Последние посты

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
4 сент., 19:56
ላለፉት ሶስት ሳምንታት ሲያወያየን የቆየው የደራሲ አበረ ሽፈራው #የዕድሜ_ገበያ_እና_ሌሎችም የአጫጭር ታሪኮች ስብስብ በ 261 ገጾችና በውስጡ ባካተታቸው 12 ታሪኮች ተቀንብቦ ለአንባቢያን ቀርቧል።ታሪኮቹ በአመዛኙ ማሕበራዊ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ሌሎች ሀሳቦችም ተዳስሰውበታል። ከእውነተኛው አኗኗራችን የሚገጥሙ (ከነባራዊው እውነት ያልራቁ) ታሪኮች በርከት ብለው የሚገኙበት መጽሐፍ ነው።ታሪኮቹ ታሪክ ብቻም አይደሉም። በታሪክ ተዋዝተው የቀረቡ ሞጋች ጽንሰ-ሀሳቦችም ጭምር እንጂ። የመምከር፣ የመሸንቆጥ፣ የማንቃት፣ የጥያቄ መፍጠር፣ የጥያቄ መመለስ እንዲሁም አዲስ ያልሆነን ነገር በአዲስ ዕይታ ለማሳየት የመሞከር ተግባራት ተንጸባርቀዋል። ስለዚህ መጽሐፉን ያነበበ ከእነዚህ ተግባራት ጋር ይተዋወቃል ማለት ነው። ተግባራቱ የሚመነጩት ጸሐፊው በጽሁፉ ውስጥ ሊያስተላልፍ ከፈለገው የታሪክ ጭብጥ መሆኑ የሚነገር ጉዳይ አይደለም።መጽሐፉ ቢነበብ ጠቃሚ ሀሳቦች የሚገኙበት ነውና በጋራ ከተወያየነው ይበልጥ በግል ንባብ ይካሄድበት ለማለት እንወዳለን። መልካም ንባብ!ልህቀት "እናንብብ ፤ እንለወጥ!"
ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
4 сент., 19:27
Live stream finished (1 hour)
4 сент., 19:26
Live stream started
4 сент., 17:58

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
4 сент., 04:52
የዛሬ ሳምንት በክፍል ሁለት የመጽሐፍ ዳሰሳችን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጠይቀናል።1. በምንና በማን ዙሪያ እንወያያለን? ንግግሮቻችን በጠቃሚ ሀሳብ ወይስ በሰዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያተኩራሉ? የቱ ይጠቅማል?2. ጊዜያችንን ለማንና ለምን እየሰጠን ነው? ዕድሜያችንን የምንሰጣቸው ነገሮች 'ጊዜ' ን ያህል ነገር ተገብቷቸው ነው ወይስ ባለማስተዋል እንዲሁ በልማድ እያደረግናቸው?ዛሬ ምሽት 3:00 ላይ ቀሪዎቹን #የዕድሜ_ገበያ መጽሐፍ ታሪኮች ይዘን በመጨረሻ ክፍል እንገናኛለን። ከቀሩን ታሪኮች ባሻገር በመጽሐፉ አጠቃላይ ይዘት ዙሪያ የማጠቃለያ ሀሳብ ይኖረናል።ኑ ሀሳብ ወዳለበት።ልህቀት "እናንብብ እንለወጥ!"


ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
2 сент., 13:41
በንጉሱ በተበረከቱ መጻሕፍት አገልግሎት የጀመረው ወመዘክርበ1936 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተመርቆ በንጉሱ በተበረከቱ መጻሕፍት አገልግሎት የጀመረው የዛሬው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ በየዘመናቱ መጠሪያውን እየቀየረ ቢመጣም ከተቋቋመበት ዓላማ አኳያ አሁን ላይ "የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት" በሚለው ስያሜ ከ2014 ጀምሮ በርካታ ሀገራዊ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ ጥንታውያን መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ ማኑስክሪፕቶች፣ የነገስታት ደብዳቤዎች፣ የጠረፍ ስምምነቶች፣ የፍርድ ቤት መዝገቦች እንዲሁም በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ቅርሶችን ጭምር በማደራጀት ታሪክን ለትውልድ በማሻገር ላይ ይገኛል።የ«ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030» ስትራቴጂካዊ ግብ አካል የሆነውን ዘመናዊ የዲጂታይዜሽን ፕሮጀክት በይፋ በማስመረቅ ሥራ የጀመረው የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት፣ ያሉትን ታሪካዊ ሀብቶች በዲጂታል መረብ ወደ መላው ዓለም ለማዳረስ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል። ይህንን ዘመናዊ አሰራር እና ልምድ ለመጋራትም አቻ ተቋማቶች ወደ ተቋሙ በመምጣት የልምድ ልውውጥ እያደረጉበት የሚገኝ ትልቅ ሀገራዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።ወመዘክር-




ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
31 авг., 04:57
https://youtu.be/L-rcrxsSJX4?si=_FgAmq60AX0wPihBYouTubeማንበብ ሙሉ ያደርጋልJoin this channel to get access to perks: https://www.youtube.com/channel/UC4yEV6VBe0Emu8sMpyij0uQ/join #ፋና ሚዲያ #fanatv #FMC #fana_media_corporation #Ethiopia YouTube Main channel: www.youtube.com/@fanamediacorporation Documentary youtube: www.youtube.…
ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
28 авг., 20:04
https://youtu.be/1zyU4W4nQ4I?si=s_Sn3JuUKFxOAEpAYouTubeIn Time Full MovieIn the not-too-distant future the aging gene has been switched off. To avoid overpopulation, time has become the currency and the way people pay for luxuries and necessities. The rich can live forever, while the rest try to negotiate for their immortality.…
ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
28 авг., 19:50
በ 'Live Stream' አብራችሁን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ከልብ ነው። ዛሬ በክፍል ሁለት የመጽሐፍ ዳሰሳችን ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ጠይቀናል።1. በምንና በማን ዙሪያ እንወያያለን? ንግግሮቻችን በጠቃሚ ሀሳብ ወይስ በሰዎች ዕለታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያተኩራሉ? የቱ ይጠቅማል?2. ጊዜያችንን ለማንና ለምን እየሰጠን ነው? ዕድሜያችንን የምንሰጣቸው ነገሮች 'ጊዜ' ን ያህል ነገር ተገብቷቸው ነው ወይስ ባለማስተዋል እንዲሁ በልማድ እያደረግናቸው?ሳምንት በመጨረሻ ክፍል እንገናኛለን። የሳምንት ሰው ይበለን።ልህቀት "እናንብብ እንለወጥ!"
ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
28 авг., 19:44
Live stream finished (1 hour)
28 авг., 19:41
Live stream started
28 авг., 18:05

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
28 авг., 05:31
የዛሬ ሳምንት የዕድሜ_ገበያ መጽሐፍ ላይ ተጽፈው በሚገኙ የመጀመሪያዎቹ አራት ታሪኮች ዙሪያ ተማክረናል። ታሪኮቹን መነሻ አድርገን ነባራዊውን ህይወታችንን በተወሰነ መልኩ ለመፈተሽም ሙከራ አድርገናል። በዋናነት ሶስት ሀሳቦች ነበሩ ሲያነጋግሩን የቆዩት።1. "ሕይወት አጭር ናት" ሲባል እንሰማለን። እኛም እንለዋለን ቃሉን። ደራሲው ግን በገጸባህሪው አማካኝነት "ሰው ያልተደላደለ ጎስቋላ ህይወት እየመራ 'ደግሞ ለዚህች አጭር ህይወት¡' ብሎ መደስኮር ይችላል ወይ?" ብሎ ይጠይቃል....- 'ከምንኖረው ኑሮ አንጻር ህይወት አጭር ልትሆንም ላትሆንም ትችላለች ማለት ነው?' ብለን እንድንጠይቅ ምክንያት ይሰጠናል ሀሳቡ።- የተደላደለ ኑሮ ውስጥ ያልተደላደሉ ጎርባጣ አለመመቸቶች የሉም ወይ ብለንም ብንጠይቅ የምንሳሳት አይመስለኝም።2. ትዳርን አስመልክቶ በትዳር ህይወት ውስጥ ካሉ ሰዎች የሚመከሩ ምክሮች 'Paradox' ይፈጥራሉ። በረከትና መርገም መሓል የሚዋልሉት እኚህ ሀሳቦች መሰንዘራቸው ሌላውን ግራ ያጋባል።- ሰዎች በትዳር ህይወታቸው እንደያሉበት የኑሮ ገጠመኝ የሚሰነዝሩት ሀሳብ መልኩን ሊለዋውጥ ይችላል። ሰሚው "ይሄ" ወይስ "ያ" ብሎ እንዳይመርጥ ተቃሮዎቹ ከአንድ አካል የሚመጡ ናቸው።- ሚዛን ያላቸው ልከኛ ሀሳቦች የማይንጸባረቁት ለምን ይሆን?3. የኛ ሳይሆኑ የኛ ናቸው ብለን የምናምናቸው የአመለካከት ውርሶች አሉን። ከልጅነት ተጽዕኖ ይፈጥሩብን የነበሩ ሰዎች ያቀበሉን ፍልስፍናም ሊሆን ይችላል። ከአንድ ጎን ብቻ አይተን የሚበቃን መስሎን ለመልበስ የሞከርነው ሀሳብ አይጠፋም።- በየትኛውም


ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
22 авг., 14:52
ጎተራ ማሳለጫ ቤተ መፅሐፍ ማነኛውም ሰው መጦ በነፃ ንፁህ አየር እየኮመኮመ ደስ ያለውን መፅሐፍ ማንበብ ይችላል ቀዝቀዝ ስለሚል ጠዋት የሞትመጡ ደረብ አድርጋችሁ ብቅ በሉ ስፍራው ማንበቢያ ብቻ ሳይሆን የሚነበብም ሆኗል።




ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
21 авг., 19:21
Live stream finished (58 minutes)
21 авг., 19:20
Live stream started
21 авг., 18:22

ልህቀት የንባብ ባህል ማጎልበቻ ማዕከል
20 авг., 09:58
አርብ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ እንገናኝ !!

Live stream finished (9 minutes)
14 авг., 19:46
Live stream started
14 авг., 19:37
