Последние посты

𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
25 сент., 04:22
🌹 አንዲት ሴት ከአላህ ጋር ያላትን ትስስር ካበጀች አላህም የትዳር አጋሯንና የልጆቿን ሁኔታ ያበጅላታል። የበጎና የደጋግ ልጆች እናትም ትሆናለች። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ በሶሻል ሚዲያ በፊልምና በተከታታይ ድራማዎች በማሳለፍ የተለያዩ ወሬ የበዛባቸው የሴቶች ስብስብ ማብዛት ላይ በመጠመድ ጊዚዋን ካባከነች... ታዲያ እንዴትስ ብላ ነው ለኡማው መልካም ልጆችን ልታነፅ የምትችለው...?! t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
24 сент., 07:26
"ማለዳው ሲነጋ፣ ምሽቱ ሲመሽ፣ ቁርኣን በእጆቹ መካከል ለተያዘለት ሰው... ምንኛ የታደለ ነው! 🌹📖" http://t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
23 сент., 13:57
የሹዐይብ ሴት ልጆች የአባታቸውን እርጅና፣ የእንስሳዎቻቸውን ጥምና የሥራውን አድካሚነት እያወቁም ከወንድ እረኞች ጋር አልተደባለቁም። ይልቁንም ወንዶቹ ጨርሰው እስኪሄዱ በትዕግሥት ጠበቁ።ዛሬ ግን አንዳንዶቹ ለትናንሽና ለትርፍ ነገሮች ወይም ለዱንያ ፍለጋ ሲሉ ከባዕድ ወንዶች ጋር መደባለቅና አብሮ አንድ ቦታ ላይ መገለል መደበኛ ነገር እየሆነ መጥቷል።ዕንቁ የሆኑና አላህን የሚፈሩ ሴት በችግር ውስጥም ቢሆኑ ሐያዕን ከመላበስ አይወገዱም! t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
23 сент., 10:19
አንድ ሰው ለጓደኛው እንዲህ አለው፦«እገሌ በጆሮህ ሲንሾካሾክ አየሁት፤ ለመሆኑ ምን አለህ?» ጓደኛውም፦ «ምስጢር ትጠብቃለህ?» ሲል ጠየቀው። ሰውየውም፦ «አዎ» አለ። ጓደኛውም፦ «እኔም እንደዚሁ ነኝ!» አለው።ምስጢር መጠበቅ የሥነ-ምግባር እና የታላቅነት መገለጫ ነው የተነገረንን ሁሉ ለሌላ ማውራት ተገቢ አይደለም። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
21 сент., 16:03
የቁርኣንህ ገጽ መለያ ክር የት ላይ ደረሰ?ቦታውን እየቀየረ ነው ወይስ ቁርኣንን በመተውህ ምክንያት በአንድ ቦታ ቆሞ ቀርቷል?ልክ እንደ ስልክህ ሁሉ የራስህ የሆነ የተለየ ቁርኣን አለህ?! t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
19 сент., 17:10
ያ ረብ! ከሃሳብ ክብደትና ከልብ ጭንቀት አቅልልልኝ፤ ነገሬን ሁሉ ላንተ አደራ ሰጥቻለሁ። ጌታዬ ሆይ! እኔ በሚታየኝ ሳይሆን አንተ ለኔ መልካም ነው ብለህ በምታየው ነገር ልቤን አረጋጋው። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
18 сент., 16:11
«ምንም ነገር ቢዘገይ አትበሳጭ፤ ከጀርባው አንተ የማታየው፣ ነገር ግን ለአንተ የተሸሸገ ትልቅ መልካም ነገር አለና።»http://t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
18 сент., 03:35

𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
17 сент., 18:03
ታሪኩ እዚህ ይጀምራል አያበቃምም......http://t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
17 сент., 03:09
«የጣፋጮችን ሁሉ ጣዕም ቀመስኩ፤ ከጤናና ከሰላም የሚበልጥ ጣዕም አላገኘሁም። የመራራዎችን ሁሉ መራርነት ቀመስኩ፤ ከሰው እጅ የመጠበቅን ያህል መራር አላገኘሁም። ድንጋይንና ብረትን ተሸከምኩ፤ ከዕዳና ከብድር የሚከብድ የከበደ ሸክም አላገኘሁም።»http://t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
14 сент., 03:59
የወላጆቹን ውለታ የሚረሳ ሰው ምስጢር አይታመንም፤ በችግር ቀን ከጎን አይቆምም፤ ከእርሱም ምንም በጎ ነገር አይጠበቅም። ለገዛ ቤተሰቦቹ ታማኝ ያልሆነ ሰው፣ ሌላውን ለማታለልና ለመክደት ወደኋላ አይልም። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
12 сент., 03:07
«ጌታዬ ሆይ! የቁርኣንን በረካ፣ የቁርኣን መጅሊሶችን እና የቁርኣን ወዳጅነትን አትንሳን። » http://t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
10 сент., 10:52
አላህ ወዳጆቻችንን ያቆይልን፣ ጤናችንን ይጠብቅልን፣ ቀልባችንን የሠጠንን ፀጋ እንዳያጣጥም የሚዘናጋ አያድርግብን፣ያለንን በማሳነስ ያጣንን በማግዘፍ ከሚጠመዱት አያድርገን። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
8 сент., 18:20
የሺሻ፣የጫት፣ የትምባሆ መሸጫ ሱቅ የከፈተውን ሰው ሁሉ አላህ ቅኑን መንገድ እንዲመራው እለምነዋለሁ፤ ልረግመው አልፈልግም፤ ይልቁንም መልካም ነገርንና የማስተዋል ልቦናን እመኝለታለሁ። ምክንያቱም የሠራው ሥራ ስንቱን ጤና አደቀቀው! የሚያቀርበው ምርት ስንቱን ቤተሰባዊ ግንኙነት አበላሸው! የማኅበረሰቡንም ገጽታ አበላሸ! ከሰዎች መካከል ለክፉ ነገር መክፈቻ፣ ለበጎ ነገር ደግሞ መዝጊያ የሆኑ አሉ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
7 сент., 13:29
የመርከዝ ኢብኑ አባስ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎች የሽኝት ፕሮግራም http://t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
6 сент., 18:12изменён
የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት🎓الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحاتየመርከዝ ኢብን አባስ የቁርአን ሂፍዝ ማዕከል ተመራቂ ተማሪዎቻችን፤ ይህንን ፅሁፍ የምጽፍላችሁ በእናንተና ባስመዘገባችሁት ውጤት ልቤ በኩራትና በደስታ ተሞልቶ ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል በነበረው የቁርአንና የእውቀት ጉዞ ላይ ቆይታችሁን አጠናቃችሁ ለዚህ ታላቅ ማዕረግ የበቃችሁ 120 ተማሪዎቻችን፣ እንኳን ለዚህ አበቃችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ! በዛሬው ዕለት የቁርአን ምርቃት ፕሮግራማችን በዚህ መልኩ ደምቆ፣ አምሮና ተውቦ በመጠናቀቁ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በያላችሁበት ቦታ ሁሉ ይጠብቃችሁ፤ ዲኑንና ኡማውን በቅንነት የምታገለግሉ ያድርጋችሁ። በቀጣይ የሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ በደረሳችሁበት ቦታ የሸሪዓን እውቀት በመቅሰም የምትተጉ፣ የሰለፎችን መልካም ጎዳናና መንገድ የምትከተሉ ያድርጋችሁ፤ ሁልጊዜም ዱዓችን ከእናንተው ጋር ነው። አብሮ በመኖር፣ አብሮ በመብላትና በመጠጣት ያሳለፍነውን የወንድማማችነት ጊዜ ስናስታውስ መለያየቱ ቢከብድም፣ ኢንሻ አላህ ወደፊትም በኸር ሥራዎች ላይ አብረን እንደምንቀጥል ሙሉ ተስፋ አለን። አላህ መልካሙን ሁሉ ይግጠማችሁ።ለአላህ ብዬ እጅግ አድርጌ እወዳችኋለሁ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
5 сент., 13:48
በተሸሁድ ጊዜ ወደ አመልካች ጣት መመልከት ከሱና ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺለተሸሁድ በሚቀመጡበት ጊዜ የግራ እጃቸውን በግራ ጭናቸው ላይ ያደርጉ ነበር። በአመልካች ጣታቸው ይጠቁሙ ነበር። እይታቸውም ከሚያመልከቱበት ጣታቸው አያልፍም ነበር። (ሶሒሕ አል-ነሳኢ)t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
4 сент., 16:07
ለደስተኛ ህይወት አምስት ወርቃማ ምክሮች ~ በራስህ ተማመን፦ በውስጥህ ላለው ማንነትና ችሎታ ቦታ ስጥ። መልካም ሰው ሁን፦ መልካም ማድረግ ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለራስህም ሰላም ይሰጣል። ሁልጊዜ ይቅር በል፦ ይቅርታ ማድረግ ከበደል ይልቅ ነፃነትን መምረጥ ነው። ቀና አስተሳሰብ ይኑርህ፦ በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ በጎውን መንገድ ለመመልከት ሞክር። ማንንም አትጎዳ፦ በንግግርህም ሆነ በተግባርህ የሌሎችን ሰላም አታደፍርስ። t.me/ibrahim_furii
𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
4 сент., 05:22
ለሰዎች ወሬ ጆሮ አትስጥ! ~ ነፍሳት ሁልጊዜ የሚከበቡትና ጥቃት የሚያደርሱት የሚያበሩትን መብራቶች ብቻ ነው። አንተም የምታበራና ስኬታማ ሰው ስለሆንክ የሰዎች ወሬ አይክበድህ፤ መንገደህን ቀጥል! t.me/ibrahim_furii


𝙞𝙗𝙧𝙖𝙝𝙞𝙢 𝙝𝙚𝙮𝙧𝙚𝙙𝙞𝙣 𝙘𝙝𝙖𝙣𝙣𝙚𝙡
2 сент., 13:32
ሐራም የሆኑ ግንኙነቶች «ጊዜያዊ ደስታ…. ዘላቂ ጸጸት።»

