gram news
Аватар канала ምክረ ሃይማኖት

ምክረ ሃይማኖት

@mikre_haymanot

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት @man_of_king ማገዝ ከፈለጋችሁ👉 cbe 1000267195758 YouTube👉 https://youtu.be/au715yj_5aU?is=qDF-RMWhAvcPN2wi Facbook👉 https://m.facebook.com/profile.php/?id=100067719306101 Tiktok 👉 https://tiktok.com/Mikre_haymanot

ПроектыENРелигия

33,800подписчиков

Открыть канал

Последние посты

  • ምክረ ሃይማኖት

    23 сент., 17:41

    የተስፋ ቅድስናን በምታድለን በእግዚአብሔር እናት በድንግል ማርያም _ ላይ እምነት ይኑራችሁ:: አማላጅነቷ በራሷ ቅድስና የተጠናከረ ስለሆነ ወደ ለእርሷ የምናቀርበው ጸሎት ፈጽሞ ያለ ዋጋ አይቀርም፡፡ በጸሎቷ አማካይነት ለኃጢአቶቻችን ምሕረትና ይቅርታ እናገኛለን፤ድኅነታችንንም እናረጋግጣለን፡፡ የምንባረከውም በጤና፣ በሀብት፣ በጥበቃና በክፉ ቀን ከጥፋት በመጋረድ ነው፡፡አባ ክሮስታድ✞ @Mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    23 сент., 12:02

    አንደበቱን የሚገዛ ነፍሱን ከኃዘን ይጠብቃል።@mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    22 сент., 17:54

    ሰማይ ታላቅ ነው ቢሉ ከአንቺ ጋር አይስተካከልም፤ ሰማይና ምድርን የሞላው በማሕፀንሽ ሞልቶአልና፡፡ ሰዎች ከአንቺ ይልቅ ምድርን ታላቅ ናት ቢሉኝ ምድርማ የእግሩ መረገጫ ብቻ ናት እላቸዋለሁ።የኖኅ መርከብ ነሽ ይሉሻል፤ የኖኅ መርከብ ግን ያዳነችው ኖኅንና ቤተሰቦቹን ነው። በአንቺ ግን ዓለም ዳነ። ታቦት ነሽ ይሉሻል ታቦቱ የያዘው በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ ሁለት ጽላትን ነበር፡፡ አንቺ ግን የዓለማትን ጌታ በኃይሉ ቃል ፀነስሽው!ቅዱስ ዲሜጥሮስ ✞ @Mikre_haymanot ✞ ✥•• ✞ ◉●✥
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    22 сент., 05:35

    переслано из @mikre_haymanot

    ሰይጣን በሩን ሲያንኳኳ እንዲከፍትለት የምትልከው ስንፍናን ነው።"Share @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
    1,4702271Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    21 сент., 18:57

    አስታውስ !!! ደካማነትህን አስታውስ፦ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ፣ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ፦ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ እምነት በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።የሰዎችን ፍቅርና ካንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ፦ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል ያንተንም ቁጣ ያበርዳል።ሞት እንዳለ አስታውስ፦ እንዲሁ በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። “ከፀሐይ በታች የተሠራውን ሥራ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ ሁሉ ከንቱ ነው፥ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።” መክብብ 1፡14 ማለትን ትረዳለህ።በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ፦ ያኔ ኃጢአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ፦ በዚህም ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህም በከንቱ በመኖርአታጠፋውም “በዋጋ ተገዝታችኋልና” 1ኛ ቆሮ. 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፦ ዲያብሎስን፣ ሥራዎቹን ሁሉ፣ ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ ኃይል ታገኛለሕና።በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ
    1,720291511Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    21 сент., 07:51

    ይህ ዓለም መድረክ ነው፤ ገብተህ ትሰራበታለህ፣ አይተህ ትማርበታለህ፣ ወጥተህ ትሄዳለህ። ስለዚህ ጥበበኛ የሆንክ አንተ በተሰጠህ ጊዜ መልካሙን ስራ።" ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግShare @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    20 сент., 10:06

    ለምን ታማርራለህ?፣ አንድ መነኩሴ ነበር፣ እጅግ መከራ ጸናበት። ከዛም በእግዚአብሔር ላይ አጉረመረመ ከመከራው ጽናት የተነሳ፣ " በውነት ሲኦል ከዚህ ይከፋልን? ሲል አማረረ! ቸር እግዚአብሔርም መላኩን እንዲያስተምረው ወደዛ ምስኪን አላዋቂ መነኩሴ ላከው። መላኩም ወደ መነኩሴው ቀርቦ ፣ ያንተ መከራ ከሲኦል የሚበልጥ መሰለህን? በል አሁን ሲኦልን አሳይሀለሁ ብሎ ነጥቆ ውርስዶ ሲኦል አስቀመጠውና " ለአምስት ደቂቃ ጠብቀኝ እመለሳለሁ" ብሎት ሄደ ። ያም መነኩሴ እጅግ ቃጠሎው ከመብዛቱ የተነሳ መቋቋም አቃተው። ጮኸ ፣ አለቀሰ። መላኩ አልመጣለትም። ለአምስት ደቂቃ ብሎት ጭራች እረስቶት የቀረ መሰለው። የተጨነቁትን ሁሌ ወደሚሰማ ወደ ቸር እግዚአብሔር ጸለየ። ማረኝ እያለ ጮኸ ። እግዚአብሔርም መላኩን "ወደ መነኩሴው ተመለስ" አለው። መላኩም ወደ መነኩሴው ተመለሰና ምን ሆንክ አለው። መነኩሴውም " ለአምስት ደቂቃ ብለህ እንዴት ይህን ያክል ዘመን ተውኸኝ?" አለው። መላኩም " ወዳጄ ጥየህ ከሄድኩ ገና ሁለት ደቂቃ እንኳ አልሞላም" አለው። ያም መነኩሴ " እጅግ ባላዋቂነቱ፣ የእግዚአብሔርን ፍርድ በመተቸቱ ( እርሱ መከራውን እንደ አቅማችን ስለሚሰጠን፣ ያውም ለጥቅማችን) ምርር ብሎ ከልቡ አልቅሶ መላኩን " ከዚህ አውጣኝ፣ እግዚአብሔር በፊት ይደርስብኝ ከነበረው መከራ መቶ እጥፍ ቢጨምርብኝ እንኳ እድሜየን ሙሉ በደስታ እቀበለዋለ " አለ። አያችሁ የሲኦል መከራ እንዲህ ነው። አንዳንድ ሰው በርግጥ የዚህን መነኩሴ አይነት ሰው ነው። ሲኦል ምን እንደሆነች ሳያውቅ ኑሮየ ሲኦል ሆነ ብሎ የእግዚአብሔርን ጭካኔ ያወራል።
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
    1,980593531Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    19 сент., 18:23

    በልብህ ውስጥ ሰላም ከሌለ፣ በየትኛውም ቦታ ልታገኘው አትችልም።"ምክረ አበው Share @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    18 сент., 17:29

    ሉቃስ 13 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁷ የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፦ እነሆ፥ ከዚህች በለስ ፍሬ ልፈልግ ሦስት ዓመት እየመጣሁ ምንም አላገኘሁም፤ ቍረጣት፤ ስለ ምን ደግሞ መሬቱን ታጐሳቍላለች? አለው። ⁸ እርሱ ግን መልሶ፦ ጌታ ሆይ፥ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፋንድያ እስካፈስላት ድረስ በዚች ዓመት ደግሞ ተዋት።
  • ምክረ ሃይማኖት

    18 сент., 07:13

    “አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።” — ምሳሌ 4፥23
    2,50054481Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    17 сент., 14:01

    ልጁ ወደ ፀጉር ቤት ገብቶ ፀጉሩን እየተስተካከለ እያለ ከፀጉር አስተካካዩ ጋር ወግ ይጀምራሉ፡፡ ስለ ብዙ ነገሮች ተነጋገሩ፡፡ ብዙ ጉዳዮችን አነሱ ጣሉ፡፡ እንዲህ እያወሩ እያለ በወሪያቸው መካከል የፈጣሪን ጉዳይ አነሱ፡፡ ፀጉር አስተካካዩ “ስማ ወዳጄ! አንተ እንደምትለው ፈጣሪ አለ ብዬ አላምንም፡፡” ሲል ሀሳብ ሰነዘረ፡፡ “ለምን እንደሱ ልትል ቻልክ?” ሲል ጠየቀው ተስተካካዩ፡፡ “ጥሩ! ፈጣሪ አለመኖሩን ለማወቅ በጣም ቀላል ነው፡፡ ውጣና ተመልከት እስኪ ንገረኝ እሰኪ ፈጣሪ ቢኖር ኖሮ እንደዚህ የታመመ ሰው መንገድ ላይ ወድቆ ታይ ነበር? ህፃናቱስ ቢሆኑ እንዲህ ይጣሉ ነበር? ፈጣሪ ቢኖርማ እንደዚህ መቸገርም ሆነ ስቃይ አይኖርም ይህ ነገር እንዲኖር ፈጣሪ ይፈቅዳል ብዬ ማሰብ አልችልም፡፡” አለ፡፡ ፀጉር ተስተካካዩ በሚገባ ሲያዳምጠው ቆየና ለማሰብ ትንሽ ጊዜ ወሰደ ነገር ግን ምላሽ ሊሰጠው አልወደደም፡፡ ወዲያውኑ ፀጉር መስተካከሉን ጨርሶ ወደ ቤቱ ሊሄድ የፀጉር ቤቱን በረንዳ እንደተሻገረ ፀጉሩን ከተስተካከለ ረዥም ጊዜ እንዳለፈው የፀጉሩ መጎፈር የሚያሳብቅ ምስኪን ሰው መንገድ ላይ ተኝቶ ይመለከታል፡፡ በዚህ ጊዜ ወደ ፀጉር ቤቱ ይመለስና “ስማስኪ ፀጉር አስተካካይ እንደሌለ ታውቃለህ?” ሲል ጠየቀው፡፡ “እንዴት የለም ትላለህ? አለሁ እንጂ እኔ ፀጉር አስተካካ እንደሆንኩ አታውቅም?” ሲል ጠየቀ አስተካካዩ:: “የለህም!” ሲል ጮኸበት ደንበኛው፡፡ “ፀጉር አስተካካዮች የላችሁም ብትኖሩማ እንደዚህ ፀጉራቸው አድጎ የሚቸጉሩ ሰዎች አይኖሩም ነበር ” አለው፡፡ አሀ… አለና ፀጉር አስተካካዩ ቀጠለ “በርግጥ ፀጉር
    2,930631010Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    17 сент., 09:27

    переслано из @mikre_haymanot

    📼ቪዲዮ ኤዲቲንግ እንሰራለን📸ግራፊክስ ዲዛይን( logo, social media posts ለ Facebook, Instagram, YouTube thumbnail እና ሌሎችም።📝ስክሪፕት እንፅፋለን (ለየትኛውም)ሶሻል ሚዲያ ካሎት እናስተዳድርሎታለን(በሙሉ እና በከፊል ኃላፊነት)።ማሰራት ምትፈልጉ በዚህ አናግሩን 👉 @Ab_man2121ቻናሉንን ይቀላቀሉ 👉 @Ab_creatives
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    17 сент., 08:16

    የምትፈልገውን ነገር አለማግኘትህ አንዳንድ ጊዜ ትልቅ ዕድል ነው።"Share @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    16 сент., 08:35

    ትናንት ታሪክ ነው፣ ነገ ምስጢር ነው፣ ዛሬ ግን ስጦታ ነው።Share @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    15 сент., 17:30

    переслано из @mikre_haymanot

    አንድ ቀን አንድ ጎረምሳ ቤተክርስትያን ዘሎ ይገባና አንዱን ካህንእናንተ ምትጠሩት እግዚአብሔር ጨካኝ ነው!!ይላቸዋልአባም ቀና ብለው ያዩትና አረ ተው ልጄ ክፉ አትናገር እሱ ደግ ነው ይሉታል።ይኼኔ ወጣቱ ሳይረጋጋ ሁሌ እዚህ እየመጣሁ ፈጣሪ ብር እንዲሰጠኝ እጠይቀዋለሁ እሱ ግን ቤት ቁጭ ብሎ ለማይጠይቀው ይሰጣል አላቸው።አባም ተገርመው ቤት ቁጭ ያለው ሰው በብሩ ምን ያደርጋል አሉት።ጎረምሳውም ቀበልአድርጎ በሽተኛ እናቱን ያሳክምበታል አላቸው።ታድያ ቄሱ ትንሽ ዝም ብለውአንተስምን ታደርግበታለህ ብለው ቢጠይቁት ንዴት ላይ ያለው ጎረምሳ ኩምሽሽ ብሎ የሚናገረው አጣ ይኼኔ ካህኑአየህ ስራህን እንኳን እግዚአብሔር ፊት ሰው ፊት መናገር ታፍርበታለህ።እግዚአብሔር ሳይጠይቁ ሚሰጣቸው እንዳሉ ሁሉ ጠይቀውም ሚከለክላቸው አሉ።አንተ ደሞ አንዱ ነህ።ብሩን ብታገኝ እንደምትጠጣበት ስለሚያቅ ቀድሞ ይከለክልሀል ብር አግኝተህ ጌታህን ካጣህ ምን ትጠቀማለህ ልጄ???Join✞ @Mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
    2,660942486Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    14 сент., 06:14

    ማለቂያ የሌለው ትግል ከአሉታዊ ሃሳቦች ጋር የምታደርገው ትግል ነው።Share @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    13 сент., 15:42

    📼ቪዲዮ ኤዲቲንግ እንሰራለን📸ግራፊክስ ዲዛይን( logo, social media posts ለ Facebook, Instagram, YouTube thumbnail እና ሌሎችም።📝ስክሪፕት እንፅፋለን (ለየትኛውም)ሶሻል ሚዲያ ካሎት እናስተዳድርሎታለን(በሙሉ እና በከፊል ኃላፊነት)።ማሰራት ምትፈልጉ በዚህ አናግሩን 👉 @Ab_man2121ቻናሉንን ይቀላቀሉ 👉 @Ab_creatives
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
  • ምክረ ሃይማኖት

    13 сент., 12:46изменён

    ከመናገርህ በፊት አስብ ቃል ከወጣ አይመለስምና።ሼር ✞ @Mikre_haymanot ✞
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
    2,7805962Открыть в Telegram
  • ምክረ ሃይማኖት

    12 сент., 06:39

    ፩ አዲሱ ዓመት (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው)ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡የጽድቅን ሥራ የምንሠራበት ከኾነ አዲሱ ቀን ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመት ለእኛ መልካም ነው፡፡ ኀጢአት የምንሠራበት ከኾነ ግን ቀኑ ብቻ ሳይኾን አዲሱ ዓመትም ክፉና መከራ የመላበት ይኾንብናል፡፡ አዲሱን ዓመት በበጐ ሥራ የምንጀምረው ከኾነ በዓመቱ በምናደርገው ማንኛውም ክንውን ላይ በጐ ተጽዕኖ ያሳድርብናል፡፡ በትግሃ ሌሊት፣ በቀዊም፣ በጾም በጸሎት እንድንበረታ ስንቅ ይኾነናል፡፡ በስካር፣ በዘፈን፣ በኀዘን የምንጀምረው ከኾነ ግን ዓመቱ ሙሉ እንዲህ የተጐሳቈለ ዓመትን እናሳልፋለን፡፡ ሕይወታችንን በከንቱ እንገፋለን፡፡ ዲያብሎስም ይህን ጥንቅቅ አድረጐ ስለሚያውቅ ዓመቱን በገቢረ ኀጢአት እንድንጀምረው እየቀሰቀሰ ነው፡፡ ፈቃዳችንን አጥፍቶ፣ ዓይነ ልቡናችንን አሳውሮ በዘፈን፣ በስካር፣ በዋይታ እንድንጀምረው በተለያየ መንገድ እየለፈፈ ነው፡፡ሰነፍ ሰው “ቀኑ ክፉ ወይም መልካም
  • ምክረ ሃይማኖት

    11 сент., 12:38изменён

    ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የደስታ የሰላምና የጤና እንዲኾንላችሁ ትሻላችሁን? እንኪያስ ገና ከጅመሩ በስካር፣ በዘፈን፣ በገቢረ ኀጢአት ለማሳለፍ አታቅዱ፡፡ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያውን ዕለት ብቻ ሳይኾን እያንዳንዱን ቀን በገቢረ ኀጢአት አትጀምሩት፡፡ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ፣ ምግባር ትሩፋት በመሥራት አሐዱ በሉ እንጂ፡፡ ዕለታት ክፉዎች ወይም ጥሩዎች የሚኾኑት በተፈጥሮአቸው እንደዚያ ኾነው አይደለም፡፡ ዕለቱን ክፉ ወይም ደግ እንዲኾን የምናደርገው እኛው ነን፡፡ የአምናው ማክሰኞ ከዘንድሮ ማክሰኞ የተለየ አይደለም፡፡ የተለየ የሚያደርገው የእኛ ብርታት ወይም ስንፍና ብቻ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅShare @mikre_haymanot
    Иллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖትИллюстрация к посту канала ምክረ ሃይማኖት
    3,29054172Открыть в Telegram