gram news
Аватар канала ከ ቁርአን አያህ...

ከ ቁርአን አያህ...

@ke_quran_ayah

ይህ channel :- ቁርአን እና የ ቁርአን አያህ ብቻ የሚለቀቁበት page ሲሆን በውስጡም :- 💫 ቁርዓናዊ ምክሮች 💫 የ ቁርዓን ተደቡሮች 💫 የ ቁርአን ጥቅሶች 💫 የ ቁርአን ቲላዋህ 💫 ቁርዓን Quiz እና ጥያቄ እና መልስ ውድድር for any thought @Mohammed_Reshid

ПроектыARРелигия

13,300подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ከ ቁርአን አያህ...

    22 сент., 16:33

    ከ ቁርአን ማዕድفَوَجَدَا عَبْدًا مِّنْ عِبَادِنَا وَآتَيْنَهُ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَعَلَّمْنَهُ مِن لَّدُنَّا عِلْمًاከእኛ ዘንድ የኾነን እዝነት የሰጠነው፣ ከእኛም ዘንድ እውቀትን ያስተማርነው የኾነን ባሪያ (ኸድርን) አገኙት።" (ሱረቱ አል-ካህፍ 18:65)ነቢዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) በምድር ላይ ካሉ ሰዎች ሁሉ እውቀት ያለው እሳቸው ብቻ እንደሆኑ ባሰቡ ጊዜ፣ አላህ ከእሳቸው የበለጠ ሚስጥራዊ እውቀት የተሰጠውን ባሪያ (ኸድርን) ሊያስተዋውቃቸው ረጅም መንገድ አስጓዛቸው። እዚህ ጋር ትልቁ #ሂክማ አላህ እውቀትን ከማንሳቱ በፊት «እዝነትን» (ራህመትን) ማስቀደሙ ነው። እዝነት የሌለው እውቀት ኩራትንና ጥፋትን እንጂ ሰላምን አይወልድም።በህይወትህ ውስጥ አላህ የተለያየ እውቀት፣ ደረጃ፣ ወይም ችሎታ ሊሰጥህ ይችላል። ነገር ግን ዋናው ቁልፍ ያገኘኸውን ጸጋ ለሰዎች በደግነትና በእዝነት መግለጽ መቻልህ ነው። ይበልጥ በተማርክና እውነትን ባወቅክ ቁጥር ለሰዎች የምታሳየው #ራህመትና ትህትና መጨመር አለበት። አላህ እውነተኛውን እውቀት የሚለግሰው ልባቸው በእዝነት ለተሞሉ ባሮቹ ብቻ ነው!🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
  • ከ ቁርአን አያህ...

    22 сент., 16:08

    https://t.me/Binaulzat
    Telegram🌱📖 ራስን በወህይ ብርሃን መገንባት ቁርኣንና ሐዲስን የሕይወታችን መሪ በማድረግ፣ ማንነታችንን የምንቀይርበትና በእውቀት አብረን የምናድግበት ልዩ መድረክ! 📖🌱 📖 የቁርኣን አንቀጾችንና ውብ የነብዩን ሐዲሶች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ እንዴት እንተገብራቸዋለን? 🌱 እስላማዊ ስነ-ምግባርን እንዴት እንላበስ? 🤝 በጋራ የምንማማርበትና አብረን የምንለወጥበት
  • ከ ቁርአን አያህ...

    22 сент., 11:34

    1,010опрос17103Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    22 сент., 05:20изменён

