Последние посты

ግጥም ብቻ
13 нояб., 19:42
አዝማሪ ቤት አፍሮ ፥ ፀሎት ሥቆም የሚያንጎራጉረኝ ፤ግራ -ገብ ነብሴ ነው፣ ከሠው ፣ ከአምላክ የለያየኝBy sostkilo@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
7 нояб., 10:59
እንደዉ ባጋጣሚ በድንገት አግኝቼህ፤ ምኑንም ሳያዉቀዉ ቀልቤ ተረታልህ፤ንግግርህ መሐል ሳቅህን ስሰማ፤ መጥፋት ያሰኘኛል ከልብህ ከተማ፤በዉስጥህ ያለዉን በቅጡ ባላዉቅም፤ አንተኑ ከመዉደድ ፍጹም አልቦዝንም፤የመጣህ ሲመስለኝ......ከልቤ ላስገባህ በራፌን ከፍቼ፤ እጠብቅሃለዉ ተስፋን ተሞልቼ፤ደግሞ ተመልሰህ ጓዝህን ሸክፈህ፤ ወደ መጣሁበት ሊሂድ ትለኛለህ፤አንተማ.....አይታክትህ መሄድ መምጣት፤ መመላለስ በሰዉ ሕይወት፤እኔ ልጅት.....በመሐል ቤት ተሰቃየሁ፤ ላንተ ብዬ ሰላም አጣሁ፤መሻትህን አላዉቅ የገጠመኝ ፍርጃ፤ የልብህ ቋጠሮ ምን እንደሆን እንጃ፤ እንጃ..........እናልህ አለሜ.......በደመነፍስ ሆነህ ባገኘኸዉ መንገድ፤ እግርህ ወደ መራህ አትምጣ ለመሄድ።✍️ዔደን ታደሰ @Ediwub @getem @getem
ግጥም ብቻ
5 нояб., 10:45
----------°--------°--------- አያስደንቅም የሚንጋጋው ሰው: አውቃለሁና ውጥኑን ሁሉ እንዳልጨረሰው! የፈለገውን ነክቶ ይተዋል፣ በምን ጽናቱ ይፈፅመዋል?፨ወከባ መሐል፧ የመረጠውን መጥጦ ሲጥለው፡ ወኔ ቢስነት ሲያልፈሰፍሰው፡ የኔ አጀብታ የኔ ፈገግታ:-ያ'ለመሠልቸት የፍቅር ክንድሽ፤(እስካሁን ድረስ እኔን መውደድሽ!) ----------°--------°---------[ዓለም] @mypoems396 @getem @getem @getem
ግጥም ብቻ
5 нояб., 09:08изменён
ተዳፍኖ እንደ ፈገገ፣ -----------------------------ቁልቁል ተቀብሮ እንዳደገ፣ ፍሬ እንዳንዠረገገ፣ እንደ ስውር ቅድስና፣ እንዳልተጮኸለት ዝና፣ ትንሽ መሆን ግዝፈት አለው፤ያ ለ መ ታ የ ት ውበት ነው።By Ze B Der@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
3 нояб., 06:09
ፈሪ---------------------------------------- ፍርሀት እያቃዠው ፥ በሆዱ “ሚቆስል “ከተነሳብኝ ግን ፥ ይሉት ጀግናነትን ገፁ ላይ ፥ የሚስል ስንት ቦቅቧቃ አለ ፥ታጋሽ የሚመስል፡፡By Habtamu Hadera@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
29 окт., 16:17
አያቴ ያ ብርቱ ! ላዲስ ትዳር መሻት ፣ ሲቃኝ ልጃገረድ ህንጣ ሲያስገነባ ፣ ሲያደላድል መንገድ አቀቡን ቁልቁል ፣ ሲወጣና ሲወርድ ለፊቱ ሀያ ዓመት ፣ የፖም ዛፍ ሲተክል እኔ የርሱ ፍሬ ፣ የዘመን ቅምጥል አዳም በቆመበት ፣ ሶስት አስር ድምሬ ከቦሌ ሩዋንዳ ፣ እርምጃ ጀምሬ ታክሲ አስቆማለሁ ፣ መጓዝ ታክቶኝ በግ’ሬ። : ብርቱ ሰው አያቴ ቆሞ ፊት ለፊቴ ጥቁር ኮፍያ ስር ፣ ሪቫን ለመድገም ለሶስተኛው ዲግሪ ፣ በሂሳብ ሲጠበብ እኔ የርሱ ፍሬ በጓንት እጎርሳለሁ ፣ እጄን ላለማጠብ። : አያቴ ያ ብርቱ ተጨንቆ ለፊቱ ታሪክ ሲያገላብጥ ፣ መጽሀፍ ሲገልጥ ፣ ኋላውን ሲመዝን ፣ መጪውን ሲለካ እንቅልፋን ሲገብር ፣ ለዚህ ፖለቲካ እኔ የርሱ ቅጣይ የረገፍኩት ዋርካ የጫቴን ከቻልኩኝ : እኔክሽ እኔካ ✌️By Mikael aschenaki@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
29 окт., 14:03
ችግራችሁ ቀላል መከራችሁ ዋዛ ረሀባችሁም ቀልድ ጥማችሁ ፈዛዛ የተሸከማችሁት ደንታም አይሰጠኝም በመቶ ቢባዛ አያሸንፈኝም የጠላት ሰራዊት ለአንድ ለብቻዬ ቢዘምት አይጥለኝም ለምን??? ሰማያዊ ቁጣ መኣት ‘ማይበግረኝ የዛን ውብ ልጅ ናፍቆት ችዬ ምኖር ሰው ነኝ።By meleti kiros@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
27 окт., 04:57
በልቤ ያለዉን- መዉደዴን ገልጬ- ልነግርሽ እልና፤ ሐረግን መሰካት -ንግግር ማሳመር - መች አዉቅበትና፤ብችልማ ኖሮ ልክ እንደገጣሚ ቃላትን መደርደር፤ ስንኝ አዋቅሬ እገጥምልሽ ነበር ጉድ እስኪባል 'ባገር።አወይ ልቤ ሞኙ- ቀን ከሌት ሳይታክት-አንቺኑ ያስባል፤ እንደ ዳዊት መፃ'ፍ-በቀን ሰባት ጊዜ- ስምሽን ይደግማል።አይንሽን አያየሁ- ፍቅሬን ለመናገር -ድፍረትን ስላጣሁ፤ እንደዉ በዝምታ- ሁሉንም ብታዉቂዉ- እያልኩ አስባለሁ ።በልቤ ሰሌዳ- በፍቅር የፃፍኩሽ-የመጀመሪያዬ፤ ቃላት ያጣሁልሽ-የተሸነፍኩልሽ -በህይወት ጉዞዬ።አንቺ ማለትማ.........ስርኩል የማያሻሽ - ለገፅታሽ ዉበት- አንዳች ማዳመቂያ ፤ የአምላክ ጥበቡ - የእጆቹ ስራ -አንቺ መደነቂያ።ለጉድለቴ ሙላት- ህይወቴ እንድትሆኚ -ለደከመዉ ጎኔ፤ እግዜርን ለመንኩት አንቺን እንዲሰጠኝ ማረፊያ ለአይኔ ።.................................................. ✍️ዔደን ታደሰ @topazionnn @getem @getem
ግጥም ብቻ
19 сент., 08:03
@mypoems396 @getem @getem @getem
ግጥም ብቻ
17 сент., 18:47
ያመሻሽ ስንኞች (በእውቀቱ ስዩም)በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤ ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤“”””” እሳቴን አንድጄ ጭራሮ ማግጄ ሰታቴየን ጥጄ ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤By Bewketu seyoum@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
17 сент., 16:05
A SPARKLEREven if that sun never rises, I'm already bright with your lights. The night becomes darker and darker, but can't destroy your smile, a sparkler.No way! The black fog centered me like a core? oh, I'm safer than ever before. And if it's not going to end, I'll choose to stay dead. smelling your fragrance instead.If this night finally decides to go away, I still won't miss the sun anyway! [ዓለም]@mypoems396 @getem
ግጥም ብቻ
16 сент., 18:28изменён
ግዜ ደጉ . . . ልክ ለመሆን ላለመሳሳት ወርቅ ዘመኔን መፈተን በ'ሳትበፍጡር ይዘት በሰው ትከሻ ፍፁም ካልሆንኩ ይሉት ንክሻገጥሜ ትግል ውድቀት ሳላምጥ ሰው እንኳን መሆን ሲያቅተኝ በቅጥ...ጊዜ ደግ አይደል...?ካጓጉል ቅዠት ነክቶ ያባንናል ወደቀ ያሉት በድሜ ይቃናል ነብር ነኝ ባዩም ግልገል ይሆናልከሆዴ አራግፎ የጅል ኩራቴን
ግጥም ብቻ
16 сент., 06:14
ሳይፀልዩ ማደር ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የተራበ ነብር ከሩቅ ተመልክታ ሚዳቆ ፀለየች "አውጣኝ አውጣኝ" አለች ለፈጠራት ጌታ ነብሩም ተርቦ ወደ አምላኩ ቀርቦ አንጀቱ ከሆዱ እንደተጣበቀ ፈቅዶ እንዲሰጠው አምላኩን ጠየቀ የሁላችን ሰሪ ፀሎታቸውንም ሰማቸው ፈጣሪ አምላክም በድምጹ ሚዳቆዋን አላት "እሩጠሽ አምልጪ ከበረታው ጠላት።" ነብሩንም አለው "እሩጥ ተከተላት ምግብ አድርገህም ብላት" ሚዳቆዋ ስትሮጥ ከነብር ለማምለጥ ነብሩም ሲከተላት ሆዱን ሊሞላባት ቋጥኙን ስትዘል እግሯ ተስፈንጥሮ
ግጥም ብቻ
12 сент., 10:10
ደርሷል ትዕዛዛችን ፣ እንብላ ከእህሉ አዘን አዘን የተቀመጥን ፣ ዳስዳስ ያለን ሁሉእንደአበሻ ገበሬ ፣ አርሶ እንዳጨደ ነዶን ከምረን ፣ እጃችን ሰብል ያዘ የመብቃትን ማዕረግ ፣ የመድረስን ከፍታ እጃችን ጨብጦ ፣ ክንዳችን ባይገታግና ግና ሆዳችን ፣ አልጠገበም ሞልቶ ሰው ሰው ተርቧል ፣ ወዳጁን አጥቶ የእራሱ ራስ ከዳ ፣ የሆዱን ሆድ ፈጀ ፍቅር እየዘራ ፣ አሜከላ አጨደሰውን ሰው ራበው ፣ ሰውን ሰው ተጠማ አበሻ በታሪኩ ፣ ዛሬ ብቸኝነት ደማ።By ናትናኤል_አበበ@getem
ግጥም ብቻ
11 сент., 05:51изменён
ብንሥቅም ፡ ባንሥቅም አደይ ቀርታ አታውቅም።by Seifu Workuመልካም አዲስ ዓመት@getem @getem @paappii
ግጥም ብቻ
11 сент., 05:49
ትዝ ይልሻል?የዛሬው ዋዜማ በጳጉሜ 5 አምናከበርሽ ነበርኩኝ የሀሳቤን ልኖር ደጅሽን ስጠናአይገርምም?ድሮ ልንል በቃን እኒያ ቀናት አልፈውትዝብት ሊሆኑን በፊደል ተጽፈውይሄውልሽ አለሜ ይሄንን እወቂ ፡ እንዳለፈው ዘመን ለእኔ ኑሪ እያለ ደጅ ይጠናል ብለሽ እንዳትጠብቂ። ፡ ባይሆን
ግጥም ብቻ
10 сент., 18:57
አዲስ አመት . . ያ...ጠቢብ ሰለሞን.......... ያማረ ቀለበት ከእጅሽ ያጠለቀዉ፤ ምን ያክል ዉበትሽ ልቡን ቢገዛዉ ነው?ከአደይቷ ይልቅ ደምቀሽ ብትታይዉ፤ ሽንፈት የማያዉቀዉ ፍቅርሽ አሸነፈው።ትዋቢበት ዘንዳ ዉብ እንቁን ለጣትሽ፤ ችግር ሲያገኝሽ ማለፊያ ለጣጣሽ፤ አንድም ለልብሽ ነዉ ማሰሪያ ለቃልሽ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ።የካም እድል ፈንታ እንቁ ዕጣ ለወጣች፤ ጸሎቷን ለማድረስ እጇን ለዘረጋች፤ህመምሽ ለሆነች ፈዋሽሽም እሷዉ፤ ለቅድስቷ ምድር አንድም ለሀገርሽ ነው።
ግጥም ብቻ
10 сент., 06:45
"እኔ ባዲስ ቀን አላምንም ቀን ከቀን አልለይም አሮጌ መሆን ነው የቀረኝ አንድ አቅም!" የሚል ድባቴያም ሰምተህ ግን አታውቅም?!ካደፈ ልብሱ አልፎ ከርሞ ልቡናውን እያስተባበረ መስኮት ግድግዳውን እያሰማመረ ድባብ የሚጨምር ደርሶ ባያየውም እንዲህ ያለውንስ አላስተዋልኸውም?!ግን ከዚ ሁሉ ረቅቀን መጠቅ ነጠቅ ብለን፣ ከአይደለም እና አዎ መሃል ወጥተን፣ ካዲስነት ጀርባ ምን ታምር ታይቶሃል?፣ እውነትም ብርሃን ያለው ይመስልሃል?!... መልስ ያበጀህ እንደው ያጣህም እንደሆን ወዴት ትሸሻለህ ተቀባይ ከመሆን?!
ግጥም ብቻ
8 сент., 13:14изменён
ድልድይ ናት ጳጉሜ ከዝያ ወደዚኛው፣ ከመጨረሽኛው~ወደ~መጀመሪያው ሲታደል አይደል ወይ ቋጭቶም ለመደምደም፣ የዓመት ቆይታን በ5 ቀን መገምገም!@mypoems396 @getem @getem @getem
ግጥም ብቻ
1 сент., 07:24
@mypoems396 @getem @getem @getem
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →