Последние посты

ኩራዝ
28 янв., 16:38
переслано из @enzira_mezmur
ጥር ፳፩ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት (አስተርእዮ ማርያም)”አስተርእዮ ማርያም“አስተርእዮ ማለት መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት(የታየበት) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል።ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ” የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉቅዱስ ዳዊት “ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር “ መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን «ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል» በማለት ገልጾታል።በቀሲስ
ኩራዝ
28 янв., 16:22
ማንም ሀዘንህን አይወስድም ስለዚህ🤨 ማንም ደስታህን እንዲወስድ አትፍቀድ
ኩራዝ
28 янв., 10:58
#መጣላት አለና: ሚስጥር አትናገር። #መታረቅ አለና፡ ክፉም አትናገር። በዚህ አለም ኑሮ የሚሻለው ነገር ብዙ ማዳመጥ ነው!! ብዙ ከመናገር 🤫
ኩራዝ
28 янв., 10:10
አስተርዮ ማርያም➯በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡➯የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡➯እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡➯ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡➯ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ኩራዝ
28 янв., 09:38
😇 ዛሬ የቅዱስ አባታችን አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 84ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው ነው።ሰው በጠፋበት ሰዓት አጽናኝ አባት ሆነው የተገኙ ስጦታችን ነዎት!ቅዱስነቶ እድሜና ጤና ይስጥዎት 🙏መልካም ልደት!!
ኩራዝ
28 янв., 08:57изменён
ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል። መጽሐፈ ሲራክ 31:11ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ ከሁለቱ ይልቅ በጎ ምክር ደስ ታሰኛለች። መጽሐፈ ሲራክ 40:25
ኩራዝ
28 янв., 08:54изменён
መሳ 16፥ 19 "በጉልበትዋም ላይ አስተኛችው ፤ አንድ ሰውም ጠርታ የራስ ጠጉሩን ሰባት ጉንጉን አስላጨችው..."ፍትወት (Lust) የራሱ ድርሻ ቢኖረውም ፣ የሳምሶን ዋነኛ እና ጥልቅ ችግር የማይመጥኑትን እና ዋጋ የማይሰጡትን ሰዎች መምረጡና አብዝቶ እንዲቀርቡት መፍቀዱ ነበር። ለምሳሌ ያህል ፦👇📍የቲምናዋ ሚስቱ እንቆቅልሹን ከነገራት በኋላ አታለለችው ፣ አሳልፋም ሰጠችው።📍ደሊላ ሦስት ጊዜ አሳልፋ ሰጠችው ፤ እሱ ግን ወደ እርስዋ መመለሱን ቀጠለ።ወገኖቼ በዛ ወሳኝ ሰዓት እሷ ብቻዋን አልነበረችም ፀጉሩን እንዲቆርጥላት አንድ ሰው ጠራች። በተመረጡ ሰዎች ላይ የሚደረግ ሴራ ብዙ ጊዜ ለብቻ አይከናወንም። ብዙውን ጊዜ ለስልጣን ፣ ለሴራ እና ለሙስና በተንኮል አብረው የሚሰሩ ተባባሪዎች አሉ።የእኔ ተወዳጆች የሰዎችን ተፈጥሮ መረዳት ጠቢብን ፣ ሞኝን እና ክፉን ለመለየት ይረዳል። ቃላት የሰውን እውነተኛ ማንነት እና እሴት እምብዛም አይገልጡም ፤ ተግባር ግን ይናገራል።ሳምሶን የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን (Red flags) ችላ በማለቱ ፣ ተባብረው ሊያጠፉት የተዘጋጁ ጠላቶቹን ወደ ህይወቱ በጣም አስጠጋ።ወከዚህ ታሪክ በመማር ማን ወደ ህይወታችሁ እንደሚገባ በጥንቃቄ ምረጡ (Guard your access)። ክህደት ብዙውን ጊዜ የሚመጣው ከተባባሪዎች ጋር ነው።መጥራት እስኪችሉ ድረስ አታቅርባቸው።
ኩራዝ
28 янв., 08:08

ኩራዝ
27 янв., 17:37
ለክብር አትጓጓ ለከንቱም ውዳሴ ፤ በከንቱ ውዳሴ አይገኙም ሥላሴ ።ኩራዝ
ኩራዝ
27 янв., 13:00
ሰዎች ሳቅህን ያያሉ እግዚአብሔር ደግሞ በልብህ የያዝከውን ህመምህን ያያል🥺
ኩራዝ
27 янв., 12:04
ማሸነፍ የምትችለዉ አእምሮህ ከስሜትህ ሲበልጥ ብቻ ነው
ኩራዝ
27 янв., 11:50
የመማር ጥቅሙ ከመሳሳት መመለስ እንጂ መርካት አይደለምቅዱስ ጀሮም
ኩራዝ
27 янв., 11:50
"በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ ለዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ "።ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ
ኩራዝ
27 янв., 11:50изменён
ዝምታ 🍃🍃🍃~► አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ከቃላት ይልቅ ውጤታማ፣ ይበልጥ ተገቢና እጅግ ጠቃሚም ነው። ወይም ደግሞ ቢያንስ - ቢያንስ ተናግሮ ከሚመጣ ጉዳት ይልቅ ሳይናገሩ የሚመጣ ጉዳት ይሻላል። በዝምታ ውስጥ ጥበብና ጥንካሬ ከመኖራቸው በተጨማሪ ክብርና ሞገስም አሉ፡፡~► አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ይናገር ዘንድ እኛ ዝም እንላለን፣እኛ ልንናገር ከምንወደው ከማንኛውም ነገር የበለጠ የእግዚአብሔር ቃል እጅግ ኃያል ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን አስመልክቶ የተናገረው ቃል ምንኛ ድንቅ ነው!«እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤እናንተም ዝም ትላላችሁ. . » 📖ዘጸ 14፥14።~► መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ፊት በዝምታ ቆይቷል። በዚያን ጊዜ እርሱ አፉን አልከፈተም ራሱንም አልተከላከለም። ጌታ ዝምታን በመረጠ ጊዜ ጲላጦስ «ይህን ጻድቅ ሰው የምወነጅልበት ምንም ዓይነት ምክንያት አላገኘሁም» በማለት ተናግሮ ነበር፡፡~► ዝምታ ትርፍ አስገኚ ይሁን እንጂ የተወሰነ መመሪያ አይደለም፡፡ ወርቃማው መመሪያ፡- ሰው ሊናገር የሚገባው በትክክለኛው ጊዜ መሆኑና ዝም ማለት የሚገባውም ዝም ማለት በሚገባው ትክክለኛ ጊዜ መሆኑ ነው።~► ሰው ዝም ሲል ልቡ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገር ስለሚፈቅድ በእርሱ ፈንታ ጌታው እንዲናገር ይጠይቃል ማለት ነው፡፡# አቡነ ሽኖዳ ሣልሳዊ
ኩራዝ
27 янв., 11:50
በዓለም ያለው እውቀት መልካምና ክፉውን ለይተን የሚያደርግ ቢሆንም አቅም ሊሰጠን አይችልም ሁል ጊዜ በመልካም መንገድ ላይ እንድትጓዙ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ ብልህና አዋቂ የሚባለውም ይህንን የሚያደርግ ሰው ነው!አባ እንጦንስ
ኩራዝ
27 янв., 11:50изменён
ጌታ ሆይ እኔ ባሪያህን የጠራህበት ቅዱስ አጠራር እንዴት ያለ ይሆን? ስንቴ ጠርተኸኝ እንዳልሰማ ጥዬ ሔጄ ይሆን? የአንተን ጥሪ ገፍቼ ለዓለም ጥሪ ጉዋጉቼ ስንቴ ሔጄ ይሆን? "አብዝቼ ብጠራቸው አጥብቀው ከፊቴ ራቁ" ካልካቸው መካከል እሆን ይሆን?እባክህን ባልሰማህም ጥራኝ : ባልመጣም ጥራኝ : ጴጥሮስ በባሕር ላይ እንደለመነህ "ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ" : እንደ አልዓዛር "ውጣ" ብለህ በቅዱስ አጠራር ጥራኝ:: እንደ ማቴዎስ ከቀራጭነት ገበታዬ ላይ : እንደ ዘኬዎስ ከዛፍ ላይ : እንደ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በሰረገላዬ ላይ ብቻ ባገኘኸኝ ቦታ ጥራኝ::ሙት በሚቀሰቅስ ማዕበል በሚገሥፅ ድምፅህ ባልሰማህም ጥራኝ : ጆሮዬ አልሰማ ካለህ እንደ ማልኮስ ጆሮ ሠጥተህ አንተን ብቻ በሚሠሙ ጆሮዎች ፈውሰኝና ጥራኝ:: ዓይኔ ዓላይ ካለህ ከአፈር በምራቅህ ለውሰህ እያየሁ እንድመጣ አድርገህም ቢሆን ጥራኝ:: አሁን በቅዱስ አጠራርህ ስትጠራኝ ካልሰማሁህ በኁዋላ ልትፈርድ ስትመጣ "እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ" የሚለው ቅዱስ አጠራርህንም ሳልሰማ መቅረቴ አይደል? አሁን ጥሪህን ካልሰማሁ በኁዋላ ቃለ ሕይወትን አልሰማምና እንደ ሥራዬ ሳይሆን እንደ አንተ አሳብና ጸጋ መጠን ጥራኝ!"ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም"
ኩራዝ
27 янв., 11:50
ለስንፍናህ ሁሉ ምክኒያት አትስጥ መልካሙን ነገር ዛሬ ስራው ክፉውን ነገር ዛሬ ተናዘዘው እያንዳንዱ የጊዜ ሽርፍራፊ የገነትና የሲኦል ሰው ለመሆን ዋጋ እንዳለው እወቅ#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን ╔═F══════════A══╗ 💚 ኩራዝ የእዉቀት አድማስ 💚 ╚═F══════════A══╝ ♡ ㅤ⌲ ˡᶦᵏᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ኩራዝ
27 янв., 11:50
"ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነጻ ያወጣውና ወደ ቀድሞው ቦታ ይመልሰው ዘንድ ወደደ።" (የሰኞ ውዳሴ ማርያም)
ኩራዝ
27 янв., 11:50изменён
+++ የጽሙና ጊዜ አለህ? +++ ❖ ❖የቆርቆሮና የብረት ጩኸት ጋጋታ ባለበት ውብና ለስላሳ የሆነውን የዋሽንት ድምጽ መስማት የሚቻለው ማን ነው? ሁከትና ረብሻ በሚነግስበት፣ የማይቋረጥ ግፊያና አለመረጋጋት ባለበት የሰዎች ግርግር ውስጥ ሆነህ እንዴት የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ልትሰማ ትችላለህ? የእግዚአብሔርን ድምጽ በአውሎ ነፋስ ፋጨት፣ በምድር መናወጥ፣ በሚያስገመግም የእሳት ድምጽ ውስጥ አታገኘውም። እርሱ የሚናገረው ከእነዚህ ሁሉ በኋላ በሚሆነው "ትንሽ የዝምታ" ጊዜ ነው።(1ኛ ነገ 19፥12)ልክ የመድኃታችንን የልብሱን ጫፍ በስውር ነክታ ከቁስሏ እንደ ተፈወሰችው ሴት፣ አንተም የነፍስህን ቁስል ለማድረቅ በመቅደሱ የሞላውን የጌታን የልብሱን ዘርፍ በምሥጢር የምትዳስስበት የብቻ ጊዜ ያስፈልግሃል።ከእሾህ ወይን ከኩርንችትም በለስ እንደማትለቅም፣ ራስህን ከዚህ ዓለም ሁከት የምትለይበት ጊዜ ሳይኖርህ እውነተኛ የነፍስ መጽናናትን ልታገኝ አትችልም። ለዚህም ነው ጌታችን በወንጌል "ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ" በማለት ያስተማረን። ላዘነችው ነፍስህ መጽናናትን፣ ለልቡናህ ዕረፍትን ትፈልጋለህ? ስለ ኃጢአትህ የምታፈሰው የንስሐን እንባስ ትሻለህ? እንግዲያውስ ከሰው ርቀህ በርረህ ወደ ፈጣሪ የምትሄድበት የጽሙና ጊዜ ይኑርህ።ጌታን ያጠመቀውና ለብዙዎች በብርሃኑ ደስ የሚያሰኝ "የሚነድ መብራት" የነበረው ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ ሁሉ በፊት ብቻውን ከአምላኩ ጋር በበረሃ ነበር። የሐዲስ ኪዳኑ ባለ ራእይ ቅዱስ ዮሐንስ እነዚያን ሁሉ ሰማያዊ ምሥጢራት የተመለከተው
ኩራዝ
27 янв., 11:01
ፈጣሪህን አመስግን ፣ ወላጆችህን አመስግን ፣ ቤተሰብህን ባለቤትህን ልጆችህን አመስግን ፣ እህቶችና ወንድሞችህን አመስግን ፣ ጓደኞችህን ፣ ጎረቤቶችህን ፣ አለቆችህን ፣ መሪዎችህን አመስግን። ሁሉንም ምንም ባይሰጡህ አብረውህ እንዲሆኑ ስለተሰጠህ እድል አመስግን። ማመስገን የማይችል ግን እንዴት ተበድሏል? ጉድፍህንና ነቀፋህን ለሚከታተሉ ብዙ ቦታ አትስጥ። ለእነርሱ አንተ በውሃ ላይ መራመድ ብትችል እንኳ አስማት እንጂ ቅድስና አይመስላቸውም፣እንዲያውም ዋና ስለማይችል ነው ሊሉህ ይችላሉ።ኩራዝ የዕውቀት አድማስ
Подписчики пишут боту, вы отвечаете реплаем, ваш аккаунт скрыт. Создаётся в одно касание.
Как это работает →