Аватар канала ለእናት

ለእናት

@lenatmom

A place designed to give information and guidance to Pregnant women, Moms and Husbands😊 For questions, contact @lenatadmin

ПроектыENСемья и дети

7,083подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ለእናት

    10 сент., 20:25

    🌼🌻🌼🌻እንኳን ለ 2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!🌼🌻🌼🌻🌼🌻🌼
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    5 сент., 08:28

    💜 ለእናቴ Project – አንዲት እናትን እንደግፍ! ከወሊድ በኋላ ላለች እናት አንድ የንፅህና መጠበቂያ ለእኛ ትንሽ ነገር ቢመስልም፣ ለእሷ ግን ክብር፣ ምቾትና እንክብካቤ ነው። 🩷 በዚህ ፕሮጀክት በተቻለ መጠን በእቃ መለገስን (in-kind donation) እንመርጣለን። ነገር ግን በገንዘብ መደገፍ ከፈለጉ፣ የእቃዎቹ ዋጋ፦ 🩷 1 Maternity Pad — 200 ብር 🧻 1 Wipes — 150 ብር 👶 1 Diaper — 750 ብር 🏥 እቃዎቹ የሚደርሱት በመንግስት ሆስፒታሎች ላይ ፣ እንዲሁም በተመረጡ ጤና ጣቢያዎች ለሚገኙ እናቶች ይሰጣሉ። ለእያንዳንዷ እናት፦ 🩷 4 Maternity Pads 🧻 2 Wipes 👶 1–2 Diapers አንድ እናትን ለመደገፍ ብዙ አያስፈልግም። አቅማችን የሚፈቅደውን እንስጥ—አንድ ላይ ብዙ እናቶችን እንደግፍ። 💜 Inkind donate drop-off location: ቦሌ ፣ጦርሐይሎች፣ ሳርቤት፣ መካኒሳ ፣ ጀሞ እንዲሁም ሰሚት ☎️ 0977733951 0911666621 0923500509 በገንዘብ ለምትደግፉን : 5045110844011 Dashen Bank account, Note that for payment reason mention : "Lenate Project " ለእናቴ Project — ክብርን ለእናት፣ እንክብካቤን ለአዲስ ሕይወት። 🩷
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    2 сент., 12:06

    ወሳኝ የሚባሉትን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ቀጠሮ ይሂዱ! የእርሶ በሁሉም ቀጠሮች ላይ መገኘት እሷ ብቻዋን እንዳልሆነች ያሳያታል። ሐኪሞችም ያስተውሉታል እንም ከእናንተጋ ያላቸውን ግንኙነት የቀይረዋል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    31 авг., 11:59

    ስለ እርግዝና ያንብቡ፤ በሳምንት አንድ ጽሑፍ እንኳ ቢሆን! ባለሙያ መሆን አያስፈልግም። እርሷ እያለፈችበት ያለውን ሁኔታ ብቻ መረዳት በቂ ነው። ለምሳሌ 28ኛ ሳምንት ላይ ምን እንደሚሰማት ማወቅ ለአስፈላጊው ነገር ቀድመው ለመዘጋጀት ይረዳል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    28 авг., 18:24

    ለእያንዳንዱ ቀጠሮ ጥያቄዎችን አስቀድመው ይፃፉ! ዝግጁ ሆነው ይምጡ። ስንተኛው ሳምንት ላይ እንዳለች፣ ይህን ሳምንት ምን ምን ምልክቶች እንደነበሯት እናም ሁለታችሁ ምን ጥያቄ እንዳላችሁ ተዘጋጅተው ይጠብቁ። ተሳታፊ ይሁኑ!
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    27 авг., 12:18

    ከባለቤቶ ጋር ወክ ያርጉ! ቀስ ያለ ዕለታዊ የእግር ጉዞ ስሜቷን፣ ደም ዝውውሯን እና እንቅልፏን ያሻሽላል። እናም አሪፍ የትስስር ጊዜን ይፈጥራል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    24 авг., 09:35

    ስሜት መዋዠቅ ከሆርሞን የሚመጣ ነው! በትንሽ ነገር ስታለቅስ ወይም ፈጥና ስትበሳጭ ምን አጥፈቼ ነው በለው አይጨነቁ በእርሶ ማክኒያት አይደለም። ሆርሞኖች በስውጧ ድንቅ ነገሮችን እያደረጉ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ ትዕግስትን ይምረጡ።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    20 авг., 14:31изменён

    የጀርባ ህመም! የጀርባ ህመም በእርግዝና ወቅት ከሚከሰቱ ህመምሞች አንዱ ነው። የባለቤቶን ጀርባ ለ10 ደቂቃ ማሸት (massage) ምርጥ የፍቅር ምልክቶች ወስጥ አንዱ ነው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    28 июл., 13:34

    የአራስ ህፃን ትኩሳት ምልክቶች ይወቁ!ከ3 ወር በታች ላለ ህፃን 38°C ወይም ከዚህ በላይ ሙቀት አስቸኳይ ህክምና ያስፈልገዋል። ሳይቆዩ ወዲያው ወደ ሐኪም ይውሰዱ።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    27 июл., 13:04