    ​ጥያቄ..? ከ አላህ ﷻ​أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَلَّن نَّجْمَعَ عِظَامَهُ​"ሰው አጥንቶቹን ፍጹም አንሰበስብም ብሎ ያስባልን?" (ሱረቱ አል-ቂያማህ : 3)​ተፈኩር ፦​በወጣትነታችን፣ በጤናችንና በጉልበታችን ተመክተን በኩራት በምድር ላይ ስንመላለስ... ሞትና መሬት ውስጥ የመበስበስ እውነት ከእኛ የራቀ ይመስለናል። አጥንቶቻችን አፈር ሆነው ከቀሩ በኋላ እንደገና እንደምንቀሰቀስ አንደኛችንም ሳናስብ ቀናቶቻችን ይነጉዳሉ።​..ነገር ግን አላህ "ሰው አጥንቶቹን ፍጹም አንሰበስብም ብሎ ያስባልን?" ሲለን፣ ያ አፈር የሆነውን አካላችንን መልሶ እንደሚያቆመውና አላህ ፊት በባዶ እግራችን ቆመን ሂሳብ እንደምናደርግ እያወቅን እንዴት አናስብም? ዛሬ ኩራታችንን ትተን ለዚያ ቀን የሚሆን ስንቅ ሰብስበን ይሆንን?​ያረብ የቂያማ ቀን ከመዋረድን ጠብቀን፣ በምህረትህም ሸፍነን... 🤲🏽​❤️‍🩹 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
    1,2602261Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    20 сент., 14:24изменён

    ስማኝማ Habibi... ዓለም "ሀብታም ሁንና አግባ" ስትልህ፣ የዓለማቱ ጌታ ግን "አግባና ሀብታም አደርግሃለሁ" ይልሃል ፦وَأَنكِحُوا الْأَيْمَىٰ مِنكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِن يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ“ከእናንተም ውስጥ ያላገቡትን፣ ከወንድ ባሪያዎቻችሁና ከሴት ባሪያዎቻችሁም ውስጥ መልካሞቹን አጋቡ። ድሆች ቢሆኑም እንኳ አላህ ከችሮታው ያበለጽጋቸዋል። አላህም (ችሮታው) ሰፊ፣ ሁሉን አዋቂ ነው።” (ሱረቱ አን-ኑር 24:32)🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
    2,3508828135Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    20 сент., 11:17

    2,190опрос17159Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    20 сент., 03:33изменён

    የ እሁድ ምርጡ ስጦታዬ 🎧ይህች ድንቅ ሱራ በዱንያ ፈተና ለዛለች ነፍሳችን ብርታት ትሰጣለች… በዱዓቸው ሰማይን ያንኳኩትን #የነቢያት ታሪክ እያስታወሰች እኛም ተስፋ እንዳንቆርጥ ብርታት ትሆነናለች… ህይወት ለጨዋታ እንዳልተፈጠረችና መመለሻችን አኺራ መሆኑን አስታውሳ ከቸልተኝነት እንድንነቃ ታደርገናለች…..ሱረቱል አንቢያዕ 🫰🏽🤍🍂 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
    2,120файл3373Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    19 сент., 17:41

    አላህ ያንቺን ልብ 💔 ሊሰብረው ሳይሆን...ቁርአን 🤝 ሃዲስ (ክፍል 7)የህይወት ሸክም ከብዶሽ፣ የያዝሽው ሁሉ እጅሽ ላይ እየተበተነብሽ 'አልቻልኩም.. እኔ እኮ ደካማ ሰው ነኝ!' ብለሽ አልቅሰሽ ታውቃለሽ? 😭 በየአቅጣጫው የተዘጋጉብሽ በሮች፣ ከባድ መከራዎች እና የመፍትሔ ማጣት ልብሽን ሲጨናንቁት.. ህይወት ሙሉ በሙሉ የጨለመችብሽ መስሎሽ ሊሆን ይችላል.. 💔ነገር ግን ቆም ብለሽ አስተውዪ! አላህ በሱረቱ አል-ኢንሺራሕ ላይ፣ በጭንቅና መከራ ውስጥ ለምትሰቃየው ለስላሳ ልብሽ የተስፋን ደወል ሲደውልላት እንዲህ ይላል፦فَإِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا ۞ إِنَّ مَعَ الْعُسْرِ يُسْرًا"ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት (እፎይታ) አልለ! ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ!" — (ሱረቱ አል-ኢንሺራሕ፦ 5-6)u see... «ከችግር ጋር» ነው ያለው፤ «ከችግር በኋላ» አላለም! ይኸውም ችግሩ ሲመጣ እፎይታውና መኽረጃው አብሮት ይወርዳል። በአረብኛ ሰዋሰው ህግ "አል-ዑስር" (ችግሩ) የተወሰነ አንድ ሲሆን፣ "ዩስራን" (እፎይታው) ግን ያልተወሰነ ሆኖ ሁለት ጊዜ ተደግሟል! ይህም ማለት፦ «አንድ ችግር በፍጹም ሁለት እፎይታዎችን አያሸንፍም!» ማለት ነው። #ዃሊቅሽ ሁለት እፎይታዎችን ደግሞ ቃል ገብቶልሽ ሳለ፣ በጊዜያዊው ፈተናሽ እንዴት ተስፋ ትቆርጫለሽ?ለመሆኑ በችግርሽ ሰዓት ታግሰሽ ብትጠብቂ፣ በሩህሩሁ ጌታሽ ዘንድ ምን እንደተዘጋጀልሽ ከሃዲስ መንደር ይህን ሹክ ልበልሽ.. 😊አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፣ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ)
    2,23046145Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    19 сент., 14:21

    ከሱረቱል ዩሱፍ በጥቂቱ..وَجَاءُوا عَلَىٰ قَمِيصِهِ بِدَمٍ كَذِبٍ ۚ قَالَ بَلْ سَوَّلَتْ لَكُمْ أَنفُسُكُمْ أَمْرًا ۖ فَصَبْرٌ جَمِيلٌ ۖ"በቀሚሱም ላይ ውሸተኛ ደምን አመጡበት፤ (ያዕቆብ) አለ፡- 'አይደለም ነፍሶቻችሁ ለእናንተ (መጥፎን) ነገር ሸለሙላችሁ፤ ስለዚህ መልካም ትዕግስትን (እታገሳለሁ)...'" (ሱረቱ ዩሱፍ 12:18)ነቢዩ ያዕቆብ (ዐ.ሰ) የሚወዱትን ልጃቸውን የዩሱፍን ደም የተቀባ #ቀሚስ ባዩ ጊዜ ልባቸው በሀዘን ተሰበረ። ነገር ግን ያዩትን ውጫዊ ምስልና የተሰጣቸውን የውሸት ወሬ ተቀብለው ከተስፋ መቁረጥ ይልቅ «ሰብሩን ጀሚል» (ያለ ማማረር የሚደረግ ውብ ትዕግስትን) መረጡ። ይህ የዩሱፍ ቀሚስ መጀመሪያ ላይ የሀዘንና የለቅሶ ምልክት ነበረ፤ በኋላ ግን የዩሱፍን በህይወት መኖር ማበሰሪያ፣ በመጨረሻም የያዕቆብን አይን ማብሪያ ሆነ። ሱብሃን አላህ 🥰በህይወትህ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ያዘጋጁብህ ሴራ፣ ወይም በአይንህ የምታየው አስከፊ ክስተት የመጨረሻው ውድቀትህ ሊመስልህ ይችላል። ነገር ግን አላህ ዛሬ አንተን ያስለቀሰህን ያንን #መከራ (ልክ እንደ ዩሱፍ ቀሚስ) ነገ ትልቅ የምስራችና የደስታህ ሰበብ ሊያደርገው ይችላል። ዛሬ ነገሮች ሙሉ በሙሉ ተስፋ የሚያስቆርጡ ቢመስሉም፣ አንተ ግን ለአላህ ውሳኔ እጅ ሰጥተህ ውብ በሆነው ትዕግስት ልብህን አፅናው!🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
  • ከ ቁርአን አያህ...

    19 сент., 09:58

    2,080опрос251681Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    19 сент., 03:25изменён

    ቲላወቱል ቁርአንየወንጀለኛነት ስሜት ከተሰማህ #የኢማን ብርሃን ልብህ ውስጥ አለ ማለት ነው ምክንያቱም ያ ብርሃን ባይኖር የጥፋተኝነት ስሜት ባልተሰማህ ነበር!!لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ... ♡♡ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ (ዙመር:53)🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    2,280видео40103Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    18 сент., 17:27

    ጁምዓ + ሱረቱል ካህፍ = ተፈኩር ♡وَتَحْسَبُهُمْ أَيْقَاظًا وَهُمْ رُقُودٌ ۚ وَنُقَلِّبُهُمْ ذَاتَ الْيَمِينِ وَذَاتَ الشِّمَالِ ۖ"እነሱም ተኝተው ሳሉ ንቁዎች ናቸው ብለህ ታስባቸዋለህ፤ ወደ ቀኝና ወደ ግራም እናገላብጣቸዋለን..." (ሱረቱ አል-ካህፍ 18:18)በዋሻው ውስጥ ለ309 ዓመታት በከባድ እንቅልፍ ውስጥ የነበሩትን ወጣቶች አላህ ዝም ብሎ አልተዋቸውም። አካላቸው በምድር ላይ እንዳይበሰብስና እንዳይጎዳ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ያገላብጣቸው ነበር። እነሱ ሙሉ በሙሉ እራሳቸውን ስተው በተኙበት፣ ምንም ማድረግ በማይችሉበት በዚያ ጨለማ ዋሻ ውስጥም እንኳ የአላህ ረቂቅ ጥበቃና እንክብካቤ (ሉጥፍ) አልተለያቸውም ነበር።በህይወትህ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ መንቀሳቀስ እስኪያቅትህ ድረስ #ነገሮች ሁሉ ተዘግተውብህ፣ ሙሉ በሙሉ የቆምክና አቅም የሌለህ ሊመስልህ ይችላል። ነገር ግን አንተ በተኛህበት፣ በጨነቀህና መውጫ በጠፋህበት በዚያ ጭንቅ ውስጥ እንኳ አላህ ለአንተ ሲል ነገሮችን እያገላበጠልህ እንደሆነ አትዘንጋ። አንተ የማታየውና የማትሰማው የአላህ ጥበቃ በየሰከንዱ ህይወትህን እየጠበቀልህ ነው። Just chill አህባቢ b/c..ۚكُلَّ يَوْمٍ هُوَ فِي شَأْنٍበየቀኑ ሁሉ እርሱ በሥራ ላይ ነው፡፡(55:29)🍂 ከ ቁርአን አያህ... Share & Join: @Ke_quran_ayah
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
  • ከ ቁርአን አያህ...

    18 сент., 13:25

    ሳምንታዊው የዱዓ ሰዓት 🤲🏽ኢላሂ...! በዱንያ ፈተናዎች የዛሉትን ነፍሶቻችንን በእርጋታና በሰኪና ሙላቸዉ። ወደ አንተ የምናደርገውን ጉዞ አግራልን፤ መጨረሻችንንም ያማረና በኢማን የደመቀ አድርግልን። አላህ ሆይ! ያጣነውን ሁሉ በላቀና በተሻለ ነገር ተካለን፤ ካንተ ውጭ ለማንም እንዳንደገፍ ቀልባችንን ባንተ እምነት ብቻ አቅናው።ጌታችን ሆይ... በራህመትህ ጥላ ስር አስጠልለን፤ ወንጀሎቻችንን በሙሉ ማርልን፤ ካንተ እዝነትና እቅፍ የሚገፋንን ማንኛውንም መንገድ ከፊታችን አርቅልን።አሚን 🤲🏽🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    2,39058511Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    18 сент., 10:25

    2,300опрос23153Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    18 сент., 05:31изменён

    የዛሬው የሂይወታችን ሂሳብ፦〰️ ​ፌስቡክ / ቲክቶክ / ቴሌግራም ላይ ያሳለፍነው ጊዜ፦ 2 ሰዓት 〰️​ ለጭንቀት፣ ለቁጣና ለብስጭት ያወጣነው ጊዜ፦ 15 ደቂቃ 〰️ ​በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ለማውረድ የሰጠነው ጊዜ፦ ???​አሁኑኑ ሂሳቡን እናስተካክል... 10 ሰከንድ ወስደን 3 ጊዜ ሰለዋት እናውርድ።​ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
  • ከ ቁርአን አያህ...

