መኖራቸው ተጠቁሟል።የቆዳ ምርት ወደ ፋብሪካ በአግባቡ የማይደርስበት ሁኔታ እንዳለ ያስረዱት ሀላፊው የትራንስፓርት አቅርቦት እጥረት በዘርፋ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል ተጠቃሽ ነው ብለዋል። ለጉዳዮ መፍትሄ ለማምጣት አሁን ላይ የአሰራር ስርአቶችን ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ ይገኛል ሲሉ አቶ አስመላሽ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
Ewunet Media
12 сент., 09:29
በብሪክስ ፕላስ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ እና የኢራን መሪዎች ተወያዩበብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ በኢትዮጵያ እና በኢራን መሪዎች መካከል ውይይት ተካሄደ።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ባደረጉት ስብሰባ በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና በአጠቃላይ የቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ መክረዋል።ውይይቱ በተለይም በቀጣናው ዘላቂ መረጋጋትን እውን ለማድረግ የውይይት እና የዲፕሎማሲያዊ መንገድ አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።ሁለቱ መሪዎች በስብሰባው ወቅት በቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች እና የደኅንነት ስጋቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያላቸውን አቋም አያንጸባርቀዋል።
Ewunet Media
11 сент., 06:01
የ13 ዓመቱ ታዳጊ የኳታር ብሔራዊ መረብ ኳስ ቡድንን በመቀላቀል ታሪክ ሠራበፈረንጆቹ 2012 የተወለደውና 2.10 ሜትር ቁመት ያለው ሙባረክ ሙሳ የተባለ የ13 ዓመት ታዳጊበወንዶች መረብ ኳስ ሻምፒዮና ላይ ኳታርን ወክሎ በመጫወት ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።ታዳጊው በዕድሜ ከእርሱ በትንሹ በ10 ዓመት የሚበልጡ የጎልማሳ ስፖርተኞች በተሳተፉበት በዚህ ውድድር ላይ ተሰልፎ መጫወቱ ብዙዎችን አጃኢብ አስብሏል።በተለይም ቡድኑ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ባደረገው ጨዋታ፡ ሙባረክ ላቅ ያለ አፈፃፀም በማሳየት ለቡድኑ ከፍተኛ ነጥብ አስመዝጋቢ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።በትንሽ ዕድሜው የአዋቂዎችን የውድድር መድረክ የተቀላቀለው ይህ ታዳጊ፡ በቁመቱና በክህሎቱ ተቃራኒ ቡድኖችን ፈተና ውስጥ በመክተት የወደፊት ተስፋነቱን አስመስክሯል።
Ewunet Media
10 сент., 19:21
የ2018 የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ተቆረጠ፡ 20 ሚሊዮን ብሩን ያሸነፈው ዕጣ ቁጥር ታወቀ!የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የእንቁጣጣሽ ልዩ ሎተሪ ዕጣ አወጣጥ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ምሽት ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሕዝብ ፊት በድምቀት ማካሄዱን አሳውቋል።በዚሁ መሠረት ከፍተኛውን የ20 ሚሊዮን ብር አንደኛ ዕጣ ያሸነፈው 2302203 የሆነው የዕጣ ቁጥር ነው።ዋና ዋና የዕጣ ቁጥሮች እና የሚያስገኙት የገንዘብ መጠን፦1ኛ ዕጣ (20,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 23022032ኛ ዕጣ (10,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 10574133ኛ ዕጣ (5,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 08295164ኛ ዕጣ (2,000,000 ብር)፦ ዕጣ ቁጥር 2161591
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →