Последние посты

Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 17:41
ኢትዮጵያ በኮፕ 32 የአፍሪካውያንን ጥቅሞች የሚያስከብሩ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮችን ታደርጋለች – ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በኮፕ 32 ጉባኤ የአፍሪካውያንን ጥቅሞች የሚያስከብሩ የአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮችን ታደርጋለች አሉ የኮፕ 32 ፕሬዚዳንት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)። ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቱርኩ የቴሌቪዥን ጣቢያ ቲ አር ቲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የአየር ንብረት ፋይናንስ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን…https://www.fanamc.com/archives/326433
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 17:21
ለብሔራዊ ጥቅም የቆመው የዓባይና ቀይ ባሕር ፎረምአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ህልውና ከዓባይ ወንዝና ከቀይ ባሕር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ነው። እነዚህ ሁለት የውሃ አካላት በርካታ ሀገራትን የሚያገናኙ እንዲሁም የተለያዩ ፍላጎቶች የሚንጸባረቁባቸው የትብብር ብሎም የግጭት መነሻዎች ናቸው። የዓባይ ወንዝን ጉዳይ በተመለከተ የናይል ተፋሰስ ኢኒሼቲቭ የተፋሰሱን ሀገራት የልማት ፍላጎትና የጋራ ጥቅም ባገናዘበ መልኩ የጋራ የውሃ ሀብትን በፍትሃዊነትና…https://www.fanamc.com/archives/326429
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 16:46
የመዲናዋ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን የሚመልሰው አዲስ ምዕራፍአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ እያደገ የመጣውን የነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማመጣጠን መንግሥት፣ የህብረት ሥራ ማህበራት እንዲሁም የግል ባለሀብቶች በተቀናጀ መልኩ የቤት ልማት ሥራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ። ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ የቤት ልማት አማራጮች 496 ሺህ 971 መኖሪያ ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ተላልፈዋል። ይህ ስኬት በቀጣይ…https://www.fanamc.com/archives/326426
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 15:48
የምናስበው ብልጽግና የአንዲትን ደሀ እናት ህይወት ካልነካ ዋጋ የለውም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 13:10
የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)አዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ እና የሕዝባችንን የመኖሪያ ቤት ጫና ለማቃለል የሚከናወኑ ስራዎች ተጠነናክረው ይቀጥላሉ አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቱሉ ዲምቱ እና በአዲስ ከተማ መርካቶ አካባቢ በተለምዶ ቅጠል ተራ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የተገነቡ ቤቶችን ጎብኝተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት በሰጡት ማብራሪያ…https://www.fanamc.com/archives/326421
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 11:59
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ ደርሷልአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 36 በመቶ ደርሷል አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፡፡ ተቋሙ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል፡፡ በሦስት ወራት ለመሙላት ከታቀደው 255 ሺህ ሜትር ኪዩብ የአርሲሲ ኮንክሪት ሙሌት ውስጥ 250 ሺህ ሜትር ኪዩብ መከናወኑ በግምገማ መድረኩ…https://www.fanamc.com/archives/326417
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 11:33изменён
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የከተማዋ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ ውይይቱ በትግራይ ክልል ሰላምና መረጋጋትን ማጠናከር፣ የማኅበረሰቡን ስጋቶችና ጥያቄዎች ማዳመጥ እንዲሁም በጋራ መግባባትና ትብብር የሰላም ግንባታ ሥራዎችን ማስፋፋት…https://www.fanamc.com/archives/326413
Fana Media Corporation S.C (FMC)
13 нояб., 11:15
የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ እየተወሰዱ የሚገኙ ተጨባጭ እርምጃዎችአዲስ አበባ፣ ሕዳር 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በፍጥነት እያደጉ ባሉ የኢትዮጵያ ከተሞች፣ በተለይም በአዲስ አበባ፣ ደረጃውን የጠበቀና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው መኖሪያ ቤት ማግኘት ለነዋሪዎች ትልቅ ፈተና ነው። የመደመር መንግሥትም የመኖሪያ ቤት ችግር ሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ተደራራቢ ጫና እና ስጋት በመረዳት ለቤት ልማት ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም መሠረት ከጉባ ብስራቶች አንዱ በሆነው የመኖሪያ…https://www.fanamc.com/archives/326410
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 19:17
"ያለምንም ጥርጥር ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች፥ የሚገባትን ቦታ ትይዛለች፤ ይህ ግን ከእኛ ጥረትና ድካም ውጪ ሊሳካ የሚችልበት ምንም መንገድ የለም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 16:48
የፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው “ድል ቁርሱ” መጽሐፍ የምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን የሕይወትና የውትድርና ጉዞ የሚዳስሰው “ድል ቁርሱ” የተሰኘ መጽሐፍ የምረቃ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡ በመጽሐፉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣…https://www.fanamc.com/archives/323041
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 16:44
"ከተሞቻችን እየዘመኑ፣ ፕሮጀክቶቻችን እያለቁ፤ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ እመርታ ከሚያሳዩ በጣት ከሚቆጠሩ ሀገራት ተርታ አንዷ ሆናለች" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 15:59
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በ81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ነውአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ቡድን በኒውዮርክ እየተካሄደ በሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። ጉባኤው “እምነትን መመለስ፣ ለውጥን መምራት፤ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግሥታት” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤው ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ…https://www.fanamc.com/archives/323036
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 14:32
https://youtu.be/8X0JManjPkYYouTubeብርሃኑን ፍለጋ ...#ፋና #አዲስ_አበባ #Ethiopia #ኢትዮጵያ #FANA_TV #FANA_NEWS #ፋና_ዜና
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 12:54
የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እንዲከበር ዝግጀት ተደርጓል – ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እንዲከበር በቂ ዝግጀት ተደርጓል አሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ…https://www.fanamc.com/archives/323029
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 12:53
የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ስኬት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል – አፍሪካውያን የዘርፉ ባለሙያዎችአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን የስንዴ ልማት ስኬት በዓይናችን አይተን አረጋግጠናል አሉ አፍሪካውያን ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች። በአፍሪካ ዘላቂ የስንዴ ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን፣ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት እና ብሔራዊ የዘር ሥርዓቶችን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ዐውደ ጥናት እየተካሄደ ነው። በዚህ ዐውደ ጥናት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉ…https://www.fanamc.com/archives/323030
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 12:36
ሚኬል አርቴታ ከአርሰናል ጋር ውሉን ለማደስ ተስማማአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ጋር የተሻሻለ አዲስ ውል ለመፈራረም ተስማምቷል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ የሚያበቃ ሲሆን ከክለቡ ጋር ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታ ላለፉት በርካታ ወራት ድርድር ሲካሄድ ቆይቷል። አሁን ላይ ታዲያ አሰልጣኝ ሚኬል…https://www.fanamc.com/archives/323026
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 11:17
የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ይከበራልአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም ይከበራል አለ የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት፡፡ በዚህም መሠረት “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ፤ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ መስከረም 23 እንዲሁም ኢሬቻ ሆረ ሀርሰዴ መስከረም 24 በቢሾፍቱ ከተማ ይከበራል። የምስጋና፣ የአንድነትና የፍቅር በዓል የሆነው ኢሬቻ የሀገርን ገፅታ…https://www.fanamc.com/archives/323020
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 11:15
ከጓሮ ወደ ሉዓላዊነት – የሌማት ትሩፋት ታሪካዊ ስኬትአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ከተለመደው የአመራረት ልማድ ወጥቶ ወደ ተደራሽና ሁለንተናዊ የምግብ ዋስትና ለመሸጋገር በሚያደርገው ጉዞ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። በዘርፉ ከተመዘገቡ ስኬቶች ውስጥ በ2015 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። መርሐ ግብሩ ዛሬ የኢትዮጵያውያን ጓሮ የልማት ማዕከል በመሆን የዕለት ተዕለት የምግብ ፍላጎትን…https://www.fanamc.com/archives/323018
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 09:47
"አንድ ሀገር ከሚያቆማት ምሰሶዎች መካከል አንደኛው የኢኮኖሚ ለውጥ ነው፤ በኢኮኖሚ አሁን ሪፎርም እየተከፋፈተ በመሆኑ ገቢያችን እና የወጪ ንግዳችን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ነው" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Fana Media Corporation S.C (FMC)
22 сент., 09:46
አሜሪካ በኢራን ጥቃት ለተጎዱ የኃይል መሠረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ የሚውል የ5 ቢሊየን ዶላር ፈንድ አቀረበችአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ የሰላጤው ሀገራት ንብረት የሆኑ እና በኢራን ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን የኃይል መሠረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት የሚውል የ5 ቢሊየን ዶላር ፈንድ ይፋ አድርጋለች፡፡ የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይፋ ያደረገው የመልሶ ግንባታ ፈንድ የሰላጤው ሀገራት የነዳጅ ማጣሪያዎችን ጨምሮ የኃይል መሠረተ ልማቶቻቸውን መልሰው በመገንባት የኃይል አቅርቦት ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ ያስችላል…https://www.fanamc.com/archives/323014
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →