Последние посты

Injibara University
24 сент., 15:20
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አጸደቀ፡፡ ================= መስክም 14/2019 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲሴኔቱ በመደበኛ ስብሰባው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የ2019 ዓ.ም የአካዳሚክ ካሌንደር ፣ የተሻሻለውን ውጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት (outcome-based curriculum) እና የአካዳሚክ ፕሮሞሽን ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አጽድቋል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት የ2019 ዓ.ም የአካዳሚክ ካሌንደርን በትምህርት ሚኒስተር አካዳሚክ ካሌንደርን መነሻ በማድረግ ተወያይቶ ያጸደቀ ሲሆን በሁለተኛው አጀንዳ በአዲሱ እና በተሻሻለውን ውጤት ተኮር ስርዓተ ትምህርት (outcome-based curriculum) ትምህርት ሚኒስቴር መነሻ የላከላቸው ፕሮግራሞችን ከዩኒቨርሲቲው ልየታ (Differentiation)፣ ከተሰጠው ተልዕኮ እና ከትኩረት መስኮቹ ጋር በማገናዘብ በየኮሌጆቹ ምሁራንና የውጭ ገምጋሚዎች አማካኝነት ግምገማ (Validation Workshop) ተካሂዶባቸው ለሴኔቱ የቀረቡ የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች በ2019 ዓ.ም የሚቀበሏቸውን ተማሪዎች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተቀብለው እንዲያስተምሩ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ሴኔቱ በ3ኛ አጀንዳው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ዲን እና መምህር የሆኑት ሀብታሙ አድማስ (ዶ/ር) በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልገሎት እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋም በሰጡት አገልግሎት አስፈላጊውን መስፈርት እና የቆይታ ጊዜ በማሟላታቸው ከረዳት ፕሮፊሰርነት ወደ ተባባሪ ፕሮፈሰርነት (Associate professor in Soil Science) እንዲያድጉ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ፕሮግራሙ በስኬት ተጠናቋል።ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!


5,160Открыть в Telegram
Injibara University
24 сент., 08:07
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ ለእርስቱ አጥናፍ መልካም ምኞታቸውን ገለጹመስከረም 13/2019 ዓ/ም: እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበሃገር አቀፍ ደረጃ በተዘጋጀው የውኃ ሙያ የክህሎት ውድድር (Skill Competition) ከእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ደረጃ በመዉጣት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር እውቅና የተሰጠው እርስቱ አጥናፍ በቻይና ሻንጋይ በሚካሄደው 48ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር (48th world skill competition-2026) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን እና ኢትዮጵያን በመወከል ለዓለም አቀፍ ውድድር ወደ ሻንጋይ አቅንቷል።የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ በቻይና ሻንጋይ በሚካሄደው የዓለም የክህሎት ውድድር እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን እና ኢትዮጵያን በመወከል በመሳተፍ ላይ ለሚገኘው እንቁ የውኃ ባለሙያው እርስቱ አጥናፍ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል። ያለህም እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!!.


2,470Открыть в Telegram
Injibara University
24 сент., 07:54
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ነባር ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው። =========መስከረም 14/2019ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበዩኒቨርሲቲው በ2019 የትምህርት ዘመን ከመስከረም 14 - 15/2019 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው ነባር መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ ናቸው።ውድ ተማሪዎቻችን አረንጓዴ፣ ጽዱና ውብ ወደሆነው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በደህና መጣችሁ !!!ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!


2,570Открыть в Telegram
Injibara University
23 сент., 13:47
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ============== ከዚህ በታች ባለው ማስታወቂያ ስማችሁ የተዘረዘራችሁ የቴክኒካል አሲስታንት አመልካቾች ለፈተና የተመረጣችሁ ስለሆነ በ19/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ብቃትና ሰው ኃብት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ተገኝታችሁ ፈተናውን እንድትወስዱ እናሳስባለን።


4,720Открыть в Telegram
Injibara University
22 сент., 05:22
ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፦ ==================


