gram news
Аватар канала Tofik Bahiru

Tofik Bahiru

@fiqshafiyamh

ПроектыARРелигия

7,750подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • Tofik Bahiru

    22 сент., 05:44

    ዛሬ ከዱሓ በኋላ የዱሓ ቡናችሁን ጠጥታችሁ የምታደርጉትን ዱዓ ልስጣችሁ: ‐ኢላሂ ያ ሳቲር! የተሰወረ ነውሬን የምትሸፍን፣ የተገለጠውን ኃጢኣቴን በምሕረትህ የምትሸፍን አዛኙ ጌታዬ ሆይ፤ ድክመታችንን በልግስናህ ሸፍን፣ ኃጢአታችንን በዐፍውህ ሰርዝ፣ ክብራችንን በዱንያም በአኺራም ጠብቅ። ያ ሳቲር! ሰዎች የማያውቁትን አንተ ታውቃለህ፤ እኛን ከራሳችን አሳፋሪ ሁኔታ ጠብቀን፣ በምሕረትህ ጋርደን፣ ሽኝታችንን በሑሰኑል‐ኺታም አድርግልን።
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
  • Tofik Bahiru

    20 сент., 16:37

    ሰይዲና አቡ ዘር [ረዲየላሁ ዐንሁ]፦ …«አንድም መልካም ሥራን ለመፈጸም አቅም ቢያንሰኝስ?» በማለት የአላህን ነቢይ [ﷺ] ጠየቁ።እርሳቸውም እንዲህ መለሱላቸው፦ «ክፋትህን ከሰዎች አርቅ፤ ይህ ከአንተ ለራስህ የምትሰጠው ሰደቃ ነው» ሙስሊም ዘግበውታል። : ከክፋቶች መካከል ደግሞ፦ መልካም ሥራ የሚሰሩትን ማስቆም፣ ተግተው የሚሰሩ ሰዎችን ማሳነስና ተስፋ ማስቆረጥ አንዱ ነው።እንግዲህ ክፉ ተግባርን መተው እንኳን ትልቅ ዋጋ ያስገኛል። ራስህ ከመልካም ሰሪዎች ስትሆን ወይም መልካም የሚሰሩትን ስትደግፍስ ምንኛ የላቀ ደረጃ ታገኝ ይሆን!?
    1,1904921Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    16 сент., 19:05

    መልስ መስጠት ግዴታ አይደለም!… : ብዙ ቤተሰቦችና መልካም ግንኙነቶች የሚፈርሱት በትላልቅ ችግሮች ሳይሆን፣ «እሱ እንዲህ አለኝ፤ እኔም እንዲህ እለዋለሁ» በሚለው እልህ ወለድ አስተሳሰብ ነው።የአንድ ወገን ቃል በአጸፋዊ ቃል ሲመለስ፣ ተጨማሪ አፀፋ ያስከትላል። ቁጣ በአጸፋዊ ቁጣ ሲመለስ የበለጠ ግለት ይጨምራል፤ ችግሩም ይበረታል።ተወዳጃችን [ﷺ] በሚታወቀው ትረካ ላይ በቅናት አነሳሽነት የተሰበረውን ሳህን ሲያዩ በቁጣ አፀፋውን አልመለሱም፤ ምግቡን ሰብስበው በሳህኑ ላይ እያኖሩ፦ «እናታችሁ ቀናች!» ብለው አለፉት።ይህ የጥበብ ትምህርት ነው፦ ሁሉም ተግባር አፀፋዊ ምላሽ አያስፈልገውም።አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَقُلْ لِعِبَادِي يَقُولُوا الَّتِي هِيَ أَحْسَنُ﴾«ባሮቼ የሚሻለውን ነገር እንዲናገሩ ንገራቸው።»አንዳንድ ጊዜ ግንኙነቶቻችንን የሚያድነው ተሟግቶ ማስረዳት ሳይሆን ዝምታ ሊሆን ይችላል። ለተቸን፣ ለዘለፈን፣ ላወገዘን ሁሉ መልስ መስጠት አይጠበቅብንም።
    2,1206993Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    15 сент., 05:39изменён

    ያንተ ኃጢአት ቢደጋገምም… የአላህ ረሕመትም ይደጋገማል!ኢማም ነወዊይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል፦«ሰውየው መቶ ጊዜ፣ ሺህ ጊዜ ወይም ከዚያም በላይ ኃጢኣት ቢደጋግም፣ በእያንዳንዱ ጊዜም ተውበት ቢያደርግ፣ ተውበቱ ተቀባይነት ያገኛል። ኃጢአቶቹም ይራገፋሉ።»ስለዚህ ኃጢአትህ መደጋገሙን ተውበትን ለመተው ምክንያት አታድርገው። የገዛ ድክመትህን እና ስንፍናህንም ከአላህ ረሕመት ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ አታድርገው።በተሳሳትክ ቁጥር ተመለስ። በወደቅክ ቁጥር ተውበት አድርግ። በደከምክ ጊዜ ከአላህ እርዳታ ጠይቅ። ጉዞህን አታቋርጥ።በየአጋጣሚው አዲስ ቀን ለመፍጠር ሞክር። ለራስህ አዳዲስ የዕድል በሮችን ክፈት። በአዲስ ቁርጠኝነት ደግመህ ተነስ። በአንተና በአላህ መሀል ንጹሕ ገጽ ለመጻፍ ጥረት አድርግ።ሙስሊም ተስፋ አይቆርጥም፤ ምክንያቱም የአላህ በር ሁሌም ክፍት ነው፤ ረሕመቱም ከኃጢአታችን የበለጠ ሰፊ ነው።﴿إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا﴾«እነሆ፣ አላህ ኃጢአቶችን ሁሉ ይምራል።»ተውበትን አታዘግይ… አሁኑኑ ወደ አላህ ተመለስ! አበቃልህ የሚሉ ሰልፈኞችን አትስማ! የኃጢኣት ሜዳ ጓዴ በተውበት ሜዳም እንፈላለግ!…
  • Tofik Bahiru pinned «ለልጆቻችን ትምህርት ምክንያት እንስጠው! : ትምህርትን ለልጆቻችን የዱንያ ስኬት መሳሪያ ብቻ አድርገን አናስተምራቸው። ትምህርታቸውን ከአላህ ውዴታ፣ ከመልካም ኒያ፣ ከሙስሊሞች፣ ከአጠቃላይ የሰው ልጅ እና ከሀገር ጥቅም ጋር እናያይዘው። አላህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፦ «﴿يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ﴾…»

    14 сент., 05:37

  • Tofik Bahiru

    14 сент., 05:34

    ለልጆቻችን ትምህርት ምክንያት እንስጠው! : ትምህርትን ለልጆቻችን የዱንያ ስኬት መሳሪያ ብቻ አድርገን አናስተምራቸው። ትምህርታቸውን ከአላህ ውዴታ፣ ከመልካም ኒያ፣ ከሙስሊሞች፣ ከአጠቃላይ የሰው ልጅ እና ከሀገር ጥቅም ጋር እናያይዘው።አላህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፦«﴿يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ﴾«አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡» : ስለዚህ ልጆቻችንን ስናስተምር፣ «ጥሩ ውጤት አምጣ የተሻለ ሥራ እንድታገኝ፣ በውጤት ከሌሎች የበላይ እንድትሆን» በሚል ቅስቀሳ ብቻ አናነሳሳቸው። እንዲህም እንበላቸው፦«እውቀትን የምትማረው አላህን ለማስደሰት፣ ራስህንና ሌሎችን ለመጥቀም፣ የሙስሊሞችን ፍላጎት ለማሟላት እና በምድር ላይ መልካም ሥራዎችን ለማስፋፋት ነው።»የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦««مَن يُرِدِ اللهُ به خيرًا يُفَقِّهْهُ في الدِّينِ» «አላህ መልካምን ለሚፈልግለት ሰው በሃይማኖት ውስጥ ጥልቅ ዕውቀት ይሰጠዋል።» ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል።የሃይማኖት ዕውቀት የሙስሊም መሠረት ነው፤ የዱንያ ዕውቀት ደግሞ ሰውንና ማህበረሰብን ለመጥቀም ከተጠቀምንበት ታላቅ የሕይወት መሳሪያ ነው። ልጃችን ሐኪም ቢሆን ሰዎችን ይረዳል፤ መሐንዲስ ቢሆን ሀገር ይገነባል፤ መምህር ቢሆን ዕውቀት ያስተላልፋል፤ ተመራማሪ ቢሆን ለሰዎች ቋሚ ችግሮች መፍትሔ ያፈላልጋል። ነገር ግን የእነዚህ ሁሉ ዋጋ የሚወሰነው በኒያ፣
  • Tofik Bahiru

    13 сент., 03:54изменён

    የቁርኣን ትምህርት ከክረምት ጋር አያበቃም! : አንዲት እናት ልጇ ቁርኣን እንዲሐፍዝ በጣም ፈለገች። ነገርግን በመንደራቸው ቁርኣን የሚያስተምር መድረሳ ወይም ኡስታዝ አልነበረም። ስለዚህ ልጇን ወደ ሩቅ መንደር ላከችው። ቤተሰቡ ድሆች ስለነበሩ የሚከፍሉት ገንዘብ አልነበራቸውም። ልጁም ኡስታዙ ዘንድ ሲደርስ የቁርኣን ሐለቃው ሞልቶ አገኘው። ኡስታዙም፦ «በዚህ ሐለቃ ውስጥ ቦታ የለም» አለው።ልጁ አዝኖ ወደ ቤቱ ለመመለስ ጉዞውን ጀመረ። ሌሊት ሲደርስበት አንድን ዛፍ ተደግፎ ተኛ። ከዚያም በመናሙ ነቢዩን [ﷺ] ተመለከተ። የደረሰበትንም ነገር ነገራቸው። ነቢዩም [ﷺ] እንዲህ አሉት: ‐ «ወደ ኡስታዝየው ተመለስና፣ ‘የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቁርኣንን አስሐፍዘው ይሉሃል’ በለው።»ልጁም፦ «ምናልባት አያምነኝም። ምን ላድርግ?» አለ።ነቢዩ [ﷺ]፦ «‘زُمَرًا زُمَرًا — ቡድን ቡድን’ የሚለውን ምልክት ንገረው» አሉት።ልጁም ከእንቅልፉ ነቅቶ ወደ ኡስታዙ ተመለሰ። የተነገረውንም አሳወቀው። መምህሩ በዚህ ጊዜ አለቀሰ። ልጁንም በክብር ተቀብሎ ሐለቃው ውስጥ ቦታ ሰጠው። ህጻኑ ስለ መናሙ ሲጠይቀው ኡስታዙ እንዲህ አለ፦«እኔም ነቢዩን ﷺ በሕልሜ አይቼ ነበር። ‘የቁርኣን ባለቤቶች በምን መልኩ ወደ ጀነት ይገባሉ?’ ብዬ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም ‘زُمَرًا زُمَرًا — በቡድን ቡድን’ እየሆኑ አሉኝ» አለው። አላህም በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፦ ﴿وَسِيقَ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ إِلَى الْجَنَّةِ زُمَرًا﴾ «ጌታቸውን የፈሩትም ወደ ጀነት በቡድን ቡድን ይነዳሉ።»
  • Tofik Bahiru

    12 сент., 07:01

    переслано из @mercy_to_the_worlds

    ከአንገትዎ በፊት አንገቴን… : በኡሑድ ዘመቻ ቀን ሰይዲና አቡ ጠልሓ [ረዲየላሁ ዐንሁ] በነቢዩ [ﷺ] ፊት ቆመው ቀስት ይወረውሩ ነበር፤ ተወዳጃችን [ﷺ] ደግሞ ከኋላቸው ተከልለው ነበር።አቡ ጠልሓ ጮሌ ቀስተኛ ነበሩ። ቀስት ሲወረወሩ የአላህ ነቢይ [ﷺ] ራሳቸውን ከፍ እያደረጉ፣ የአቡ ጠልሓ ቀስት የሚያርፍበትን ስፍራ ይመለከቱ ነበር።አቡ ጦልሓ ደረትዎን ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፦''هكذا بأبي وأمي يا رسول الله، لا يصيبك سهمٌ، نحري دون نحرك!''«የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንደዚህ [ደረቴን ከፍ አድርጌ እከላከልልዎታለሁ።] አባቴና እናቴ ቤዛ ይሁኑልዎ፣ ቀስት አይመታዎም። የአንቱን አንገት ከመንካቱ በፊት የኔ አንገት ይቅደም!» : አቡ ጠልሓ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ለነቢዩ [ﷺ] ራስዎን እንደ ግንብ፣ ደረትዎን እንደ ጋሻ አድርገው ይዋጉ ነበር። በነቢዩ [ﷺ] እና በጠላት መካከል ነፍስዎን ግርዶ አድርገው ተገንነታቸውን አረጋግጠዋል።ይህ የእውነተኛው የሶሓቦች ፍቅር ግልፅ ምስክር ነው፤ ቃል ብቻ ሳይሆን ራስን ለሚወዱት መስዋዕት ማድረግ የታየበት!… : ከአንገትዎ በፊት አንገቴ!💚
  • Tofik Bahiru

    11 сент., 08:05изменён

    «ሰጪ አንበሳ እንጂ፣ ተቀባይ ተኩላ አትሁን!» : አንድ ባለጸጋ አባት ነበር። ልጁን ከልክ በላይ በቅንጦት አሳድጎት ነበር። ምንም እንዳይጎድለው ሁሉንም ያሟላለት ነበር። ያልደከመበትን ሀብት በጭካኔ እንዲያወድም ሰልጦት፣ ነዋይ ይበትን ነበር።…ወደ ኋላ ይህ ነገር ያሳስበው ጀመር።…እኔ ከሞትኩ ይህ ልጄ ሀብቴን ማስተዳደር ስለማይችል የተውኩለትን ንብረት ያጠፋዋል የሚል ስጋት ገባው።ስለዚህ ልጁ ራሱን እንዲችል፣ ሥራን እንዲያውቅና የአባቱን ሀብት በትክክል እንዲጠብቅ ንግድ እንዲሞክር ወደ ሩቅ አገር ከሚሄድ ቅፍለት ጋር ላከው።ወጣቱም ሊሸጥ፣ ሊገዛ፣ ሊገበያይ ጉዞውን ጀመረ።ነገርግን በመንገድ ላይ ግን አንድ አስገራሚ ክስተት ተመለከተ።አንድ አንበሳ ጥንቸል አደነ፤ ከዚያም ምግብ ለማግኘት መንቀሳቀስ የማይችል ዕውር ተኩላ የሚገኝበት ዋሻ አጠገብ ወስዶ ጣለውና ሄደ። ወዲያው ዕውሩ ተኩላ እያነፈነፈ መጣና የተጣለለትን ትኩስ አደን ተመገበ።…ወጣቱም ይህን ትእይንት ሲመለከት እንዲህ አለ፦«አላህ በጉድጓዱ ውስጥ የተሸሸገ ይህን ዕውር ተኩላ እንኳን አልረሳውም፤ ሲሳዩን ደጃፉ ላይ ጣለለት። ለተራው አውሬ ይህንን ያደረገ ጌታ እኔንማ አይተወኝም።»
    2,6605821Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    10 сент., 10:28

    ኢማም አሽ‐ሸዕቢይ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የተከበሩና የተዋቡ ሰዎች በፍጥነት ያፈቅራሉ፤ በዝግታ ይጠላሉ። ከብር እንደተሰራ ኩባያ ናቸው፤ ለመሰበር ይዘገያሉ፣ ከተሰበሩም በፍጥነት ይጠገናሉ።ወራዳና ክፉ ሰዎች ደግሞ በዝግታ ያፈቅራሉ፤ በፍጥነት ይጠላሉ። እንደ የሸክላ ጽዋ ናቸው፤ በፍጥነት ይሰበራሉ፣ ለመጠገን ግን ይዘገያሉ።» 📚 ረውደቱል ዑቅላእ
  • Tofik Bahiru

    8 сент., 18:40

    ሷሊሖቹ: ‐ ሶላት ሲሰግዱ «አላህ ሆይ በዚህች ሶላት ውስጥ የፈጸምኩትን ማረኝ።» ይሉ ነበር።…ዐጂብ ለኔ አትልም?!
    2,7404781Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    8 сент., 10:10изменён

    የተባረከ ገንዘብ…የአላህ ነቢይ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል፦ «ከገቢዎች ሁሉ ምልካሙ፣ ሠራተኛው በቅንነትና በታማኝነት በእጁ ሰርቶ የሚያገኘው ገቢ ነው።» አሕመድ፣ በሐሰን ሰነድ ዘግበውታል። : በታማኝነት እና በቅንነት መሥራት: ‐ ማጭበርበርን መተው፣ ሥራንም አሳምሮ በሚገባ ማከናወን ማለት ነው። : ስለዚህ ሙያህን፣ ዓቅምን ሳትቆጥብ በብቃት አከናውን፤ ደንበኛህን አታታልል፤ የምታውቀውን ጉድለት አትደብቅ፤ የምታገለግላቸውን ሰዎች አታንገላታ፤ ቃልህን ጠብቅ፤ የተሰጠህን ኃላፊነትም በአደራ ተወጣ። : እውነተኛ ባለሙያ ማለት የመዓት ገንዘብ የሚያከማች አይደለም፤ ሰዎችን የሚያገለግል፣ ሥራውን የሚያከብር እና በሐቀኝነት የሚሠራ ሰው ነው። ይህ ሰው በሚሰራው ስራ ገንዘብ አያጣም። አኺራውንም ይሸምትበታል! ሠዎችን አስደስተህ የምታገኘው ገንዘብ ደግሞ ላንተና ለቤተሰብህም በረከት ነው! አላህ ያግዝህ!
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
  • Tofik Bahiru

    8 сент., 03:39

    ህያው ቀልብ…አንድ የአላህ ወዳጅ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፦«አንድ ሰው አላህ ዘንድ ቅርብ መሆኑን በምን ያውቃል?»እርሱም እንዲህ መለሰ፦ «ቀልቡ አላህን ሲያስታውስ ይረጋጋል፤ ነፍሱ ከኃጢአት ስትርቅ ደስ ይላታል፤ ከሰዎች ጋር ደግሞ በርህራሄ ይኖራል።»የሰው ሕያውነት ከውጭ አይጀምርም፤ ከቀልብ ውስጥ ይጀምራል። በዚክር ቀልብህን አጽዳ። በተውበት ነፍስህን ያሳርፍ። በርኅራኄህ የአላህን እዝነት ጥራ። በነቢዩ [ﷺ] ፍቅር ምግባርህን አሳምር። በደጋጎች ተረክ መንገድህን አቅና። ትኩረትህን የአኺራ ስኬት ላይ አንጠልጥል። ለምትኖርባት ዱንያም መልካምን አበርክት። አላህ ያግዝህ!
    2,3504321Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    7 сент., 18:39

    💥 ማስታወሻ ====== በተወዳጃችን [ﷺ] ሐዲስ ላይ እንዲህ የሚል ተወርቷል: ‐ «አላህን ሳይዘክር የተኛ ሰው የቂያማ ቀን "ቲራ" ይሆንበታል ይመጣል።» አቡዳዉድ ዘግበውታል "ቲራ":— ብስጭት፣ የሚያስጠይቅ ነገር ወይም ጉድለት ማለት ነው። : ከመኝታ በፊት: ⚀ አየቱል‐ኩርሲይ ⚁ "ቢስሚከላሁም‐መ አሙቱ ወአሕያ" ⚂ ሱረቱል‐ኢኽላስ [ቁልሁወላሁ አሐድ] እና ሙዐዊዘተይን እና ⚃ ስንተኛ ቀኝ እጃችንን በጉንጫችን ስር አድርገን እንዲህ እንበል: ‐ «አላሁም‐መ ቂኒ ዐዛበከ የውመ ተብዐሱ ዒባደክ» : እንቅልፍ የሁሉም ፍጥረት እጣ ነው። የማይተኛው አንድዬው ብቻ ነው። ሁለመናችን በርሱ ጥበቃ ስር እንደሚያድር አምነን እንተኛ! መልካም መኝታ! http://t.me/fiqshafiyamh
  • Tofik Bahiru

    6 сент., 18:19изменён

    የአላህ መልክተኛ [ﷺ] በሌሊት ከእንቅልፋቸው ሲነሱ፦ ❶ «ዐሥር ጊዜ «አላሁ አክበር»፤ ❷ ዐሥር ጊዜ «አልሐምዱ ሊላህ»፤ ❸ «ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ» ዐሥር ጊዜ፤ ❹ «ሱብሓነል-መሊኪል-ቁዱስ» ዐሥር ጊዜ፤ ❺ «አስተግፊሩላህ» ዐሥር ጊዜ፤ ❻ «ላ ኢላሃ ኢለላህ» ዐሥር ጊዜ ይሉ ነበር። ከዚያም፦ ❼ ዐሥር ጊዜ «አላህ ሆይ! ከዱንያ ጭንቀትና ከቂያማ ቀን ጭንቀት በአንተ እጠበቃለሁ።» ይሉ ነበር። ከዚያም የሌሊት ሶላት ይጀምሩ ነበር።»📚 አሕመድና አቡ ዳውድ ዘግበውታል፤ ይህ ቃል አቡ ዳውድ ያስተላለፉት ሲሆን በሐሰን ሰነድ የተዘገበ ነው።
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
  • Tofik Bahiru

    6 сент., 13:24

    переслано из @mercy_to_the_worlds

    ከጥም በላይ የሆነ ፍቅር…ሰይዲና ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ [ረዲየላሁ ዐንሁ] የረሱለላህ [ﷺ] በልባቸው የነበራቸውን ቦታ ሲገልጹ፦««كان رسولُ الله ﷺ أحبَّ إلينا من أموالِنا وأولادِنا وآبائِنا وأمّهاتِنا، ومن الماءِ الباردِ على الظمأ»»«የአላህ መልእክተኛ [ﷺ] ከገንዘባችን፣ ከልጆቻችን፣ ከአባቶቻችን እና ከእናቶቻችን በላይ እኛ ዘንድ የተወደዱ ነበሩ፤ በከባድ ጥም ጊዜ ከሚጠጣ ቀዝቃዛ ውሃም በላይ የተወደዱ ነበሩ።»💧 አስቡት!… ከፍተኛ ጥም ላይ ያለ ሰው ለቀዝቃዛ ውሃ ያለው ፍላጎት ምን ያህል ነው!?… በጥም ለነደደ አንጀት ጠብታ ውሃ ያለው ዋጋ ምን ያህል ነው?!… ከዚያ በላይ ነበር ለሶሓቦች የነቢዩ [ﷺ] ፍቅር!ይህ ሰሐቦች ለነቢዩ [ﷺ] የነበራቸው ፍቅር አጭር መግለጫ ነው። በእርግጥም የአላህን ነቢይ [ﷺ] መውደድ በአንደበት ብቻ የሚገለጽ መፎክር አይደለም። ሱናቸውን መከተል፣ ስነ-ምግባራቸውን መላበስ፣ ለፍጥረት ሁሉ ርኅራኄና ምሕረት ማሳየትን የሚያካትት ሰፊ ጉዳይ ነው።
  • Tofik Bahiru

    6 сент., 07:32

    переслано из @mercy_to_the_worlds

    መከራን ያረከሰ ፍቅር… የኡሁድ ቀን ነበር። የጦርነቱ ዜና ከበኑ ዲናር የሆነች አንዲት ሴት ዘንድ መጣ። መጀመሪያ አባቷ መሰዋታቸው ተነገራት። እሷም፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ብላ ጠየቀች። ከዚያ ወንድሟ መሰዋቱ ተነገራት። እንደገና፦ «ነቢዩስ ﷺ ምን ሆኑ?» ከዚያ ባሏ መሰዋቱ ተነገራት። አሁንም ጥያቄዋ አንድ ነበር፦ «ነቢዩ ﷺ ምን ሆኑ?!»… : ከዚያም የአላህ መልእክተኛ ﷺ በሕይወት እንዳሉና ደህና እንደሆኑ ሲነገራት፣ ወደ እርሳቸው በፍጥነት ሄደች። እርሳቸውን ባየች ጊዜም፣ በአትኩሮት ደህንነታቸውን ተመልክታ ካረጋገጠች በኋላ፦«كل مصيبة بعدك جلل» «ከእርስዎ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም መከራ ትንሽ ነው።» አለች።እስቲ ይህን ፍቅር አስቡ!… አባቷ ሞተዋል፤ ግን የነቢዩ ﷺ ዜናን ትጠይቃለች።
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
  • Tofik Bahiru

    5 сент., 19:51

    የመድረሳችን የልጆች የክረምት ጊዜ ልዩ የትምህርት መርሀ‐ግብር በሰላም ተጠናቆ፣ በድምቀት፣ በጎ እንቅስቃሴና አበርክቶ የነበራቸው ወዳጆቻችንን አመስግነን ዘግተናል። አልሐምዱሊላህ! ዘላቂ አላህ ያድርግልን! አላህ ይቀበለን!
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
    2,2703941Открыть в Telegram
  • Tofik Bahiru

    4 сент., 10:11

    переслано из @mercy_to_the_worlds

    ከሞት በላይ የሆነ ፍቅር…በአንድ ወቅት የነቢዩ ﷺ ሶሓቦች ወደ አንድ አካባቢ ለዳዕዋ ተልከው ነበር። ነገር ግን ከሃዲያን በመንገድ አጥምደው ያዙአቸው። በግፍ የገደሉትን ገድለው የተወሰኑትን ወደ መካ በእስር አመጧቸው።ከእነርሱም መካከል ዘይድ ኢብኑ ደሲናህ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ነበሩ። ወደ መካ ወስደው ለሶፍዋን ኢብኑ ኡመያህ ሸጧቸው። ሶፍዋንም ዘይድን የአባቱን ሞት ለመበቀል ሊገድላቸው አሰበ።…የግድያው ቀን ደረሰ። ዘይድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ከሞት ጋር ፊት ለፊት ቆሙ።…በዚያን ጊዜ አቡ ሱፍያን ወደ እርሳቸው ቀርቦ እንዲህ አላቸው፦«ዘይድ ሆይ! ሙሐመድ [ﷺ] አሁን በአንተ ቦታ ቢሆንና አንተ በቤተሰቦችህ መካከል ብትሆን፣ ሙሐመድ [ﷺ] ላንተ ቤዛ እንዲገደሉ ትመኛለህ?»ዘይድ [ረዲየላሁ ዐንሁ] ምንም ሳያመነቱ መለሱ፦«በአላህ እምላለሁ! ሙሐመድ [ﷺ] አሁን ባሉበት ቦታ እሾህ እንኳን እንዲወጋቸው፣ እኔ ግን በቤተሰቦቼ መካከል በሰላም እንድሆን አልወድም!» ሱብሐነላህ! እኔ ድኜ ቤተሰቦቼ ጋር ለመመለስ እርሳቸው በዚያ ፈንታ አይደለም መገደል እሾህ እንዲወጋቸው እንኳን አልሻም አሉ!…አቡ ሱፍያን በዚህ መልስ በጣም ተደንቀው እንዲህ አሉ: ‐
  • Tofik Bahiru

    3 сент., 04:14

    አላህ ሆይ! የተሟላ ኢማንን፣ እውነተኛ እርግጠኝነትን፣ መልካም ሥራን፣ ሰፊ ሲሳይን፣ ላንተ የተዋረደና አንተን የሚፈራ ልብን፣ አንተን በማስታወስ የሚጠመድ ምላስን፣ ሐላልና መልካም ሲሳይን፣ ሁሉንም መልካም ነገር የሚያካትት በረከትን፣ የሚስሰማና ተቀባይነት የሚቸረው ዱዓን፣ ደህናና ሰላማዊ ቤትን፣ ጤናማ ሰውነትን፣ መልካም መጨረሻን፣ ጀነትን መታደልና በእሳት ከመቀጣት መዳንን እንለምንሃለን። : አላህ ሆይ፣ ሁሉንም ልመናዎቻችንን በችሮታህ ሙላልን። አሚን።
    Иллюстрация к посту канала Tofik BahiruИллюстрация к посту канала Tofik Bahiru
    2,2405042Открыть в Telegram