    17 сент., 14:35изменён

    ♡♡إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ"እኛ ማንኛውንም ነገር በልክ (በልክነቱ) ፈጠርነው።" (አል-ቀመር - 49)የእያንዳንዱ ህመምህ ማብቂያ፣ የእያንዳንዱ ዱዓህ ምላሽ ልክ እንደ ሰማይ ከዋክብት በስፍራውና በሰዓቱ ተለክቶ ተቀምጧል። አትቸኩል፣ አትጨነቅ፤ ሰዓቱ ሲደርስ ማንም ሊያስቆመው አይችልም።ያኔ ነገሮች ሁሉ ባሰብከው መልኩ ተስተካክለው፣ የህይወትህ ገጽታ ሲያምር..."ኢላሂ! ለካስ እኔ የቸኮልኩት ቀጠሮህን ባለማወቅ ነበር፤ ያንተ ምርጫ ግን ምንኛ ያምራል!" ብለህ በደስታ የምትረካበት ቀን ይመጣል። 🫰🏽🤍 Inshallah
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
  • ከ ቁርአን አያህ...

    17 сент., 10:22

    2,340опрос23876Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    17 сент., 05:01

    ،يَا زَكَرِيَّا إِنَّا نُبَشِّرُكَ بِغُلَامٍ اسْمُهُ يَحْيَىٰ لَمْ نَجْعَل لَّهُ مِن قَبْلُ سَمِيًّا{ سُورَةَ مَرْيَمَ } آيَة ٧🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    2,360голосовое36Открыть в Telegram
  • ከ ቁርአን አያህ...

    16 сент., 17:48

    ሱረቱል ሙልክ (ተፈኩር - ክፍል 12) ​ባለፈው ክፍላችን በሰው፣ በስልጣንና በኔትወርክ ተማምነን የምንገነባውን የሀሰት መተማመን Illusion ማፍረስ እንዳለብን አይተናል። ዛሬ ደግሞ አላህ በፊታችን ላይ አንድ እጅግ የሚረብሽ፣ ነገር ግን ልብን ሰርስሮ የሚገባ ትልቅ ጥያቄን ይጠይቀናል። የሁለት አይነት ተጓዦችን አካሄድ እና እሱ የሰጠንን የውስጥ መሳሪያዎች Sensors እንድንገመግም guide ያረገናል፦
  • ከ ቁርአን አያህ...

    16 сент., 13:36изменён

    ..أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ«እኔን መከራ አገኘኝ፤ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ…» (ሱረቱ አል-አንቢያእ፣ 21:83)ኡኽታዬ.. ህይወት ደጋግማ ስትሰብርሽና በሰዎች ምክንያት ልብሽ ሲደማ፣ ስብራትሽን ይዘሽ ወደ አዛኞች ሁሉ አዛኝ ወደሆነው ጌታሽ ሮጠሽ ተጠጊ። #ነቢዩላህ አዩብ (ዐ.ሰ) በበሽታና በችግር ለዓመታት ከተፈተኑ በኋላ ይሄንን አያህ ተጠቅመው ነበር አላህን የለመኑት። አላህም ህመማቸውን ወደ ጤና፣ ጭንቀታቸውን ወደ ደስታ ቀየረው። አንቺም ልብሽ በሃዘን ሲደቅ፣ የሰማዩ ጌታ ከ እናትሽ በላይ እንደሚያዝንልሽና እንደሚራራልሽ አስታውሽ፤ ሲጠግንሽም ደግሞ ዳግም እንዳትሰበሪ አርግቶ ነው። ♡♡🍂 ከ ቁርአን አያህ...
    Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...Иллюстрация к посту канала ከ ቁርአን አያህ...
    2,54046632Открыть в Telegram