gram news
Аватар канала ከገጠምኩ

ከገጠምኩ

@kegetemku_leyesus

ወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle

ПроектыENРелигия

24,947подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ከገጠምኩ

    21 сент., 18:58

    переслано из @grow_to_god

    📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹየምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
  • ከገጠምኩ

    18 сент., 19:11

    переслано из @jesusfollowing

    kingdom sound የዝማሬ ህብረት የተዘመሩ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን button ተጭነው ይቀላቀሉ
  • ከገጠምኩ

    16 сент., 19:45

    የማንሰራራት አመት-------ሰላም የአባቴ ብሩካን እንዴት ከረማቹ ? በብዙ ተጠፋፋን አይደልጌታ እረድቶን ዛሬ ተገናኝተናል ከእንግዲህ አልጠፋምከረፈደም ቢሆን ልበላቹ ለኢዲሱ አመት 2019 እንኳን አደረሳቹሰሞኑ በውስጤ የከበደ ሀሳብ ላካፍላቹ" ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።" (የሐዋርያት ሥራ 15:16-17)ኢሄ አመት ለእኔ የማንሰራራት አመት ይሆናል ብዬ ጀምርያለውማንሰራራት ማለት ሙሉ የነበረ ነገር በተለያየ ምክንያት ጎድሎወደ ሙሉነቱ ሲመለስ የከሰረ መልሶ ትርፋማ ሲሆን የታመመ ወደ ጤንነት ሲመለስ እና መሰል ጉዳዮች ማንሰራራት ማለት እንችላለን
    1,3101461Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    16 сент., 03:22

    መዝሙረ ዳዊት 102:25-27 (AMH) •••••••••• ²⁵ አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። ²⁶ እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል፤ ²⁷ አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
  • ከገጠምኩ

    20 авг., 12:04

    ጣፍጥልኝ ዮሴፍ አስቻለው -New Albumሰምቼ ያልጠገብኩት መዝሙር ▷ ▸@Kegetemku_leyesus◂ ◁ ▷ @kegetemku_leyesus◁ △Join Us△
    6,720файл148Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    18 авг., 17:14изменён

    ፍቅር ያዘኝ ፍቅር ያዘኝ ከእየሱሴ መዳኛ ሁኗል ለነፍሴ የወደደበት መዉደድ ፍቅሩን ይገልፃል ያፈሰሰው ደሙ ከኃጢያት ያነጻናል ከሱ ነው በፍቅር መያዜ ነፍስ አስካይቀርልኝ በመስቀል ሙቶ ነው መዉደዱን ያሳየኝ ኧረ ስለሱማ መግለጫ ቃላቶች ያጥሩኛል የእዉነት የሚያፈቅር ከወዴት ይገኛል ፍቅር ታየ ባደባባይ እርቃን ዋለ ለኔ ሊታይ ከ አባቱ ሊያስታርቀኝ ክብሩን ጥሎ ሂወት ሰጠኝ ገባሁ ሰማይ ከአብ ፊት ያለ ከልካይ እኔ ስቆም የሱ ደም ነው ለኔ ሚታይ አብ አቀፈኝ ወራሽ ሆንኩኝ የመንግስቱ ፅድቄ ሆነኝ ጌታ አየሱስ የናዝሬቱ ለዚህ እኮ ነው መሽነፌ ለሱ ፍቅር ተገዛሁኝ ከሱ ዉጪ ሁሉም ይቅር
    5,96024118Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    16 авг., 17:24

    ቶሎ ናአባ ኢየሱስ የኔ ሙሽራ በሰማይ ያለኸው ቤቴን ልትሰራ እመጣለሁ ብለህ ያኔ የነገርከኝ በክብር ታጅበህ እኔን ልትወስደኝ መቼ ይሆን ጌታ ቀኑ የምትመጣበት ፊትለፊት ካንተ ጋር ምንተያይበት. ትዝ ይልሃል አባ ያኔ ቃል ስትገባ የሐዋርያቱ ነፍስ በሃዘን ተከባ ወላጅ እንደሌላቸው አልተዋችሁም ብለህ ስትነግራቸው እንደምትመጣ ዳግም የመምጣትህን ዜና ለዓለም እያወሩ አመታትን አልፈው ዘመን ተሻገሩ. ይኸው በኔም ዘመን ዜናው ይነገራል የመምጣትህ ጉዳይ በብዙ ይወራል በሰሜን በደቡብ በምዕራብ በምስራቅ ሕፃን ወጣቱ ከትንሽ እስከ ትልቅ በሁሉም አቅጣጫ ስላንተ ይሰማል የመምጣትህ ተስፋ በልባችን ገብቷል.
    4,9603365Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    14 авг., 19:02

    ልብ ስጠኝልብ ስጠኝ አባ አንተን የሚፈራ በሄደበት ሁሉ ስምህን የሚጠራ በቃልህ ተመክሮ ለፈቃድህ የሚኖር አንተን ለማስደሰት ዘወትር የሚጥር ልብ ስጠኝ አንተ የምትወደውን ልትሰራ ስትመጣ ላንተ ሚገኘውን. ሰው ሁሉ ፈቃዱን በሚፈፅምበት ካንተ ሃሳብ ርቆ ጠፍቶ በሄደበት በፈጠርከው ፍጥረት እጅግ ተፀፅተህ ልታጠፋ ስትል ሁሉንም ፈፅመህ ላንተ እንደተገኘ ኖህ ተለይቶ ራሱን ለፈቃድህ ሃሳብ አስገዝቶ ልብ ስጠኝ ጌታ አንተ ምታርፍበት ከሰማይ ስታየው ምትደሰትበት. ልብ ስጠኝ ልብ ስጠኝ አባ እንደ ዳዊት ያለ ሙሉ ማንነቱን አንተ ላይ የጣለ ፈቃድ እና ሃሳቡን ቃልህ ውስጥ ሰውሮ
    4,5801891Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    14 авг., 07:00изменён

    React And Share @Kegetemku_leyesus
    3,490видео226Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    4 авг., 06:11

    ብርቄ ነህብርቄ ነህ ሁሌ የማለምድህ የኔ ነህም ብዬ የማላቃልልህ በኔ ዘንድ ዋጋህ እጅግ ውድ የሆነ በቤት በጓዳዬ ደምቆ የገነነ ኢየሱሴ ለኔ ውዱ ነገሬ ነህ ውድ ከተባለው ሁሉ ትለያለህ. የነፍሴ ረሃብ የሁል ጊዜ ጥማት የአይኖቼ ማረፊያ የየዕለት ጉጉት አውርቼ አውርቼ ዘውትር የማልጠግብህ መሽቶ እስኪነጋ ዘውትር ምናፍቅህ የቅርብ ቤተኛ የቤቴ እንግዳ ምንም የማልደብቅህ የሚስጥሬ ጓዳ የዘላለም ምንጬ የመኖር ዋስትና ኢየሱስ አንተ ነህ ለኔ የህይወት መና. ፊትህን ፈልጌ መቼም የማልጠግብህ አብሬህ እየዋልኩ ፍፁም የማለምድህ ማለዳ ማለዳ አዲስ ምትሆንብኝ በዕድሜ ብዛት ከቶ ማትቀልብኝ
    5,6404499Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    3 авг., 18:35изменён

    .....ከወዴት ወድቀሻልዝና ክብር ሞልቶ በረከት በጓዳ ዝናሽ ከፍፍ ብሏል በቤትሽ ጓዳችግር አይተሰብም በስጋም በነብስ ንግድሽም ደርቷል ሄድ መለስለአምላክ ያለሽ ጽናት ሀሰትን መጥላትሽ ብርቱ እምነት ትጋት ጥንካሬሽልቤን አሸነፈው ትዕግስት ሚዛናዊነት በሁሉ ተወዳጅ ማይነጥፍ እውነትግናግና ኤፌሶን ማታሽ ተበላሸ ከወዴት ወድቀሻል ያ ሀያል ፍቅርሽን የት ጥለሻልወደር አልባ ነበር መያያዝሽ መሰረቱ
    Telegramከገጠምኩወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle
  • ከገጠምኩ

