gram news
Аватар канала Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

@fdre_molsofficial

FDRE, Ministry of Labor and Skills

ПроектыENРазноеПодтверждён Telegram

70,397подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    6 нояб., 17:50

    "የሥራ ማዕከላት ግንባታ በጥራትና በፍጥነት ተገንብተው ለታለመላቸው ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።" ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበየሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በክልሉ እየተገነቡ የሚገኙትን ዘመናዊ የሥራ ማዕከላት የግንባታ ሂደትና ያሉበትን የአፈጻጸም ደረጃ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።በመስክ ምልከታው ወቅት እንደተገለጸው፤ የተጀመሩት የሥራ ማዕከላት ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በፍጥነትና በጥራት ተጠናቀው ለታለመላቸው የልማትና የወጣቶች አገልግሎት ዓላማ መዋል እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል።የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ እንደገለጹት እየተገነቡ ያሉ የሥራ ማዕከላት ለወጣቶችና ለሥራ ፈላጊዎች በአንድ ማዕከል (One-Stop Service) ፈጣንና የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግንባታው ጥራትና ደረጃ ሳይጓደል በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለታለመለት ዓላማ መዋል ይገባቸዋል።ግንባታውን እያከናወኑ የሚገኙ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸዉ የግንባታውን ሥራ ጥራትና ደረጃዉን በጠበቀ መልኩ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ ሙሉ አቅማችዉን አቀናጅተዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዋል።የሥራ ማዕከላት የአገልግሎት አሰጣጥን ማቀላጠፍ ፣ የሥራ ፈላጊዎችና ኢንተርፕራይዞች የሚያስፈልጓቸውን የተለያዩ አገልግሎቶች በአንድ ቦታ እንዲያገኙ ያስችላል ሲል የዘገበው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    6 нояб., 13:17

    ሥልጠናን ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁና ምርታማ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሰራ ነው፡፡ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታየቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱን ከሥራ ገበያውና ከኢንዱስትሪው ተጨባጭ ፍላጎት ጋር በማስተሳሰር ብቁ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ለማፍራት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) ገለጹ።ሚኒስትር ዴኤታው ይህን የገለጹት የSTEP IV – Horti-Skills የሆርቲካልቸር ክህሎት ልማት ፕሮጀክት ማስጀመሪያና የትግበራ ዕቅድ ዝግጅት መድረክ ላይ ነው።የክህሎት ልማት ስኬት የሚለካው በሚሰለጥኑ ዜጎች ቁጥር ብቻ ሳይሆን፣ ሠልጣኞች በሥራ ገበያው በሚኖራቸው ተሳትፎ፣ በሚያገኙት የሥራ ዕድል፣ በሚፈጥሩት የራስ ሥራና ለኢኮኖሚው በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ መሆኑን አስረድተዋል።ፕሮጀክቱ በሥልጠና ተቋማትና በሆርቲካልቸር ኢንዱስትሪው መካከል ያለውን ትስስር በማጠናከር፣ የክህሎት ክፍተቶችን በመሙላትና የአሰልጣኞችን ብቃት በማሳደግ የዘርፉን የሰው ኃይል አቅም በማጠናከር ላይ ያተኩራል።ሆርቲካልቸር የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የሀገርን ተወዳዳሪነት ለማጠናከርና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም ያለው ዘርፍ ነው።ይህንን አቅም ለመጠቀም ዘመናዊ ቴክኒካዊ፣ አስተዳደራዊ፣ ዲጂታልና የሥራ ፈጠራ ክህሎቶች የተላበሰ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ ነው።ፕሮጀክቱ የግሉን ዘርፍ በክህሎት ፍላጎት መለየትና በሙያ ደረጃዎች ዝግጅት ላይ በማሳተፍ፣ ተግባራዊ ሥልጠናንና የሥልጠና ጥራትን በማሻሻል፣ የተቋማትን ባለቤትነትና የውጤቶችን ዘላቂነት በማጠናከር ላይ ያተኩራል። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በዘርፉ የሥራ ቅጥርና የሥራ ፈጠራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል።ፕሮጀክቱ በጀርመንና በኔዘርላንድስ መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ፣ በGIZ ትግበራና ከአጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የሚከናወን ነው፡፡ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    9,340255332Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    5 нояб., 16:52

