gram news
Аватар канала FMC Sport ፋና ስፖርት

FMC Sport ፋና ስፖርት

@fmcsport

This is Fana Media Corporation’s (FMC) Sport official Telegram channel. @Fanatelevision @afanoromofana @tigrignafana For more updates please visit https://fanamc.com/amharic/

ПроектыENСпортПодтверждён Telegram

36,600подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    22 сент., 11:14изменён

    ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃልአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ጉዳት እንዳጋጠመው ክለቡ ይፋ አድርጓል፡፡ተጫዋቹ ያጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት በማድሪድ ደርቢ ጨዋታ መሆኑም ተመላክቷል፡፡በዚህም ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።ሪያል ማድሪድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ በ7ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ መርሐ ግብር በአትሌቲኮ ማድሪድ 2 ለ 1 መሸነፉ ይታወሳል፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    22 сент., 06:01изменён

    የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለትአዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዴንማርክ ኮፐንሃገን በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ልዑኩ ቡድኑ አዲስ አበባ ሲደርስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህንን ጨምሮ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ከዓለም 2ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    21 сент., 13:20

    በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል - አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌአዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ፡፡ዋሊያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሲያደርጉ የቆዩትን ዝግጅት አስመልክተው አሰልጣኙ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።ብሔራዊ ቡድኑ በአዲስ አበባ፣ አዳማ እና ሀዋሳ ከተሞች ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸው፤ በማጣሪያው ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።ከተጫዋቾች ምርጫ ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ ተጫዋቾችን የመረጥነው ወቅታዊ ብቃታቸውን መሰረት አድርገን ነው ብለዋል።በዝግጅት ወቅት ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን፣ ከሀዋሳ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የዝግጅት ጨዋታ ማድረጋቸውን የገለጹት አሰልጣኙ፤ ጠንከር ያሉ ተጨማሪ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ለማግኘት ብንሞክርም አልተሳካም ነው ያሉት።እንደ አሰልጣኝ የማምንበት የጨዋታ ስልት ቢኖረኝም፤ አሁን ባለው ሁኔታ በየትኛውም የጨዋታ መንገድ ለማሸነፍ አቅደን ነው የተዘጋጀነው ብለዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በመጪው አርብ በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ከሱዳን ጋር እንዲሁም በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር በባህር ዳር ስታዲየም ይጫወታል።በዳንኤል እንዳለ
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    21 сент., 12:02

    ሉዊስ ዴላፎንቴ በስፔን ብሔራዊ ቡድን ውላቸውን አራዘሙአዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያላቸውን ውል ለረጅም ዓመታት አራዝመዋል፡፡በዚህም አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ የስፔን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው እስከ ፈረንጆቹ 2032 ድረስ የሚቆዩ ይሆናል፡፡አሰልጣኝ ሉዊስ ዴላፎንቴ የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከ16 ዓመታት በኋላ የዓለም ዋንጫን እንዲያሳካ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡አሰልጣኙ በ2026 በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ የተካሄደውን የዓለም ዋንጫ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ጋር ማሳካታቸው አይዘነጋም፡፡የአሰልጣኙን ውል ማራዘም ይፋ ያደረጉት የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ራፋኤል ሎዛን እንዳሉት ዴላ ፎንቴ በስፔን ብሄራዊ ቡድን ታሪክ በጣም ስኬታማ ከሆኑት መካከል አንደኛው ነው፡፡በዚህም እንደ ሀገር በመተማመን ላይ የተመሰረተ የተረጋጋ ፕሮጀክት ማስቀጠል እንፈልጋለን ብለዋል።በሰለሞን በቀለ
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    21 сент., 11:44

    ግራኒት ዣካ ከስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ታገደአዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አምበል ግራኒት ዣካ ከብሔራዊ ቡድኑ ታግዷል፡፡ግራኒት ዣካ በፈረንጆቹ 2022 የአርሰናል ተጫዋች በነበረበት ወቅት ማድረግ የሚጠበቅበትን ክትባት ሳያደርግ በሃሰት የኮቪድ ሰርተፍኬት ወስዷል በሚል መጠርጠሩን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡በዚህም የ33 ዓመቱ ተጫዋች ዣካ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፤ የስዊዘርላንድ እግርኳስ ፌዴሬሽን አምበሉን ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ አድርጓል፡፡ፌዴሬሽኑ ግራኒት ዣካ በቀጣይ በሚደረጉ የኔሽንስ ሊግ ሦስት ጨዋታዎች ላይ እንደማይሳተፍ በመግለጽ፤ ውሳኔው የጋራ ስምምነት ስለመሆኑም ተጠቁሟል፡፡የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን አሁን ትኩረቱ በቀጣይ የሚደረጉ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ መሆኑም ተገልጿል፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    21 сент., 06:39

    እግር ኳስን ለማቆም ጫፍ ደርሶ የነበረው ኮከብ – ራፊንሃአዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የቢቢሲ ስፖርት አምደኛው ጊሌም ባላጌ፥ ብራዚላዊው ኮከብ “የእግር ኳስ ህልሜ አክትሞለታል” የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰበትን አጋጣሚ ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይተርካል። በብራዚሏ ፖርቶ አሌግሪ ከተማ የተወለደው ራፋኤል ዲያዝ ቤሎሊ (ራፊንሃ) እግር ኳስን የጀመረው እንደ አብዛኞቹ ተጫዋቾች ለኳስ ባለው ፍቅር ብቻ አልነበረም። ስኬታማ እግር ኳስ ተጫዋች…https://www.fanamc.com/archives/322935
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    21 сент., 06:35

    የአርሰናል ያልተጠበቀው ሽንፈትከደቂቃዎች በኋላ በኤክስትራ ታይም ስፖርት ቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን#ስፖርት_ፖድካስት #ፖድካስት #ፋናፖድካስት #ፋናሚዲያኮርፖሬሽን #fanapodcast #fanadigitalmedia #fanamediacorporation #PoodkaastiiFaanaa #fanadigitalmedia فانا_عربي_بودكاست
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    20 сент., 17:28

    ማንቼስተር ዩናይትድና ፉልሃም አቻ ተለያዩአዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ከፉልሃም ጋር 1 አቻ ተለያይቷል፡፡ምሽት12:30 ላይ በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፉልሃም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ችሎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ማቲያስ ኩኛ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ባስቆጠራት ግብ ማንቼስተር ዩናይትድ ነጥብ ተጋርቷል፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 18:15

    የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀረአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣሪያ ጨዋታ በታንዛኒያ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡በዚህም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሳያልፍ ቀርቷል፡፡ታንዛኒያ፣ ሱዳን፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።የፍጻሜ ተፋላሚ የሚሆኑት ሁለት ብሔራዊ ቡድኖች ሴካፋ ዞንን ወክለው በአፍሪካ ዋንጫ ይሳተፋሉ።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
    2,130311Открыть в Telegram
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 18:02

    ሃሪ ኬን - በ98 ጨዋታዎች 100 ግቦችአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሃሪ ኬን በጀርመን ቡንደስ ሊጋ አስደናቂ ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል፡፡በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሆትስፐር በግብ አስቆጣሪነቱ የሚታወቀው ሃሪ ኬን ወደ ጀርመን ካቀና በኋላም በግብ አስቆጣሪነቱ ቀጥሏል፡፡በ2023/24 የውድድር ዓመት ባየርን ሙኒክን የተቀላቀለው ሃሪ ኬን ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ዓመታት የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡የ33 ዓመቱ ተጫዋች ሃሪ ኬን ወደ ጀርመን ካቀና በኋላ በ98 የጀርመን ቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።ዲተር ሙለር ከዚህ ቀደም በ129 የቡንደስ ሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ክብረ ወሰኑን ይዞ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ሃሪ ኬን በ98 የቡንደስሊጋ ጨዋታዎች 100 ግቦችን በማስቆጠር ክብረ ወሰኑን የግሉ አድርጓል፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 16:00

    ሻምፒዮኑ አርሰናል በብራይተን 3 ለ 0 ተሸነፈአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ብራይተን አርሰናልን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ፓስካል ግሮስ፣ ኮስቱላስ እና አንድሬስ አሰቆጥረዋል፡፡ሻምፒዮኑ አርሰናል በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ብራይተን በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች 16 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል፡፡በዚህም በ2026/27 የውድድር ዓመት እስካሁን በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች በርካታ ግቦችን በማስቆጠር ቀዳሚው ቡድን ነው፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 13:36

    አስቶንቪላ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አስቶንቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ በተደረገው ጨዋታ የአስቶንቪላን የማሸነፊያ ግቦች ማንዛምቢ፣ ጃክሰን እና ቡንዲያ አስቆጥረዋል፡፡ቶተንሃም ሆትስፐርን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ኮነር ጋላገር እና ቫንሄክ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ቶተንሃም ሆትስፐር በውድድር ዓመቱ በሊጉ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች በአንዱም ማሸነፍ አልቻለም፡፡ በሦስቱ ተሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል፡፡አስቶንቪላ በበኩሉ በዚህ የውድድር ዓመት በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን ማሳካት ችሏል፡፡የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ከብራይተን፣ ኤቨርተን ከኢፕስዊች ታውን እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከሃል ሲቲ ይገናኛሉ፡፡ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ኖቲንግሃም ፎረስት ከኮቨንትሪ ሲቲ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 12:38

    ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስመዘገበችአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ሺህ ሜትር ሴቶች በዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር የዓለም የጎዳና ላይ ውድድር ኢትዮጵያ በአትሌት ልቅና አምባው የወርቅ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ አትሌት አለሺኝ ባወቀ 5ኛ ደረጃን አስመዝግባለች።አትሌት ልቅና አምባው በውድድሩ 14:41 በመግባት ድንቅ ብቃቷን በማሳየት አሸንፋለች፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    19 сент., 09:26

    በዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ የ1 ማይል ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ 2ኛ ወጣችአዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ የሴቶች የ1 ማይል ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች፡፡በኮፐንሃገን፤ ዴንማርክ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር የሴቶች የ1 ማይል ውድድር ተካሂዷል፡፡በውድድሩ ፍሬወይኒ ኃይሉ ፈረንሳዊቷን አጋቲ ጉሊሞት ተከትላ 2ኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ ስታሸንፍ፤ ብርቄ ሀየሎም 29ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    18 сент., 21:57

    ቼልሲ በብሬንትፎርድ ተሸነፈአዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ብሬንትፎርድ ቼልሲን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች ጄደን አንቶኒ፣ ኢጎር ቲያጎ እና ፋቢዮ ካርቫልሆ አስቆጥረዋል።ቼልሲ በውድድር ዓመቱ በሊጉ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    18 сент., 15:32

    አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙአዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመታት ውል የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሹመዋል።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    18 сент., 12:07

    ብሬንትፎርድ ከቼልሲ...አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ብሬንትፎርድ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት በጂቴክ ኮሙኒቲ ስታዲየም ይከናወናል፡፡ቼልሲ በሊጉ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች 7 ነጥቦችን በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ 6 ነጥብ ያለው ብሬንትፎርድ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።ሁለቱ ቡድኖች ባደረጓቸው ያለፉት 5 ጨዋታዎች ቼልሲ በሁለቱ ሲያሸንፍ፤ በሦስቱ አቻ ተለያይተዋል።ባለፉት አራት ጨዋታዎች ምንም ሽንፈት ያላስተናገደው ብሬንትፎርድ፤ አንድ ጨዋታ ሲያሸንፍ በሶስቱ ከተጋጣሚዎቹ ጋር ነጥብ ተጋርቷል፡፡በሊጉ 4ኛ ሳምንት ጨዋታ ነጥብ ጥለው የተገኛኙት ሁለቱ ቡድኖች ወደ ድል ለመመለስ የሚያደርጉት ፉክክር ይጠበቃል።በምሽቱ ጨዋታ ቼልሲ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ 3ኛ ከፍ ሲያደርግ፤ ብሬንትፎርድ ከታከታታይ 3 ጨዋታ አቻ ውጤት መልስ የመጀመሪያ ድሉ ይሆናል።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    17 сент., 19:27

    አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን ይሳተፋልአዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮዽያዊው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በበርሊን ማራቶን እንደሚሳተፍ የውድድሩ አዘጋጆች አረጋግጠዋል።የበርሊን ማራቶን አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፈረንጆቹ 2026 የሚያደርገው የመጀመሪያ ይፋዊ ውድድሩ ነው።አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 2016 እና 2019 በበርሊን ማራቶን የተሳተፈ ሲሆን፤ ሁለቱንም ውድድር በቀዳሚነት ማጠናቀቁ አይዘነጋም።​​በሴቶች ደግሞ ኢትዮዽያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ ተጠባቂ ናት።የ2026 የበርሊን ማራቶን ውድድር በፈረንጆቹ መስከረም 27 የሚካሄድ ይሆናል።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    16 сент., 21:02

    ማንቼስተር ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ዋንጫ ተሰናበተአዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ዙር የካራባኦ ካፕ ዋንጫ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በብራይተን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።ምሽት 4 ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ኮስቱላስ፣ ግሮስ እና ኩይፐር ከመረብ አሳርፈዋል።ማንቼስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ደግሞ ሌሲ እና ማውንት በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥረዋል።ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ዩናይትድ ከካራባኦ ካፕ ዋንጫ ተሰናብቷል።
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት
  • FMC Sport ፋና ስፖርት

    16 сент., 17:24

    ማንቼስተር ዩናይትድ ከብራይተንአዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ዙር የካራባኦ ዋንጫ መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብራይተንን ያስተናግዳል፡፡ማንቼስተር ዩናይትድ በሳምንቱ መጨረሻ በማንቼስተር ደርቢ ከደረሰበት ሽንፈት ለማገገም የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡በሊጉ ጥሩ ጅማሮ ላይ የማይገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በካራባኦ ካፕ ውድድር የሚኖረው ጉዞ ተጠባቂ ነው፡፡ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማንቼስተር ዩናይትድ ሁለቱን አሸንፏል፡፡ተጋጣሚው ብራይተን በበኩሉ ሦስት ጊዜ ድል አድርጓል፡፡በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ኮቨንትሪ ሲቲ ከአስቶንቪላ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ላይ ኤቨርተን ከወልቭስ እንዲሁም ፍሌትውድ ታውን ከሼፊልድ ዩናይትድ ይገናኛሉ፡፡
    Иллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርትИллюстрация к посту канала FMC Sport ፋና ስፖርት