    1 авг., 13:27

    ..............ዘጸአት.......በራስ ቀለም ኑሮ ተራራውን መዞር የዘውትር ተለምዶ ባለንበት መኖርመሄድን ስንሻ ቆመን ተራምደናል ሩቅ እያሰብን ከሰፈር ቀርተናልመጠራታችን ነበር ለሰማይ ቤት የጠፋን ሳለን የተሰጠን ህይወትየመስቀሉን ጣር የአብ ማስታወሻ የደሙ ውጤት ከሰማይ መድረሻሆኖ ኖሮ እያለ ሆነን ያልተገኘን በግላችን ድንኳን ታስረን ተቀምጠንዘመን እንዳያልፍ ከዘመኑ ጋራ ኋላ እንዳይቆጨን ጨለማው ሳይበራ
    Telegramከገጠምኩወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle
    3,920442Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    29 июл., 13:41

    በተንጣለው ግቢ ላይ ከተሰራው አራት ደረጃ ፎቅ ኤልያስ ጥቁር ቆዳ ጫማ ጥቁር ሱፍ በነጭ ሸሚዝ ለብሶ ዘንጦ ግቢው ውስጥ ወደቆመችው ቅንጡ መኪና እየሄደ ነው አባቱም በርይሁን ሁለተኛ ፎቅ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ልጁን ቁልቁል እየተመለከተ በመገረም እያየው ፈገግ አለኤልያስ ምንም እንኳን የ 22 ዓመት ወጣት ቢሆንም በአባቱ ድርጅትም በጣም ወሳኝ ሚባል ስራ የሚሰራ ጠቃሚ ሰው ነው።አሁንም እየሄደ ያለው ከተለያየ ሀገር የመጡ ከድርጅታቸው ጋር ፓርትነር ለመሆን የመጡ እንግዶች ለማናገር ነው።አባቱም ከስር ከስራቸው እያስከተሉ ሁሉንም ነገር አስተምረውታል ከስራቸው የማይጠፋው ትንሹ ልጃቸው ዛሬ አድጎ ድርጅቱን ወክሎ ከውጭ ሀገር ከመጡ እንግዶች ለመወያየት እንደሚሄድ ሲያስቡ ፈገግ አሉኤልያስ ወደ ቅንጡ መኪናው ገብቶ መኪናው ሲያስነሳ ዘበኛው ትልቁን የግቢ በር ከፈተለት ኤልያስም መኪናው እየነዳ ከግቢ ወጣ።ከግቢው ወጥቶ ዋናው መንገድ ላይ እንደገባ ከአስፖልቱ ጎን ባለው ሜዳ ላይ ኳስ ተጫውተው ደክሟቸው ከመሬት ጭቃ እያነሱ አንዳቸው አንዳቸው ሰውነት ላይ ሲመርጉ አየ።ወዲያው የልጅነት ትዝታው በፊቱ ውልብ አለበትኤልያስ የሀብታም ልጅ ስለሆነ በልጅነቱ እንደማንኛውም ህፃን ጎርፍ እየተራጨ እና መሬት እየፈጨ አላደገም ይልቁንም እንደዚህ በሚያደርጉት ከፎቅ ላይ ሆኖ ከግቢ ውጪ በሚጫወቱት እየቀና እንጂ ።እርሱ ውድ ውድ የሚባሉ አሻንጉሊት መጫወቻ ተገዝቶለት በእነርሱ እየተጫወተ አለፍ ሲል የተለያየ ፓርክ መናፈሻ እየሄደ እንዲሁ እንደርሱ ካሉ የሀብታም ልጆች ከወላጆቹ ጋር ውድ በሆኑ ሆቴሎች
    5,0401752Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    28 июл., 13:13

    ትንቢተ ኢሳይያስ 41:8-10,13 (AMH) •••••••••• ⁸ ባሪያዬ እስራኤል፥ የመረጥሁህ ያዕቆብ፥ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፥ ⁹ አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና። አንተ ባሪያዬ ነህ፥ መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ፥ ¹⁰ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ። ........... ¹³ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር። አትፍራ፥ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
  • ከገጠምኩ

    20 июл., 14:20изменён

    .....መስታወትከመድረኩ በስተጀርባ ካለው ክፍል የሚወጣው ድምጽ እየረበሸኝ መስበክ አልቻልኩም ነበር፣ ወደ ኋላ ሁለት እርምጃዎች ተራምጄ ከመጋረጃው በስተጀርባ ያለውን መስኮት ልዘጋው ፈለኩ ግን አልቻልኩምድራሙ፣ኪውቦርዱ እና ሌሎች የሳውንድ ሲስተም እቃዎች የምስባኩን ጀርባ ማንም እንዳይተላለፍ ዘግተውታልእንደምንም ብዬ ስብከቴን ጨረስኩና ወደ ቤት አመራሁ።///////___///ማታ ብቸኝነቱ ሲያስጨንቀኝ የቀን ውሎዬን ለመጻፍ በዘረጋሁት ደብተር ላይ የመጨረሻው ሀረግ ...<< መስታወት >>የሚል ነበርመስታወት የላይኛውን ገጽታ ባለንበት ሁኔታ ሆኖ ለራሳችን ያስተጋባልናል፣ስንስቅ ይስቃል፣እያለቀስን ብንመለከተው መልሶ ያለቅስብናል ፣ እያወራንም ብናየው ንግግራችንን አንድ በአንድ በምላሱና በከናፍሮቹ እንቅስቃሴ የሚደግምልንን ሰው ያሳየናል ግንመስታወቱን ዞር ስናረግ እውነተኛውን ኑሮ እንቀጥለዋለን\\\\\\\|\\\\\\\ወደ ቤት ስገባ የሚበላ የለም የሚቀመስ ነገር የለም ፣ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን በሰው ፊት የደላ የሞላው አገልጋይ
    Telegramከገጠምኩወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle
    6,080141Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    18 июл., 10:19

    ቀኑን አስታውሰዋለሁ ጀርባዬን ሰጥቼ በቃ አሁን አድገለያለሁ ያልኩበትንየሚገርመው ግን ምንም እንኳን በትምህርቴ ከፍተኛ ደረጃ ብይዝም፣ራሴን የማስተዳደር አቅም ያለኝ ቢመስለኝም ፣ለወላጆቼ አሁንም ልጅ ነኝያደኩ የመሰለኝ ከእኔ እንጂ ለአባቴ አልነበረምእና አንድ ቀን አባቴን ጠየኩ (( በእውነቱ ከሆነ ይሄ ጥያቄ መነሳት የነበረበት ጊዜው አልነበረም))አባቴ ፣በቃ እኔ ከቤት መውጣት እፈልጋለሁ ፣እንደምታየኝ አሁን አድጌያለሁ ፣ክፉና ደጉን ለይቼ አውቄያለሁ ስለዚህ መርቀህ ሸኘኝ አልኩትአባቴ በጣም አዘነ ስለኔ በጣም ተጨነቀእኔም በየቀኑ ማደጌን እየነገርኩ ራሴን ችዬ መኖር እንደምችል በመናገር ነዘነዝኩትበስተመጨረሻም አባቴ ፈቀደልኝ በጣም ደስ አለኝ ፣ ከዚህ በኋላ የት ገባህ የት ወጣህ፣ጓደኞችህ ማናቸው ውሎህ አዳርህ የት ነው የሚል በሌለበት በራራራሴ አለም ከራሴ ጋር በነጻነትና በተድላ የምኖርበትን ጣፋጭ ጊዜያትን እያሰብኩ ከቤት ወጣሁለጥቂት ቀናት ልቤ እንዳሻኝ ሆንኩ ፣ኋላ ቀስ በቀስ የከበቡኝ ተበተኑ፣አይዞህ እኛ አለንልህ ያሉት ሁሉ ተቀየሩብኝ የያዝኩት ሀብቴ ከእጄ አለቀ
    Telegramከገጠምኩወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle
    5,310138Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    26 июн., 19:57

    የናፈከኝ እለትየናፈከኝ እለት የምድሩ ጫጫታ፣ ዝባዝንኬ ወሬ ከሰዎች ጨዋታ። ጭራሽ ትዝ አይለኝም፣ ልቤ ሰማይ እንጅ ምድር አይገኝም። የናፈከኝ እለት አንተን ብቻ ሳስብ፣ በሮቼን ስዘጋ በሰበባ ሰበብ። ናፍቆቴ ጉጉቴ ፍቅሬ የኔ ጌታ፣ በሚገጥመኝ ችግር ቅንጣት አይረታ። እንዲ ነው ሚያደርገኝ ፊቴ እንኳን ያበራል አንተጋ እንደዋልኩኝ ፀዳልህ ይናገራል ይሄነው አምላኬ እኔን ሚናፍቀኝ ለልጁ ሳይራራ ነው እኮ የወደደኝ እና የኔ ጌታ እና የኔ ፍቅር፣ ናፍቆት ናፍቆት ብዬ ባፌ ብቻ እንዳልቀር። ልቤን አንተ ያዘው፣ አንተው ጋር ይቀመጥ ሌባ በማይሰርቀው፣ ረቡኒዬ ሆይ እኔ እናፍቅሃለው።
    8,100231616Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    25 июн., 15:20

    የምናብ ፅሁፍ#ነግህ_መቼ_ነውዮስ እና ቤኪ የልብ ወዳጆች ናቸው። ሰው ሁሉ እነርሱ ሲያይ መደነቅ ይይዘዋል። አይደለም ጓደኛ በወንድማማቾች እንኳ እንደዚህ ሚዋደዱ ለመኖራቸው እንጃ ይላሉ። ሌሎች የስጋ ዘመዶች እንደሆኑ ያወራሉ።ሁለቱም በእውነተኛ ፍቅር ይዋደዳሉ ዮስ ስልኩ ይጠራል አንስቶ ቤኪ ይላል ወዬ ነፍስ አለው። አትመጣም እንዴ? የተለመደ ቦታ እንገናኝ ቻው ተባብለው ስልኩ ተዘጋ።ዮስ ዛሬም አትነግረውም አታወራለትም ይለዋል ውስጡ?ቆይ እስከዛሬ አብረን እየኖርን ያላነሳሁት ዛሬ ምን ብዬ ነው ወንጌል ኢየሱስ ብዬ ማወራው?ዛሬ ቀኑ ስለሆነ።አይ ነገ እነግረዋለው ስለ እምነት ጉዳይ ክርክር አንስቼበት በዚያው እመሰርለታለው
    6,980208653Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    24 июн., 19:09изменён

    ያልተገደበ ደስታ ➡️ መንፈስ ቅዱስ-------የህይወት ምንጭ ነህ፣ከውስጥ ምትፈልቅ ከጉልበት ከወገብ አልፈህ ምታጥለቀልቅ ከዓለም ያይደለህ፣ምትፈልቅ ከጓዳ ቁስልን ምትሽር፣ፈውስ ለተጎዳ ኢየሱስ ገላጭ፣ድንቅ አስተማሪ የአማኞች ወዳጅ፣አብሮ ነዋሪ በክብርህ መተህ፣እኛን ስትነካ ምንጭ ሆነህ ፈልቀህ፣ጠጥተን ስንረካ በመገኘትህ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ስታስደንቀን ያልተገደበ ደስታ ምንለው፣ምንቦርቅበት ምድር ሲጠበን የደስታው ገደብ፣ ሚነካው ጣራ በጌታው ሳቅ ነው፣ሚስቀው ባርያ አዎ ፊትህ አይተን ነው፣ፈገግ ምንለው ካንተ ስንውል ነው፣ምንቦርቀው ሀይል ምናገኘው፣ምንሆነው ጀግና በሌላ አይደለም፣በአንተ ህልውና
    5,06014631Открыть в Telegram
  • ከገጠምኩ

    23 июн., 15:14изменён

    ....ታውቅበታለህመስራትን ስትፈልግ በደካማው አፈር ሰበብን ፈልገህ ስትገባ ሰፈርበሰው መሰል መልአክ ነብይ ትልክና ከመበለቷ ቤት ዘልቀህ ትገባናየባሪያህን ድካም የኖረውን ዘመን በክህነት በታማኝ ሲያገለግል አንተንዘመኑን ሲጨርስ ሲሰበሰብ ሞቶ ያልከፈለው እዳ ለሚስቲቱ ትቶእንዳለ አውቀኸው በቤቱ ጓዳ ታውቅበታለህ አንተ ማገዝ የተጎዳከሰማይ ማድጋ ዘንበል ሲል በቃልህ ዱቄቱን ስታዘው ከላይ ሲፈስልህ
    Telegramከገጠምኩወደ ቻናላችን እንኳን በደህና መጣችሁ በዚህ ቻናል ኢየሱስን ከፍ የሚያደርጉ ግጥሞች ፅሁፎች መዝሙሮችና ላይቭ ፕሮግራሞች ይኖሩናል አብረውን ይቆዩ ሀሳብ አስተያየት ካለ በዚህ ያናግሩን @ErmiyAs_kifle
    5,0509652Открыть в Telegram
Скачать ряд в CSV
Бот обратной связи для своего канала — бесплатно

Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.

Как это работает →
Создать бота