5,860Открыть в Telegram
Injibara University
21 сент., 17:24

4,320Открыть в Telegram
Injibara University
21 сент., 17:24
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ልዑካን እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ ============= መስከረም 11/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ሥራ አስፈፃሚ ከተወሰኑ የአርቲስት አባላት ጋር በጋራ በመሆን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲን የባህል ሙዝየም፣ የግቢውን አረንጓዴ ውበት፣ የአዳራሽ ግንባታ ሂደትንና የመሳሰሉትን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ጎብኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አርቲስት አሊ ከማል ዩኒቨርሲቲውን ከጎበኙ በኋላ በሰጡት አስተያየት ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተ ጥቂት ዓመታት ቢሆንም ትምህርት ክፍሎችን በማስፋፋትም ሆነ በአጠቃላይ በግቢው ውስጥ የተከናወነው ተግባር የአመራሩን ተግባብቶ መሥራትና ቁርጠኝነት ልምድ ሊወሰድበት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አርስት ከማል የግቢውን ውበትና መሰረተ-ልማት ሲገልጹም 30 ዓመት የተለፋበት ይመስላል በማለት አድንቀው አረንጓዴ ልማት ከተሠራበት በጥቂት ዓመታት ማልማት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ማሳያ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ የጉብኝት ፕሮግራሙ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የሥራ ሂደት ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች ከልዑክ አባላቱ ጋር በተገኙበት ተካሂዷል።ያለህን እምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!


4,680Открыть в Telegram
Injibara University
19 сент., 14:05



5,840Открыть в Telegram
Injibara University
19 сент., 14:05
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከአስተዳደርና ከአውትሶርስ ዘርፍ ሰራተኞች ጋር የ2018 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አደረገ። =============================== መስከረም 9/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበዩኒቨርሲቲው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአስተዳደርና በአውትሶርስ ዘርፍ ላይ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን በመለየት በትኩረት ተገምግሟል።የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) በግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የአስተዳደርና አውትሶርስ ዘርፎች ለዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደት መሳለጥና ዉጤታማ ክንውን ጉልህ ሚና ያላቸው የስራ ክፍሎች መሆናቸውን ጠቅሰው መድረኩ በዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት የሥራ ክንውኖችን በመገምገም በቀጣይ ለ2019 በጀት ዓመት ግብዓት የሚሆኑ ገንቢ ሀሳቦች የሚንፀባረቁበት ከመሆኑ በተጨማሪ ለወደፊት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የመፍትሔ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚረዳ ወሳኝ የውይይት ፕሮግራም መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።የዩኒቨርሲቲው የ2018 እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አቶ ልንገረው አትንኩት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ በዩኒቨርሲቲው የተከናወኑ ዋና ዋና የስራ ክንውኖች፣ በዕቅድ አፈጻጸሙ ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይቶች ተደርገውበታል።ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ባካሄደው የተማሪዎች የእርካታ5,740Открыть в Telegram
Injibara University
18 сент., 17:10



6,740Открыть в Telegram
Injibara University
18 сент., 17:07изменён
በተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ ሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሄደ፡፡ ============================ መስከረም 8/2019 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲበእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሚገኙ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ውጫዊ የሥርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ ወርክሾፕ (External curriculum validation workshop) ተካሂዷል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማጎልበቻ፣ ማረጋገጫ እና ኦዲቲንግ ዳይሬክተር ዓለም አምሳሉ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ሪፎርሞች ማድረጉን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው በእነዚህ ሪፎሞች መሰረት ቫሊዴሽንና አካዳሚክ አክረዲቴሽን እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ዳይሬክተሩ አያይዘውም የስርዓተ ትምህርት ግምገማው ሲካሄድ ከዩኒቨርሲቲው ርዕይ ፣ ተልዕኮ እና የትኩረት ዘርፍ እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀት እና ቴክኖሎጅን ጭምር በማካተት መሆን እንደሚገባቸው ገልፀዋልየእንጅባራ ዪኒቨርሲቲ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ታደለ ሽፈራው (ረ/ፕ) በበኩላቸው ኮሌጁ በ8 የቅድመ ምረቃ እና በ7 ድህረ ምቃ ፕግራሞች ላይ የተግባር ትምህርት፣ ቴክኖሎጅን እና ሀገር በቀል ዕውቀትን በማካተት በውጤት ላይ የተመሰረተ ስርዓተ ትምህርት ማረጋገጫ (outcome Based Curriculum validation) መደረጉን ተናግረዋል፡፡የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ድህር6,240Открыть в Telegram
Injibara University
17 сент., 15:24



7,310Открыть в Telegram