    በ22 ቀናት ንቅናቄ ከ25 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች ተፈጠሩየአዲስ አበባ ከተማ ሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የሁለተኛው ዙር የ22 ቀናት የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ ዕቅድ አፈጻጸምን ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች ጋር ገምግሟል።በግምገማው በንቅናቄው ወቅት 25,944 የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸው፣ ከ406.6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መመቻቸቱና 746 ኢንተርፕራይዞች መደራጀታቸው ተገልጿል።በተጨማሪም 29,409 ሥራ ፈላጊዎች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ56 ሺህ በላይ ዜጎች በለስላሳና ቴክኒክ ክህሎት ሥልጠናዎች ተሳትፈዋል።የግምገማ መድረኩን የመሩት የቢሮው የሥራ ስምሪትና ምግብ ዋስትና ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ለገሰ፣ ከመጀመሪያው ዙር ንቅናቄ የተገኙ ልምዶችንና የታዩ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ የተቀናጀና ውጤትን ያማከለ አፈጻጸም ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።ሁሉም ክፍለ ከተሞች በአንድ ዕቅድና የሪፖርት ሥርዓት በመመራት፣ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩም አቅጣጫ ሰጥተዋል።ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    10,0004751Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    5 нояб., 12:11

    መሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ማሳደግና አስተዳደሩን ማጠናከር ለሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ ነውየመሥሪያ ቦታ አቅርቦትና አስተዳደርን ማሻሻል የኢንተርፕራይዞችን ዘላቂ ዕድገት ከማረጋገጥ ባለፈ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠርና የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።ለዚህም የመሥሪያ ቦታዎችን በበቂ መጠን ከማቅረብ ባሻገር በፍትሐዊነትና በግልጽ የአስተዳደር ሥርዓት መምራት ይጠይቃል።በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ ውስጥ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንደ ወሳኝ ግብዓት ተቀምጧል።በዚህ መሠረት በ2019 በጀት ዓመት 11,487 ሼዶችን በመገንባት፣ ሼድ ለሚፈልጉና ለማይፈልጉ የሥራ መስኮች 126,300 ሄክታር የለማ መሬት በማዘጋጀት 49,500 ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል።በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንተርፕራይዞች አቅም ግንባታ ዴስክ ኃላፊ አቶ መላኩ ወልደዮሐንስ እንዳብራሩት፣ የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት ለኢንተርፕራይዞች የሥራ መጀመሪያ መሠረት ብቻ ሳይሆን ለዘላቂ ዕድገታቸውና ለሽግግር ሂደታቸው ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።የመሥሪያ ቦታ አቅርቦት በተገቢው ሁኔታ ካልተመራ የሼድ እጥረት እንዲባባስና አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች ወደ ሥራ እንዳይገቡ እንቅፋት እንደሚሆንም አመልክተዋል።በመሆኑም የመሥሪያ ቦታ አቅርቦትን ለማስፋፋትና አስተዳደሩን ለማሻሻል በተለይ የግሉን ዘርፍ በሼድ ግንባታና አቅርቦት ማሳተፍ፣ ክፍት የሆኑ የመንግሥትና የወል ቦታዎችን ለመሥሪያ ቦታነት ማዋል እንዲሁም የሼድ አስተዳደር ሥርዓትን ማጠናከር ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው።በተለይም የሼድ ማኔጅመንት ሲስተምን በመጠቀም ያሉትን ሼዶች በሙሉ ወደ ሲስተሙ ማስገባት፣ የመሥሪያ ቦታ ምደባን በግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ማከናወንና ዜጎች በእኩል ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል።ከአሠራር ሥርዓት ውጪ የተያዙ ሼዶችን ማስመለስም የሼድ አቅርቦትን ለማሳደግና የተሻለ የቦታ አጠቃቀም ለመፍጠር አስፈላጊ ነው።ከዚህ ጋር ተያይዞ የኢንተርፕራይዞች የሽግግር ጊዜ በአግባቡ መምራት ይገባል። የሽግግር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገሩና የለቀቁት ሼድ ለሌሎች አዳዲስ ኢንተርፕራይዞች እንዲሸጋገር በተገቢው ሁኔታ መከታተል ያስፈልጋል። ይህም ውስን የመሥሪያ ቦታዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀምና ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል።በአጠቃላይ የመሥሪያ ቦታ ጉዳይ የሼድ ግንባታና ምደባ ብቻ ሳይሆን የኢንተርፕራይዞችን የዕድገት ጉዞ የሚወስን ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው።ስለሆነም በየደረጃው የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት የሼድ አስተዳደር ሥርዓቱን በተግባር በማዋል፣ የተጀመሩ የማሻሻያ ሥራዎችን በቁርጠኝነት በመፈጸምና የመሥሪያ ቦታዎችን በፍትሐዊነት በማስተዳደር ለኢንተርፕራይዞች ዘላቂ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ በማዋል የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል።ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    5 нояб., 07:17изменён

    በክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ጋር በመተባበር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑ ተገለጸየቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፣ ሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን በጋራ ገመገመ፡፡ በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል በክልሉ የሚገኙ ኮሌጆች የሚሰጡት የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ከተቋሙ ጋር በቅንጅት የሚተገበር በመሆኑ በእያንዳንዱ አፈጻጸም ላይ ተናቦና ተባብሮ መስራት እንደሚጠበቅ አብራርተዋል።በዚህም ረገድ የተቋማቱን እቅድና አፈጻጸም በጋራ መገምገም እና እንደአስፈላጊነቱ ተደጋግፎ ወደላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።አክለውም የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየሰራቸው ያሉ ስራዎች የሚደነቁና ለሌሎች ተቋማት ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸው በቀጣይ እቅዶችን መከለስና ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር አብሮ መለወጥ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አመላክተዋል።የአሶሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተመስገን ሀይሉ የኮሌጁን የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፤ እንደዝግጅት ምዕራፍ በመደበኛ እና በማታው እንዲሁም በተለያየ ደረጃ በአጫጭር ስልጠናዎች ሰልጣኞች እየሰለጠኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በሩብ ዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት የነበረው የተመዛኞችን ውጤታማነት የማሻሻል ስራም በሚጠበቀው ልክ ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል።በተጨማሪም ኮሌጁ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመሳተፍ ምርትና አገልግሎቱን ማስተዋወቁን፣ ሰልጣኞች ወደ ተቋሙ እንዲመጡ በተለያየ ደረጃ የንቅናቄ ስራዎች መሰራታቸውን እና ከስልጠና ባሻገር ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመድረስና በማህበራዊ እና ሌሎች ሀገራዊ ኢኒሼቲቮች ላይ በመሳተፍ የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።ዲኑ አክለውም ተቋሙ የውስጥ አሰራሩን ከማዘመንና ለሰራተኛው ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር የምርትና አገልግሎት አቅሙን በማሻሻል በሩብ ዓመቱ ከ48 ሚሊየን ብር በላይ የውስጥ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አብራርተዋል። በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ኮሌጁ እንደተቋም የተጣለበትን ኃላፊነት እየተወጣበት ያለው መንገድ ለሌሎች አርአያ እንደሚሆንና በማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።ከምንም በላይ ተቋሙ የተቀናጀ አመራር በመስጠት ብቁ የሰው ሀይል ከማፍራት ባሻገር የውስጥ ገቢውን በአስደናቂ ሁኔታ ማሳደግ መቻሉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።መረጃው -የቤ/ጉ/ክ/መ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡ጥቅምት 26/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    4 нояб., 13:01

    የክህሎት ሥነ-ምህዳርን ማዘመን ለዘላቂ ሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሥራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡በዚሁ መድረክ ላይ ከፍተኛ የክልል የሥራ ኃላፊዎች፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ተዋንያን ተሳትፈዋል።በዘርፉ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት በተነሳሽነት፣ በቁርጠኝነትና በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡ የመፍጠን፣ የመፍጠር እንዲሁም የመስፈንጠር ስልቶችን መከተልና ለጋራ ግብ የየዘርፎቹ መስተጋብር መቀናጀትና መጠናከር እንዳለበትም በመድረኩ ተጠቅሷል፡፡የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ፤ ሀገራዊ እና ክልላዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ ጥራቱን የጠበቀ፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀ እና አምራች የሆነ የሰለጠነ የሰው ሃይል ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።አቶ ሙስጠፋ አያይዘውም ከድህነት እና ከሥራ አጥነት ለመላቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀና አዲስ አስተሳሰብን የተከተለ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።ይህ የንቅናቄ መድረክ የክልሉን የሥራ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥነ-ምህዳር በማዘመን ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን ከመድረኩ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች ቀርበው የዳበረ ውይይት እንደሚደረግባቸው ተገልጿል።መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው፡፡ጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    10,0002622Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    4 нояб., 08:40

    በሥራና ተግባር ትምህርት ብቁና ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ ነውየማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ክልላዊ የሥራና ተግባር ትምህርት አተገባበር የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ መድረኩን ሲከፍቱ እንደገለፁት፤ በክልሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠውን የሥራና ተግባር ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ልዩ ልዩ ኢንሼቲቮችን በመንደፍ ወደ ተግባር ተገብቷል።ዘርፉ እንደ ሀገር በሥራ እድል ፈጠራ ረገድ የተቀመጠለትን ግብ ያሳካ ዘንድ ትምህርት ቤቶች ላይ ክህሎትን ከማስረጽ ባለፈ በሙያ የተደገፈ ትምህርትን መስጠት ይገባል ብለዋል።በዚሁ መሰረት በክልሉ በአንደኛ መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ግንዛቤውን በማስረጽ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቂ የሆነ የሥራና ተግባር ትምህርት በማቅረብ ብቁና ሥራ ፈጣሪ የሆኑ ወጣቶችን ለማፍራት በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። ባለፉት ሁለት አመታት ከ24ሺ በላይ ተማሪዎች የሥራና ተግባር ትምህርት ወስደው መመረቃቸውንም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።ይህ ተግባር ተማሪዎች በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው በደረጃ ሁለት ለመቀጠል ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ያሉት አቶ አንተነህ በቀጣይም ይህን በማጠናከር ብቁ የሆኑ ዜጎችን ለማፍራት ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ትምህርት ቤቶች ከቴክኒክና ሙያ፣ ከጤናና ከግብርና መዋቅሮች ጋር ተቀናጅተው እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል ሲሉ አክለዋል።በሌላ በኩልም አቶ አንተነህ እንደገለጹት የተማሪዎችን መጠነ ማለፍ ለማሻሻል «ኢጁኬሽናል ዴቨሎፕመንት ትረስት» ከሚባል ሀገራዊ ኢንሼቲቭ ጋር በመቀናጀት ወደ ዩኒቨርስቲ፣ ወደ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ወደ ሌሎች የሥራ መስኮች የሚገቡ ተማሪዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።ኢንሼቲቩ ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የአቅም ግንባታ በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን ለሴቶችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ በማድረግ፣ ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት፣ የማጠቃሻ መጽሃፍት ድጋፍ በማድረግና የአይሲቲ መሰረተ ልማትን በመዘርጋት በኩል ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።መረጃው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ነውጥቅምት 25/2019 ዓ.ም ለተጨማሪ መረጃ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን ይጎብኙ Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    10,3002341Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    3 нояб., 14:58изменён

    የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታበሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ትብብር በሥስት ዙሮች በተለያዩ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው የፋውንዴሽን ክህሎት የአሰልጣኞች ስልጠና የማጠናቀቂያ መርሃግብር ተካሂዷል፡፡በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፉን ለማሻሻልና ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውን ከማሻሻል ጀምሮ አዲስ ስትራቴጂ ተቀርጾ በእነሱም ላይ ግንዛቤ የማስጨበጥና የማወያየት ስራዎች መሰራታቸውን አውስተዋል፡፡የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ የአሰልጣኞች አቅም ግንባታ አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ባለፉት ዓመታት ብዙ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡የቴክኒካል ክህሎት ክፍተቶችን በመለየት በተሰጡ ስልጠናዎችም ለውጥ ማግኘት መቻሉን አስረድተዋል፡፡አሁን ላይ የተገኘው ክፍተት የልል ክህሎት (soft skills) በመሆኑ በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንድ ዜጋ ቴክኒካል ክህሎት ስላለው ብቻ ተወዳዳሪ መሆን ስለማይችል ዜጎች ለሁሉም ነገር ዝግጁ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሰልጣኖች ይህንን የልል ክህሎት ስልጠና በትምህርታቸው ተካቶ እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ይህም አሰራር ግዴታ በመሆኑ ሰልጣኞች የማስፈጸም ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በቀጣይም ስልጠናውን ከላይኛው መዋቅር ጀምሮ እስከ ክላስተር ደረጃ ማስፋፋት እንደሚጠበቅ በመግለጽ፣ በእስካሁኑ ሂደት አበርክቶ ለነበራቸው አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡የኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ደ/ር ሐሰን ሁሴን በበኩላቸው፤ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ ለተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡም አርአያ የሚሆን ዜጋ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ልጣኞችም በሙያቸው ለተማሪዎችና ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እንዲሁም ዜጎችን መለወጥ የሚችሉ እንዲሆኑ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡ሀገራችን ኢትዮጵያ ያላት ትልቁ ሀብት ወጣት በመሆኑ እነሱን ለአለም ተወዳዳሪ አድርጎ የማውጣት እና የነገውን የኢንተርፕራይዝ ማስፋፊያ አሻራ የማሳረፉ ኃላፊነት በእጃቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ተሳታፊዎችም በበኩላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን መሰል ስልጠና በማዘጋጀቱ ደስታቸውን ገልጸው የተሰጣቸው ኃላፊነት ትልቅ መሆኑን በመገንዘብ የተጣለባቸውን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    22 сент., 06:51

    በግብርና ዘርፍ ለወጣቶች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል አበረታች ጅምርበሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ ከእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና ከአጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት በግብርና ዘርፍ ለወጣቶች የሥራ ዕድልና የገቢ ምንጭ ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራትን አከናውኗል።በዚህም በ10 ማህበራት ለተደራጁ 148 ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በ32 ሚሊዮን ብር ወጪ 10 ትራክተሮች ተገዝተው ለተጠቃሚዎቹ ተላልፈዋል።ትራክተሮቹም የግብርና ሥራን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማስፋትና የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማሳደግ የሚያግዙ ናቸው።የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትብብር መሥራት የወጣቶችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት የቢሮው አመራሮች፣ በISVCD ፕሮጀክት ድጋፍ የተገኙት ትራክተሮች የግብርና ዘርፉን ዘመናዊነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራና የገቢ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶችም ከሙያዊ ስልጠናና ከተጨማሪ ድጋፍ በመጠቀም ወደ ሥራ እንዲገቡና ዘላቂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።ይህ ተግባር በሲዳማ ክልል የወጣቶችን የሥራ ዕድል ለማስፋት፣ የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ከተወሰዱ ተግባራዊ እርምጃዎች መካከል የሚጠቀስ አመርቂ ሥራ መሆኑ ተገልጿል። መረጃው የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው።መስከረም 13/2019 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    22 сент., 06:44

    በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የውድድር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታወቀየ48ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ከመስከረም 13–16 ቀን 2019 ዓ.ም በቻይና ሻንጋይ ይካሄዳል።በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንም ሻንጋይ የገባ ሲሆን ለውድድሩ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡በውድድሩ በ64 የሙያ አይነቶች ከ68 ከሀገራት የተወጣጡ 1380 በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር መረጃ ያመለክታል፡፡በዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር የኢትዮጵያ የቴክኒክ ተወካይ ዶ/ር ሀፍቶም ገ/እግዚአብሔ እንደገለጹት፣ ውድድሩ የባለሙያዎቻችንን የክህሎት ብቃት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማሳየትና ወጣቶች ወደ ሙያ እንዲገቡ ከማነሳሳት አኳያ ሚናው የላቀ ነው፡፡የሀገራችንን የክህሎት ልማት ሥርዓት ለማዘመን፣ ከዓለም አቀፍና ከኢንዱስትሪ መስፈርቶች ጋር ለማጣጣምም ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ ገልፀው በውድድሩ ኢትዮጵያ በዘጠኝ የሙያ አይነቶች እንደምትሳተፍ ገልፀዋል፡፡በዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር የኢትዮጵያ ረዳት የቴክኒክ ተወካይ እና ተጠሪ በበኩላቸው አቶ አያሌው ሣህለ፤ የኢትዮጵያ ተሳትፎ በተወዳዳሪነት ብቻ ሳይሆን ባለሙያዎች በመዛኝነት ይሳተፋሉ፡፡ይህም የሀገራችንን የሙያ ሥልጠናና ምዘና ሥርዓታችንን ለማሻሻል ከፍተኛ አቅም የሚገኝበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ኢትዮጵያ እ.አ በ2024 የዓለም አቀፍ የክህሎት ውድድር ድርጅትን 88ኛ አባል ሀገር መሆኗ ይታወሳል፡፡ በዚያው ዓመት በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው 47ኛው ዓለም አቀፍ የክህሎት
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    10 сент., 21:00

    እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን፣ አደረሳችሁ!
    19,900149713214Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    4 сент., 17:45

    የሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ሰርተፊኬት አገኘየሲዳማ ክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የISO 9001:2015 ዓለም አቀፍ የጥራት ማኔጅመንት ሥርዓት ሰርተፊኬትን ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት በይፋ ተረክቧል።ሰርተፊኬቱ እንደ ሀገር ለአንድ የክልል የሥራና ክህሎት ቢሮ የተሰጠ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ ስኬቱ በክልሉ የመንግሥት ተቋማት ዘመናዊና ጥራት ያለው አገልግሎት የማስፈን ጥረትን የሚያፋጥን እና ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል።የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነቢሃ መሀመድ በበኩላቸው፣ ሰርተፊኬቱ ቢሮው የጥራት አሠራሩን ለማጠናከር ያደረገውን ተነሳሽነት የሚያሳይ በመሆኑ፣ የተገኘውን ደረጃ በማስጠበቅ ለተገልጋዮች የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ አሳስበዋል።የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ማዓዛ አበራ፣ ቢሮው የISO 9001:2015 መስፈርቶችን በአግባቡ በማሟላቱ ሰርተፊኬቱን ማግኘት መቻሉን ገልጸው፣ የተገኘውን የጥራት ደረጃ ለማስቀጠል ጥረቱ እንዲጠናከር አሳስበዋል።የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ ደግሞ ስኬቱ የተጠናከረ ቡድናዊ ሥራና ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ሪፎርም ውጤት መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰርተፊኬቱ የተገልጋዮችን እርካታና የዜጎችን የሥራ ዕድልና የክህሎት ልማት ፍላጎት በተሻለ ደረጃ ለማሟላት ተጨማሪ ብርታት እንደሚሆን ገልጸዋል።ነሀሴ 29/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Off
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    29,40012323887Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    3 сент., 17:56

    በአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የተገኙ ውጤቶችን የበለጠ ማላቅየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሰኞ ነሐሴ 25 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ የምክክር መድረክ ለዘርፉ ዕድገት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ተጠሪ ተቋማት ፣ የክልል አስፈፃሚ አካላት፣ የስኪል ኢትዮጵያና ኢንተርፕራይዞች ዕውቅና በመስጠት ተጠናቋል፡፡አማራ ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ድሬዳዋ አስተዳደር፣ ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች፣ ድሬዳዋ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዘርፉ ባስመዘገቡት ውጤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡በዕውቅና እና ማጠቃለያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ክብርት ነቢሃ መሃመድ በአምስት ዓመታት በዘርፉ የተገኙ ውጤቶችን በላቀ መልኩ ለማስቀጠል የሚያስችል ስንቅ ከመድረኩ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡በክህሎት ልማት ዘርፍ የስልጠና ደረጃና ጥራትን ለማሳደግ ፣ የተጀመሩ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የክህሎት ባለቤቶችን በስፋት ለማፍራት የሚያስችሉ ጉልህ ተግባራት በትኩረት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል፡፡ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር እንደ ሀገር ያለውን የሥራ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ሥራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩም ጠቁመዋል፡፡በኢንዱስትሪ ሰላምና ጤንነት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት ፣የምክክር ሥርዓትን በአግባቡ ማሳለጥ እንደሚገባም አሳስበዋል ።በተቋም ግንባታ አስቀድመው የተጀመሩ
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    2 сент., 14:14

    “የኢትዮጵያ ማንሰራራት”የ2018 ዓ.ም. የጳጉሜን ቀናት “የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራሉ።የዘንድሮ የጳጉሜን ቀናት ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸውን እመርታዎች ለመዘከር፣ የማንሰራራቷን ጉዞ ለማጉላት እና የተሻለ ነገን ለመገንባት ያለንን የጋራ ተስፋና ቁርጠኝነት ለማጠናከር የተዘጋጁ ናቸው። እያንዳንዱ የጳጉሜን ቀን የራሱ ልዩ ትርጉምና ዓላማ አለው።🟢 ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀንጳጉሜን 1 ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ የዕድገት ጉዞ በመውጣት በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች የሚዘከሩበት ቀን ነው።በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በዕዳ ቅነሳ፣ በቱሪዝምና በውጭ ምንዛሬ ዘርፎች የተመዘገቡ እመርታዎች ይወሳሉ።🔵 ጳጉሜን 2 — የማንሰራራት ቀንጳጉሜን 2 ኢትዮጵያ ወደ ሁለንተናዊ ልማት የተሸጋገረችበትን፣ ከጎታች ማነቆዎች በመውጣት የማንሰራራቷን ጉዞ የሚያሳዩ ሁነቶች የሚቀርቡበት ቀን ነው።በኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በከተሞች ገጽታና በገጠር ኮሪደር ልማት የተገኙ ውጤቶች ይገለጣሉ።🔴 ጳጉሜን 3 — የፅናት ቀን
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    21,100681311Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    2 сент., 14:14

  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    2 сент., 13:06

    ከፈጠራ ሀሳብ ወደ ገበያ፦ ለስታርታፖች የሚያስፈልግ ምቹ ምህዳርአቤል ማስረሻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በነበረው ቆይታ፣ የአካል ጉዳተኛ ጓደኛው ይገጥመው የነበረውን ፈታኝ ሁኔታ በመነሳት፣ የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ወገኖች መፍትሄ የሚሆን የኤሌክትሪክ ዊልቼር ፈጥሯል።ይህ ሀሳብ ወደ ተግባር ሊሸጋገር የቻለው የአቤል ንድፈ ሀሳብ እውቀትን ከተግባራዊ ክህሎት ጋር በማጣመር ነው።እንደ አቤል ማብራሪያ መሰል የፈጠራ ሥራዎች ወደ ዘላቂ ንግድ እንዲሸጋገሩ ፋይናንስ፣ የማምረቻ ቦታ፣ ጥሬ ዕቃ፣ የገበያ ትስስር፣ እንዲሁም ቀልጣፋ ሕግና አሠራር አይነተኛ ሚና ይጫወታሉ።የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአምስት ዓመት የልማት ጉዞ የምክክር ጉባኤ ላይ አቤልን ጨምር ውጤታማ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎች የተሳተፉበት የፓናል ውይይት «ከሥልጠና ወደ ሥራ፣ ከፈጠራ ሀሳብ ወደ ንግድ ልማት» በሚል ርዕስ ተካሂዷል።ወጣቶች ፈጠራቸው ወደ ምርት፣ ምርታቸው ወደ ገበያ፣ ገበያቸውም ወደ ዘላቂ ንግድ የሚሸጋገርበትን ምቹ ምህዳር መፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት ይፈልጋል።በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚገኘው ተግባራዊ ክህሎት በስታርታፕ ምህዳር በተገቢው ሁኔታ ከተደገፈ፣ የወጣቶች ፈጠራ ከግል ስኬት ባሻገር ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋፅኦ ሊያበረክት እንደሚችል በውይይቱ ላይ በስፋት ተነስቷል፡፡ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsF
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    2 сент., 07:37

    # አሁን የአምስት ዓመት ጉዞ ቅኝት የፓናል ውይይትየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአምስት ዓመት የልማት ጉዞውን አስመልክቶ እያካሄደው የሚገኘው የምክክር መድረክ በሦስተኛ ቀን ውሎውበዘርፉ ፖሊሲ፣ ተቋማዊ እሳቤና የሥርዓት እይታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይትን እያስተናገደ ይገኛል፡፡የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ፣ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሃመድ ያለፉት አምስት ዓመታት ዘላቂ አሰራሮችን በሥርዓታዊ እይታ ለመገንባት ጥረት የተደረገበት ጉልህ የመሸጋገሪያ ወቅት እንደነበር ገልፀዋል፡፡በአምስት ዓመት ጉዞ ውስጥ በርካታ አወንታዊ ውጤቶችን ማስመዝገብ መቻሉን የገለፁት ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ወደፊት ዘርፉ የሚጠበቅበትን ግቦች ለማሳካት ደግሞ ጥልቅ ግምገማና ተከታታይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ውይይቱ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡የፖሊሲውን ውጤታማነት መፈተሸና ባለፉት አመታት በተጨባጭ የተሠሩ ሥራዎችን መገምገም የውይይቱ ዋንኛ ትኩረት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ነሀሴ 27/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    20,0002987Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    30 авг., 14:13

    የዘርፉ የአምስት ዓመታት የልማት ጉዞ ሀገር አቀፍ ጉባኤ ነገ ይጀምራልየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉን የአምስት ዓመታት የልማትና የሪፎርም ጉዞ በመገምገም፣ የቀጣይ የልማት ዘመን አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥበት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ነገ በአዲስ አበባ መካሄድ ይጀምራል።ለአራት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ሥራዎች በጥልቀት ይገመገማሉ፤ በዘርፉ አንኳር ጉዳዮች ዙሪያም የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ።ከዚሁ ጎን ለጎን የክህሎት ኢትዮጵያ የሁለተኛው ዙር (2.0)ማጠቃለያ እና የቀጣዩ ዙር ይፋዊ ማብሰሪያ መርሃ ግብር እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ይካሄዳል።በኤክስፖው ሁለተኛው ዙር የክህሎት ኢትዮጵያ መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በመርሃ ግብሩ በታቀፉ ወጣቶች የተሰሩ፣ ችግር ፈቺ የሆኑና ወደ ምርትና አገልግሎት የተሸጋገሩ ውጤታማ ቴክኖሎጂዎች ለእይታ ይቀርባሉ።እንዲሁም ባለፉት አምስት ዓመታት በተተገበረው የክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ ውጤት ያመጡና ማሳያ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችና ሥራ ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የተመረጡ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ያስተዋውቃሉ።ጉባኤው ያለፉትን አምስት ዓመታት የሚዘክር ብቻ ሳይሆን፣ የተገኙ ውጤቶችን መነሻ በማድረግ የቀጣይ ዘመን የሥራ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ፣ ክህሎትን ከሥራ፣ ከፈጠራ፣ ከቴክኖሎጂ እና ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር የሚያስተሳስር ሀገር አቀፍ መድረክ ነው።በጉባኤው የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለድርሻና አጋር
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    25,90069296554Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    28 авг., 04:06

    ሥራ ፈጣሪ እና ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ያለመ የፋዌ (FAWE) የሁለተኛ ዙር ተማሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አጋር የሆነው Forum for African women educationalist (FAWE) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን የሁለተኛ ዙር የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ዓመታዊ ጉባኤ አካሄደ፡፡ጉባኤው ትምህርት ፈልገው አቅም ላጡ ወጣቶች፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለተፈናቃዮች እና ለስደተኞች በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ገብተው ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ ነው፡፡በዚሁ መሠረት በፕሮግራሙ ከታቀፉ 396 ተማሪዎች መካከል 326ቱ ሴቶች፣ 60ቹ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ እና 40 የሚሆኑት ደግሞ የተለያዩ የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥልጠናና የተቋማት አቅም ግንባታ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሁዲን አባሞጋ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል FAWE አንዱ መሆኑን አንስተዋል፡፡ተማሪዎቹ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ስልጠና አግኝተው የተሻለ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከፌዴራል እስከ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮዎች የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመው በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙም አስረድተዋል፡፡ተማሪዎቹ በመጪው ጊዜ ሥራ ፈጣሪ፣ ብቁ ተወዳዳሪ፣ ትጋት የተሞላባቸው እና ለሀገር የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግም
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    27,9007415743Открыть в Telegram
  • Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

    14 авг., 04:27

    የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን ገመገመየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ አፈጻጸምን በጋራ ገምግሟል።በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳን ጨምሮ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።በመድረኩ በሚኒስትር ዴኤታው ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የቀጣይ የትኪረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።ነሀሴ 8/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር Official Website: mols.gov.et Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE Telegram: https://t.me/FDRE_MoLSofficial TikTok: tiktok.com/@mols_official Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYI
    Facebookየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopiaየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia. 246,394 likes · 7,198 talking about this. This is the Official Facebook Page of the Ministry of Labor and Skills of Ethiopia....
    39,7001205265Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота