gram news
Аватар канала The Federal Supreme Court of Ethiopia

The Federal Supreme Court of Ethiopia

@fscethiopiapr

Federal Supreme Court is the highest court in Ethiopia. It is constitutionaly established court. It is also one of the three pillars of the federal state that assures the check and balance in & among.

ПроектыENПраво

19,100подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    22 сент., 14:32

    የፈተና ጥሪ ማስታወቂያየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሃሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ባወጣው የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XI እና የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XIII የስራ መደቦች ላይ የጽሁፍ ፈተና ወስዳችሁ ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ ስማችሁ ከዚህ በታች የተገለጸ በመሆኑ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ እንድትገኙ እየገልጽን፤ በተመሳሳይ የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XII የቃል ፈተና መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ እንደሚሰጥ እናሳውቃለን፡፡የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ 👉ዌብ ሳይት ↠ https://www.fsc.gov.et/ 👉ፌስቡክ ↠ https://web.facebook.com/FSCEthiopia 👉 ትዊተር (ኤክስ) ↠ https://x.com/federalsupreme1 👉 ሊንክድኢን ↠ https://tinyurl.com/supereme-court-of-ethiopia 👉ቴሌግራም ↠ https://t.me/fscethiopiaPR 👉ዋትስአፕ ↠ https://tinyurl.com/fscethiopia 👉ዩቲዩብ ↠ https://www.youtube.com/@fscethiopia 👉ቲክቶክ ↠ https://tiktok.com/@federal.supreme.court
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    18 сент., 20:53

    ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወኑ የዲጂታላይዜሽን ሥራዎችን ጎበኙ ‎ ‎መስከረም 08/2019 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) ‎ ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመገኘት የዲጂታላይዜሽንና የሪፎርም ሥራዎችን ጎብኝተዋል። ‎ ‎ክቡር ፕሬዝዳንቱ በክልሉ ሲደርሱ የሐረሪ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሰላህዲን ተውፊቅ፣ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ ሱልጣን አብዱሰላም እንዲሁም ሌሎች የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ‎ ‎ክቡር አቶ ቴዎድሮስ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከናወኑ የሚገኙ አጠቃላይ የለውጥ እና የሪፎርም ሥራዎችን በአካል ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን፤ በጉብኝታቸውም ወቅት፣ በተለይም የዳኝነት አሰራሮችን ዘመናዊ ለማድረግ እና በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እየተደረጉ ያሉ ውጤታማ የዲጂታላይዜሽን እንቅስቃሴዎችን አፈጻጸም ተዘዋውረው ለማየት ችለዋል። ‎ ‎በሐረሪ ክልል በነበራቸው የሥራ ጉብኝት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶችን የትብብር ማዕቀፍ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ክቡር ፕሬዝዳንቱ በቆይታቸው በክልሉ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን እና የተለያዩ የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ‎ ‎በሥራ ጉብኝታቸው ማጠናቀቂያ ላይ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ከክልሉ አመራሮች ጋር በመሆን የአረንጓዴ አሻራ
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    17 сент., 17:37

    የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑ ተገለጸመስከረም 7/2019 (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት)የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አስታወቁ።በድሬደዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን አገልግሎት ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን፤ አገልግሎቱ በተጀመረበት ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትን ጨምሮ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራው የፍትህ ስርዓቱን ተደራሽ፣ ግልጽና ውጤታማ በማድረግ የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል ብለዋል።በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ የተጀመረውን የስማርት ኮርት ስርዓት በመላው አገሪቱ በማስፋት ፈጣንና ግልጽ አገልግሎት በማስፈን የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ እንደተቻለ የገለጹት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፤ የፍርድ ቤቶችን መረጃ አያያዝ ለማዘመን ተግባራዊ የተደረጉ የዲጂታል አገልግሎቶችም ፈጣንና ተደራሽ ፍትህን ለማስፋት ማስቻላቸውን ገልጸዋል።በዛሬው ዕለት በድሬደዋ ተመርቆ ወደ አገልግሎት የገባው የዲጂታል አገልግሎት አሰራር በክልሎች የተጀመሩትን አበረታች ውጤቶች በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ለተከናወኑት ተግባራት ማሳያ
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    16 сент., 06:58изменён

    የፈተና ጥሪ ማስታወቂያየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሃሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ባወጣው የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XII ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ ላይ ያመለከታችሁ አመልካቾች ለፈተና የማለፊያ ነጥብ ተወስኗል።በዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲ መመረቂያ ነጥብ (GPA) ለወንድ 3.5 እና በላይ ለሴት 3.00 እና በላይ ያላችሁ አመልካቾች የተመረጣችሁ በመሆኑ አርብ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 6 ኪሎ ቅጥር ጊቢ እንድትገኙ እያሳወቅን ስም ዝርዝራችሁ እዚህ በተያያዘው ፒዲ ኤፍ ላይ ተገልጿል፡፡
    6,380файл157Открыть в Telegram
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    16 сент., 06:47изменён

    የፈተና ጥሪ ማስታወቂያየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሃሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ባወጣው የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XI ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ ላይ ያመለከታችሁ አመልካቾች ለፈተና የማለፊያ ነጥብ ተወስኗል።በዚሁ መሰረት የዩኒቨርሲቲ መመረቂያ ነጥብ (GPA) ለወንድ 3.5 እና በላይ ለሴት 3.00 እና በላይ ያላችሁ አመልካቾች የተመረጣችሁ በመሆኑ አርብ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 6 ኪሎ ቅጥር ጊቢ እንድትገኙ እያሳወቅን ስም ዝርዝራችሁ እዚህ በተያያዘው ፒዲ ኤፍ ላይ ተገልጿል፡፡
    6,360файл75Открыть в Telegram
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    16 сент., 06:44изменён

    የፈተና ጥሪ ማስታወቂያየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ነሃሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ባወጣው የህግ ጉዳዮች ፀሀፊ ደረጃ XIII ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ ላይ ያመለከታችሁና የተመረጣችሁ አመልካቾች አርብ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 6 ኪሎ ቅጥር ጊቢ እንድትገኙ እያሳወቅን ስም ዝርዝራችሁ እዚህ በተያያዘው ፒዲ ኤፍ ላይ ተገልጿል፡፡
    6,050файл31Открыть в Telegram
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    10 сент., 15:50

    የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2019 ዓ/ም አዲስ አመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤ አዲሱ አመት የሠላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    10 сент., 08:23

    ‎የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ነሀሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ ውሳኔ የሰጠባቸው መዝገቦች ዝርዝር ‎ተ.ቁ መ. ቁ. የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልገውም 1. ‎5405/13 " 2. ‎6270/14 " 3. ‎6409/14 " 4. ‎6426/14 " 5. ‎6467/14 " 6. ‎6605/14 " 7. ‎6620/14 " 8. ‎6623/14 " 9. ‎6625/14 " 10. ‎6648/14 " 11. ‎6759/14 " 12. ‎6827/14 " 13. ‎6945/14 " 14. ‎7012/14 " 15. ‎7014/14 " 16. ‎7015/14 " 17. ‎7083/14 " 18. ‎7149/14 "
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    9 сент., 10:13

    አጣሪ ጉባዔው በ66 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ እና አቅጣጫ ሰጠ።የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች እና በሁለቱ ንዑስ አጣሪ ጉባዔዎች አስፈላጊው ቅድመ ማጣራት እና ምርመራ ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት ሕገ መንግሥታዊ የትርጉም አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 66 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።ጉባዔው ሰሞኑን በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ባደረገው ስብሰባ ከተወያየባቸው 66 አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 45 በሚሆኑ የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።በሌላ በኩል በቁጥር 16 የሚሆኑ አቤቱታዎች ተጨማሪ ማጣራት እና ምርመራ ተደርጎባቸው በድጋሚ ለውሳኔ እንዲቀርቡ ጉባዔው አዝዟል።በዕለቱ ጉባዔው ከተወያዬባቸው አቤቱታዎች መካከል 4 አቤቱታዎች በጉባዔው የአሠራር ሥነ ስርዓት መሰረት እንዲቋረጡ የተወሰ ሲሆን፤ በአንድ ሌላ ጉዳይ ላይ የባለሙያ አስተያዬት (hearing) እንዲደረግበት አቅጣጫ ተቀምጧል።የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 82 መሠረት የተቋቋመ እና 11 አባላት ያሉት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 84 መሠረት የተሰጠው ተቋም መሆኑ ይታወቃል።መረጃው የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ነው!
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    8 сент., 12:20

    ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓትን ለማስፈን ያለመ ስልጠና ለዳኞች እና ለፖሊስ አባላት ተሰጠጳጉሜን 03/2018 ዓ/ም (ፌ/ጠ/ፍ/ቤት)በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት፤ ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ሂደት ትግበራን በተመለከተ ለመርማሪ ፖሊስ አባላት እና ለክቡራን ዳኞች በሁለት ዙር የተከፈለ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ‎ ‎ይህ ስልጠናው በህጻናት ዙሪያ የሚሰሩ የፍትህ አካላትን ሙያዊ አቅም እና የስነ-ልቦና ዝግጁነት ለማጎልበት ያለመ ስልጠና ሲሆን፤ በመጀመሪያ ዙር ህጻናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የምርመራ ስራን ለሚያከናውኑ የፖሊስ አባላት እና አመራሮች ህጻናትን ያማከለ የምርመራ ሂደት አተገባበርን ለማጠናከር የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል። ‎ ‎እንዲሁም በሁለተኛው ዙር የስልጣና መርሃ ግብር ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተወጣጡ ዳኞች ህጻናትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ የዳኝነት አገልግሎት ሲሰጡ የሚገጥማቸውን የስነ-ልቦና ጫና ተቋቁመው ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በተለይም የስሜት ብስለትን የማዳበር ክህሎት እና ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍርድ ሂደት ትግበራ ላይ ያተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ተዳስሰዋል። ‎ ‎በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የህጻናት ፍትህ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክብርት ዳኛ ህውስት አሸናፊ በስልጠናው ላይ እንደገለጹት፤ በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለህጻናት ተስማሚ የሆነ የፍትህ ስርዓት በመገንባት ረገድ
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    6 сент., 07:23

    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    6 сент., 07:23

    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    6 сент., 07:23

    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    6 сент., 07:23изменён

    ‎የብሪክስ አባል ሀገራት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች ጉባኤ ተጠናቀቀ‎ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም፤ (ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) ‎ ‎በህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አዘጋጅነት ከነሐሴ 29 እስከ ጳጉሜን 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በህንድ ሲካሄድ የቆየው የብሪክስ (BRICS) አባል ሀገራት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች ጉባኤ ተጠናቋል። ‎ ‎በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአዘጋጅ ሀገሯ ህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ሱርያ ካንት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የየአባል ሀገራቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች ቁልፍ መልዕክቶቻቸውን አቅርበዋል። ‎ ‎በጉባኤው ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረትም ቁልፍ መልዕክታቸውን ባቀረቡበት ወቅት፤ ለውይይት የተመረጡት ርዕሰ ጉዳዮች ወቅታዊና አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመው፣ የብሪክስ አባልና አጋር ሀገራት የሕግ አሰራር ልምዶቻቸውን እንዲለዋወጡ፣ በፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ እንዲሁም የክርክር አፈታት ሥርዓትን ለማዘመን በቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። ለዚህም በኢትዮጵያ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተከናወኑ ተግባራትን በምሳሌነት አንስተዋል።‎ዝርዝር መረጃውን በሚቀጥለው ሊንክ በመግባት ከፌስቡክ ገጻችን ማግኘት ይችላሉ። 👇 ‎https://www.facebook.com/share/p/18x1KHZvjBJ/
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    2 сент., 16:44изменён

    የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠየፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ነሃሴ 27 2018 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫ ሰጥቷል። በዚሁ መሰረት፡- 1. ጉባኤው ዶክተር ጸጋየ ብርሃኔን የፌደራል ተከላካይ ጠበቆች ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥቷል፡፡2. በአንድ የዲሲፕሊን መዝገብ ክስ የቀረበባቸው ሁለት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ለቀረበባቸው ክስ መልስ እንዲሰጡ ሲል ወስኗል፡፡3. የጡረታ መውጫ እድሜያቸው በመድረሱ በጡረታ ለመሰናበት ጥያቄ ያቀረቡ አንድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በጡረታ እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡4. ከዳኞች የመኖሪያ አፓርታማ ህንጻ አስተዳደር ጋር በተያያዘ ተወያይቶ አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡መረጃው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ነው።
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    1 сент., 18:37

    ‎በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የ5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ ውይይት ተካሄደ ‎ ‎ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) ‎ ‎የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የአምስት ዓመት (2019–2023 ዓ.ም) ስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ ላይ የፍርድ ቤቱ የሥራ ክፍል ኃላፊዎችና የቡድን መሪዎች ውይይት አካሂደዋል። ‎ ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ድሪባ ፈዬራ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፤ የቀጣይ አምስት ዓመታት የስትራቴጂክ ዕቅድ ረቂቅ በተለያዩ የዝግጅት ምዕራፎች አልፎ ከአብይ ኮሚቴው ጋር ውይይት ተደርጎበት አሁን ደግሞ ከዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች ተጨማሪ ግብዓት እንዲሰበሰብበት መቅረቡን አስረድተዋል። ‎ ‎ከዚህ ቀደም ከፍርድ ቤቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ከዳኞች ጋር ተመሳሳይ ውይይቶች መደረጋቸውን አስታውሰው፤ ይህ መድረክ ከእያንዳንዱ የሥራ ክፍል አኳያ ሊካተቱ የሚገባቸውን ዝርዝር ጉዳዮች በጋራ በመለየት ረቂቅ ሰነዱን በላቀ ደረጃ ለማዳበር ያለመ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ‎ ‎በስትራቴጂ ሰነዱ የተካተቱ ዋና ዋና ግቦች፣ ስትራቴጂያዊ ተግባራትና የትኩረት መስኮችን አስመልክቶ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አልሀምዱ አብዶ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን፤ ተሳታፊዎች በቀረበው ረቂቅ ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ለዕቅዱ መዳበር ጠቃሚ ናቸው ያሏቸውን ሐሳብና አስተያየቶች አንስተዋል። ‎ ‎ረቂቅ ዕቅዱ በተሟላና በተጠናከረ መልኩ ለማጠናቀቅ በቀጣይም በተለያዩ ደረጃዎች የምክክር መድረኮች በማካሄድ ጸድቆ ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲሸጋገር
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia
  • The Federal Supreme Court of Ethiopia

    29 авг., 18:01

    ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ በስልጠናና በእውቅና መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ ‎ ‎ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም (የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት) ‎ ‎ዓመታዊ የሠራተኞች መድረክ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሠራተኞችን መብት፣ ግዴታና የዲሲፕሊን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮችን በማካሄድ ተጠናቋል። ‎ ‎በመድረኩ በመሰረታዊ የሠራተኞች መብቶችና ግዴታዎች፣ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሥልጣንና ኃላፊነት እንዲሁም በልዩ ልዩ የሕግ ማዕቀፎችና ድንጋጌዎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አሮን ደጎል ተሰጥቷል። ‎ ‎በቀረበው ስልጠና ላይ ከሰራተኞች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በሥነ-ምግባራቸውና በታታሪነታቸው የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሶስት ሰራተኞች እንዲሁም ተቋሙን ለረዥም ዓመታት አገልግለው በጡረታ ለተሰናበቱ አምስት ሰራተኞች የዕውቅናና የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሂዷል። ‎ ‎የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አበባ እምቢአለ በመድረኩ የማጠቃለያ ንግግራቸው፣ ባለፉት ሁለት ቀናት የተካሄዱት መድረኮች ፍርድ ቤቱ ያከናወናቸውን ተግባራት፣ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችንና የተወጣበትን መንገድ በመገምገም የቀጣይ የጋራ አቅጣጫ የተቀመጠበት መሆኑን ገልጸዋል። ‎ ዝርዝር ዘገባውን ከታች 👇 የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከፌስቡክ ገጻችን ላይ ያግኙ፦
    Иллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of EthiopiaИллюстрация к посту канала The Federal Supreme Court of Ethiopia