    የህፃናት ማሳጅ (Baby massage)!ለህፃናት ቀላል ማሳጅ ማድረግ የደም ዝውውርን ያሻሽላል፣ የምግብ መፈጨትን ይረዳል፣ የሆድ ቁርጠት ይቀንሳል እናም ትስስርዎን ያጠናክራል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    18 июл., 12:38

    ፎርሙላ ምግብ መጠቀም ስህተት አይደለም! በምርጫም ሆነ በሃኪም ትዕዛዝ፣ የፎርሙላ ምግብ ለህፃናዎን አስፈላጊውን ንጥረነገር/ማዕድን ይሰጠዋል። ዋናው ነገር የሚመገብ፣ የተረጋጋ፣ የሚወደድ ህፃን መሆኑ ነው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    17 июл., 12:25

    ለሊት ማጥባት ጊዜያዊ ነው!እነዚያ የለሊትጊዜዎች አስቸጋሪ ናቸው ግን ለዘላለም አይቆዩም። አብዛኛዎቹ ህፃናት በ3-4 ወር ውስጥ የለሊት እንቅልፋቸው እየረዘመ ስለሚመጣ ያኔ ይቆማል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    16 июл., 13:01

    ህፃኑ የመጀመሪያውን ጡት እስኪጨርስ ይቆዩ!ቶሎ ቶሎ ጡት እየቀየሩ ማጥባት ህፃኑ ከአንዱ ጡት የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር እንዳያገኝ ያደርጋል። ህፃኑ ራሱ ሲለቅ ወይም ሲተኛ ሌላውን ያቅይሩ።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    15 июл., 11:56

    የቅድመ ወሊድ ዮጋ ለሰውነትዎ ጠቃሚ ነው! የጀርባ ህመምን ይቀንሳል፣ ዕንቅልፍ ያሻሽላል እናም ዳሌዎን ለወሊድ ያዘጋጃል። 15 ደቂቃ በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት መስራት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    14 июл., 15:01изменён

    የእርግዝና ማስታወሻ መፃፍ ይጀምሩ!ሦስት ዓረፍተ ነገሮች ብቻ ቢሆኑም። እንደ 'ዛሬ ተሰምቶኝ ነበር...'፣ 'የህፃኑ ኪሎ በዚ … ያህል ጨምሯል’ የመሳሰሉትን። ይህን ማድረግ ጠቃሚ ልምድ ነው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    13 июл., 20:24

    ጓደኛ ያብጁ!የቲሌ-ግራም ግሩፕ፣ የቅድመ ወሊድ ትማህርት ቤት፣ የኦንላይን የእናቶች ግሩፕ የመሳሰሉትን በመቀላቀል እንደርሶ ያሉ እናቶችን ጓደኛ ያብጁ። ይህን ጉዛ ብቻዎን መጓዝ የለቦትም እናም እደርሶ ካሉ እናቶች ጋር አብረው ጉዞዎን ይጀምሩ።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    11 июл., 14:14

    ህፃኑ ሲተኛ ትንንሽ ጥፍሮቹን ይቁረጡ!የአራስ ህፃን ጥፍር በፍጥነት ያድጋል እና በቀላሉ ይቧጭራል። ስለዚህ የህፃን ጥፍር መቁረጫ በመጠቀም ጥልቅ እንቅልፍ ላይ ሳሉ ጥፍራቸውን ይቁረጡላቸው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    10 июл., 12:33

    ሁሌም እየተማሩ ነው! እያንዳንዱ የህፃኖ ልቅሶ ፈጣን መልስ የለውም እናም ይህ ምንም ችግር የለውም። ምክኒያቱም እርስዎና ህፃኖ እርስ በርሳቹ እየተማማራችሁ ነው። ይሄ ደሞ ጊዜ ስለሚወስድ ታጋሽ መሆን አስፈላጊ ነው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    5 июл., 10:53изменён

    ህፃኑ በሚጠባበት ጊዜ ሁሉ ውሃ ይጠጡ!በመመገቢያ ወንበርዎ አጠገብ የውሃ ጠርሙስ ያስቀምጡ። ጡት በማጥባት ወቅት ውሃ የሚጠጡ ከሆነ ኃይልዎን፣ ጥሩ ስሜት እንዲኖሮት እና የወተት ምርትዎን እንዲጨምር ያደርጋል።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
  • ለእናት

    2 июл., 17:27изменён

    የእርሶን መልክ ህፃናዎ ከሁሉም በላይ ለማየት የሚወደው ነገር ነው!አራስ ህፃናት ከ20-30 ሴ.ሜ ርቀት ድረስ በደንብ ያያሉ፣ ከእቅፍዎ እስከ ፊትዎ ድረስ ያለው ርቀት ልክ ይሄ ነው።
    Иллюстрация к посту канала ለእናትИллюстрация к посту канала ለእናት
    2,9701132Открыть в Telegram